EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation) – Telegram
EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)
138K subscribers
38.2K photos
458 videos
80 files
13.1K links
EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation) @etvafaanoromoo1
@ETVkidschannel
@EBCWORLD1
@etventertainment1
Download Telegram
ተልዕኳቸውን በጀግንነት ፈጽመው ለተመለሱ ልዩ የፀረ-ሽብር አመራርና አባላት አቀባበል ተደረገ
*************

ተልዕኳቸውን በጀግንነት ፈጽመው ለተመለሱ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ልዩ ፀረ ሽብር መምሪያ አመራርና አባላት በኮልፌ ፈጥኖ ደራሽ ካምፕ ደማቅ አቀባበል ተደርጓል፡፡

አመራርና አባላቱ በተለያዩ ግዳጆች ላይ ከአራት ዓመት በላይ ቆይተው ሲመለሱ የወንጀል መከላከል ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል መላኩ ፋንታና የማኔጅመንታቸው አባላት በተገኙበት ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል፡፡

የልዩ ፀረ-ሽብር አባላቱ የኦነግ ሸኔ የሽብር ቡድን በሚንቀሳቀስባቸው በምዕራብ ወለጋ፣ ቄለም ወለጋ፣ ምሥራቅ ወለጋ፣ ሆሮ ጉድሩ እና ምዕራብ ሸዋ ዞኖች እንዲሁም በተለያዩ የሀገራችን አካባቢዎች በተልዕኮ ላይ ቆይተው አሁንም ለሌላ ፖሊሳዊ ተልዕኮ እንደተመለሱ ተጠቁሟል፡፡

የልዩ ፀረ-ሽብር ኃይሉ ያካበተውን ልምድና ሙያዊ ብቃት ተጠቅሞ በተሰማራባቸው አካባቢዎች ሁሉ በፀረ-ሰላም ኃይሎች ላይ ሕጋዊ እርምጃ በመውሰድና በመቆጣጠር በርካታ ድሎችን ሲጎናፀፍ የቆየ መሆኑ ተጠቅሷል፡፡

የልዩ ፀረ-ሽብር ኃይል አመራርና አባላት በቀጣይ የሚሰጣቸውን ተልዕኮ በጥሩ ፖሊሳዊ ሙያና ስነ-ምግባር ለመፈፀም የተዘጋጁ መሆናቸውን መናገራቸውን ከፌደራል ፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
👍11633👎13👏12
Live stream finished (13 hours)
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አፅቀ ሥላሴ በአል ሸባብ ጥቃት በደረሰው ጉዳት የተሰማቸውን ጥልቅ ሃዘን ለሶማሊያ መንግስት ገለፁ
****************

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አፅቀ ሥላሴ አሸባሪው አልሸባብ ከሰሞኑ በሶማሊያ በፈፀመው የሽብር ጥቃት በደረሰው ጉዳት የተሰማቸውን ጥልቅ ሃዘን ለሶማሊያ መንግስት እና ህዝብ ገለፁ።

አምባሳደር ታዬ ባስተላለፉት የሃዘን መልዕክት፤ በሽብር ቡድኑ ጥቃት ምክኒያት በደረሰው የሰው ሕይወት መጥፋት እና አካል ጉዳት ጥልቅ ሃዘን በኢትዮጵያ መንግስት እና ህዝብ እንዲሁም በራሳቸው ስም የተሰማቸው ጥልቅ ሃዘን ገልፀዋል።

ሚኒስትሩ፤ በልምምድ ወቅት ወታደራዊ መኮንኖችን ኢላማ በማድረግ የተፈፀመውን ጥቃት የወንጀል ተግባር መሆኑን ገልጸው፤ የወንጀል ተግባሩን ኢትዮጵያ በፅኑ እንደምታወግዘውም አስታውቀዋል።

ጥቃቱ አልሸባብ የሽብር ቡድን በሶማሊያ እና በክፍለ አህጉሩ ደህንነት አደጋ መደቀኑን በግልፅ ያረጋገጠ መሆኑን በመግለፅ፤ የአካባቢው ሃገራት በፀረ ሽብር የሚያደርጉትን ትብብር ሊያጠናክሩ እንደሚገባም አመልክተዋል።

የሶማሊያን ሰላም እና ደህንነት በጋራ ለማረጋገጥ ኢትዮጵያ ትብብሯን አጠናክራ በቁርጠኛነት እንደምትቀጥልም ሚኒስትሩ መግለጻቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።
👍5316
የሲዳማ ክልል ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤውን ማካሄድ ጀመረ
**********************

የሲዳማ ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር 3ኛ ዓመት የስራ ዘመን 6ኛ መደበኛ ጉባኤውን ማካሄድ ጀምሯል።

ምክር ቤቱ ለሁለት ቀናት በሚያካሄደው መደበኛ ጉባኤው የአሰፈፃሚ ተቋሟት የ6ወር አፈፃፀም ሪፖርት ፤ተጨማሪ በጀት እና ሹመትን በተመለከቱ አጀንዳዎች ላይ ይመክራል ተብሎ ይጠበቃል።

በሚካኤል ገዙ
👍239👏2
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ፀሐፊና የአፍሪካ ቀንድ የአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ ጋር ተወያዩ
************************

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ፀሃፊ ሞሊ ፊ፣ እና የአፍሪካ ቀንድ የአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ማይክል ሀመር ጋር ተወያይተዋል።

ውይይቱ በአህጉራዊ እና በባለብዙ ወገን ጉዳዮች ላይ ያተኮረ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል ።
👍49👎1211👏2
44ኛው የአፍሪካ ኅብረት የሥራ አስፈጻሚዎች ምክር ቤት መደበኛ ስብስባ ተጀመረ
******************************

44ኛው የአፍሪካ ኅብረት የሥራ አስፈጻሚዎች ምክር ቤት መደበኛ ስብስባ ዛሬ በኅብረቱ ዋና መቀመጫ አዲስ አበባ ተጀምሯል።


ስብሰባው "ለ21ኛው ክፍለ ዘመን የሚመጥን አፍሪካዊ ማስተማር፤ የማይበገሩ የትምህርት ሥርዓቶች በመገንባት በአፍሪካ ሁሉን አቀፍ፣ የሕይወት ዘመን፣ ጥራትና አግባብነት ያለው የትምህርት ተደራሽነትን ማስፋት“ በሚል የአፍሪካ ሕብረት ባዘጋጀው የ2024 መሪ ቃል ነው የሚካሄደው።

በስብሰባው የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ኮሚሽነር ሙሳ ፋኪ ማኅማት፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች፣ ዲፕሎማቶችና የኅብረቱ ተቋማት አመራሮች ተገኝተዋል።

ምክር ቤቱ በዋናነት የአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጣና ትግበራ ለማፋጠን ባለፈው አንድ ዓመት የተሰራውን ሥራ በተመለከተ በሚቀርበው ሪፖርት ላይ ምክክር ያካሄዳል።

በተለይም ነጻ የንግድ ቀጣናውን ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችል የኃብት ማሰባሰብ ሥራዎች፣ ቅንጅታዊ አሰራር፣ በታሪፍና የንግድ ሰንሰለት ዙሪያ በተሰሩ ሥራዎች ዙሪያም ይመክራል።

የአፍሪካ ኅብረት ከአገራትና ከባለብዙ ወገን ተቋማት ጋር በተመለከተ ያለውን አጋርነት በተመለከተ የሚደነግገውን ረቂቅ ፖሊሲና ስትራቴጂ ዘሪያ እንደሚወያይም ይጠበቃል።https://www.facebook.com/EBCzena/posts/791657002988481
👍458👎1
ኢትዮጵያ አማርኛ የአፍሪካ ኅብረት የሥራ ቋንቋ እንዲሆን ጠየቀች
***************

አማርኛ የአፍሪካ ኅብረት የሥራ ቋንቋ እንዲሆን ኢትዮጵያ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀ ሥላሴ በኩል ጥሪ አቀረበች።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀ ሥላሴ፤ አማርኛ የአፍሪካ ኅብረት የሥራ ቋንቋ እንዲሆን ጥያቄ ያቀረቡት በአዲስ አበባ እየተካሄደ ባለው 44ኛው የአፍሪካ ኅብረት የሥራ አስፈጻሚዎች ምክር ቤት መደበኛ ስብስባ ነው።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀ ሥላሴ በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት፤ ኢትዮጵያ ያቀረበችው ጥያቄ ከአፍሪካ የ2063 አጀንዳ ጋር የሚጣጠም መሆኑን አንስተዋል።

ያም ብቻ ሳይሆን የአፍሪካን አገር በቀል ቋንቋዎች ለማጠናከር ከተያዘውን የአፍሪካ ኅብረት ግብ ጋር አብሮ የሚሄድ መሆኑንም ነው በማብራሪያቸው ያነሱት።

የቀድሞው የአፍሪካ አንድነት ድርጅት ቻርተር የተፈረመው አማርኛን ጨምሮ በአራት ቋንቋዎች መሆናቸውን ያነሱት አምባሳደር ታዬ፤ አማርኛን የአፍሪካ ኅብረት የሥራ ቋንቋ ማድረግ የአፍሪካ የቋንቋ ብዝኃነት መቀበል እና የጋራ ማንነትን ማጠናከር ነው ብለዋል።

ይህም አህጉሪቱን ወደ ተሻለ ደረጃ ለማድረስ እገዛ እንደሚያደርግ መጠቆማቸውን የዘገበው ኢዜአ ነው።
👍15027👏11👎10
የኢትዮጵያ ህልም የነበረው ኅብረት ተሳክቷልን?
****************

ኢትዮጵያ ለአፍሪካ እና በቅኝ ግዛት ሥር ለነበሩት ሀገራት ነጻነት የከፈለችው ዋጋ ውድ ነው፡፡ ነጻነቷን ጠብቃ የኖረችው ኢትዮጵያ ብቻዋን የመንግሥታቱ ማኅበር አባል በነበረችበት ወቅት የአውሮፓውያንን የግፍ ወረራ አውግዛለች፤ ብቻዋንም በፍትህ አደባባይ ቆማለች፡፡

የኢትዮጵያ የፍትህ አደባባይ ጩኸት የገለጠው የአውሮፓውያን ግፍ አውዳሚው የሁለተኛ ዓለም ጦርነት እንዲከሰት አድርጓል፡፡ ይሁንና ከታሪክ ያልተማረው ዓለም አሁንም ኢትዮጵያ፣ የአፍሪካን እና የጭቁን ሕዝቦችን ጩኸት እየሰማ ባለመሆኑ ዓለም መከራ ውስጥ እንድትኖር አድርጓታል፡፡

ኢትዮጵያ የዓለም ኅብረቶችን መሥራች ሆና በአባልነት የምትቀላቀለው በዓለም ላይ ፍትህ እንዲሰፍን፣ ጉልበተኞች አቅመ ቢሶችን እንዳይጨፈልቁ እና ሁሉም የዓለም ሕዝብ በእኩልነት የመኖር መብቱ እንዲከበርለት ነው፡፡

ለዚህም ነው ራሷ ነጻነቷን ስላስከበረች በቃ ብላ ያልተቀመጠችው፡፡ አፍሪካውያን ወንድሞቿ ነጻ ሳይወጡ ነጻነቷ ሙሉ ስለማይሆን አፍሪካውያን ከቅኝ ግዛት ነጻ እንዲሆኑ የታገለችው፡፡ የዓለምን ፍትህ የማይሻው የምዕራባውያኑ ጎራ ይህን የኢትዮጵያን ጥረት ለማሰናከል እና አፍሪካን ድምጽ አልባ ለማድረግ ዛሬም ኢ-ፍትሃዊ ጫናውን እንደቀጠለ ነው፡፡

ኢትዮጵያ አፍሪካ ነጻነቷን እንድታገኝ ካደረገቻቸው ትግሎች ጎን ለጎን አፍሪካውያን ኅብረት ፈጥረው የሚደርስባቸውን ጫና እንዲቋቋሙ እና ሕዝቦቻቸው ወደ ተሻለ ህይወት እንዲሸጋገሩ ስትሰራ ቆይታለች፡፡
https://www.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid0taa67HvPawF3sNSrRCjMEQVw2szFxEWgwjPzvxoA34xN6B3dwGcgNXeC3RyVzYPFl
👍6512👏4