EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation) – Telegram
EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)
138K subscribers
38.2K photos
458 videos
80 files
13.1K links
EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation) @etvafaanoromoo1
@ETVkidschannel
@EBCWORLD1
@etventertainment1
Download Telegram
ከ20 በላይ ዩኒቨርስቲዎች ተማሪዎቻቸውን እያስመረቁ ነው
***********

በአገሪቱ የሚገኙ ከ20 በላይ ዩኒቨርስቲዎች በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ያሰለጠኗቸውን ተማሪዎች በማስመረቅ ላይ ይገኛሉ።

በዛሬው ዕለት ተማሪዎቻቸውን እያስመረቁ ከሚገኙ ዩኒቨርስቲዎች መካከል አዲስ አበባ፣ ወለጋ፣ ደብረብርሃን፣ አርባምንጭ፣ ጅግጅጋ፣ ድሬዳዋ እና ሰመራ ዩኒቨርስቲዎች ይገኙበታል፡፡
👍8216👎8👏2
የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በተለያዩ መስኮች ያሰለጠናቸውን ተማሪዎቹን እያስመረቀ ነው
*******************

የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ለ73ኛ ጊዜ ተማሪዎችን እያስመረቀ ሲሆን በዛሬው ዕለት በተለያዩ መስኮች ያሰለጠናቸውን 8 ሺህ 868 ተማሪዎቹን በማስመረቅ ላይ ይገኛል።

በምረቃ መርሃግብሩ ላይ ፕሬዚዳንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴ፣ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ጨም ሌሎች የስራ ኃላፊዎች እና እንግዶች ተገኝተዋል።

በአጠቃላይ በዛሬው ዕለት ከሚመረቁ ተማሪዎች መካከል 35 በመቶ ሴቶች ናቸው።

ዩኒቨርስቲው በ18 ካምፓሶቹ በ276 የተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ተማሪዎችን አሰልጥኖ አስመርቋል።
https://www.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid02A2dbK9sRryJqcR7tzP1r41jFLg16BV8kpfvF26XXgA91PbujcbhSwc7AwqZ6abm9l
👍3910👎8👏5
የጅማ ዩኒቨርሲቲ በዛሬው ዕለት ያስመረቃቸው መንትዮች
****************************

የጅማ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች አስመርቋል።

ከተመራቂዎችም መካከል በጅማ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የነበሩ ሶስት የተለያዩ መንትዮች ተመርቀዋል።

ተመራቂ ሜላት ደቻሳ በኤሌክትሪካል ኢንጂነሪንግ የተመረቀች ሲሆን መንትያዋ ሜሮን ደቻሳ በአርክቴክቸር የትምህርት ዘርፍ መመረቅ ችላለች።

የጅማ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት መረጃ እንደሚያመለክተው፣ እዩኤል ብዙአየሁ እና ኢዩአኪ ብዙአየሁ የተባሉ መንትዮች በኮምፒዩተር ሳይንስ የተመረቁ ተማሪዎች ናቸው።

በተመሳሳይ፣ አሊይ በዳሶ እና አማን በዳሶ በሲቪል ምህንድስና መመረቃቸውን የጅማ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት መረጃ ያመለክታል።
👍8130👎8👏5
ለአርቲስት እጅጋየሁ ሽባባው(ጂጂ) የክብር ዶክትሬት ተሰጣት
*******************

እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ለአርቲስት እጅጋየሁ ሽባባው(ጂጂ) የክብር ዶክትሬት በዛሬው ዕለት ሰጥቷታል።

የክብር ዶክተሬቱን በወላጅ እናቷ በወ/ሮ ተናኜ አማካኝነት ተቀብላለች።

ድምፃዊት፣ ገጣሚ፣ የዜማ ደራሲ እና ተዋናይት የሆነችው ሁለገቧ አርቲስት ጂጂ፣ የሀገሯን ባህልና ሙዚቃ ለዓለም በማስተዋወቅ እንዲሁም በኪነጥበብ የአዊን ህዝብ ቋንቋ እና ባህል በማሳደግ ላበረከተችው አስተዋፅኦ ነው የክብር ዶክትሬቱ የተበረከተላት።

እንጅባራ ዩኒቨርሲቲው በተለያዩ ዘርፎች ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች ዛሬ አስመርቋል።
👍8621👎9
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለአቶ ቢኒያም በለጠ እና አርቲስት ደበበ እሸቱ የክብር ዶክትሬት ዲግሪ ሰጠ
**********************************

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በተሰማሩበት መስክ አገርንና ህዝብን በቀናነት ላገለገሉት ለአቶ ቢኒያም በለጠ እና አርቲስት ደበበ እሸቱ የክብር ዶክትሬት ዲግሪ ሰጥቷል።

ዩኒቨርሲቲው ለመቄዶኒያ በጐ አድራጎት ማህበር መስራች አቶ ቢኒያም በለጠ ላከናወኗቸው የበጎ አድራጎ ስራዎች የክብር ዶክትሬት በዛሬው እለት የሰጠ ሲሆን፣ አቶ ቢኒያም በሰው ልጆች ደህንነት ለሀገር የማይታካ አስተዋጽኦ ማበርከታቸው በመድረኩ ተገልጿል።

የክብር ዶክትሬት የተሰጣቸው አርቲስት ደበበ እሸቱም የህይወቱ ጥሪ በሆነው የኪነ ጥበብ ዘርፍ ለአገር ትልቅ ውለታ መዋሉ ለዚህ ክብር እንዳበቃው ተነግሯል።

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በመደበኛ ፣ በማታና በርቀት ትምህርት መርሐ ግብር ያሰለጠናቸውን 8 ሺህ 642 የቅድመ ምረቃና ድሕረ ምረቃ ተማሪዎችን በሚሊኒየም አዳራሽ እያስመረቀ ነው።

በምርቃት ስነ ስርዓቱ ላይ የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ፣ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንንን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ እንግዶችና የተመራቂ ቤተሰቦች ተገኝተዋል።
👍10435👎13👏8
54 ኮርሶችን A+ ያገኘው ተመራቂ ተማሪ የወርቅ ሜዳሊያውን ለእናቱ አበረከተ
**********************************

54 ኮርሶችን A+ ያገኘው ተመራቂ ተማሪ "ለእኔ ሳይሆን ስለእኔ ብዙ ለከፈለችው ወላጅ እናቴ" ይሁንልኝ በማለት ሜዳልያውን እንደተቀበለ ወደ እናቱ ሮጦ በመሄድ አጥልቆላታል።

በእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ የዋንጫ እና የወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚ የሆነው ተመራቂ ተማሪ ዳግም ተስፋዬ ይህን አስደናቂ ተግባር ፈጸሟል።

ተመራቂው በዕፅዋት ሳይንስ ትምህርት ክፍል ከወሰዳቸው 64 ኮርሶች 54ቱን ኮርሶች A+ በማምጣት ተሸላሚ ሆኗል።

በወንደሰን ሞላ
👍28484👏45👎9
የብዙ ሺህ አረጋውያን እና አቅመ ደካሞች ዋርካ - አቶ ቢኒያም በለጠ
*******************

ሰዎች ተክለሰውነቱን እና ገፅታውን በመመልከት ስለ እርሱ በልባቸው ይሆናል ያሉትን ይገምታሉ። የሰውን ዓላማ እና ሊደርስበት የሚቻለው ሕልም ማወቅ የሚቻለው የዛ ሰው ሥራዎች ስለ እሱ ሲመሰክሩላቸው ነው።

የ10 ልጆች አባት አቶ በለጠ አዲስ እና እናት ወይዘሮ ፅጌ በቀለ ከልጆቻቸው የአካል ምቾት እና ድሎት ይልቅ ያስጨንቃቸው የነበረው በልባቸው ውስጥ የተዘራው ፍቅር እና መልካም ሥነ ምግባር ነበር። በስብዕናቸው ላይ የተደከመባቸው ልጆችም ለሰው ልጆች ፍቅርን፣ ርኅራሄን፣ ትህትናን እና ማካፈልን መለያቸው አደረጉ።

በሚያዝያ ወር 1968 ዓ.ም የተወለደው ቢንያም በለጠ ከእናቱ ፅጌ በቀለ እና ከአባቱ በለጠ አዲስ በአዲስ አበባ ተወለደ። በአዲስ አበባ ኮተቤ ብረታ ብረት አካባቢ ያደገው ቢንያም፣ ዕድሜው ለትምህርት ሲደርስ ወደ ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ትምህርት ቤት አመራ።
https://www.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid029cpmJCyfKRj7s5MFBSBDgvutGi4QpNE7AHjj8qW4HsTjLEwthT33KKjD4ftfe8vql
👍9725👎9👏3
www.ebc.et
**********
በእጅዎ ባለ ስልክ፣ቢያሻዎ በኮምፒውተርዎ መከታተል እንዲችሉ ዘምኖ እና ምቹ ሆኖ ቀርቦልዎታል፡፡
ከዘመኑ ሚዲያ ተቀዳሚ አማራጭ እየሆነ የመጣው የድረ ገፅ አካል የሆነው www.ebc.et በአዳዲስ ገጽታዎች እና አቀራረብ ወደ እናንተ መድረሱን ይቀጥላል፡፡
👏32👍20👎1312
አንጋፋው አጥቂ ሳላዲን ሰዒድ ጫማውን ሰቀለ
****************

በተለያዩ ክለቦች እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን ተጫዋች የነበረው ሳላዲን ሰዒድ ከእግር ኳስ ራሱን አገለለ።

በኢትዮጵያ እግር ኳስ ከታዩ ምርጥ አጥቂዎች መካከል አንዱ የሆነው ሳላዲን ሰዒድ ከስኬታማ የአስራ አምስት ዓመታት በላይ የእግር ኳስ ህይወት ቆይታ በኋላ በዛሬው ዕለት ጫማ መስቀሉን ገልጿል።

ሳላዲን ለእግር ኳስ ቤተሰቡ ያለውን ምስጋናም ማቅረቡን ሶከር ኢትዮጵያ ዘግቧል፡፡

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ከዚህ ቀደም ለቅዱስ ጊዮርጊስ የተጫወተ ሲሆን አምና በሲዳማ ቡና ቆይታ ማድረጉ የሚታወስ ነው፡፡
👍11119👏10👎9