EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation) – Telegram
EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)
138K subscribers
38.2K photos
458 videos
80 files
13.1K links
EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation) @etvafaanoromoo1
@ETVkidschannel
@EBCWORLD1
@etventertainment1
Download Telegram
ወደ ጎረቤት ሀገር ሊሻገር የነበር አደንዛዥ እፅ፣ የዝሆን ጥርስ፣ ደረቅ ጫት እና ነዳጅ በቁጥጥር ስር ዋለ
**********************

በሁመራ ከተማ፣ ዲማ፣ ባዕከር እና ራዊያን ኬላ በተደረገ ፍተሻ ወደ ጎረቤት ሀገር ሱዳን ሊሻገር የነበረ አደንዛዥ ዕፅ፣ የዝሆን ጥርስ፣ ደረቅ ጫት፣ እና ነዳጅ በመከላከያ ሠራዊቱ በቁጥጥር ስር ዋለ።

እቃዎቹ በቁጥጥር ስር የዋሉት ሕብረተሰቡ ለህግ አካላት ባደረገው ጥቆማ በመነሻነት በተደረገ ክትትል መሆኑን ሌተናል ኮሎኔል ግርማ በድዬ ተናግረዋል።

ሠራዊቱ በኬላዎችም ይሁን በሌላ መንገድ የሚዘዋወሩ ህገ-ወጥ ዝውውሮችን በመቆጣጠር ሀገራዊ ግዴታውን እየተወጣ እንደሆነም ሌተናል ኮሎኔል ግርማ ገልጸዋል።
https://www.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid0JLTdtK9S9XsAyt17BFY3Y9KZBe89AEscGoMLhkNTiKA3eYQsHUpinSkiaKNndTEPl
👍6719👎18👏6
ትዊተር ሜታን ፍርድ ቤት ሊያቆመው መሆኑን አስታወቀ
******************

የፌስቡክ እናት ኩባንያ የሆነው ሜታ “ትሪድስ” የተሰኘ እና የትዊተር ተቀናቃኝ የሆነ አዲስ መተግበሪያን ይፋ ካደረገ በኋላ ትዊተር ኩባንያውን ሊከስ መሆኑን አስታውቋል።

ሜታ የቀድሞ ሠራተኞቼን በመቅጠር የንግድ ምሥጢሮቼ ላይ ስርቆት ፈጽሟል ሲል ትዊተር በጠበቃው በኩል ለሜታ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ማርክ ዙከርበርግ የክስ ደብዳቤ መላኩ ታውቋል።

የትዊተር ባለቤት የኤለን መስክ ጠበቃ የሆኑት አሌክስ ስፒሮ የጻፉት ደብዳቤ “ሜታ ስልታዊ እና ሕገ-ወጥ በሆነ መንገድ የትዊተርን የንግድ ምሥጢሮች እና ሌሎች የአዕምሮአዊ ንብረቶችን አለአግባብ በመዝረፍ ላይ መሰማራቱን” የሚገልጽ ነው።

https://www.facebook.com/photo/?fbid=657377266416456&set=a.637938368360346
👍68👎1811
በተጠናቀቀው በጀት በአዲስ አበባ ከ416 ሺህ በላይ ዜጎች የስራ እድል ተፈጥሯል- ከንቲባ አዳነች አቤቤ
**********************************

በ2015 በጀት በመዲናዋ ከ416 ሺህ በላይ ዜጎች የስራ እድል መፈጠሩን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።

ሶስተኛው የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ሁለተኛ ዓመት የስራ ዘመን አራተኛ እና የበጀት ዓመቱ ማጠቃለያ መደበኛ ጉባኤ እያካሄደ ነው።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አበቤ ለከተማዋ ምክር ቤት የአስተዳደሩን የ2015 በጀት ዓመት አፈጻጸም ሪፖርት በማቅረብ ላይ ናቸው።
https://www.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid0Md2pKCoFzcPqtxQvHoxvqR4EULq5besoEH7iskftJsZtqahz2eJHMV6oEDUQpj8jl
👎96👍7015👏4
ሐምሌ 10 ቀን 2015 ዓ.ም በአንድ ጀንበር 500 ሚሊዮን ችግኞች በኅብረት!
👍79👎518
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከእንግሊዙ የአውሮፕላን ሞተር አምራች “ሮልስ ሮይስ” ኩባንያ ጋር ስምምነት ተፈራረመ
**************************

ስምምነቱ አየር መንገዱ በቀጣይ ለሚረከባቸው ኤርባስ A350-1000 አውሮፕላን ሞዴል ሞተሮች አጠቃላይ የሰርቪስ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል መሆኑን ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
👍8714👏11👎9
ለድምፃዊት እጅጋየሁ ሽባባው የዕውቅና ሽልማት ተሰጠ
*********************

ለ15ኛ ጊዜ የተካሄደው የአማራ ክልል ባህል እና ኪነ ጥበባት ፌስቲቫል ለድምፃዊት እጅጋየሁ ሽባባው (ጂጂ)፣ ለጌትነት እንየው እና ለአበበ ብርሃኔ የዕውቅና ሽልማት ሰጥቷል።

ገና በልጅነት ዘመኗ ጀመሮ ስለ ሀገር እና ስለ ሀገር ፍቅር በማቀንቀን በብዙዎች ልብ ውስጥ የገባችው እጅጋየሁ ሽባባው ላደረገችው አስተዋፅዖ ነው ሽልማት የተበረከተላት። ጂጂ ለሀገር ባቀነቀነቻቸው ዘፈኖቿ ብዙዎችን አስተሳስራለች።

https://www.facebook.com/EBCmezenagna/posts/pfbid02SnbWBc4CbYiUpgBLpJ4FFYnwvGknw4tHkXYPc4hPuVdXChXZimyNwBYRzLpQzxenl
👍9917👏12👎10
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የሰላም ልዑካን መቐሌ ገቡ
***********************************************

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የሰላም ልዑካን ትግራይ ክልል መዲና መቐሌ ገብተዋል።

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ፣ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ፣ የሀገር ሽማግሌዎች መቐሌ አሉላ አባ ነጋ ኤርፖርት ሲደርሱ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ አማኑኤል አሰፋ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፣ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት እና የሰላም ልኡካኑ ከትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር ከአቶ ጌታቸው ረዳ ጋር በመቐሌ አሉላ አባ ነጋ ኤርፖርት ተገናኝተው መወያየታቸውን የኢኦተቤ መገናኛ ብዙኀን አገልግሎት ሥርጭት ድርጅት መረጃ ያመለክታል።
👍62👎178👏5
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በትግራይ ክልል በሰው ሰራሽና በተፈጥሮ አደጋ ለተፈናቀሉ ወገኖች የሚውል የ20 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገች
********************

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትሪያሪክ ብፁእ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ድጋፉን ዛሬ ለትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጌታቸው ረዳ አስረክበዋል።

ብፁእ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ በርክክብ ሥነ ስርዓቱ ላይ እንዳሉት፥ ድጋፉ በተፈጥሮና ሰው ሰራሽ አደጋ ከቤት ንብረታቸው ለተፈናቀሉ ወገኖች የሚውል ነው።

“የሃይማኖት መሪዎች ግጭት ሳይሆን ሰላም፣ ውድመት ሳይሆን ልማት ለማረጋገጥ ሃላፊነት አለብን” ያሉት ብፁእነታቸው ወደፊትም አስፈላጊው ድጋፍ እንደሚደረግ አስታውቀዋል።

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጌታቸው ረዳ ለተደረገው ድጋፍ አመስግነዋል።

የሃይማኖት መሪዎች ለሰላምና ልማት መረጋገጥ ሚናቸው የላቀ መሆኑን ተናግረዋል።

የተጀመረው መልካም ተግባር ተጠናክሮ እንዲቀጥልም መጠየቃቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
👍6523👎17👏8
የአዲስ አበባ ከተማ ለ6 ወራት የቤት ኪራይ ጭማሪ ማድረግ የማይቻል መሆኑን አስታወቀ
**********************************

ለሚቀጥሉት 6 ወራት የቤት ኪራይ ጭማሪ ማድረግ እንዲሁም ተከራይ ማስወጣት የማይቻል መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አሳውቋል።

የከተማ አስተዳደሩ ካቢኔ የኑሮ ውድነቱ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው የከተማዋ ነዋሪዎች ላይ የሚያሳድረውን ጫና ለመቀነስ የቤት ኪራይ ጭማሪ እንዳይደረግ በተለያዩ ተከታታይ ጊዜያት ውሳኔ ማሳለፉን አስተዳደሩ አስታውሷል።

በቀጣይም በግል ከሚደረግ ስምምነት ውጪ ማንኛውም አከራይ ለሚቀጥሉት 6 ወራት የቤት ኪራይ ጭማሪ ማድረግ እንዲሁም ተከራይ ማስወጣት የማይቻል መሆኑን የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ ጽህፈት ቤት መረጃ ያመላክታል።
👍126👎43👏1810
ትናንት ምሽት በሀገሪቱ በርካታ አካባቢዎች ተቋርጦ የነበረው የኃይል አቅርቦት ወደነበረበት ተመልሷል
********************************

ትናንት ምሽት በሀገሪቱ በርካታ አካባቢዎች ተቋርጦ የነበረው የኃይል አቅርቦት ወደነበረበት መመለሱን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታውቋል።

የኃይል መቋረጡ የተከሰተው በጊቤ 3 የኃይል ማመንጫ ጣቢያ ላይ ባጋጠመ የቴክኒክ ችግር ምክንያት መሆኑን አገልግሎቱ በማኅበራዊ ትስስር ገፁ ባሰፈረው ጽሁፍ ገልጿል።

ተቋርጦ የነበረው የኃይል አቅርቦት ወደነበረበት የተመለሰው በማመንጫ ጣቢያው ላይ ያጋጠመውን የቴክኒክ ችግር ለማስተካከል በተደረገ ከፍተኛ ጥረት መሆኑንም ጠቅሷል።

የተፈጠረው ችግር እስኪፈታ በትግዕስት ለተጠባበቁ ደንበኞቹም ተቋሙ ምስጋና አቅርቧል።
👍146👎3113👏7
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከግብፅ ፕሬዝደንት አብዱልፈታህ አልሲሲ ጋር መከሩ
************
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው እንዳስታወቁት ከግቡፁ ፕሬዝደንት አብዱልፈታህ አልሲሲ ጋር በግብፅ ካይሮ መክረዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ "በግብጽ ካይሮ ከፕሬዚዳንት አብዱልፈታሕ ኤልሲሲ ጋር በሁለትዮሽ እና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ ትብብር በሰፈነበት መንፈስ ውይይቶች አካሂደናል።" ሲሉም ነው የገለጹት።
በውይይታቸውም የሁለትዮሽ ትብብር ጉዳዮች እንዲሁም ወቅታዊ የቀጠናው ሁኔታዎች መነሳታቸውን ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስታውቀዋል።
https://www.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid0w8YCBmBKyTyWfkAfgRb59bDJCSQYLuuEkThPmN2AdYzqR2hZDrHLaVRTLzDYVCf7l
👍56👎179👏1