"የካዛንቺስ አካባቢን ለኑሮ ምቹ ለማድረግ በምንሰራው ስራ የከተማችን ነዋሪዎች እንዲተባበሩ ጥሪ አቀርባለሁ" - ከንቲባ አዳነች አቤቤ
*****************
የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ማምሻውን ካዛንቺስ አካባቢ በኮሪደር ልማት መልሶ ማልማት የሚነሱ የተወሰኑ ተነሺዎችን ቤት ጎብኝተዋል::
ከንቲባዋ ይህን አስመልክቶ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ፤ "ከሚያማምሩ ፎቆች ጀርባ እጅግ በጣም አሳዛኝ እግር መዘርጊያ እንኳን የሌላቸው፣ በቆርቆሮ እና በሸራ የተለበዱ ያረጁ፣ መፀዳጃና መኖሪያ ቤት የተቀላቀሉ፣ መፀዳጃ የሌላቸዉ በቆጥ ላይ ሳይቀር የሚኖሩ እንዲሁም ማብሰያ ቦታ ሳይኖር የሚኖሩበት አስቸጋሪ እና ለመኖር ከባድ ሁኔታ ውስጥ መሆናቸውን አይተናል" ብለዋል::
እኛ ጎብኝተን ለመውጣት እንኳን አስቸጋሪ መሆኑን አየን እነሱ ግን ለረዥም አመታት እንደኖሩበት ስናስብ በእጅጉ አዝነናል ሲሉም ገልፀዋል::
ይህንን ሁኔታ ከመቀየር በላይ ቅድሚያ የምንሰጠው ምንም ስራ የለም ያሉት ከንቲባዋ፤ "እንደተለመደው ሁሉ የከተማችን ነዋሪዎች ተባብረን ይህንን አካባቢ በመቀየር ለነዋሪዎችና ለኑሮ ምቹ እንድናደርግ ጥሪ አቀርባለሁ" ብለዋል::

👍57❤9👏4👎3
በጋምቤላ ክልል በደረሰ የመኪና አደጋ የ7 ሰዎች ህይወት አለፈ
*********************
በጋምቤላ ክልል በጂካዎ ወረዳ ትላንት ምሽት በደረሰ የመኪና አደጋ የ7 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተገልጿል፡፡
አደጋው ያጋጠመው ከጋምቤላ ከተማ ወደ ኑዌር ዞን በመጓዝ ላይ የነበረ አምቡላንስ በጂካዎ ወረዳ የባሮ ወንዝን ድልድይ ጥሶ ወንዝ ውስጥ በመግባቱ መሆኑን የጋምቤላ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡
በአደጋው እስካሁን የ7 ሰዎች ህይወት ማለፉንም የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ኡጉላ ኡጁሉ ተናግረዋል፡፡
የአደጋው መንስኤ በመጣራት ላይ መሆኑን የጠቆሙት ኮሚሽነሩ፤ ከሟቾች ውስጥ የጤና ባለሙያዎች እንደሚገኙበት አመላክተዋል፡፡
በትራፊክ አደጋ በዜጎች ህይወት እና አካል ላይ የሚደርሰው ጉዳት ለመቀነስ አሽከርካሪዎች በኃላፊነት ስሜት ሊያሽከረክሩ አንደሚገባም አሳስበዋል፡፡
ሚፍታህ አብዱልቃድር

👍21❤2
ኢትዮጵያ ለምን ለጎረቤት ሀገራት የኤሌክትሪክ ኃይል ታቀርባለች?
**********************
ኢትዮጵያ ለኬንያ፣ ጅቡቲ እና ሱዳን የኤሌክትሪክ ኃይልን በዝቅተኛ ታሪፍ እያቀረበች መሆኗ ከጎረቤት ሀገራት ጋር በትብብር አብሮ ለማደግ ቁርጠኛ መሆኗ ማሳያ መሆኑን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሞገስ መኮንን ገለፁ።
በዚህም መሰረት ለሱዳን እና ጅቡቲ ለእያንዳንዳቸው 100 ሜጋ ዋት ለኬንያ ደግሞ 200 ሜጋ ዋት እየተላለፈ ነው ብለዋል።
ይህም ለጎረቤቶቻችን ቅድሚያ በመስጠት የጋራ እድገትን እውን ለማድረግ የተቀረጸውን የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ተግባራዊ እያደረገች መሆኑን ተናግረዋል፡፡
''ኢትዮጵያ ብቻዋን የማደግ ፍላጎት የላትም፤ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲያችን ከጎረቤት ሀገራት ጋር አብሮ ማደግና መልማት፣ ጎረቤቶቻችንን ከእኛ ተጠቃሚ የሚሆኑበትን እድል መፍጠር፣ እኛም ከጎረቤቶቻችን ጋር አብሮ ለማደግ አብሮ ለመልማት እድል ይሰጣል'' ብለዋል።https://www.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid02AixLpEBdXgRo69daCbW98MBxAAemPG4cuQdyUS6MTPfsnNmcPLTrrfCM7MP8Uey5l?cft[0]=AZUxeLMs7OZNXri8LkJZy2wdztKknz36KoUcYT20eDTHQb8vnB32gwPLYC71tzRyTkQt1j2fj977nynnIc-q9ijlwY70lxJqAhH7pG1UnEgCChGd49PF2G5vj77nY4Y5nJg6qjIzkjD7NYM1glJfUD4prlzulvGA2dGAM22FC_JLiMNoBOa497XQUATzHV5I4bE&tn=%2CO%2CP-R

👍20❤8👏4👎1
በሊባኖስ ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ጥሪ ቀረበ
*****************
በሊባኖስ በተለይም በደቡብ እና ምሥራቅ የሀገሪቱ አካባቢዎች ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በሊባኖስ የኢትዮጵያ ቆንስላ ጄኔራል ጽሕፈት ቤት ጥሪ አቅርቧል፡፡
ጽሕፈት ቤቱ በደቡብ እና ምሥራቅ ሊባኖስ ያለው የፀጥታ ችግር እየተባባሰ መምጣቱን ተከትሎ በአካባቢዎች ያሉ ዜጎችን ለይቶ ማወቅ አስፈላጊ ሆኖ መገኘቱን ጠቁሟል፡፡
በመሆኑም በአካባቢው የሚኖሩ ወገኖች ከታች በተቀመጠው መሠረት ስማቸውን ፓስፖርት ላይ አንደተፃፈው፣ የፓስፖርት ቁጥር እና ስልክ ቁጥራቸውን እንዲያስመዘግቡ ጥሪ አቅርቧል፡፡
በዚሁ መሠረት በደቡብ ሊባኖስ (ታየር፣ ሱር፣ ቢንት ጅቤል፣ ማርጃዩን፣ ነበትዬ፣ ሳይዳ እና አካባቢው) የሚገኙ ወገኖች በስልክ ቁጥር 03-7354 51 ወይም 03-87-10-89 እንዲሁም በምሥራቅ ሊባኖስ (አልቤክ፣ ቤካ ሸለቆ እና አካባቢው) የሚገኙ ደግሞ በስልክ ቁጥር 81 77-62-51 ወይም 81-63-07-98 በመደወል እንዲመዘገቡ ጄኔራል ጽሕፈት ቤት አሳስቧል፡፡

👍37❤10👏6
የዓለም አቀፍ አሸማጋይ ድርጅት ምስረታ ላይ ያተኮረ ምክክር ተካሄደ
*******************
የዓለም አቀፍ አሸማጋይ ድርጅት ምስረታ ላይ ያተኮረ ገላፃ እና ምክክር በአዲስ አበባ ተካሄዷል፡፡
መድረኩ ሰላማዊ እና ምቹ ዓለም በመፍጠር ሂደት ውስጥ ሽምግልናን ውጤታማ የግጭት አፈታት ዘዴ ለማድረግ የሚደረገውን ጥረት እንደሚያግዝ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የመካከለኛው ምስራቅ፣ እስያ እና ፓሲፊክ አገራት ጉዳዮች ዳይሬክተር ጀኔራል አምባሳደር ንጉስ ከበደ ተናግረዋል።
የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስተር የህግ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጄኔራል ማ ዢንሚን በበኩላቸው፤ ድርጅቱ ዓለማቀፍ አለመግባባቶችን በሽምግልና የሚፈታ የመጀመርያው የበየነ-መንግሥታት ድርጅት እንደሚሆን ገልጸዋል፡፡
በተጨማሪም ድርጅቱ የዓለም አቀፉን ማኀበረሰብ ሰላም፣ ጸጥታ፣ ፍትሃዊነት እንዲሁም ሁሉንም ወገን አሸናፊ የሚያደርግ ትብብርን ያበረታታል ብለዋል።
መድረኩን የመሩት በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የህግ ጉዳዮች ዳ/ጄኔራል አምባሳደር ረታ አለሙ ኢትዮጵያ የድርጅቱን ምስረታ መርሆች እና ሂደት ደጋፊ መሆኗን ገልጸው የተቀሩ የአፍሪካ አገራትም ድርጅቱን እውን ለማድረግ በሚደረገው ጥረት ላይ እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ድርጅቱ በሁለትዮሽ እና በባለብዙ ወገን መድረኮች አለመግባባቶች ሲከሰቱ መፍትሔ ለመስጠት እንደሚያስችልም አስታውቀዋል፡፡
በምክክር መድረኩ ላይ የኢትዮጵያና የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ ተቀማጭነታቸውን በአዲስ አበባ ያደረጉ የአፍሪካ አገራት የዲፕሎማቲክ ማኀበረሰብ አባላት፣ ምሁራን እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች መታደማቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

👍29❤9
📣ማስታወቂያ 📣
ክቡራን ደንበኞቻችን ባንካችን የሚሰጠዉን አገልግሎት በተመለከተ ማንኛውም ጥያቄ ለመጠየቅ ወይም እገዛ ለማግኘት 871 ላይ በነፃ ይደዉሉ::
Kabajamtoota Maamiltoota keenya,tajaajila Baankii keenyaan walqabatee gaaffii ykn gargaarsa barbaaddan kamiifuu 871 irratti bilisaan nuuf bilbilaa.
#Siinqee_Bank #Baankii_Siinqee #ሲንቄ_ባንክ
#EMPOWERED_TOGETHER
#etv #EBC

👍19❤7
ኢትዮጵያ በተ.መ.ድ. ጠቅላላ ጉባኤ ላይ በመሳተፍ ላይ ትገኛለች
*********************
ኢትዮጵያ በኒውዮርክ እየተካሄደ በሚገኘው 79ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) ጠቅላላ ጉባኤ እየተሳተፈች ነው።
በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሤ የተመራ የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን በመድረኩ በመሳተፍ ላይ ይገኛል።
በልዑካን ቡድኑ ውስጥ የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር)፣ የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ እና የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ/ር) ይገኙበታል።

👍50❤16👏3👎2
ለመስቀል ደመራ በዓል ዝግ የሚደረጉ መንገዶችን የአዲስ አበባ ፖሊስ ይፋ አደረገ
*******************
መስከረም 16/2017 ዓ/ም በመስቀል አደባባይ በሚከበረው የመስቀል ደመራ በዓል ምክንያት የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይፈጠር የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ ስለሚሆኑ አሽከርካሪዎች አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡
የ2017 ዓ/ም የመስቀል ደመራ በዓል በሠላም እንዲከበር የፀጥታ አካላት ዝግጅታቸውን አጠናቀው ወደ ስራ መግባቸው የሚታወቅ ሲሆን መስከረም 16 ቀን 2017 ዓ/ም ከረፋዱ 5:00 ሰአት ጀምሮ እስከ መርሀ ግብሩ ፍፃሜ ድረስ ለተሽከርካሪዎች ዝግ የሚደረጉ መንገዶችን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል።
https://www.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid0aRuqEGqSyWTc22gR31RUfndmEnWaYhHdQo6zfkYjdVvCfjvupWUUth4ahCba8Cedl

Facebook
Ethiopian Broadcasting Corporation
ለመስቀል ደመራ በዓል ዝግ የሚደረጉ መንገዶችን የአዲስ አበባ ፖሊስ ይፋ አደረገ
*******************
መስከረም 16/2017 ዓ/ም በመስቀል አደባባይ በሚከበረው የመስቀል ደመራ በዓል ምክንያት የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይፈጠር የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ ስለሚሆኑ አሽከርካሪዎች አማራጭ መንገዶችን...

👍12
በሕዝብ ማመላለሻ አውቶብስ ላይ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ28 ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተገለፀ
*******************
መነሻውን ወላይታ ሶዶ አድርጎ ወደ ዳዉሮ ዞን እየተጓዘ በነበረ የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ላይ ከፍተኛ የትራፊክ አደጋ ደርሶ እስካሁን 28 ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተገልጿል።
መለስተኛ የህዝብ ማመላለሻ አውቶብሱ በኪንዶ ዲዳዬ ወረዳ፣ ፋታታ ቀበሌ ግእርባ ወንዝ ውስጥ በመግባቱ አደጋ የተከሰተ መሆኑ ተጠቁሟል።
የዞኑ የሠላም እና ፀጥታ መምሪያ ኃላፊ ኮማንደር ተስፋዬ ሳፓ በተለይ ለኢቢሲ እንደገለፁት የሟቾች ቁጥር ከላይ ከተገለፀው ሊጨምር ይችላል።
በትግስቱ ቡቼ

👍22❤4
ኢቢሲ ወደ ይዘት
#የዛሬይቱ_ኢትዮጵያ
ነገን ዛሬ
የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ወደ ይዘት በሚል በጀመረው ለውጥ መሰረት አዳዲስ የይዘትና የአቀራረብ ማሻሻያዎችን በማድረግ ወደ ተመልካቾች የተለያዩ ዝግጅቶችን ማድረስ ጀምሯል።
ከእነዚህ አዳዲስ ፕሮግራሞች አንዱ የሆነው የዛሬይቱ ኢትዮጵያ- ነገን ዛሬ ፕሮግራም የሀገራችንን እድገትና ልማት፣ የኢትጵያን ልዕልና የሚያረጋግጡ፣ ሰላምና ልማትን የሚያፋጥኑ፣ ዜጎች የጋራ ታሪክ፣ የጋራ ተስፋ፣ የጋራ ሀገር እንዲፈጥሩና እንዲያፀኑ የሚያሰችሉ ይዘቶች ፤ ጠንካራ ሀገረ መንግስት ለመገንባት የሚያስችሉ የአስተሳሰብ፣ ፍልስፍናዊ ጉዳዮች፣ ኪነ-ጥበባዊ፣ የባህል፣ የታሪክ፣ የእምነት፣ የልማትና የማህራዊ መስተጋር ጉዳዮች በስፋት የሚዳሱበትና ውይይት የሚደረግበት ሳምንታዊ ፕሮግራም እነሆ ዛሬ ይጀምራል።
የዛሬይቱ ኢትዮጵያ - ነገን ዛሬ በየሳምንቱ ረቡዕ ከምሽቱ 3 ሰዓት ጀምሮ ወደ እናንተ እናደርሳለን።
ዛሬ ምሽት 3 ሰዓት ላይ በኢቲቪ ዜና ብቻ ይጠብቁን
የዛሬይቱ ኢትዮጵያ
ነገን ዛሬ
ትርክት ትናንት ፤ ዛሬና ነገ
#etv #EBC #የዛሬይቱ_ኢትዮጵያ

👍29❤6👎2
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የመስቀል ደመራ በዓልን በሰላም ለማክበር ከሃይማኖት አባቶች ጋር ውይይት አደረገ
*************
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የመስቀል ደመራ በዓልን በሰላም ለማክበር ከሃይማኖት አባቶች ጋር በዋና መሥሪያ ቤቱ ውይይት አድርጓል።
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል፥ ኅብረተሰቡ የመስቀል ደመራ በዓልን በሰላም እንዲያከብር፤ ከውጭ ሀገራት የሚመጡ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን፣ ቱሪስቶች፣ የሃይማኖት መሪዎች እና ሌሎች ታዳሚዎችም በዓሉን በሰላም አክብረው ወደ መጡበት እንዲመለሱ በቂ የሰው ኃይል እና አነፍናፊ ውሾችን በመጠቀም የተጠናከረ ፍተሻ በማካሄድ አካባቢዎቹን የማጥራት ሥራ እየተሠራ መሆኑን ገልፀዋል።
ፖሊስ የተለያዩ አደረጃጀቶችን በመፍጠር ኦሬንቴሽን በመስጠት ወደ ሥራ መግባቱን እና የፖሊስ ሠራዊቱ በፖሊሳዊ ሥነ-ምግባር በጨዋነት ፍተሻውን እንደሚያካሄድ የገለፁት ኮሚሽነር ጀነራል፤ ሕዝቡም ፍተሻው ለጋራ ጥቅም መሆኑን በመገንዘብ ቀና ትብብር እንዲያደርግ መልዕክት አስተላልፈዋል።
የሃይማኖት አባቶች በበኩላቸው፥ የፀጥታና ደኅንነት አካላት በዓሉ በሰላም እንዲከበር ተግተው መሥራታቸውን አንስተው ለሠሩት የቅድመ ወንጀል መከላከል ተግባር ምስጋና አቅርበዋል።
የተከለከሉና የተፈቀዱ ነገሮችን በመለየት ለምዕመናን ግንዛቤ የማስጨበጥ ሥራ ማከናወናቸውንም ተናግረዋል።
ሁላችንም የየድርሻችንን በመወጣት፤ ችግሮቻችንን በመቀራረብና በሰላማዊ መንገድ በመፍታት፤ ሰላምን አንግሶ ጥላቻን በማስወገድ በዓሉን በሰላም፣ በደስታ እና በፍቅር ማክበር ይጠበቅብናል ሲሉ የሃይማኖት አባቶች መልዕክት ማስተላለፋቸውን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ መረጃ ያመለክታል።

👍22❤3👏3