EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation) – Telegram
EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)
138K subscribers
38.2K photos
458 videos
80 files
13.1K links
EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation) @etvafaanoromoo1
@ETVkidschannel
@EBCWORLD1
@etventertainment1
Download Telegram
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከእንግሊዙ የአውሮፕላን ሞተር አምራች “ሮልስ ሮይስ” ኩባንያ ጋር ስምምነት ተፈራረመ
**************************

ስምምነቱ አየር መንገዱ በቀጣይ ለሚረከባቸው ኤርባስ A350-1000 አውሮፕላን ሞዴል ሞተሮች አጠቃላይ የሰርቪስ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል መሆኑን ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
👍8714👏11👎9
ለድምፃዊት እጅጋየሁ ሽባባው የዕውቅና ሽልማት ተሰጠ
*********************

ለ15ኛ ጊዜ የተካሄደው የአማራ ክልል ባህል እና ኪነ ጥበባት ፌስቲቫል ለድምፃዊት እጅጋየሁ ሽባባው (ጂጂ)፣ ለጌትነት እንየው እና ለአበበ ብርሃኔ የዕውቅና ሽልማት ሰጥቷል።

ገና በልጅነት ዘመኗ ጀመሮ ስለ ሀገር እና ስለ ሀገር ፍቅር በማቀንቀን በብዙዎች ልብ ውስጥ የገባችው እጅጋየሁ ሽባባው ላደረገችው አስተዋፅዖ ነው ሽልማት የተበረከተላት። ጂጂ ለሀገር ባቀነቀነቻቸው ዘፈኖቿ ብዙዎችን አስተሳስራለች።

https://www.facebook.com/EBCmezenagna/posts/pfbid02SnbWBc4CbYiUpgBLpJ4FFYnwvGknw4tHkXYPc4hPuVdXChXZimyNwBYRzLpQzxenl
👍9917👏12👎10
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የሰላም ልዑካን መቐሌ ገቡ
***********************************************

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የሰላም ልዑካን ትግራይ ክልል መዲና መቐሌ ገብተዋል።

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ፣ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ፣ የሀገር ሽማግሌዎች መቐሌ አሉላ አባ ነጋ ኤርፖርት ሲደርሱ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ አማኑኤል አሰፋ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፣ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት እና የሰላም ልኡካኑ ከትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር ከአቶ ጌታቸው ረዳ ጋር በመቐሌ አሉላ አባ ነጋ ኤርፖርት ተገናኝተው መወያየታቸውን የኢኦተቤ መገናኛ ብዙኀን አገልግሎት ሥርጭት ድርጅት መረጃ ያመለክታል።
👍62👎178👏5
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በትግራይ ክልል በሰው ሰራሽና በተፈጥሮ አደጋ ለተፈናቀሉ ወገኖች የሚውል የ20 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገች
********************

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትሪያሪክ ብፁእ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ድጋፉን ዛሬ ለትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጌታቸው ረዳ አስረክበዋል።

ብፁእ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ በርክክብ ሥነ ስርዓቱ ላይ እንዳሉት፥ ድጋፉ በተፈጥሮና ሰው ሰራሽ አደጋ ከቤት ንብረታቸው ለተፈናቀሉ ወገኖች የሚውል ነው።

“የሃይማኖት መሪዎች ግጭት ሳይሆን ሰላም፣ ውድመት ሳይሆን ልማት ለማረጋገጥ ሃላፊነት አለብን” ያሉት ብፁእነታቸው ወደፊትም አስፈላጊው ድጋፍ እንደሚደረግ አስታውቀዋል።

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጌታቸው ረዳ ለተደረገው ድጋፍ አመስግነዋል።

የሃይማኖት መሪዎች ለሰላምና ልማት መረጋገጥ ሚናቸው የላቀ መሆኑን ተናግረዋል።

የተጀመረው መልካም ተግባር ተጠናክሮ እንዲቀጥልም መጠየቃቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
👍6523👎17👏8
የአዲስ አበባ ከተማ ለ6 ወራት የቤት ኪራይ ጭማሪ ማድረግ የማይቻል መሆኑን አስታወቀ
**********************************

ለሚቀጥሉት 6 ወራት የቤት ኪራይ ጭማሪ ማድረግ እንዲሁም ተከራይ ማስወጣት የማይቻል መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አሳውቋል።

የከተማ አስተዳደሩ ካቢኔ የኑሮ ውድነቱ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው የከተማዋ ነዋሪዎች ላይ የሚያሳድረውን ጫና ለመቀነስ የቤት ኪራይ ጭማሪ እንዳይደረግ በተለያዩ ተከታታይ ጊዜያት ውሳኔ ማሳለፉን አስተዳደሩ አስታውሷል።

በቀጣይም በግል ከሚደረግ ስምምነት ውጪ ማንኛውም አከራይ ለሚቀጥሉት 6 ወራት የቤት ኪራይ ጭማሪ ማድረግ እንዲሁም ተከራይ ማስወጣት የማይቻል መሆኑን የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ ጽህፈት ቤት መረጃ ያመላክታል።
👍126👎43👏1810
ትናንት ምሽት በሀገሪቱ በርካታ አካባቢዎች ተቋርጦ የነበረው የኃይል አቅርቦት ወደነበረበት ተመልሷል
********************************

ትናንት ምሽት በሀገሪቱ በርካታ አካባቢዎች ተቋርጦ የነበረው የኃይል አቅርቦት ወደነበረበት መመለሱን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታውቋል።

የኃይል መቋረጡ የተከሰተው በጊቤ 3 የኃይል ማመንጫ ጣቢያ ላይ ባጋጠመ የቴክኒክ ችግር ምክንያት መሆኑን አገልግሎቱ በማኅበራዊ ትስስር ገፁ ባሰፈረው ጽሁፍ ገልጿል።

ተቋርጦ የነበረው የኃይል አቅርቦት ወደነበረበት የተመለሰው በማመንጫ ጣቢያው ላይ ያጋጠመውን የቴክኒክ ችግር ለማስተካከል በተደረገ ከፍተኛ ጥረት መሆኑንም ጠቅሷል።

የተፈጠረው ችግር እስኪፈታ በትግዕስት ለተጠባበቁ ደንበኞቹም ተቋሙ ምስጋና አቅርቧል።
👍146👎3113👏7
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከግብፅ ፕሬዝደንት አብዱልፈታህ አልሲሲ ጋር መከሩ
************
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው እንዳስታወቁት ከግቡፁ ፕሬዝደንት አብዱልፈታህ አልሲሲ ጋር በግብፅ ካይሮ መክረዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ "በግብጽ ካይሮ ከፕሬዚዳንት አብዱልፈታሕ ኤልሲሲ ጋር በሁለትዮሽ እና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ ትብብር በሰፈነበት መንፈስ ውይይቶች አካሂደናል።" ሲሉም ነው የገለጹት።
በውይይታቸውም የሁለትዮሽ ትብብር ጉዳዮች እንዲሁም ወቅታዊ የቀጠናው ሁኔታዎች መነሳታቸውን ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስታውቀዋል።
https://www.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid0w8YCBmBKyTyWfkAfgRb59bDJCSQYLuuEkThPmN2AdYzqR2hZDrHLaVRTLzDYVCf7l
👍56👎179👏1
ሐምሌ 10 ቀን 2015 ዓ.ም በአንድ ጀንበር 500 ሚሊዮን ችግኞች በኅብረት!
48👍34👎34👏6
www.ebc.et
**********
በእጅዎ ባለ ስልክ፣ቢያሻዎ በኮምፒውተርዎ መከታተል እንዲችሉ ዘምኖ እና ምቹ ሆኖ ቀርቦልዎታል፡፡
ከዘመኑ ሚዲያ ተቀዳሚ አማራጭ እየሆነ የመጣው የድረ ገፅ አካል የሆነው www.ebc.et በአዳዲስ ገጽታዎች እና አቀራረብ ወደ እናንተ መድረሱን ይቀጥላል፡፡
👍37👏14👎1312
በሩሲያ የዋግነር ኃይሎችን ትጥቅ የማስፈታት ዘመቻ ተጠናክሮ መቀጠሉ ተሰማ
****************

የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር የዋግነር ግሩፕ የጦር መሣሪያዎችን ከቡድኑ ተዋጊዎች እየተረከበ መሆኑን በቃል አቀባዩ በኩል አስታውቋል።

የግል ወታደራዊ ቡድን የሆነው ዋግነር ግሩፕ መፍረሱን ቀጥሏል ሲል የሩሲያ መንግሥት ገልጿል።

እንደ ሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር ገለጻ፣ በመቶዎች የሚቆጠሩ ታንኮች፣ እንደ 'ግራድ' እና 'ኡራጋን’ ዓይነት የዘመኑ የሮኬት ማስወንጨፊያ ሥርዓቶችን እንዲሁም ‘ፓንሲር’ የተሰኙትን ዘመናዊ አየር መቃወሚያ ሚሳኤል ሥርዓቶችን ጨምሮ ከ2 ሺህ በላይ ከባድ እና ቀላል የጦር መሣሪያዎች በመንግሥት ጦር ሥር እንዲውሉ ተደርገዋል።

በቁጥጥር ሥር ከዋሉት 20 ሺህ የነፍስ ወከፍ ጦር መሣሪያዎች እንዲሁም 2 ሺህ 500 ቶን ተተኳሾችን ያካተተው የጦር ትጥቅ ወደ ጥገና ክፍል ተወስዶ ለጥገና ወይም ለጦር ግንባር እንዲውል እንደሚደረግ የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር መግለጹን የዘገበው አር.ቲ ኒውስ ነው።
👍13420👏14👎10
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለ2026ቱ የዓለም እግር ኳስ ዋንጫ ለማለፍ በምድብ ማጣሪያው የሚገጥማቸው ሀገራት ይፋ ሆነዋል
***********************

በኮትዲቫሯ መዲና አቢጃን ዛሬ ይፋ በሆነው ድልድል የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በምድብ አንድ ከግብፅ፣ ቡርኪና ፋሶ፣ ጊኒ ቢሳዎ፣ ሴራሊዮን እና ጂቡቲ ጋር ተደልድሏል።

በምድብ ሁለት ናይጄሪያ እና ደቡብ አፍሪካ የሚገኙት ድልድል በአመዛኙ ጠንካራው ምድብ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።

54 የአፍሪካ ሀገራት በ9 ምድቦች ውስጥ የማጣሪያ ጨወታቸውን የሚያደርጉ ሲሆን ከየምድባቸው ቀዳሚ ሆነው የሚያጠናቅቁ 9 ሀገራት 48 ብሔራዊ ቡድኖች ለመጀመሪያ ጊዜ በሚሳተፉበት የአሜሪካ፣ ሜክሲኮ እና ካናዳ የጣምራ አዘጋጅት የዓለም ዋንጫ ላይ በቀጥታ የሚያልፉ ይሆናል።

በሰለሞን አባቡ
👍7033👎16👏6