Advanced Freshman – Telegram
Advanced Freshman
27.4K subscribers
650 photos
9 videos
59 files
206 links
🔔ይህ ቻናል freshman ለሚማሩ ተማሪዎች የተዘጋጀ እና በዉስጡ የተለያዩ የዩንቨርስቲ መረጃዎችን, አጋዥ መፅሐፍቶች, ቲቶሪያል, mid እና final ፈተናዎችን ሚያዘጋጅ እና ተማሪዎች ወደ ሚፈልጉበት ዲፓርትመንት እንዲገቡ ሚያግዝ ነው ::

📩Owner:- @Bekijum
Download Telegram
Forwarded from Remedial Class
የ Remedial Special Class ዝግጅታችን ተጀመሯል።

ትምህርቱ እና ሌሎች ሚጠቅሟቹ materials የሚሰጠው በቴሌግራም Private Group ሲሆን: ለመረዳት በጣም ግልፅ የሆኑ ኖቶች,Video, Voice, PDF እና Diagram ይሆናል::

በተጨማሪም:-
📝በቂ Note እና አጋዥ መፅሐፍት፣
🔗በአማርኛ ፅሁፍ, diagram ማብራሪያ፣
📹እርስ በርስ ምትረዳዱበት group
Review questions ፣ ግልፅ እና በቀላሉ እንድትረዱ በማድረግ ትምህርቱ ይሰጣል።

✔️ያልተመዘገባችሁ ተማሪዎች
ይህን
➡️@Remedialtutor_bot ቦት ተጠቀሙ::

ለበለጠ መረጃ :@Remedial_supportbot


🙀 መልካም የRemedial ጉዞ ይሁንላችሁ🥰

ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
JOIN:
@Remedial2018batch
JOIN:
@Remedial2018batch
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
17🙏3👍1
አዲሱ መመሪያ‼️
ሴት ተማሪዎች የጥፍር፣ የፀጉርና የከንፈር ቀለም መቀባት፣ ቅንድብ መቀንደብና መኳኳል፣ አላስፈላጊ ጌጣ ጌጦችን አድርጎ ወደ ትምህርት ቤት መሄድ የሚከለክል መመሪያ ትምህርት ሚኒስቴር አዘጋጀ፡፡

ትምህርት ሚኒስቴር የተማሪዎችን ሥነ ምግባር ለመቆጣጠር ያዘጋጀው ረቂቅ መመሪያ ማንኛውም ተማሪዎች ከተፈጥሮ ጸጉራቸው በስተቀር አርቴፊሻል ፀጉር መቀጠል አይችሉም ተብሏል፡፡

ከዚህ ባለፈም በትምህርት ቤት ውስጥ አላስፈላጊ የሆኑ የኢትዮጵያዊነት ባህልን የማይገልፁ በዓላት በተለይም እንደ ክሬዚ ዴይ፣ ኦልድ ዴይ፣ ቤቢ ዴይ፣ ቶማቶ ዴይ፣ ከለር ዴይ፣ ቫላንታይን ዴይ እና ሌሎችም የበዓል ቀናቶች ተብለው የሚከበሩ በዓላት ማክበር በመመሪያው ተከልክሏል፡፡

በትምህርት ቤት የደንብ ልብስ በተገቢ መንገድ መልሰብ ሲል ባወጣው መመሪያ ስር ሴቶች ጉርድ ቀሚስ ከባት በታች የሆነ ቁመት ያለው ለብሶ መገኘት አለባቸው ተብሏል፡፡ 

ከደንብ ልብስ ውጪ ቢሆን ከአካባቢው ባህል ጋር የማይቃረን አለባበስ መልበስ ይጠበቅባቸዋል ይላል ረቂቅ መመሪያው፡፡

ትምህርት ቤት ውስጥ መፈፀም የተከለከሉ ድርጊቶች ብሎ ከዘረዘራቸው መካከል ደግሞ የትምህርት ቤቱን መምህራን፣ የትምህርት አመራር፣ ሠራተኞችና ሌሎች የትምህርት ማህበረሰብ አካላትን መዝለፍ፣ መስደብ፣ ማንቋሸሽና አካላዊ ጥቃት መፈጸም ቅጣት የሚያስከትል ተግባር ነው ተብሏል፡፡

ተንቀሳቃሽ ስልክ ወይም ሞባይል እና የሙዚቃ ማዳመጫ መሣሪያዎችን ትምህርት ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ ይዞ መገኘት ረቂቅ መመሪያው ከልክሏል፡፡

በቃል፣ በምልክትም ሆነ በጽሑፍ ፀያፍ ነገሮችን መግለፅ፤ ጨዋነት የጎደላቸውን እንዲሁም ሐይማኖታዊና ፖለቲካዊ ይዘት ያላቸውን ምስሎችና ጽሑፎች በትምህርት ቤት ውስጥ ይዞ መገኘትና ማሰራጨት አይፈቀድም፡፡

በትምህርት ቤት ግቢ ውስጥ የማንኛውንም ዓይነት የኃይማኖት አምልኮ ሥርዓትና የፖለቲካ እንቅስቃሴዎችን ማካሄድ ይከለክላል፡፡

ማንኛውም ተማሪ አገራዊ እሴት ያልሆኑና መጤ የሆኑ ነገሮችን በሰውነት ላይ ምልክት ማድረግ፤ ከአገራዊ እሴት ጋር የሚቃረኑ አሉታዊ መጤ ምልክቶችን በሰውነት ላይ መነቀስ፣ ማሳየት፣ ማድረግ፣ መጠቀም ፍፁም የተከለከለ ነው ብሏል ረቂቅ መመሪያው፡፡

ከ9 እስከ 12ተኛ ክፍል ላሉ ተማሪዎች አንድ ተማሪ በሥነ-ምግባር ጉድለት እጅ ከፍንጅ ከተያዘና የመማር ማስተማሩን ሂደት የሚያውክ ሆኖ ከተገኘ ውሳኔ እስኪሰጠው ከትምህርት ቤት ሊታገድ እንደሚችልም በመመሪያው ሰፍሯል፡፡

ተማሪዎች ተደጋጋሚ ጥፋት አጥፍተው ሲገኙ በተለይም ከ7 እስከ 12ተኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎች እስከ 1 ዓመት ድረስ እንደ ጥፋቱ መጠን ታይቶ ከትምህርት ሊታገዱ ይችላልም ሲል ረቂቅ መመርያው አስቀምጧል፡፡

በሌላ በኩል በትምህርት ቤቶችና አካባቢ የትምህርት አዋኪ ጉዳዮችን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር ለሚኒስትሮች ምክር ቤት የቀረበ ረቂቅ ደንብ ተሰናድቷል፡፡

በዚህ ረቂቅ ደንብ ትምባሆ(ሲጋራ፣ ሺሻ)፣ ጫት፣ አልኮል የናርኮቲክ እና ሳይኮትሮፒክ ዝርያ ያላቸው አደገኛ ህገ ወጥ መድኃኒቶች እና ሱስ አስያዥ ዕፆች ትምህርት ቤት አካባቢ መሸጥም ሆነ ይዞ መገኘትን ይከለክላል።

የአልኮል መሸጫ እና ማከፋፈያ ቤቶች፣ የሲጋራ መሻጫ ሱቆች፣ ሺሻ ቤቶች፣ ጫት መሸጫና መቃሚያ ቤቶች፣ ጭፈራ ቤቶች፤ ቁማር ቤቶች፤ የእንግዳ ማረፊያ ቤቶች እና የሰውነት መታሻ ወይም ማሳጅ ቤቶች በትምህርት ቤቶች በ500 ሜትር ርቀት ውስጥ መክፈት አይቻልም፡፡

ፊልም ማጫዎቻ ቤቶች፣ ፕሌይ ስቴሽን ቤቶች፣ ዲ.ኤስ.ቲቪ ቤቶች፣ ከረንቡላ፣ ፑል፣ ጆተኒ፣ ቢንጎ እና የስፖርት ቁማር መጫወቻ ቤቶችም በትምህርት ቤት አቅራቢያ መክፈትን ከልክሏል።

🌟JOIN:@ADVANCED_FRESHMAN
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
😁7655👏25👍15😭6🫡4👎3🙏2
ትናንት ህዳር 11/2018 ዓ.ም ጠዋት ላይ በደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ ተማሪዎች "የምግብ እጥረት አለ ይስተካካከል" ብለው ሰላማዊ ሰልፍ በወጡበት  የግቢው ዘበኞች ተኩስ ከፍተው የ2 ተማሪዎች ህይወት እንዳለፈ እና ሌሎች ላይ ጉዳት እንደደረሰ የደረሰን መረጃ ያመላክታል።

ምንጭ :- (አዩዘሀበሻ)

🌟JOIN:@ADVANCED_FRESHMAN
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
😭260💔33😢129😱9
Advanced Freshman
ትናንት ህዳር 11/2018 ዓ.ም ጠዋት ላይ በደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ ተማሪዎች "የምግብ እጥረት አለ ይስተካካከል" ብለው ሰላማዊ ሰልፍ በወጡበት  የግቢው ዘበኞች ተኩስ ከፍተው የ2 ተማሪዎች ህይወት እንዳለፈ እና ሌሎች ላይ ጉዳት እንደደረሰ የደረሰን መረጃ ያመላክታል። ምንጭ :- (አዩዘሀበሻ) 🌟JOIN:@ADVANCED_FRESHMAN
" በምግብ በአቅርቦቱ ላነሷቸው ጥያቄዎች ተገቢው ምላሽ ሊሰጥ፣ እነርሱም ጥያቄዎቻቸውን በነጻነት አንስተው መግባባት ተደርሷል " - ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ

ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ምን አለ ?

ለጉዳዩ ምላሽ እንዲሰጡና ችግሩን ለመቅረፍ ምን እየተሰራ እንደሆነ የጠየቃቸው የደባርቅ ዩኒቨርሲቲ የህዝብ እና አለምአቀፍ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ አምሳሉ ተበጀ፣ ተማሪዎች ቅሬታ የማቅረብ እንቅስቃሴ ማድረጋቸውን አምነዋል።

" ጥያቄዎች አንስተው ነበር ችግሩን ለመፍታት በተፈጠረ መድረክ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ተማሪዎችም በተገኙበት ተወያይተው መግባባት ላይ ተደርሷል " ሲሉ ተናግረዋል።

ተማሪዎቹ፣ " የምግብ ችግር አለብን " በማለት ጭምር ሰላማዊ ሰልፍ ወጥተዋል፤ መግባባት ላይ የተደረሰው በምን መልኩ ነው ? ሲል ቲክቫህ ኢትዮጵያ ላቀረበው ጥያቄ፣ " ከዚህ ጋር በተገናኘ በአቅርቦቱ ላነሷቸው ጥያቄዎች ተገቢው ምላሽ እንደሚሰጥ፣ እነርሱም ጥያቄዎቻቸውን በነጻነት አንስተው ይሄ መግባባት ተደርሷል " ብለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያም፣ በደፈናው መግባባት ላይ ተደርሷል ሳይሆን ላነሱት ቅሬታ ምን ማስተካከያ ልታደርጉ ነው መግባባት ላይ የተደረሰው ? ሲል በድጋሚ የጠየቃቸው አቶ አምሳሉ፣ መስተካከል ያለባቸው የጠየቋቸው የቀን ሽፍት ማድረግና መሰል ጉዳዮች እንዳሉ ገልጸዋል።

" ለምሳሌ 'ረቡዕ የሆነው የሩዝ ምግብ ቅዳሜ ይሁንልን' " እንዳሉ ተናግረው፣ " ከዚህ በፊት ይቅር ብለው የነበረውን ፓስታ ይዘጋጅልን ብለዋል፤ በመጠንም ያነሱት ጥያቄ አለ " ሲሉ ያከሉ ሲሆን፣ የተግባቡት ይህን ሊያስተካክሉ መሆኑን ገልጸዋል።

" የሞቱና የቆሰሉ ተማሪዎች አሉ " ስለመባሉ ስንጠይቃቸው ደግሞ፣ " መረጃው የለኝም " ያሉ ሲሆን፣ ስለጉዳዩ እያብራሩልን አይደል እንዴ እንዴት መረጃው የለኝም ይላሉ ? ስንላቸው፣ " ያለኝን መረጃ ነው የምናገረው፤ ስለዛኛው (ግድያው) መረጃ የለኝም " ብለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ፣ ለጉዳዩ ተጨማሪ ማብራሪያ እንዲሰጥ የዩኒቨርሲቲውን ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት ቢጠይቅም ጉዳይ እንደማይመለከተው በመግለጽ፣ ምላሽ ከመስጠት ተቆጥቧል። የተማሪዎች ኀብረት መረጃው በፕሬዚዳንት ደረጃ ይሰጥ ተብሏል ቢልም፣ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ግን ስልክ ለማንሳት ፈቃደኛ አልሆኑም።

" በጥይት ቆሰሉና ተገደሉ " ስለተባሉ ተማሪዎች መረጃው ደርሶት እንደሆን የጠየቅነው የኢትዮጵያ ተማሪዎች ኀብረት ግን፣ " የሞተም ሆነ የቆሰለ የት፣ በማን? " የሚለውን መረጃ እያጠናቀረ መሆኑን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

ውይይት በተደረገበት ወቅት አንድ ተማሪ ምን አለ?

" ዩኒቨርሲቲው ጊዜ ስጡኝ ብሎን ነበር። ግን አመት ከርመን ስንመጣ ያቆየን ረሃብ ነው። ሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች መስከረም 5 ነው የገቡት። እኛ የሁለተኛ አመት ተማሪዎች ጥቅምት 17 ነው የገባነው። ግን መስከረም 5 ከገባ ተማሪ ጋር ነገ የመውጫ ፈተና የምንፈተነው። ለምን ?

እናንተ ናችሁ ፓለቲካን የምንትሰብኩብን እንጅ እኛ ለመማር ነው የመጣነው። እኛ ጥያቄያችን ርቦናል የሚል ነው። ከተለያዬ ቦታ ነው የመጣነው፤ ስልካችንን እየተዘረፍን፤  በሬ እያሸጥን ነው ለመማር የመጣነው።

በዓለማችን ትልቁ መሳሪያ ትምህርት ነው። ስለዚህ አስተምሩን፤ መግቡን ኢትዮጵያን እናሳድጋት ነው ያልነው። ሌላ የፓለቲካ አጀንዳ የለንም። ሞትማ በነበርንበት ቦታ ሞልቷል። ምግባችንን አስተካክሉልን፣ እንማር " ብሏል።

Via:- TIKVAH

🌟JOIN:@ADVANCED_FRESHMAN
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
40😢35👍16👏5💔2
Forwarded from Remedial Class
እስካሁን ለ2018 ሪሚድያል ተማሪዎቻቸው ጥሪ ያደረጉ ዩኒቨርሲቲዎች ዝርዝር!

1. ሰላሌ ዩኒቨርሲቲ:- ህዳር 2 እና 3
2. ቦረና ዩኒቨርሲቲ:- ህዳር 8 እና 9
3. ቀብሪ ደሃር ዩኒቨርሲቲ:- ህዳር 4 - 7
4. ጅግጅጋ ዩንቨርስቲ:- ህዳር 5-8
5. ባህርዳር ዩንቨርስቲ:- ህዳር 11 እና 12
6. ጋምቤላ ዩንቨርስቲ:- ህዳር 15 እና 16
7. ራያ ዩንቨርስቲ:- ህዳር 22 እና 23
8. ጅንካ ዩንቨርስቲ:- ተራዝሟል
9. ደባርቅ ዩንቨርስቲ:- ህዳር 25 እና 26
10.ኦዳ ቡልቱም ዩንቨርስቲ:- ህዳር 25 እና 26
11.ድሬ ደዋ ዩንቨርስቲ:- ህዳር 20 እና 21
12.አርባ ምንጭ ዩንቨርስቲ:- ህዳር 25 እና 26
13. መቱ ዩንቨርስቲ :- ታህሳስ 1 እና 2
14. መቅደላ አምባ ዩንቨርስቲ:- ህዳር 25 እና 26
15. አምቦ ዩንቨርስቲ:- ህዳር 29 እና 30
16. ቡሌ ሆራ ዩንቨርስቲ:- ህዳር 29 እና 30
17. ወሎ ዩንቨርስቲ:- ህዳር 25 እና 26
18. አሶሳ ዩንቨርስቲ:- ታህሳስ 2 እና 3
19.ደብረ ታቦር ዩንቨርስቲ :- ህዳር 25 እና 26
20. ወልድያ ዩንቨርስቲ:- ታህሳስ 6 እና 7
21. ሰመራ ዩንቨርስቲ:- ህዳር 25 እና 26
22. ጎንደር ዩንቨርስቲ:- ህዳር 29 እና 30
23. ወራቤ ዩንቨርስቲ:- ታህሳስ 2 እና 3
24. ደብረ ማርቆስ ዩንቨርስቲ:- ታህሳስ 2 እና 3
.

#️⃣ቻናላችንን ዘንድሮ Remedial ለሆኑ ተማሪዎች share ያድርጉ🤔

JOIN: @Remedial2018batch
JOIN: @Remedial2018batch
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
39🙏7👍3🆒2
#BahirDarUniversity

ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ወደ ራስ ገዝ የኒቨርሲቲነት ለመሸጋገር ዝግጅቱን ማጠናቀቁን ገለፀ፡፡

ራስ ገዝ እንዲሆኑ በመንግሥት ከተለዩ አስር ዩኒቨርሲቲዎች መካከል ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ አንዱ መሆኑ ይታወቃል።

በዚህም ዩኒቨርሲቲው ራስ ገዝ ለመሆን የሚያስችለውን የተሟላ ዝግጅት ማድረጉን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት መንገሻ አየነ (ዶ/ር) ለኢዜአ ተናግረዋል።

ዩኒቨርሲቲው የሰው ኃይል ስምሪት፣ ሃብት የማመንጨት አቅም፣ አስተዳደራዊ መዋቅር እና ሌሎች ተግባራትን በማካተት የደረሰበትን ውጤት ለትምህርት ሚኒስቴር መላኩን ፕሬዝዳንቱ ገልፀዋል።

ትምህርት ሚኒስቴር በሚሰጠው ፈቃድ መሰረት ዩኒቨርሲቲው የራስ ገዝነት አሰራሩን ተቀብሎ ተግባራዊ እንደሚያደርግ ፕሬዝዳንቱ ጠቁመዋል።

🌟JOIN:@ADVANCED_FRESHMAN
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
34👍7🆒1
ሰላም ቤተሰብ 😊የተለያዩ ሚጠቅሟችሁን material እያዘጋጀን ስለሆነ ይበልጥ ብዛታችሁን ለማወቅ ከታች vote አድርጉ
Anonymous Poll
64%
Freshman ተማሪ ነኝ
13%
Remedial ተማሪ ነኝ
19%
>2nd year ተማሪ ነኝ
4%
Highschool ተማሪ ነኝ
40👍11
Forwarded from Campus ተማሪ
JU 2017 MidExam Collections.pdf
2.2 MB
Jimma University (JU) 2017 MidExam Collections

😬 Mathematics
😬 Physics
😬 Mathematics
😬 Logic
😬 Economics

ቻናላችንን ለሌሎች share ያድርጉ😀

✈️ @CAMPUS_TEMARI
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
12🙏7👍5
#MoE

➡️ አምስት የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ራስገዝ ለመሆን ለትምህርት ሚኒስቴር ጥያቄ አቅርበዋል፡፡

🔺ባሕር ዳር፣ ጅማ፣ ጎንደር፣ አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ እና አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲዎች ራስገዝ ለመሆን ጥያቄ ያቀረቡ ዩኒቨርሲቲዎች መሆናቸውን በትምህርት ሚኒስቴር የአስተዳደርና መሰረተ ልማት መሪ ሥራ አስፈፃሚ ሰለሞን አብርሃ (ዶ/ር) ለኢዜአ ተናግረዋል።

🔺ዩኒቨርሲቲዎች በአስተዳደር፣ በፋይናንስ፣ በሰው ሃብት፣ በአካዳሚክ ጉዳዮች እና በምርምር ዘርፍ ባላቸው ቁመና እና በሚያስመዘግቡት ውጤት መሰረት ወደ ራስገዝነት እንደሚሸጋገሩ ጠቁመዋል፡፡

አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ከሁለት ዓመት በፊት ቀድሞ ራስ ገዝ መሆኑ ይታወሳል ።

➡️በመሆኑም እነዚህ ዩኒቨርሲቲዎች ራስ ገዝ ከሆኑ በኋላ ከ Entrance በተጨማሪ ሌላ ፈተና ተፈትነው ተማሪዎችን የሚቀበሉ ይሆናል!

JOIN: @ADVANCED_FRESHMAN
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
17👍10🔥1
ይህንን ያውቃሉ?

ጥናቶች እንደሚያሳዩት ተማሪዎች በቀን የተማሩትን ነገር ሲተኙ አንጎላቸው መረጃውን ያጠናክራል። ስለዚህ ከረዥም ትምህርት በኋላ ትንሽ እንቅልፍ መውሰድ ከሌላ ሰዓት ትምህርት የበለጠ ውጤታማ መሆን ያስችላል።

JOIN: @ADVANCED_FRESHMAN
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
😇2918👍10🙏8😎6🫡2🔥1🕊1
Forwarded from Campus ተማሪ
➡️Jima university 2017 Physics mid exam

ቻናላችንን ለሌሎች share ያድርጉ😀

✈️ @CAMPUS_TEMARI
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
7🙏5👍2
University grading system

#️⃣A+   --------> ብርቄ ነሽ
Range  ፡ ከ90 በላይ
Multiplied by: 4

#️⃣A       -------> አስቤሽ አላውቅም
Range : 85-90
Multiplied by:4

#️⃣A-       ----->አለም 9 ናት
Range : 80-85
Multiplied by:3.75

#️⃣B+     ------>ጌጤ ነሽ
Range:    75-80
Multiplied by:3.5

#️⃣B      ------->  ነይልኝ በሞቴ
Range : 70-75
Multiplied by:3

#️⃣B-       ----->አንቺን ከሚከፋሽ
Range :65-70
Multiplied by:2.75

#️⃣C+     -----> የኔ ማር
Range : 60-65
Multiplied by:2.5

#️⃣C   --------> አንለያይም
Range : 50-60
Multiplied by:2

#️⃣C-  -------> በቴስታ ማለት ነበር
Range:45-50
Multiplied by:1.75

#️⃣D    -------> የኔው ጉድ
Range: 40-45
Multiplied by:1

#️⃣FX  -------> አንቺ ባትኖሪ እኮ
Range : 30-40
Multiplied by:tempo 0 ኮርሱን በድጋሚ የመፈተን እድል ይፈጥራል፤ በድጋሚው ፈተና ግን ከ40 በላይ ካላመጡ F ይሆናል

#️⃣F  --------> ጥሎብኝ
Range ከ30 በታች
Multiplied by: 0 ኮርሱን እንደገና መማር ያስገድዳል በቀጣዩ ዓመት ማለት ነው።

JOIN: @ADVANCED_FRESHMAN
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
56👍29😘7🫡4🙏3🤗3👌2🤝2🕊1
🧑‍🔬ስለ ህክምና ማወቅ ያለባችሁ 10 ነገሮች ❗️

«
🟢ብዙውን ጊዜ ስለ ሙያው ሳያውቅ መድሃኒትን ለመቀላቀል ውሳኔዎች እየተደረጉ ናቸው:: ከዚህ በታች ወደ ህክምና ከመቀላቀል በፊት ባገኛቸው የምመኘውን ከልምዶቼ እውነቶችን ዘርዝሬአለሁ። ይህ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎችን እንዲሁም የህክምና ትምህርትን በተገቢው እና በመረጃ በተደገፈ የቅጥር ሂደት ለማሻሻል የበኩሉን እንደሚረዳ ተስፋ አደርጋለሁ።
 


1⃣. የሕክምና ሙያ የታሰበው ጽንፍ መቋቋም ለሚችሉ ግለሰቦች ብቻ ነው:: መድሃኒት ለስላሳ መንገድ አይደለም::ብዙ ውጣ ውረዶች አሉት።
🔻🔹🔹

2⃣. ይህ ሙያ እንደ ቤተሰብ ባህል መወሰድ የለበትም:: አያቴ ሐኪም ነው፣ አባቴ ሐኪም ነው፣ እናም ዶክተር መሆን አለብኝ። ይሄ አይሰራም!!!
🔺🔺🔺

3⃣. የሕክምና ሙያ የሚጠብቀውን ዋጋ ለሚገነዘቡ ሰዎች ነው:: በአንድ ቀን ውስጥ ምንም ነገር አይከሰትም:: ወይም በአንድ ወር ውስጥ ወይም በዓመት ውስጥ እንኳን ለመመስረት በአጠቃላይ አመታትን ይወስዳል። ስሜት የሚጫወተው እዚያ ነው። ለምታደርጉት ነገር በጣም የምትጓጉ ከሆነ, መጠበቅ የጊዜ ጉዳይ ነው::
🔻🔹🔹

4⃣. የሕክምና ሙያው ለማይነጻጸር ነው:: ጓደኛዬ ውጭ ሀገር እየሰራ ነው, መሄድ አለብኝ ወይም የአክስቴ ሴት ልጅ እያገባች ነው... አሁንም ኮሌጅ ነኝ። አንድ ሰው ራሱን ከሌላ ሰው ጋር ባነጻጸረበት ቅጽበት፣ ሁሉንም ዓይነት የመንፈስ ጭንቀት ውስጥ የሚያስገባ ባዶነት ይፈጥራል።
🔹🔻🔸

5⃣. የሕክምና ሙያ የመንፈስ ጭንቀትን ለመዋጋት በቂ ጥንካሬ ላላቸው ነው:: ትምህርቱ ከባድ እና ብዙ ፈተናዎች አሉት።
🔺🔺🔺

6⃣. አንድ ሰው ለጥናት ጊዜ እና አስደሳች ጊዜ ግልጽ የሆኑ ድንበሮችን ማዘጋጀት ያስፈልገዋል:: በህክምና ውስጥ ለፈተናዎች ብቻ አይሰለጥኑም, በአብዛኛው በታመሙ እና በሞት መካከል ለሚቆሙበት ቀን ነው::
🔻🔹🔹

7⃣. በሕክምና ትምህርት ትምህርቱ አያልቅም:: የመጀመሪያ ዲግሪ የሚፈጀው 'ሰባት አመት ብቻ' ነው፣ ከሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የሚያውቋቸው ሁሉ የመጀመሪያ ዲግሪዎን እየሰሩ ነው የሚመረቁት። ከዚያም በመረጡት መስክ ላይ በመመስረት ከ3-5 ዓመታት ልዩ ሙያ ይመጣል:: ከዚያ ከ2-3 ዓመታት ንዑስ-ስፔሻላይዜሽን ይከተላል....
🔹🔻🔸

8⃣. ማህበራዊ ህይወት ይከፈላል:: ከሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የመጡ ጓደኞችህ እና ዘመዶችህ ከሜድ ተማሪነትህ በኋላ በትዕቢት ምክንያት የምትርቃቸው አድርገው ያስባሉ። ትክክለኛ ምክንያቶችዎን የሚረዳ ሌላ የህክምና ተማሪ ብቻ ነው። ተማሪው ሁልጊዜ የሚያጠናው ነገር አለ::
🔺🔺🔺

9⃣. የሥርዓተ-ሥርዓት ተዋረድ፣ በመሠረቱ የሕክምና መሰላልን መነሳት ማለት ከሥሩ መጀመርን ይጨምራል፣ ከእርስዎ ለሚበልጡ ሁሉ መልስ ይስጡ። በመጨረሻ ደረጃውን እስክትወጣ ድረስ ይህን ታደርጋለህ.
🔻🔹🔹

1⃣0️⃣. ህይወታችሁን በሙሉ ታቆማላችሁ:: ህይወታችሁን ለመተው ተዘጋጁ፣ ምክንያቱም የጊዜ ቁርጠኝነት ከምታስቡት በላይ ነው። ቅዳሜና እሁድ እና ምሽቶችዎን ደህና ሁን ይበሉ። ትዳር፣ ልጆች፣ ቤት፣ መኪና... እነዚህ ነገሮች ዘግይተው ይመጣሉ። ለዚያ ምቾት ሊሰማዎት ይገባል::  »

✍️ዶክተር ቤተልሄም👩‍🔬

ስለ medicine ተጨማሪ መረጃዎችን ከፈለጋችሁ ከዶክተር አንደበት በvoice🎙 አጠር ያለ ማብራሪያ አዘጋጅተን ፖስት እናደርጋለን:: comment ላይ አሳዉቁን👇

ይቀጥላል.....ከተመቻቹ 🥺👍❤️

JOIN:@ADVANCED_FRESHMAN⭐️
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
49👍13🙏7🥰4
👨‍💻COMPUTER SCIENCE💻

Computer science ምን አይነት Department ነው


💻Computer Science  በአካዳሚክ ተቋም ወይም በቴክኖሎጂ ላይ ያተኮረ የTechnology field ሲሆን   ከኮምፒዩተር ጋር ተዛማጅ በሆኑት ነገር ላይ ያቶክራል ።

💻ኮምፒውተር  ሳይንስ አብዛኛው ጊዜ በኮምፒዩተር ሳይንስ እና ተዛማጅ ዘርፎች ውስጥ የማስተማር፣ የምርምር እና የፈጠራ ስራዎችን የማከናወን ሃላፊነት አለበት። 

አብዛኛው ጊዜ ኮምፒውተር ሳይንስ ስትማሩ የምትወስዱት ኮርስ እነዚህ ናቸው
💻Software Development
💻Computer system
💻HARDWARE
💻Artificial Intelligence (AI)
💻Data science
💻Cyber security
እና ሌሎችንም ጨምሮ ከኮምፒዩተር ጋር የተያያዙ በርካታ ርዕሰ ጉዳዮች አሉ::

🎓 በ ቅድመ ምረቃ ዲግሪ መርሐ ግብር የስንት አመት ትምህርት ነው

🟢በኢንጅነሪንግ field ስር የሚመደብ ሆኖ : ድሮ 4 ዓመት ሲሰጥ የነበረው አሁን ላይ ፍሬሽማንን ጨምሮ 5 ዓመት እንዲሆን ተደርጎአል::

📚 COMPUTER SCIENCE  የሚገቡ ተማሪዎች ልክ እንደ SOFTWARE ENGINEERING ተማሪዎች ግዴታ ማወቅ ያለባቸው ነገሮች አለ እሱም  Programming Language🖱

💻 COMPUTER SCIENCE የሚማር ተማሪ ከታች የተዘረዘሩትን የ Programming Language የትምህርት ዘርፍ መውሰድ እና ማወቅ ይጠበቅበታል።

    📚Some of main programming languags are🔺
    
💻C++           
💻JAVA          
💻JAVASCRIPT
💻CSS
💻C#
💻PHP
💻PYTHON
💻HTML

📚 በ COMPUTER SCIENCE የተመረቀ ሰው ምን ምን ስራዎችን መስራት ይችላል

🟢አንድ በCOMPUTER SCIENCE የተመረቀ ተማሪ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ሞያዎች ላይ ተመርክዞ Bank ቤቶችን ጨምሮ የተለያዩ የመንግስት እና የግል ድርጅት ላይ ተቀጥሮ መስራት ይችላል።

🏷Data Scientist/Analyst
🏷Database Administrator
🏷Network Administrator
🏷Systems Analyst
🏷Cybersecurity Analyst
🏷IT Consultant
🏷Machine Learning Engineer
🏷Artificial Intelligence Specialist
🏷Cloud Computing Engineer
🏷Quality Assurance Tester  እና ብዙ    የስራ እድል አለ::

በቀላሉ አማርኛ  COMPUTER
የሚገባበት ቦታ  ሁሉ ላይ የComputer science ተመራቂ ይገባል 😎

   💸 ገቢውስ ምን ያክል ነው😋

💻 አንድ የComputer science
ምሩቅ በአሁን ሰዓት በ ወር  ከ10,000  እስከ 15,000ብር  እና ከዛ በላይ ያገኛል ግን በየመስሪያ ቤት ወይም በየ ደርጅት ይለያያል: በዛ ላይ ከ መደበኛ ስራ ውጪ በግል የራሳችሁን ስራ ለመስራት ስለሚመች በጣም አሪፍ ገቢ ይኖራችኋል።

💻ይህ የCOMPUTER SCIENCE  አጭር ማብራሪያ ነው። ስለ COMPUTER SCIENCE ሙሉ INFO ለመስጠት በጣም ብዙ ማብራሪያ ስለሚፈልግ እኛ ከሰጠናችሁ Info በተጨማሪም  በዚህ ዲፓርትመንት የተማሩ senior ተማሪዎችን ለመጠየቅ ሞክሩ😊::ካስፈለገም እኛ ቀጥታ senior ተማሪዎችን ከናንተ ጋር እናገናኛቿለን::

ይቀጥላል.....

JOIN: @ADVANCED_FRESHMAN⭐️
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
43👍11🥰5