EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation) – Telegram
EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)
137K subscribers
38.4K photos
462 videos
80 files
13.2K links
EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation) @etvafaanoromoo1
@ETVkidschannel
@EBCWORLD1
@etventertainment1
Download Telegram
የወላይታ ዞን ለአቶ ሽመልስ አብዲሳ የወላይታ ህዝብ ስጦታ አበረከተ
*********

የወላይታ ዞን ለኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ የወላይታ ህዝብ ስጦታ አበርክቷል።

ስጦታው የንጉስ ካዎ ጦና እና በምስራቅ አፍሪካ ብቸኛ የሆነው የአጆራ መንትያ ፏፏቴ ሲሆን ስጦታውን የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሳሙኤል ፎላ፣ የዞኑ የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ አሳምነው አይዛን ጨምሮ የሀገር ሽማግሌዎች በወላይታ ህዝብ ስም አበርክተዋል።

ለተደረገው ደማቅ አቀባበልና ለተወዳጁ ስጦታ ርዕሰ መስተዳድሩ ምስጋና አቅርበዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ በወላይታ ሶዶ ከተማ በሚኖራቸው ቆይታ "ከዕዳ ወደ ምንዳ" 4ኛ ዙር የመንግስት አመራሮች ስልጠና ላይ በመገኘት የዕለቱን ማጠቃለያ ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።
👎4025👍22
ሰሜን ኮሪያ በአዲሱ የስለላ ሳተላይቷ የኋይት ሃውስን እና የፔንታጎንን ምስል አግኝቻለሁ አለች
************

የሰሜን ኮሪያ የብሔራዊ ኤሮስፔስ ቴክኖሎጂ አስተዳደር በቅርቡ በሳተላይት ስለተላኩ ምስሎች አጭር ማብራሪያ ሰጥቷል።

ሰሜን ኮሪያ እንዳስታወቀችው በወታደራዊ የስለላ ሳተላይቷ አማካኝነት ዋይት ሃውስን እና ፔንታጎንን ጨምሮ የተለያዩ ወታደራዊ ቦታዎችን ምስል መግኘቷን ገልጻለች።

ባለፈው ሳምንት ሰሜን ኮሪያ በዚህ አመት ሶስተኛ ሙከራዋ የሆነውን የስለላ ሳተላይቷን ወደ ህዋ "በተሳካ ሁኔታ" ማምጠቋን አስታውቃ ነበር።

የሰሜን ኮሪያ መሪ ኪም ጆንግ ኡን የጣሊያንን ዋና ከተማ ሮም፣ ከፓስፊኳ ደሴት ጉዋም ህዋ የተነሳ የአሜሪካ አንደርስን አየር ሃይል ማዘዣ እና ሌሎች ምስሎችን ስለመመልከታቸው የኮሪያ ማእከላዊ የዜና ኤጀንሲ ዘግቧል።

በተጨማሪም በኖርፎልክ የሚገኘውን የአሜሪካ የባህር ኃይል ጣቢያ እና በቨርጂኒያ ኒውፖርት ኒውስ ዶክያርድ፣ የተነሱትን ዝርዝር ምስሎች እንዲሁም ዋሽንግተን ውስጥ ኋይት ሃውስ እና ፔንታጎን እንዲሁም "ሌሎች ዕቃዎች" የሚል ዝርዝር ምስሎች ለፕሪዚዳንቱ ቀርቦላቸዋል።

"አራት የአሜሪካ የባሕር ኃይል የኑክሌር ተሸካሚዎች እና አንድ የእንግሊዝ አውሮፕላን ተሸካሚ በኖርፎልክ የባሕር ኃይል ጣቢያ እና በኒውፖርት ኒውስ ዶክያርድ ምስሎች ላይ ተስተውሏል ሲል ዘገባው አክሎ ገልጿል።
👍5915
በገበታ ለትውልድ ፕሮጀከት የተያዘው የደንቢ ተፈጥሮ ምን ይመስላል?
**********************

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ቤንች ሸኮ ዞን የሚገኝ እና በ1972 ዓ.ም ለኃይል ማመንጫ ተብሎ የተገነባ ቦታ ነበር፤

በ1986 ዓ.ም የግንባታ ሥራው ተጠናቅቆ እስከ 1995 ዓ.ም ድረስ በአካባቢው ላሉ 5 ከተሞች 0.8 ሜጋ ዋት በማመንጨት የ24 ሰዓት የመብራት አገልግሎት መስጠት ችሏል።

ግልገል ጊቤ ቁጥር 1 የኃይል ማመንጫ ለአካባቢው የመብራት አገልግሎት መስጠት ሲጀምር ደንቢ ወደ ቱሪስት መስህብነት ተለውጦ በአከባቢው ማኅበረሰብ ዘንድ እየተጎበኘ ቆይቷል።

ደንቢ በውስጡ 90 ሔክታር ላይ ያረፈ ሐይቅ፣ ከ50 ሜትር በላይ ርዝመት ያላቸው ሁለት ፏፏቴዎች እና 640 ደረጃዎች ይገኙበታል።

ደንቢ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የገበታ ለትውልድ ፕሮጀክት ውስጥ ተካቶ የግንባታ ቅድመ ዝግጅት ላይ ይገኛል።

በናርዶስ አዳነ
👍5811👎1
አሜሪካ ለጋዛ ሰብአዊ እርዳታ የሚውሉ ሶስት ወታደራዊ አውሮፕላኖችን ወደ ግብፅ ልትልክ ነው
***********

በእስራኤል እና በሃማስ መካከል በተደረገው ጊዜያዊ የተኩስ አቁም ስምምነት ተከትሎ አሜሪካ በጋዛ ድጋፍ ለሚሹ ወገኖች የሚሆን ሰብአዊ እርዳታ የጫኑ ሶስት ወታደራዊ አውሮፕላኖችን ከማክሰኞ ጀምሮ ወደ ግብፅ እንደምትልክ የሀገሪቱ ባለስልጣናት አስታውቀዋል።

እርዳታ የጫኑት አውሮፕላኖች ምግብ፣ የህክምና ቁሳቁሶችን እና ሌሎች ለሰብዓዊ አገልጋሎት የሚያግዙ መሳሪያዎችን የሚይዙ ናቸው ተብሏል፡፡

በፈረንጆቹ ጥቅምት 7 በሃማስ እና በእስራኤል መካከል ከተቀሰቀሰው ጦርነት ወዲህ አሜሪካ እርዳታ የጫኑ አውሮፕላኖችን ወደ ጋዛ ስትልክ ይህ የመጀመሪያው መሆኑም ተጠቅሷል።

በረራዎቹ የጀመሩት የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ወደ ጋዛ ተጨማሪ ርዳታ ለመላክ የተኩስ አቁም ስምምነት መራዘሙን እጠቀማለሁ ካሉ ከአንድ ቀን በኋላ ሲሆን፤ የተኩስ አቁም ስምምነት ጊዜውን የበለጠ ለማራዘም ዓለም አቀፍ ጥረቶች ይቀጥላሉ ተብሏል።

በዛሬው ዕለት የጋዛው የተኩስ አቀም መራዘሙን ተከትሎ እስራኤል ተጨማሪ 33 እስረኞችን ሀማስ ደግሞ 11 ታጋቾችን መልቀቃቸው ተጠቅሷል።

በድርድሩ በርካታ አካላት የተሳተፉ ሲሆን፤ በዚህም እስካሁን 58 ታጋቾች ነጻ የወጡ ሲሆን ከአርብ ዕለት ጀምሮ 117 ፍልስጥኤማውያን እስረኞች መለቀቃቸውም ተዘግቧል።

በእስራኤል እና በሐማስ መካከል ለአራት ቀናት የተደረሰው ጦርነት ጋብ የማድረግ ስምምነት ዘላቂ እንዲሆን ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ግፊት እያደረገ መሆኑን ቢቢሲ ዘግቧል።
👍686👎4
Live stream finished (5 hours)
ኢትዮ ቴሌኮም 5ጂ የሞባይል ኔትዎርክ አገልግሎትን በጅግጅጋ ከተማ አስጀመረ
*********************
ኢትዮ ቴሌኮም የአምስተኛው ትውልድ 5ጂ የሞባይል ኔትዎርክ አገልግሎትን በምስራቅ ምስራቅ ሪጅ ጅግጅጋ ከተማ አስጀምሯል።
የ5ጂ የሞባይል ኔትዎርክ አገልግሎት እስከ 10 ጊ.ባ በሰከንድ የሚደርስ ከፍተኛ ፍጥነት ያለው ገመድ አልባ የኔትዎርክ ቴክኖሎጂ ነው።
የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ት ፍሬህይወት ታምሩ የአምስተኛው ትውልድ 5ጂ የሞባይል ኔትዎርክ አገልግሎት ዘመኑ የደረሰበት ከፍተኛው ቴክኖሎጂ መሆኑን አንስተዋል።
አገልግሎቱ ምርታማነትን ለማሳደግ እና ቀልጣፋ አገልግሎትን ተደራሽ ለማድረግ ያግዛል።
በተለይ የግብርና፣ የማዕድን፣ የትምህርት ፣ የጤና እና የመረጃ ልውውጥን በማሳደግ ዲጂታል ኢኮኖሚን ለማዳበር ያለው ፋይዳ የጎላ ነው ብለዋል።
የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ኢብራሂም ኡስማን በክልሉ የ5ጂ ኔትዎርክ አገልግሎት በጅግጅጋ መጀመሩ የአካባቢውን ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ለማሳደግ ያግዛል።
የጅግጅጋ ከተማ ከአዲስ አበባ እና አዳማ በመቀጠል የአምስተኛው ትውልድ 5G የሞባይል ኔትዎርክ አገልግሎት ተጠቃሚ የሆነች ሶስተኛዋ ከተማ ናት።
በማስጀመሪያ መርሀ ግብሩ ላይ የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ኢብራሂም ኡስማን፣ የጅግጅጋ ከተማ ከንቲባ ኢኒጂነር ዚያድ አብዲ፣ የመንግስት ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች እና የአካባቢው ነዋሪዎች ተገኝተዋል።
በቴድሮስ ታደሰ
👍388👏1
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በቼክ ሪፐብሊክ መንግስት ጽሕፈት ቤት በጠቅላይ ሚኒስትር ፔትር ፊያላ አቀባበል ተደረገላቸው
**********************************

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በቼክ ሪፐብሊክ መንግስት ጽሕፈት ቤት በጠቅላይ ሚኒስትር ፔትር ፊያላ በይፋዊ አቀባበል ሥነ ሥርዓት አቀባበል ተደርጎላቸዋል::

ሁለቱ መሪዎች በሁለትዮሽ ውይይታቸው በመከላከያ ዘርፍ የቆየ ትብብራቸውን በማስፋት በግብርና፣ በማዕድን ልማት እና ቱሪዝም ትብብራቸውን ለማጠናከር መወሰናቸውን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

የቼኩ ጠቅላይ ሚኒስትር ባላፉት ቅርብ ሳምንታት ኢትዮዽያን በመጎብኘት ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጋር ውይይት አድርገው እንደ ነበር ይታወሳል።
👍8921👎14👏9