EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation) – Telegram
EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)
138K subscribers
38.3K photos
462 videos
80 files
13.1K links
EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation) @etvafaanoromoo1
@ETVkidschannel
@EBCWORLD1
@etventertainment1
Download Telegram
ለአርቲስት እጅጋየሁ ሽባባው(ጂጂ) የክብር ዶክትሬት ተሰጣት
*******************

እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ለአርቲስት እጅጋየሁ ሽባባው(ጂጂ) የክብር ዶክትሬት በዛሬው ዕለት ሰጥቷታል።

የክብር ዶክተሬቱን በወላጅ እናቷ በወ/ሮ ተናኜ አማካኝነት ተቀብላለች።

ድምፃዊት፣ ገጣሚ፣ የዜማ ደራሲ እና ተዋናይት የሆነችው ሁለገቧ አርቲስት ጂጂ፣ የሀገሯን ባህልና ሙዚቃ ለዓለም በማስተዋወቅ እንዲሁም በኪነጥበብ የአዊን ህዝብ ቋንቋ እና ባህል በማሳደግ ላበረከተችው አስተዋፅኦ ነው የክብር ዶክትሬቱ የተበረከተላት።

እንጅባራ ዩኒቨርሲቲው በተለያዩ ዘርፎች ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች ዛሬ አስመርቋል።
👍8621👎9
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለአቶ ቢኒያም በለጠ እና አርቲስት ደበበ እሸቱ የክብር ዶክትሬት ዲግሪ ሰጠ
**********************************

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በተሰማሩበት መስክ አገርንና ህዝብን በቀናነት ላገለገሉት ለአቶ ቢኒያም በለጠ እና አርቲስት ደበበ እሸቱ የክብር ዶክትሬት ዲግሪ ሰጥቷል።

ዩኒቨርሲቲው ለመቄዶኒያ በጐ አድራጎት ማህበር መስራች አቶ ቢኒያም በለጠ ላከናወኗቸው የበጎ አድራጎ ስራዎች የክብር ዶክትሬት በዛሬው እለት የሰጠ ሲሆን፣ አቶ ቢኒያም በሰው ልጆች ደህንነት ለሀገር የማይታካ አስተዋጽኦ ማበርከታቸው በመድረኩ ተገልጿል።

የክብር ዶክትሬት የተሰጣቸው አርቲስት ደበበ እሸቱም የህይወቱ ጥሪ በሆነው የኪነ ጥበብ ዘርፍ ለአገር ትልቅ ውለታ መዋሉ ለዚህ ክብር እንዳበቃው ተነግሯል።

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በመደበኛ ፣ በማታና በርቀት ትምህርት መርሐ ግብር ያሰለጠናቸውን 8 ሺህ 642 የቅድመ ምረቃና ድሕረ ምረቃ ተማሪዎችን በሚሊኒየም አዳራሽ እያስመረቀ ነው።

በምርቃት ስነ ስርዓቱ ላይ የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ፣ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንንን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ እንግዶችና የተመራቂ ቤተሰቦች ተገኝተዋል።
👍10435👎13👏8
54 ኮርሶችን A+ ያገኘው ተመራቂ ተማሪ የወርቅ ሜዳሊያውን ለእናቱ አበረከተ
**********************************

54 ኮርሶችን A+ ያገኘው ተመራቂ ተማሪ "ለእኔ ሳይሆን ስለእኔ ብዙ ለከፈለችው ወላጅ እናቴ" ይሁንልኝ በማለት ሜዳልያውን እንደተቀበለ ወደ እናቱ ሮጦ በመሄድ አጥልቆላታል።

በእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ የዋንጫ እና የወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚ የሆነው ተመራቂ ተማሪ ዳግም ተስፋዬ ይህን አስደናቂ ተግባር ፈጸሟል።

ተመራቂው በዕፅዋት ሳይንስ ትምህርት ክፍል ከወሰዳቸው 64 ኮርሶች 54ቱን ኮርሶች A+ በማምጣት ተሸላሚ ሆኗል።

በወንደሰን ሞላ
👍28484👏45👎9
የብዙ ሺህ አረጋውያን እና አቅመ ደካሞች ዋርካ - አቶ ቢኒያም በለጠ
*******************

ሰዎች ተክለሰውነቱን እና ገፅታውን በመመልከት ስለ እርሱ በልባቸው ይሆናል ያሉትን ይገምታሉ። የሰውን ዓላማ እና ሊደርስበት የሚቻለው ሕልም ማወቅ የሚቻለው የዛ ሰው ሥራዎች ስለ እሱ ሲመሰክሩላቸው ነው።

የ10 ልጆች አባት አቶ በለጠ አዲስ እና እናት ወይዘሮ ፅጌ በቀለ ከልጆቻቸው የአካል ምቾት እና ድሎት ይልቅ ያስጨንቃቸው የነበረው በልባቸው ውስጥ የተዘራው ፍቅር እና መልካም ሥነ ምግባር ነበር። በስብዕናቸው ላይ የተደከመባቸው ልጆችም ለሰው ልጆች ፍቅርን፣ ርኅራሄን፣ ትህትናን እና ማካፈልን መለያቸው አደረጉ።

በሚያዝያ ወር 1968 ዓ.ም የተወለደው ቢንያም በለጠ ከእናቱ ፅጌ በቀለ እና ከአባቱ በለጠ አዲስ በአዲስ አበባ ተወለደ። በአዲስ አበባ ኮተቤ ብረታ ብረት አካባቢ ያደገው ቢንያም፣ ዕድሜው ለትምህርት ሲደርስ ወደ ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ትምህርት ቤት አመራ።
https://www.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid029cpmJCyfKRj7s5MFBSBDgvutGi4QpNE7AHjj8qW4HsTjLEwthT33KKjD4ftfe8vql
👍9725👎9👏3
www.ebc.et
**********
በእጅዎ ባለ ስልክ፣ቢያሻዎ በኮምፒውተርዎ መከታተል እንዲችሉ ዘምኖ እና ምቹ ሆኖ ቀርቦልዎታል፡፡
ከዘመኑ ሚዲያ ተቀዳሚ አማራጭ እየሆነ የመጣው የድረ ገፅ አካል የሆነው www.ebc.et በአዳዲስ ገጽታዎች እና አቀራረብ ወደ እናንተ መድረሱን ይቀጥላል፡፡
👏32👍20👎1312
አንጋፋው አጥቂ ሳላዲን ሰዒድ ጫማውን ሰቀለ
****************

በተለያዩ ክለቦች እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን ተጫዋች የነበረው ሳላዲን ሰዒድ ከእግር ኳስ ራሱን አገለለ።

በኢትዮጵያ እግር ኳስ ከታዩ ምርጥ አጥቂዎች መካከል አንዱ የሆነው ሳላዲን ሰዒድ ከስኬታማ የአስራ አምስት ዓመታት በላይ የእግር ኳስ ህይወት ቆይታ በኋላ በዛሬው ዕለት ጫማ መስቀሉን ገልጿል።

ሳላዲን ለእግር ኳስ ቤተሰቡ ያለውን ምስጋናም ማቅረቡን ሶከር ኢትዮጵያ ዘግቧል፡፡

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ከዚህ ቀደም ለቅዱስ ጊዮርጊስ የተጫወተ ሲሆን አምና በሲዳማ ቡና ቆይታ ማድረጉ የሚታወስ ነው፡፡
👍11119👏10👎9
https://news.1rj.ru/str/etvafaanoromoo1
***************
የኢቲቪ አፋን ኦሮሞ የቴሌግራም ቻናል
Etv Afaan Oromoo ቤተሰብ ይሁኑ
ለአዳዲስ መረጃዎች፣ መዝናኛ እና ትምህርታዊ ፕሮግራሞች ትክክለኛውና Verified የሆነውን
የቴሌግራም ቻናልን ቤተሰብ ይሁኑ፡፡
👎86👍5522👏15
በወራቤ ከተማ አንዲት እናት በአንድ ጊዜ 3 ልጆችን በሰላም ተገላገሉ
*********************

በወራቤ ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል አንዲት እናት ሁለት ሴት ልጆችን እና አንድ ወንድ ልጅ በአንድ ጊዜ በሰላም ተገላግለዋል።

ከሆስፒታሉ ማህጸን እና ጽንስ ክፍል የተገኘው መረጃ እንደሚያሳየው ሕፃናቱ 2.7 ፣ 2.6 እና 2.5 ኪሎ ግራም ይመዝናሉ።

እናት ወ/ሮ ሀይሪያ ኑርሰቦ ከአልቾ ውሪሮ ወረዳ በሪፈር ወደ ሆስፒታሉ መሔዳቸው እና በቀዶ ሕክምና ሦስቱን ልጆች መገላገላቸው ታውቋል።

https://www.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid0fg9TurMJ9ojyr96bxnRfHtWQgrJe5dPQtY1osVoTEPZz6R1oC7m7TipiydTid7hwl
👍7117👎8👏4
እንጦጦ ፓርክ አካባቢ እየተንቀሳቀሱ ወንጀል ሲፈፅሙ የነበሩ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር ዋሉ
****************

በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 ልዩ ቦታው እንጦጦ ፓርክ መግቢያ ቅዱስ ሚከኤል ቤተ ክርስቲያን አካባቢ እየተንቀሳቀሱ ወንጀል ሲፈፅሙ የነበሩ ሦስት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ።

ግለሰቦቹ የአካባቢውን ጭር ማለት እና የፖሊስ አባላትን እግር ጠብቀው ወንጀል ሲፈፅሙ መቆየታቸውን የምርመራ መዝገባቸው ያስረዳል። ...

https://www.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid0QKYB96VDJJKGsJvqG2bxRD4ENR61FNGEjM8mjFT4zah5YS5rfnV4oRqWzB7AEBErl
👍10217👎14👏7
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ሶስት የዳቦ ፋብሪካዎችን መረቁ
*******************************

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ሶስትየዳቦ ፋብሪካዎችን መርቀዋል።

በኮልፌ አራት መንታ እና ብርጭቆ አካባቢዎች ላይ ነው የዳቦ ፋብሪካዎች የተገነቡት።

ፋብሪካዎቹ በቀን እስከ 1 ሚሊዮን ዳቦ የሚያመርቱ ሲሆን በሙሉ አቅማቸው ወደ ስራ ሲገቡ የማምረት አቅማቸው እስከ1 ነጥብ 6 ሚሊዮን ከፍ ይላል።

ከለውጡ በፊት አዲስ አበባ በቀን ዳቦ የማምረት አቅሟ 3 መቶ ሺ ሲሆን አሁን ላይ ከ 4 ሚሊዮን በላይ መሆኑ በምረቃ ስነ ስርዓቱ ተገልጿል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በ3ቱም ፋብሪካ በተገነቡባቸው አካባቢዎች ለሚገኙ አቅመ ደካሞች የዳቦ መጋገሪያ ማሽኖችን አበርክተዋል።


በጥላሁን ካሳ
👍45👏22👎2011
ከድሬዳዋ 10ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ከባድ የጭነት መኪና ተገልብጦ መንገዱ በመዘጋቱ የትራፊክ ፍሰቱን እያስተጓጎለ ነው
*******************************************

ከድሬዳዋ 10ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ሀርላ በሚባለው አካባቢ ከባድ የጭነት መኪና ተገልብጦ መንገዱ በመዘጋቱ የትራፊክ ፍሰቱን እያስተጓጎለ ነው።

መንገዱ የኢትዮ - ጂቡቲ ወጭና ገቢ ንግድ መተላለፊያ በመሆኑ በሺዎች የሚቆጠሩ ከባድ ተሽከርካሪዎች መንቀሳቀስ አልቻሉም።

የአካባቢው ትራፊክ ፖሊሶች በስፍራው የተገኙ ሲሆን ችግሩ ሌሊት ላይ መፈጠሩን ተናግረዋል።

ከድሬዳዋ ወደ አዲስአበባ የሚሄዱ የህዝብ ትራንስፖርት ተሽከርካሪዎችም ማለፍ ባለመቻላቸው መንገደኞች መጉላላት እየደረሰባቸው ይገኛል ።

የመንገዱን ፍሰት ወደነበረበት ለመመለስ የሚመለከተው አካል አፋጣኝ መፍትሔ ያሻል ነው ያሉት።

በሞላ አለማየሁ
👍648👎8
የአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ለቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው የክብር ዶክትሬት ሰጠ
*********************************

የአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ የ2015 ዓ.ም ተመራቂ ተማሪዎችን እያስመረቀ ነው።

ዩኒቨርሲቲው ለቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው የክብር ዶክትሬት ሰጥቷል።

የክብር ዶክትሬቱ የተሰጠው ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በትምህርትና የተለያዩ ዘርፎች ላይ ለዜጎች እያበረከቱት ላለው ተግባር እውቅና ለመስጠት እንደሆነ ተገልጿል።
https://www.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid02syj186XeXXqYKikozagd5dUksfTKRp1PpkjrwsMXyhNuxrdn6SBnSDQudB7qtsJNl
👍76👎3619
ሸይኽ ሐጅ ኢብራሂም ቱፋ በአሜሪካ ሚኒሶታ ከሚገኘው "ኢስላሚክ ዩንቨርስቲ" እና ከአርሲ ዩኒቨርሲቲ የክብር ዶክትሬት ተበረከተላቸው
*****************************************

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ዋና ፕሬዝዳንት የሆኑት ሸይኽ ሀጅ ኢብራሂም ቱፋ በኢትዮጵያ ሰላም፣ በሃይማኖቶች መከባበር እንዲሁም በሀገራዊና ኃይማኖታዊ ልማት ባበረከቱት አስተዋጽኦ በዛሬው ዕለት በአሜሪካ ከሚገኘው የሚኒሶታ ኢስላማዊ ዩኒቨርስቲ እንዲሁም ከአርሲ ዩኒቨርሲቲ የክብር ዶክትሬት አግኝተዋል።

ሸይኽ ሀጅ ኢብራሂም ቱፋ በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት አርሲ ዞን በቀድሞ አጠራር በአርሲ ክፍለሀገር በአርባጉጉ አውራጁ በ1984 የተከሰተዉን የእርስ በእርስ ጦርነት በመግታትና በማስቆም በወቅቱ የአርሲ ዞን ሀገረ ስብከት ኃላፊ ከሆኑት ብጹዕ አቡነ ናትናዔል ጋር በመጣመር የሰላም ዘብነታቸውን አረጋግጠዋል።

በኦሮሚያ ክልል በወለጋና በተለያዩ አከባቢዎች በመንግስትና በታጣቂዎች መካከል ሕይወታቸውን አደጋ ላይ በመጣል ለሰላም በመትጋት እርቅና ሰላም ያሰፈኑባቸው በርካታ አጋጣሚዎች ታይተዋል።
https://www.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid02KMYsDSMMkofNAK9r3FV8E18z2JQgCz1XZVQM4bs7Lrj5fLizmr9V85naj5jDvgV1l
👍86👎2212
ድሬድዋ መግቢያ ሀርላ አካባቢ የትራፊክ ፍሰቱ ወደ መደበኛ እንቅስቃሴው ተመልሷል
***********************************

በዛሬው ዕለት ከድሬዳዋ 10 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ሀርላ በሚባለው አካባቢ መንገዱን ዘግቶት የነበረው እቃ ጫኝ ኮንቴነር በክሬን በመነሳቱ የትራፊክ ፍሰቱ ወደ መደበኛ እንቅስቃሴው ተመልሷል።

አሽከርካሪዎች እና ተሳፋሪዎች የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ኢቢሲ) መረጃውን ለሚመለከታቸው አካላት በፍጥነት በማድረስ እንዲፈታ ስላደረገ አመስግነዋል።

ከድሬዳዋ 10ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ሀርላ በሚባለው አካባቢ ከባድ የጭነት መኪና ተገልብጦ መንገዱ በመዘጋቱ የትራፊክ ፍሰቱን እያስተጓጎለ መሆኑን በጠዋት ዘገባችን አድርሰን እንደነበር ይታወሳል።

በሞላ አለማየሁ
👍629👎7👏1