BeWide Technologies – Telegram
BeWide Technologies
292 subscribers
78 photos
18 links
Pioneering AI-powered software development, IT solutions, and branding for transformative growth. From intelligent web design and custom systems to dynamic mobile apps

Elevate your digital presence with us

Be wide—Be wise

Contact us through @BeWideTech
Download Telegram
BeWide Technologies
Photo
ቢዋይድ ቴክኖሎጂስ፣ ከሀሩን ሚዲያ እና መወዳ ስኩል ጋር በመተባበር ያዘጋጁት ቴክኖሎጂና ኢስላማዊ ማንነት ላይ ያተኮረ ልዩ የክረምት ስልጠና በአዲስ አበባ ካራ በሚገኘው መወዳ ትምህርት ቤት እየተሰጠ ይገኛል።

የስልጠናው ዓላማ ሙስሊም ተማሪዎች የክረምት ጊዚያቸው በቴክኖሎጂ እና በኢስላማዊ ተርቢያ እንዲያሳለፉ ለማድረግ ያለመ ነው።

ስልጠናው ትኩረቱን ያደረገው፦ ድረ ገፅ ማበልፀግ (Web Development) የሞባይል መተግበሪያ ማበልፀግ (App Development)፣ የማንነት እነፃ (Personal Development) ፣የእምነትና የእሴት መሰረታውያን(Foundations of Islamic Truth and Values)፣ ልምድ ማጋራት (Mentorship) ፣እስልምናንና እስላማዊ ታሪክን መረዳት (Understanding Islam and Islamic History)እና ሌሎችም ኮርሶችን ያካተተ የክረምት ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል።

ስልጠናውን እየወሰዱ ያሉ ተማሪዎች ስልጠናውን አስመልክቶ ለሀሩን ሚዲያ በሰጡት አስተያየት እንደገለፁት በርካታ ቁምነገር ያገኙበት ስልጠና መሆኑን አንስተው ከዋናው ትምህርታቸው ጎን ለጎን ይህን መሰል ስልጠናዎችን መውሰዳቸው ለወደፊቱ ለሚኖራቸው ራዕይ መንደርደሪያ እንደሚሆናቸው ተናግረዋል።

ይህ ስልጠና መጪው ትውልድ ከታች ጀምሮ ከቴክኖሎጂ ጋር በማስተዋወቅ በቀጠይ በትክኖሎጂው ዘርፍ ላይ ቀዳሚ ትውልድ ለመፍጠር እጅግ ከፍተኛ ሚና ይኖረዋል ያለው ደግሞ የሀሩን ሚዲያ የሀገር ውስጥ ስቱዲዮዎች ስራ አስኪያጅ አቶ ባህሩ አባስ ነው።

https://youtu.be/g7tx8xAx3Pc?si=o2DYNdGs7HY8tdbz

©ሀሩን ሚዲያ

BeWide Technologies
#BeWide_BeWise

@BeWide_Tech
🔥7🥰21