የአዲስ አበባ ስታድየም ከመጪው መስከረም ወር ጀምሮ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግን ያስተናግዳል፡- የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር
***********
የአዲስ አበባ ስታድየም ከመጪው መስከረም ወር ጀምሮ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግን ለማስተናገድ ዝግጁ መሆኑን የባህልና ስፖርት ሚኒስትር አቶ ቀጄላ መርዳሳ ገለፁ።
የስታድየሙ እድሳት በከፊል መጠናቀቁን ተከትሎ ጨዋታን ማድረግ እንደሚቻል ሚኒስትሩ ተናግረዋል።
የስታድየሙ ሁለተኛ ምዕራፍ 65 በመቶ መጠናቀቁ የተገለፀ ሲሆን በቀጣይ 3 ወራት ውስጥ ቀሪ ስራዎች እንደሚጠናቀቁም ገልፀዋል።
https://www.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid02mYSD8CmktVLipG8fTDpQnqt1fd2VtNQ3edk4EDz9XEapCYRM3PKB8EURmWdEvVVyl

👍57👎20❤14
አርባ ምንጭ ከተማ ከፕሪሚየር ሊጉ የወረደ ሶስተኛ ክለብ መሆኑ ተረጋገጠ
አርባ ምንጭ ከተማ በ2015 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የወረደ ሶስተኛው ክለብ መሆኑ ተረጋግጧል።
በፕሪሚየር ሊጉ የ30ኛ ሳምንት መርሐ-ግብር ላለመውረድ በሚደረገው ፉክክር ውስጥ ወሳኝ የሆኑ ሁለት ጨዋታዎች በተመሳሳይ ሰአት ሲካሄዱ፤ ወልቂጤ ከተማ እና አዳማ ከተማ አንድ አቻ ወጥተዋል።
በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተመሳሳይ ሰዓት በተካሄደው ጨዋታ ሃዋሳ ከተማ እና አርባ ምንጭ ከተማ አንድ እኩል ወጥተዋል።
ውጤቶቹን ተከትሎ ወልቂጤ ከተማ በ35 ነጥብ 13ኛ ደረጃን ይዞ በፕሪሚየር ሊጉ መቆየቱን ሲያረጋግጥ፤ በአንጻሩ አርባ ምንጭ ከተማ በ34 ነጥብ 14ኛ ደረጃን ይዞ ከፕሪሚየር ሊጉ መውረዱ ተረጋግጧል።
ኢትዮ ኤሌክትሪክ እና ለገጣፎ ለገዳዲ ወደ ኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ቀድመው የወረዱ ክለቦች መሆናቸው ይታወሳል፡፡

👍83👎11❤8👏6
ፈረንሳዊው ኮከብ ተጫዋች ኪሊያን እምባፔ በካሜሮን ጉብኝት እያደረገ ነው
**********************
የ24 ዓመቱ እግር ኳስ ተጫዋች ኪሊያን እምባፔ የወላጅ አባቱ ዊልፍሬድ እምባፔን ሀገር ለመጎብኘት ካሜሩን ደርሷል፡፡
ኪሊያን እምባፔ ያውንዴ አየር ማረፊያ ሲደርስም 400 የሚጠጉ ሰዎች በካሜሩን ባህላዊ ጭፈራ ታጅበው አቀባበል አድርገውለታል፡፡
"ካሜሮናዊውን ወንድማችንን በማየታችን ኮርተናል። ደማቅ አቀባበልም አድርገንለታል" ሲሉም ተደምጠዋል።
ከፓሪሱ ክለብ ጋር የመቆየቱ ነገር አጠራጣሪ የሆነዉ እምባፔ ለሶስት ቀናት በካሜሩን ቆይታ የሚያደርግ ሲሆን በዛሬዉ ዕለት መስማት የተሳናቸዉ ትምህርት ቤትን ይጎበኛልም ተብሏል፡፡
ተጫዋቹ በእሱ የበጎፈቃድ ድርጅት እየተደገፉ ያሉ ትምህርት ቤቶችንም ይጎበኛል ነው የተባለው።
በነፃነት ጫንያለዉ

👍80👎14❤10
"ኅብር ህይወቴ" የተሰኘው የኤሜሪተስ ፕሮፌሰር ባሕሩ ዘውዴ ግለ ታሪክ መፅሐፍ ተመረቀ
*****************
ለረጅም ዓመታት በኢትዮጵያ ታሪክ ዙሪያ ምርምር እና ጥናት በማድረግ የሚታወቁት ኤሜሪተስ ፕሮፌሰር ባሕሩ ዘውዴ በራሳቸው የህይወት ታሪክ ዙሪያ የሚያጠነጥነው "ኅብር ሕይወቴ" ግለ ታሪክ መፅሃፍ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በዋናው ግቢ 6 ኪሎ ካምፓስ ራስ መኮንን አዳራሽ ተመርቋል።
መፅሃፉ በ3 ዋና ክፍሎች የተከፈለ ሲሆን የፕሮፌሰሩን የልጅነት፣ ወጣትነት እና ጉልምስና ዕድሜያቸውን ባሳለፉበት አካዳሚያዊ፣ ፖለቲካዊ እና ማህበራዊ የህይወት ዑደቶች ዙሪያ የሚያጠነጥን ነው፡፡
ፕሮፌሰር ባሕሩ ዘውዴ በርካታ ጥናታዊ ፅሁፎችን ጨምሮ በኢትዮጵያ ዘመናዊ ታሪክ ዙሪያ የሚያጠነጥኑ መፅሃፍቶችን ለንባብ ያበቁ ሲሆን ስለ ኢትዮጵያ ታሪክ በተለያዩ ሃገራት ዩኒቨርሲቲዎች ተጋባዥ መምህር በመሆን አስተምረዋል፡፡
"ኅብር ሕይወቴ ግለ ታሪክ" የተሰኝውን መጽሐፍ የኢትዮጵያ ጥናት ተቋም ወዳጆች ማሕበር፣ የኢትዮጵያ ጥናት ተቋም፣ የታሪክ ክፍለ ትምህርት፣ የአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ የውጭ ግንኙነት ክፍል በጋራ በመሆን ነው ያስመረቁት።

👍50👎10❤9
በኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙኃን ታሪክ ደማቅ ዐሻራ ያኖሩት አንጋፋው የሚዲያ መሪ፡- አቶ አማረ አረጋዊ
*********************
አቶ አማረ አረጋዊ የቀድሞው የኢትዮጵያ ቴሌቪዠን ዋና ሥራ አስኪያጅ እና ከሀገሪቱ አንጋፋ የሚዲያ መሪዎች ውስጥ ግንባር ቀደም ናቸው። ከ40 ዓመታት በላይ በጋዜጠኝነት እና በሚዲያ መሪነት ያገለገሉት አቶ አማረ፣ ከኢቲቪ በተጨማሪ በሪፖርተር ጋዜጣ መሥራችነታቸው፣ በኢትዮጵያ የሚዲያ ካውንስል ምሥረታ እና ለጋዜጠኝነት እና ኮሙዩኒኬሽን ዕድገት ባላቸው አበርክቶት ይታወቃሉ።
በኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙኃን ታሪክ ውስጥ ደማቅ ዐሻራ ያሳረፉት አንጋፋው ጋዜጠኛ እና የሚዲያ መሪ አቶ አማረ አረጋዊ፣ የኢቢሲ አዲሱ የሚዲያ ኮምፕሌክስ ምርቃትን ምክንያት በማድረግ የዛሬው የአርዓያ ሰብ አምድ ባለታሪካችን አድርገናቸዋል።
አቶ አማረ ታኅሣሥ 29 ቀን 1947 ዓ.ም ከአባታቸው አቶ አረጋዊ ወ/ኪዳን እና ከእናታቸው ወ/ሮ ዘነበች ገ/ማርያም በመቐለ ከተማ የተወለዱ ሲሆን፣ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን በትውልድ ከተማቸው መቐለ ተምረዋል።
https://www.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid08Eskiqtz522UZ6pL6dDgFsp2V6vHKoj1jyxwmrBg53wKggBUWFQY6aNQwiPytuJkl

👍47👎9❤5👏1
ተወዳጁ ሙዚቀኛ ብስራት ሱራፌል ''ማለፊያ'' የተሸኘ ሁለተኛ አልበሙን ለአድማጭ ሊያደርስ ነው
*********************
ተወዳጁ ሙዚቀኛ ብስራት ሱራፌል ''ማለፊያ'' የተሸኘ ሁለተኛ አልበሙን ለአድማጭ ሊያደርስ ነው።
በሀገሪቱ የሙዚቃ ኢንዱስትሪ ውስጥ በአጭር ጊዜ ተደማጭና ታዋቂ ለመሆን የቻለውና የበርካታ ግጥምና ዜማ ደራሲ የሆነው ድምፃዊ ብስራት ሱራፌል ሁለተኛ አልበሙን ከኤላ ቲቪ ጋር በመሆን የፊታችን ሀምሌ 14 ቀን 2015 ዓ.ም ለአድማጭ እንደሚያደርስ ዛሬ በሀገር ፍቅር ቴአትር አዳራሽ በተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቋል ።
ከዚህ ቀደም ቃል በቃል የተሰኘ የመጀመሪያ አልበሙንና የተለያዩ ነጠላ ዜማዎችን በመስራት በሙዚቃ አፍቃሪያን ዘንድ ተወዳጅና ታዋቂ ለመሆን የቻለው አርቲስት ብስራት ሱራፌል ''ማለፊያ'' የተሰኘው አዲሱ አልበም ለ 4 አመታት ያህል የተለፋበትና ከ20 በላይ በሙዚቃው ኢንዱስትሪ ስመ ጥር የሆኑ ባለሙያዎች በግጥም በዜማ እንዲሁም በቅንብር የተሳተፉበት መሆኑ ተገልጿል።
https://www.facebook.com/EBCmezenagna/posts/pfbid02ts9tHcaPAEZuuycwubxTDvjpUdukm5nkJfbM83PABM6WMpeEieXZT5AaaGU43nq3l

👍24👎11❤10
ወደ ጎረቤት ሀገር ሊሻገር የነበር አደንዛዥ እፅ፣ የዝሆን ጥርስ፣ ደረቅ ጫት እና ነዳጅ በቁጥጥር ስር ዋለ
**********************
በሁመራ ከተማ፣ ዲማ፣ ባዕከር እና ራዊያን ኬላ በተደረገ ፍተሻ ወደ ጎረቤት ሀገር ሱዳን ሊሻገር የነበረ አደንዛዥ ዕፅ፣ የዝሆን ጥርስ፣ ደረቅ ጫት፣ እና ነዳጅ በመከላከያ ሠራዊቱ በቁጥጥር ስር ዋለ።
እቃዎቹ በቁጥጥር ስር የዋሉት ሕብረተሰቡ ለህግ አካላት ባደረገው ጥቆማ በመነሻነት በተደረገ ክትትል መሆኑን ሌተናል ኮሎኔል ግርማ በድዬ ተናግረዋል።
ሠራዊቱ በኬላዎችም ይሁን በሌላ መንገድ የሚዘዋወሩ ህገ-ወጥ ዝውውሮችን በመቆጣጠር ሀገራዊ ግዴታውን እየተወጣ እንደሆነም ሌተናል ኮሎኔል ግርማ ገልጸዋል።
https://www.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid0JLTdtK9S9XsAyt17BFY3Y9KZBe89AEscGoMLhkNTiKA3eYQsHUpinSkiaKNndTEPl

👍67❤19👎18👏6
ትዊተር ሜታን ፍርድ ቤት ሊያቆመው መሆኑን አስታወቀ
******************
የፌስቡክ እናት ኩባንያ የሆነው ሜታ “ትሪድስ” የተሰኘ እና የትዊተር ተቀናቃኝ የሆነ አዲስ መተግበሪያን ይፋ ካደረገ በኋላ ትዊተር ኩባንያውን ሊከስ መሆኑን አስታውቋል።
ሜታ የቀድሞ ሠራተኞቼን በመቅጠር የንግድ ምሥጢሮቼ ላይ ስርቆት ፈጽሟል ሲል ትዊተር በጠበቃው በኩል ለሜታ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ማርክ ዙከርበርግ የክስ ደብዳቤ መላኩ ታውቋል።
የትዊተር ባለቤት የኤለን መስክ ጠበቃ የሆኑት አሌክስ ስፒሮ የጻፉት ደብዳቤ “ሜታ ስልታዊ እና ሕገ-ወጥ በሆነ መንገድ የትዊተርን የንግድ ምሥጢሮች እና ሌሎች የአዕምሮአዊ ንብረቶችን አለአግባብ በመዝረፍ ላይ መሰማራቱን” የሚገልጽ ነው።
https://www.facebook.com/photo/?fbid=657377266416456&set=a.637938368360346

👍68👎18❤11