የአማራ ህዝብ ጥያቄዎች የሁሉም ኢትዮጵያውያን ጥያቄዎች ሆነው ምላሽ እንዲያገኙ ጥረት እየተደረገ ነው፡- አቶ ደስታ ሊዳሞ
******************************
የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድ አቶ ደስታ ሌዳሞ ከብልፅግና ፓርቲ አመራሮች እና የባሕር ዳር ከተማ የሥራ ኃላፊዎች ጋር በመሆን ከባሕር ዳር ከተማ ነዋሪዎች ጋር ውይይት አድርገዋል።
ርዕሰ መስተዳድሩ ኢትዮጵያውያን የሰላምን ዋጋን ጠንቅቀው የሚረዱ መሆናቸውን ጠቅሰው፣ የአማራ ክልልን ሰላም ወደ ነበረበት ለመመለስ ህዝቡ እና መንግሥት በጋራ ሊረባረቡ እንደሚገባም ተናግረዋል።
በባሕር ዳር ከተማ እየተከናወኑ ያሉ የልማት ተግባራትን ተዘዋውረው ማየታቸውን የተናገሩት አቶ ደስታ፣ ልማቶቹ ተጠናክሩው መቀጠል እንዳለባቸውም ጠቁመዋል።
የአማራ ህዝብ ጥያቄዎች የሁሉም ኢትዮጵያውያን ጥያቄ ሆኖ ምላሽ ያገኛል ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ፣ ለዚህም የበኩላቸውን እንደሚወጡ አረጋግጠዋል።
የአማራ ህዝብን ጥያቄ ሰላማዊ ባልሆነ መንገድ ለማሳካት የሚሞክሩ ኃይሎች ከዚህ ድርጊታቸው ሊቆጠቡ እንደሚገባ ያሳሰቡት አቶ ደስታ፣ ይህ አካሄድ የአማራ ህዝብን የሚጎዳ እና ጥያቄዎቹም እንዳይመለሱ እንቅፋት የሚፈጥር ነው ብለዋል።
የባሕር ዳር ከተማ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ጎሹ እንዳላማው ኢትዮጵያ ብሔሮችና ብሔረሰቦች በጋራ ተባብረው የገነቧት ብዝሃነት የሚታይባት ሀገር ናት ብለዋል።
https://www.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid0uGpogi7RCbot9JHzGnVHiA1fvgDu5KoY8X2RigRLPBW8RRjxXEZnazBCA37GKZhFl

👍27👎9❤3👏1
"ከተረጂነት ወደ ምርታማነት ለተሟላ ሀገራዊ ሉዓላዊነት እና ክብር" በሚል መሪ ቃል በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወላይታ ሶዶ ከተማ የህዝብ መድረክ እየተካሄደ ነው
**********************
መድረኩን የብልፅግና ፓርቲ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል እና የኦሮሚያ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍቃዱ ተሰማ ፣ የአፋር ክልል ም/ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኤሌማ አቡበከር እና የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ረዳት የመንግሥት ተጠሪ አቶ ዮሐንስ በየነ እየመሩ ይገኛሉ።
በአካባቢው የሚገኙ የተፈጥሮ ፀጋዎችን በአግባቡ በመጠቀም ምርትና ምርታማነት በማሳደግ ከተረጂነት ለመላቀቅ በሚያስችሉ ጉዳዮች ከህብረተሰቡ ጋር መወያየት የመድረኩ ዓላማ እንደሆነ ተገልጿል ።
በመድረኩ የክልሉ፣ የዞን እና የከተማ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች የተገኙ ሲሆን፣ ከከተማው የተለያዩ የማኅበራዊ መሠረቶች የተወጣጡ የህብረተሰብ ክፍሎችም እየተሳተፉ ይገኛሉ ።
በትዕግስቱ ቡቼ

👍40❤2
በመዲናዋ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ስራዎች ለክልሎችም ተሞክሮ የሚሆኑ ናቸው - አቶ አረጋ ከበደ
********************
በአዲስ አበባ ከተማ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ስራዎች ለክልሎችም ተሞክሮ እንደሚሆኑ የአማራ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ ተናግረዋል፡፡
የአማራ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ እና የግብርና ሚኒስትሩ ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) በአዲስ አበባ የተገነቡ የልማት ስራዎችን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።
ርዕሰ መስተዳድሩ እና የግብርና ሚኒስትሩ ከጎበኟቸው ፕሮጀክቶች መካከል፤ የለሚ ኩራ የግብርና ምርት መሸጫ ማዕከል፣ የእንስሳት ልማት እና ልህቀት ማዕከል፣ ለነገዋ የሴቶች ተሃድሶ እና ማበልፅጊያ ማዕከል እንዲሁም ሌሎች የልማት ስራዎች ይገኙበታል፡፡
በአዲስ አበባ የተከናወኑ የልማት ስራዎች እና ታላላቅ ፕሮጀክቶች የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ መሆናቸውን ርዕሰ መሥተዳድሩ ገልጸዋል፡፡
በተለያዩ ክፍለ ከተሞች የተገነቡት የልማት ስራዎች የኑሮ ውድነቱን ከማቃለል አንጻር ጉልህ ሚና እንዳላቸውም ማመላከታቸውን ከከንቲባ ጽ/ቤት የማኀበራዊ የትስስር ገጽ የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

👍30❤5👎1
"ዛሬ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ብፁዕ አቡነ ማትያስ ጋር በመሆን በኮሪደር ልማት ምክንያት በፈረሱ ቤቶች ምትክ በቤተክርስቲያኒቱ የሚገነባ ህንፃ የመሠረተ ድንጋይ አስቀምጠናል።
ቤተ ክህነት የከተማውን ልማት ሥራ በላቀ ሁኔታ በመደገፍ እና ለኮሪደር ልማት ስራዎች መጀመር፤ በማፍረስ ሂደትም ሆነ መልሶ በመገንባት ሂደት እንዲሁም ህንፃዎችን በማደስ ላደረገችው ተሳትፎ እና ተግባራዊ የሆነ ምላሽ ከልቤ ለማመስገን እወዳለሁ።
በዚህ አጋጣሚ ከቤተክርስቲያንቱ ለቀረበልኝ ምስጋናም እጅግ በጣም አድርጌ አመሰግናለሁ ።"
ከንቲባ አዳነች አቤቤ

❤25👍23👎5