EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation) – Telegram
EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)
138K subscribers
38.2K photos
458 videos
80 files
13.1K links
EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation) @etvafaanoromoo1
@ETVkidschannel
@EBCWORLD1
@etventertainment1
Download Telegram
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አፅቀሥላሴ ከአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ ጋር ተወያዩ
*******************

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አፅቀሥላሴ በዚሁ ወቅት፥ በኢትዮጵያ እና በአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን መካከል ያለው ግንኙነት ሥር የሰደደ መሆኑን አንስተው፤ ሀገሪቱ እንደ ሕብረቱ አባልነቷ እና መቀመጫነቷ ለኮሚሽኑ ስታደርገው የቆየችውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል አረጋግጠዋል።

የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ በበኩላቸው፥ አምባሳደር ታዬ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው በመሾማቸው የደስታ መግለጫ አስተላልፈው፤ ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ደህንነት እና መረጋጋት ያላትን ቁልፍ ሚና አውስተዋል።
👍8728👏7👎2
Live stream finished (1 day)
የተለያዩ ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች አዲስ አበባ ገቡ
**********

በ44ኛው የአፍሪካ ህብረት የአስፈፃሚዎች ምክር ቤት ስብሰባ የሚሳተፉ የተለያዩ ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች አዲስ አበባ መግባት ጀምረዋል።

ከትላንት ምሽት ጀምሮ የሶማሊያ፣ ቡሩንዲ፣ ኬፕቨርድ፣ ኮሞሮስ እና የካሜሮን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች አዲስ አበባ የገቡ ሲሆን፤ በዛሬው ዕለትም የቱኒዚያ፣ የደቡብ ሱዳን፣ ጋና እና የአልጀሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች አዲስ አበባ ገብተዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮቹ በቦሌ አለምአቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ አቀባበል ማድረጋቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

የህብረቱ የአስፈፃሚዎች ምክር ቤት ስብሰባ ከነገ ጀምሮ ለሁለት ቀናት የሚካሄድ ይሆናል።
👍393👏2
ተልዕኳቸውን በጀግንነት ፈጽመው ለተመለሱ ልዩ የፀረ-ሽብር አመራርና አባላት አቀባበል ተደረገ
*************

ተልዕኳቸውን በጀግንነት ፈጽመው ለተመለሱ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ልዩ ፀረ ሽብር መምሪያ አመራርና አባላት በኮልፌ ፈጥኖ ደራሽ ካምፕ ደማቅ አቀባበል ተደርጓል፡፡

አመራርና አባላቱ በተለያዩ ግዳጆች ላይ ከአራት ዓመት በላይ ቆይተው ሲመለሱ የወንጀል መከላከል ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል መላኩ ፋንታና የማኔጅመንታቸው አባላት በተገኙበት ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል፡፡

የልዩ ፀረ-ሽብር አባላቱ የኦነግ ሸኔ የሽብር ቡድን በሚንቀሳቀስባቸው በምዕራብ ወለጋ፣ ቄለም ወለጋ፣ ምሥራቅ ወለጋ፣ ሆሮ ጉድሩ እና ምዕራብ ሸዋ ዞኖች እንዲሁም በተለያዩ የሀገራችን አካባቢዎች በተልዕኮ ላይ ቆይተው አሁንም ለሌላ ፖሊሳዊ ተልዕኮ እንደተመለሱ ተጠቁሟል፡፡

የልዩ ፀረ-ሽብር ኃይሉ ያካበተውን ልምድና ሙያዊ ብቃት ተጠቅሞ በተሰማራባቸው አካባቢዎች ሁሉ በፀረ-ሰላም ኃይሎች ላይ ሕጋዊ እርምጃ በመውሰድና በመቆጣጠር በርካታ ድሎችን ሲጎናፀፍ የቆየ መሆኑ ተጠቅሷል፡፡

የልዩ ፀረ-ሽብር ኃይል አመራርና አባላት በቀጣይ የሚሰጣቸውን ተልዕኮ በጥሩ ፖሊሳዊ ሙያና ስነ-ምግባር ለመፈፀም የተዘጋጁ መሆናቸውን መናገራቸውን ከፌደራል ፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
👍11633👎13👏12
Live stream finished (13 hours)
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አፅቀ ሥላሴ በአል ሸባብ ጥቃት በደረሰው ጉዳት የተሰማቸውን ጥልቅ ሃዘን ለሶማሊያ መንግስት ገለፁ
****************

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አፅቀ ሥላሴ አሸባሪው አልሸባብ ከሰሞኑ በሶማሊያ በፈፀመው የሽብር ጥቃት በደረሰው ጉዳት የተሰማቸውን ጥልቅ ሃዘን ለሶማሊያ መንግስት እና ህዝብ ገለፁ።

አምባሳደር ታዬ ባስተላለፉት የሃዘን መልዕክት፤ በሽብር ቡድኑ ጥቃት ምክኒያት በደረሰው የሰው ሕይወት መጥፋት እና አካል ጉዳት ጥልቅ ሃዘን በኢትዮጵያ መንግስት እና ህዝብ እንዲሁም በራሳቸው ስም የተሰማቸው ጥልቅ ሃዘን ገልፀዋል።

ሚኒስትሩ፤ በልምምድ ወቅት ወታደራዊ መኮንኖችን ኢላማ በማድረግ የተፈፀመውን ጥቃት የወንጀል ተግባር መሆኑን ገልጸው፤ የወንጀል ተግባሩን ኢትዮጵያ በፅኑ እንደምታወግዘውም አስታውቀዋል።

ጥቃቱ አልሸባብ የሽብር ቡድን በሶማሊያ እና በክፍለ አህጉሩ ደህንነት አደጋ መደቀኑን በግልፅ ያረጋገጠ መሆኑን በመግለፅ፤ የአካባቢው ሃገራት በፀረ ሽብር የሚያደርጉትን ትብብር ሊያጠናክሩ እንደሚገባም አመልክተዋል።

የሶማሊያን ሰላም እና ደህንነት በጋራ ለማረጋገጥ ኢትዮጵያ ትብብሯን አጠናክራ በቁርጠኛነት እንደምትቀጥልም ሚኒስትሩ መግለጻቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።
👍5316
የሲዳማ ክልል ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤውን ማካሄድ ጀመረ
**********************

የሲዳማ ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር 3ኛ ዓመት የስራ ዘመን 6ኛ መደበኛ ጉባኤውን ማካሄድ ጀምሯል።

ምክር ቤቱ ለሁለት ቀናት በሚያካሄደው መደበኛ ጉባኤው የአሰፈፃሚ ተቋሟት የ6ወር አፈፃፀም ሪፖርት ፤ተጨማሪ በጀት እና ሹመትን በተመለከቱ አጀንዳዎች ላይ ይመክራል ተብሎ ይጠበቃል።

በሚካኤል ገዙ
👍239👏2
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ፀሐፊና የአፍሪካ ቀንድ የአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ ጋር ተወያዩ
************************

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ፀሃፊ ሞሊ ፊ፣ እና የአፍሪካ ቀንድ የአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ማይክል ሀመር ጋር ተወያይተዋል።

ውይይቱ በአህጉራዊ እና በባለብዙ ወገን ጉዳዮች ላይ ያተኮረ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል ።
👍49👎1211👏2