EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation) – Telegram
EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)
137K subscribers
38.4K photos
462 videos
80 files
13.2K links
EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation) @etvafaanoromoo1
@ETVkidschannel
@EBCWORLD1
@etventertainment1
Download Telegram
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ ከማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ እና ከፖርቱጋል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ጋር ተወያዩ
*********************

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ ከማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሲልቪ ባይፖ-ተሞን ጋር በሁለትዮሽ እና ቀጣናዊ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል።

በተመሳሳይ ሚኒስትሩ ከፖርቱጋል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጃኦ ጎሜዝ ክራቪኝዎ ጋር በሁለትዮሽ እና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል።

አምባሳደር ታዬ ኢትዮጵያ ከፖርቱጋል ጋር በቱሪዝም፣ በትምህርት፣ በንግድ እና በኢንቬስትመንት ዘርፎች ተባብራ መስራት ትፈልጋለች ብለዋል።

የፖርቱጋሉ ሚኒስትር በበኩላቸው አገራቸው የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ትግበራን እንደምትደግፍ መግለጻቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
👍48👏87
ከነገ ጀምሮ የአፍሪካ ሕብረት ጉባኤ እስኪጠናቀቅ ለአሽከርካሪዎች ዝግ የሚሆኑ መንገዶች
************************

37ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ እና 44ኛው የሚኒስትሮች ስራ አስፈፃሚ ም/ቤት ስብሰባ በሰላምና በስኬት ለማጠናቀቅ እንዲቻል በሚከናወነው የፀጥታ ስራ እና የትራፊክ ፍሰቱ የተሳለጠ እንዲሆን አሽከርካሪዎች ሌሎች ተለዋጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠይቋል።

በዚሁ መሠረት ከነገ ሐሙስ የካቲት 7 ቀን ጀምሮ ጉባኤው እስከሚጠናቀቅ፡-
• ከፓርላማ መብራት - በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር - መስቀል አደባባይ - ፍላሚንጎ - ኦምሎፒያ - ወሎ ሰፈር - ጃፓን ኤምባሲ - ፍሬንድ ሺፕ - ቦሌ ቀለበት መንገድ - ኤርፖርት
• ከፓርላማ መብራት - በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር - ብሔራዊ ቤተ-መንግሥት - ፍልውሃ - ብሔራዊ ቴአትር - ሜክሲኮ አደባባይ - አፍሪካ ሕብረት አዳራሽ ዙሪያ
• ከፓርላማ መብራት - ብሔራዊ ቤተ-መንግሥት - ወዳጅነት ፓርክ - ንግድ ማተሚያ ቤት - ሞናርክ ሆቴል - ቴዎድሮስ አደባባይ - ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል - ኢትዮጵያ ቴሌቪዥን - ብሔራዊ ቴአትር - ሜክሲኮ አደባባይ - አፍሪካ ሕብረት ባሉ መንገዶች እንግዶች ሲያልፉ አሽከርካሪዎችም ሆኑ እግረኞች ለእንግዶቹ ቅድሚያ በመስጠት ተባባሪ እንዲሆኑ እና ሌሎች ተለዋጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ ፖሊስ አሳስቧል።

https://ebc.et/newsdetails.aspx?newsid=5856
👍548👎4
የአፍሪካ አገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮችን ጨምሮ የተለያዩ አገራት አምባሳደሮች የዓድዋ ድል መታሰቢያን ጎበኙ
*************************

በጉብኝት መርሐ ግብሩ ላይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ፣ የሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች እና የሃይማኖት ተቋማት መሪዎችን ጨምሮ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

በጉብኝቱ ላይ ለተገኙ ታዳሚዎች በዓድዋ ጦርነት የቀደሙ አባቶች ለነጻነት ስለከፈሉት መስዋዕትነት፣ የትግል ሂደት እንዲሁም ስለድል መታሰቢያው አጠቃላይ ይዘት ማብራሪያ መሰጠቱን ኢዜአ ዘግቧል።

በዚያው በዓድዋ ድል መታሰቢያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴ የ44ኛው የሕብረቱ የአስፈፃሚ ምክር ቤት ስብሰባ ተሳታፊ ለሆኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች እና ሌሎች እንግዶች የእራት ግብዣ ማድረጋቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
👍3711👏5👎1
ሁለተኛው ዙር የመውጫ ፈተና በዛሬው ዕለት በጤና ትምህርት ፕሮግራሞች መሰጠት መጀመሩን የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ
************************

በዚሁ መሠረት ዛሬ ጠዋት 15 ሺህ 440 ተማሪዎች በ23 የጤና ፕሮግራሞች የመውጫ ፈተናውን የወሰዱ ሲሆን፤ ከሰዓት 14 ሺህ 807 ተማሪዎች በ13 ፕሮግራሞች ተፈትነዋል።

የመውጫ ፈተናው በሁሉም የፈተና ማዕከላት (ከተሞች) በመሰጠት ላይ ሲሆን፤ የፈተና አሰጣጡን ፍትሃዊነትና ተዓማኒነት ለማስጠበቅ እንዲሁም አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ የተመደቡ ታዛቢዎችም በየተመደቡባቸው ተቋማት በመገኘት ስራ መጀመራቸው ተገልጿል።

ሁለተኛ ዙር የመውጫ ፈተናው በ47 የመንግሥት ተቋማት በ84 የፈተና ማዕከላት የሚሰጥ ሲሆን፤ በመንግሥትና በግል ተቋማት ለመጀመሪያ ጊዜ የሚፈተኑትን ጨምሮ 149 ሺህ 145 ተፈታኞች በ204 የፈተና ፕሮግራሞች እንደሚፈተኑ ተጠቁሟል።

ሁለተኛ ዙር የመውጫ ፈተናው የካቲት 11 ቀን 2016 ዓ.ም እንደሚጠናቀቅ ከትምህርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
👍579👎6👏3
"በእኛ ሁኔታ የሚያስፈልገን ልማት ነው፣ የሚያስፈልገን እርሻ ነው፣ የሚያስፈልገን ራስን መመገብ እና የተረፈውን ሸጦ መጠቀም ነው። የማያስፈልገን ደግሞ መባላት ነው።" - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
👍10026👎15
"የጎበኘናቸው የልማት ስራዎች ለህዝቡ ዕድገት ወሳኝ በመሆናቸው በቅርብ ተከታትለን ለፍፃሜ እናደርሳቸዋለን" - አቶ ተመስገን ጥሩነህ
**********

በአማራ ክልል ጉብኝት የተደረገባቸው የልማት ስራዎች ለህዝቡ ዕድገት ወሳኝ በመሆናቸው የቅርብ ክትትል በማድረግ ለፍፃሜ ለማድረስ አንደሚሰራ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ ገለፁ፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልእክት፤ በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ለተደረገላቸው ደማቅ አቀባበል ምስጋና አቅርበዋል።

በአማራ ክልል በነበራቸው ቆይታ ከጠቅላላ የክልሉ አመራር ጋር በፀጥታ እና በልማት ስራዎች ዙሪያ ያደረጓቸው ውይይቶች ማርሽ ቀያሪ እንደነበሩ ጠቅሰዋል።

"የጎበኘናቸው የልማት ስራዎችም ለክልሉ ህዝብ ዕድገት ወሳኝ በመሆናቸው በቅርብ ተከታትለን ለፍፃሜ እናደርሳቸዋለን" ሲሉም ገልጸዋል።
👍6120👎5👏2
በአዳማ ከተማ ለሽብር ወንጀል ሊውል የነበረ በርካታ ሕገ-ወጥ የጦር መሳሪያ ተያዘ
**************

በአዳማ ከተማ ለሽብር ወንጀል ሊውል የነበረ በርካታ ሕገ-ወጥ የጦር መሳሪያ እና ጥይት በፍተሻና በሕዝብ ጥቆማ በቁጥጥር ስር ዋለ።

በአዳማ ከተማ ፖሊስ ከሌሎች የፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት በከተማው በተለያዩ ጊዜያት የሽብር ተግባር ለመፈፀም መነሻቸውን አዋሽ ሰባት፣ ሰበታ እና ሌሎች አካባቢዎች በማድረግ በተሽከርካሪ ታግዘው ሕገ-ወጥ መሣሪያውን ወደ አዲስ አበባ ከተማ እና ወደ ሌሎች አካባቢዎች በማዘዋወር የሽብር ተግባር ለመፈፀም የሞከሩ አሸባሪዎችንና ተባባሪዎቻቸውን ከህብረተሰቡ በተገኘ ጥቆማ እና በተደረገ ጥብቅ ፍተሻ በቁጥጥር ስራ መዋል መቻሉ ተጠቅሷል፡፡

በዚህም 61 ቦንብ፣ 6 ሺህ የክላሽንኮቭ ጠመንጃ ጥይት፣ 4 ሺህ 983 የሽጉጥ ጥይት፣ 1 ሺህ 879 የብሬን ጥይት፣ 17 ክላሽንኮቭ ጠመንጃ፣ 18 የተለያየ አይነት ሽጉጥ፣ ዘጠኝ የብሬን ሸንሸን (ሰንሰለት)፣ አንድ ስናይፐር፣ አንድ ላውንቸር፣ ሁለት ቁንቡላ፣ አንድ የጦር ሜዳ መነጽር እና 242 ሺህ 220 ብር መያዙን የአዳማ ከተማ ፖሊስ ገልጿል።

ህገ-ወጥ የጦር መሣሪያዎችንና ጥይቶችን ለሽብር ቡድኑ ሊያስተላልፉ የነበሩ ተጠርጣሪዎች እና የመኪናው ሾፌርም ከነ-ኤግዚብቱ በቁጥጥር ሥር ውለው ምርመራ እየተጣራባቸው እንደሚገኝ የአዳማ ፖሊስ ዋና መምሪያ ጠቁሟል።
https://www.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid02E48btinTYvnD7w27AFXY2qWzLECSxVXdHU4TykT5YxuAuSCgfJJ4HesMdwsyhtKul
👍6012👏7
ከአፍሪካ አንድነት ድርጅት እስከ አፍሪካ ኅብረት
*********************

• በ1955 ዓ.ም የአፍሪካ አንድነት ድርጅት ቻርተር ተፈርሞ ድርጅቱ ተመሰረተ፤

• ቻርተሩን ፈርመው ድርጅቱን የመሰረቱት 32 ሀገራት ነበሩ፤

• በ1994 ዓ.ም ድርጅቱ ወደ ኅብረት ሲሸጋገር የአባላቱ ቁጥር 53 ደረሰ፤

• በ1991 ዓ.ም በሊቢያዋ ሰርጥ በተካሄደ ጉባኤ "በሰርጥ አዋጅ" የአፍሪካ ኅብረት እንዲመሰረት ተወሰነ፤

• በ1992 ዓ.ም የአፍሪካ ኅብረት ምስረታ ሕግን ያጸደቀው የሎሜ የመሪዎች ጉባኤ ተካሄደ፤

• በ1993 ዓ.ም በሉሳካ በተካሄደ የመሪዎች ጉባኤ የኅብረቱ ሮድ ማፕ ጸደቀ፤

• ሐምሌ 2 ቀን 2003 ዓ.ም ደቡብ ሱዳን 54ኛ የኅብረቱ አባል ሆነች፤

• በ1994 ዓ.ም በደቡብ አፍሪካዋ ደርባን በተካሄደ የመሪዎች ጉባኤ የኅብረቱ መመስረት ይፋ ሆነ፣
👍47👏95👎1
ኢትዮጵያ እና አንጎላ በኢኮኖሚና በፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመስራት ስምምነት ተፈራረሙ
**********

ኢትዮጵያ እና አንጎላ በኢኮኖሚና በፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ በጋራ መስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል።

ስምምነቱ ሁለቱ ሀገራት ከዚህ ቀደም ያላቸውን ትብብር የሚያጠናክር እነደሆነ ተገልጿል።

በተለይም የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ አንጎላ የሚያደረገውን በረራ ማሳደግ በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ ከስምምነት ተደርሷል።

ስምምነቱን የውጭ ጉዳይ ሚንስትር አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴ ከአንጎላ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ቴቴ አንቶኒዮ ጋር ተፈራርመዋል።

በሌላ በኩል አምባሳደር ታዬ ከዚምባብዌ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ዶክተር ፍሬድሪክ ሻቫ ጋር የሁለትዮሽ ውይይት አካሂደዋል።

በማህሌት ታደለ
27👍21👏5