EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation) – Telegram
EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)
138K subscribers
38.3K photos
462 videos
80 files
13.1K links
EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation) @etvafaanoromoo1
@ETVkidschannel
@EBCWORLD1
@etventertainment1
Download Telegram
በገበታ ለትውልድ ፕሮጀከት የተያዘው የደንቢ ተፈጥሮ ምን ይመስላል?
**********************

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ቤንች ሸኮ ዞን የሚገኝ እና በ1972 ዓ.ም ለኃይል ማመንጫ ተብሎ የተገነባ ቦታ ነበር፤

በ1986 ዓ.ም የግንባታ ሥራው ተጠናቅቆ እስከ 1995 ዓ.ም ድረስ በአካባቢው ላሉ 5 ከተሞች 0.8 ሜጋ ዋት በማመንጨት የ24 ሰዓት የመብራት አገልግሎት መስጠት ችሏል።

ግልገል ጊቤ ቁጥር 1 የኃይል ማመንጫ ለአካባቢው የመብራት አገልግሎት መስጠት ሲጀምር ደንቢ ወደ ቱሪስት መስህብነት ተለውጦ በአከባቢው ማኅበረሰብ ዘንድ እየተጎበኘ ቆይቷል።

ደንቢ በውስጡ 90 ሔክታር ላይ ያረፈ ሐይቅ፣ ከ50 ሜትር በላይ ርዝመት ያላቸው ሁለት ፏፏቴዎች እና 640 ደረጃዎች ይገኙበታል።

ደንቢ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የገበታ ለትውልድ ፕሮጀክት ውስጥ ተካቶ የግንባታ ቅድመ ዝግጅት ላይ ይገኛል።

በናርዶስ አዳነ
👍5811👎1
አሜሪካ ለጋዛ ሰብአዊ እርዳታ የሚውሉ ሶስት ወታደራዊ አውሮፕላኖችን ወደ ግብፅ ልትልክ ነው
***********

በእስራኤል እና በሃማስ መካከል በተደረገው ጊዜያዊ የተኩስ አቁም ስምምነት ተከትሎ አሜሪካ በጋዛ ድጋፍ ለሚሹ ወገኖች የሚሆን ሰብአዊ እርዳታ የጫኑ ሶስት ወታደራዊ አውሮፕላኖችን ከማክሰኞ ጀምሮ ወደ ግብፅ እንደምትልክ የሀገሪቱ ባለስልጣናት አስታውቀዋል።

እርዳታ የጫኑት አውሮፕላኖች ምግብ፣ የህክምና ቁሳቁሶችን እና ሌሎች ለሰብዓዊ አገልጋሎት የሚያግዙ መሳሪያዎችን የሚይዙ ናቸው ተብሏል፡፡

በፈረንጆቹ ጥቅምት 7 በሃማስ እና በእስራኤል መካከል ከተቀሰቀሰው ጦርነት ወዲህ አሜሪካ እርዳታ የጫኑ አውሮፕላኖችን ወደ ጋዛ ስትልክ ይህ የመጀመሪያው መሆኑም ተጠቅሷል።

በረራዎቹ የጀመሩት የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ወደ ጋዛ ተጨማሪ ርዳታ ለመላክ የተኩስ አቁም ስምምነት መራዘሙን እጠቀማለሁ ካሉ ከአንድ ቀን በኋላ ሲሆን፤ የተኩስ አቁም ስምምነት ጊዜውን የበለጠ ለማራዘም ዓለም አቀፍ ጥረቶች ይቀጥላሉ ተብሏል።

በዛሬው ዕለት የጋዛው የተኩስ አቀም መራዘሙን ተከትሎ እስራኤል ተጨማሪ 33 እስረኞችን ሀማስ ደግሞ 11 ታጋቾችን መልቀቃቸው ተጠቅሷል።

በድርድሩ በርካታ አካላት የተሳተፉ ሲሆን፤ በዚህም እስካሁን 58 ታጋቾች ነጻ የወጡ ሲሆን ከአርብ ዕለት ጀምሮ 117 ፍልስጥኤማውያን እስረኞች መለቀቃቸውም ተዘግቧል።

በእስራኤል እና በሐማስ መካከል ለአራት ቀናት የተደረሰው ጦርነት ጋብ የማድረግ ስምምነት ዘላቂ እንዲሆን ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ግፊት እያደረገ መሆኑን ቢቢሲ ዘግቧል።
👍686👎4
Live stream finished (5 hours)
ኢትዮ ቴሌኮም 5ጂ የሞባይል ኔትዎርክ አገልግሎትን በጅግጅጋ ከተማ አስጀመረ
*********************
ኢትዮ ቴሌኮም የአምስተኛው ትውልድ 5ጂ የሞባይል ኔትዎርክ አገልግሎትን በምስራቅ ምስራቅ ሪጅ ጅግጅጋ ከተማ አስጀምሯል።
የ5ጂ የሞባይል ኔትዎርክ አገልግሎት እስከ 10 ጊ.ባ በሰከንድ የሚደርስ ከፍተኛ ፍጥነት ያለው ገመድ አልባ የኔትዎርክ ቴክኖሎጂ ነው።
የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ት ፍሬህይወት ታምሩ የአምስተኛው ትውልድ 5ጂ የሞባይል ኔትዎርክ አገልግሎት ዘመኑ የደረሰበት ከፍተኛው ቴክኖሎጂ መሆኑን አንስተዋል።
አገልግሎቱ ምርታማነትን ለማሳደግ እና ቀልጣፋ አገልግሎትን ተደራሽ ለማድረግ ያግዛል።
በተለይ የግብርና፣ የማዕድን፣ የትምህርት ፣ የጤና እና የመረጃ ልውውጥን በማሳደግ ዲጂታል ኢኮኖሚን ለማዳበር ያለው ፋይዳ የጎላ ነው ብለዋል።
የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ኢብራሂም ኡስማን በክልሉ የ5ጂ ኔትዎርክ አገልግሎት በጅግጅጋ መጀመሩ የአካባቢውን ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ለማሳደግ ያግዛል።
የጅግጅጋ ከተማ ከአዲስ አበባ እና አዳማ በመቀጠል የአምስተኛው ትውልድ 5G የሞባይል ኔትዎርክ አገልግሎት ተጠቃሚ የሆነች ሶስተኛዋ ከተማ ናት።
በማስጀመሪያ መርሀ ግብሩ ላይ የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ኢብራሂም ኡስማን፣ የጅግጅጋ ከተማ ከንቲባ ኢኒጂነር ዚያድ አብዲ፣ የመንግስት ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች እና የአካባቢው ነዋሪዎች ተገኝተዋል።
በቴድሮስ ታደሰ
👍388👏1
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በቼክ ሪፐብሊክ መንግስት ጽሕፈት ቤት በጠቅላይ ሚኒስትር ፔትር ፊያላ አቀባበል ተደረገላቸው
**********************************

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በቼክ ሪፐብሊክ መንግስት ጽሕፈት ቤት በጠቅላይ ሚኒስትር ፔትር ፊያላ በይፋዊ አቀባበል ሥነ ሥርዓት አቀባበል ተደርጎላቸዋል::

ሁለቱ መሪዎች በሁለትዮሽ ውይይታቸው በመከላከያ ዘርፍ የቆየ ትብብራቸውን በማስፋት በግብርና፣ በማዕድን ልማት እና ቱሪዝም ትብብራቸውን ለማጠናከር መወሰናቸውን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

የቼኩ ጠቅላይ ሚኒስትር ባላፉት ቅርብ ሳምንታት ኢትዮዽያን በመጎብኘት ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጋር ውይይት አድርገው እንደ ነበር ይታወሳል።
👍8921👎14👏9
አሜሪካ ሰሜን ኮሪያ በአዲሱ ሳተላይቷ አማካይነት አገኘሁት ያለችውን ምስል ማረጋገጥ አይቻልም አለች
**********************

ሰሜን ኮሪያ ሰሞኑን ባመጠቀችው የስለላ ሳተላይት አማካይነት የአሜሪካ ቤተመንግሥት፣ የመከላከያ ቢሮን ጨምሮ ቁልፍ የመከላከያ ህንጻዎችን ምስል ማገኘቷን ይፋ አድርጋለች።

ይሁን እንጂ የአሜሪካው ፔንታጎን፤ የሰሜን ኮሪያ ሳተላይት የአሜሪካ አስተዳደር ሕንፃዎችን ፎቶ እንዳገኘች ማረጋገጥ እንደማይቻል ተናግሯል።

አንድ የአሜሪካ መከላከያ ክፍል ቃል አቀባይ ለስፑትኒክ አንደገለጹት፤ የሰሜን ኮሪያ የስለላ ሳተላይት የኋይት ሃውስ፣ የፔንታጎን እና የአሜሪካ አውሮፕላን ተሸካሚዎችን ፎቶ ስለማግኘታቸው ማረጋገጥ አልተቻለም።

ይህ በአንዲህ እንዳለ፤ የሰሜን ኮሪያ የስለላ ሳተላይት ፒዮንግያንግ የሕዋ ቡድን እንድትቀላቀል ስለማድረጉ ተገልጿል።

የሰሜን ኮሪያ አዲሱ የስለላ ሳተላይት ራሳቸውን ችለው የጠፈር አቅም ካላቸው የተመረጡ አገራት መካከል አስቀምጧታል።

ይህም ብቻ ሳይሆን፤ ሀገሪቱ የኑክሌር ባላስቲክ ሚሳኤሎችን የመከለል ኃይል በማሳደግ ስትራቲጂክ ተጽዕኖ እንዳለው ነው የተገለጸው።
👍445
የዋጋ ግሽበት
👍81
Live stream finished (16 hours)
የአማራ ክልል ከፍተኛ አመራሮች በክልሉ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ እየተወያዩ ነው
****************

የአማራ ክልል ከፍተኛ አመራሮች በክልሉ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ውይይት እያካሄዱ ይገኛሉ።

በመድረኩ ላይ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አረጋ ከበደ ባደረጉት ንግግር "በክልሉ በተፈጠረው ግጭት እና አለመረጋጋት የተነሳ ከወትሮው በተለየ ሁኔታ ማከናወን ያለብንን የልማት ስራ ለማከናወን እንቅፋት ሆኗል" ብለዋል።

መከላከያ ሠራዊት ፣ የክልሉ የፀጥታ ኃይል፣ አጠቃላይ አመራሩ እና ሰላም ወዳዱ ህዝብ በቅንጅት በሰሩት ስራ አብዛኛው የክልሉ አካባቢዎች አንፃራዊ ሰላም እንዲገኝ ማድረጋቸውን ገልፀዋል።

የክልሉን ሰላም ለማረጋገጥ እና ወደ ልማት ስራዎች ለመመለስ ባለው ፍላጎት በተከታታይ ግንዛቤ የማሳደግ ስራዎች በመሰራታቸው አሁን ለተገኘው አንጻራዊ ሰላም ከፍተኛ አስተዋፅዖ ማበርከቱን ርዕሰ መስተዳድሩ ገልጸዋል።https://www.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid02wTwp6mnThyTaQecvcMd6E9HpuSvy2K5A3iaPVuD7j52tTi4BQp5McDBefVSVt7rvl
👍29👎143