EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation) – Telegram
EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)
138K subscribers
38.3K photos
462 videos
80 files
13.1K links
EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation) @etvafaanoromoo1
@ETVkidschannel
@EBCWORLD1
@etventertainment1
Download Telegram
ለመስቀል ደመራ በዓል ዝግ የሚደረጉ መንገዶችን የአዲስ አበባ ፖሊስ ይፋ አደረገ
*******************

መስከረም 16/2017 ዓ/ም በመስቀል አደባባይ በሚከበረው የመስቀል ደመራ በዓል ምክንያት የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይፈጠር የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ ስለሚሆኑ አሽከርካሪዎች አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡

የ2017 ዓ/ም የመስቀል ደመራ በዓል በሠላም እንዲከበር የፀጥታ አካላት ዝግጅታቸውን አጠናቀው ወደ ስራ መግባቸው የሚታወቅ ሲሆን መስከረም 16 ቀን 2017 ዓ/ም ከረፋዱ 5:00 ሰአት ጀምሮ እስከ መርሀ ግብሩ ፍፃሜ ድረስ ለተሽከርካሪዎች ዝግ የሚደረጉ መንገዶችን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል።
https://www.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid0aRuqEGqSyWTc22gR31RUfndmEnWaYhHdQo6zfkYjdVvCfjvupWUUth4ahCba8Cedl
👍12
በሕዝብ ማመላለሻ አውቶብስ ላይ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ28 ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተገለፀ
*******************
መነሻውን ወላይታ ሶዶ አድርጎ ወደ ዳዉሮ ዞን እየተጓዘ በነበረ የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ላይ ከፍተኛ የትራፊክ አደጋ ደርሶ እስካሁን 28 ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተገልጿል።
መለስተኛ የህዝብ ማመላለሻ አውቶብሱ በኪንዶ ዲዳዬ ወረዳ፣ ፋታታ ቀበሌ ግእርባ ወንዝ ውስጥ በመግባቱ አደጋ የተከሰተ መሆኑ ተጠቁሟል።
የዞኑ የሠላም እና ፀጥታ መምሪያ ኃላፊ ኮማንደር ተስፋዬ ሳፓ በተለይ ለኢቢሲ እንደገለፁት የሟቾች ቁጥር ከላይ ከተገለፀው ሊጨምር ይችላል።
በትግስቱ ቡቼ
👍224
ኢቢሲ ወደ ይዘት

#የዛሬይቱ_ኢትዮጵያ
ነገን ዛሬ

የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ወደ ይዘት በሚል በጀመረው ለውጥ መሰረት አዳዲስ የይዘትና የአቀራረብ ማሻሻያዎችን በማድረግ ወደ ተመልካቾች የተለያዩ ዝግጅቶችን ማድረስ ጀምሯል።

ከእነዚህ አዳዲስ ፕሮግራሞች አንዱ የሆነው የዛሬይቱ ኢትዮጵያ- ነገን ዛሬ ፕሮግራም የሀገራችንን እድገትና ልማት፣ የኢትጵያን ልዕልና የሚያረጋግጡ፣ ሰላምና ልማትን የሚያፋጥኑ፣ ዜጎች የጋራ ታሪክ፣ የጋራ ተስፋ፣ የጋራ ሀገር እንዲፈጥሩና እንዲያፀኑ የሚያሰችሉ ይዘቶች ፤ ጠንካራ ሀገረ መንግስት ለመገንባት የሚያስችሉ የአስተሳሰብ፣ ፍልስፍናዊ ጉዳዮች፣ ኪነ-ጥበባዊ፣ የባህል፣ የታሪክ፣ የእምነት፣ የልማትና የማህራዊ መስተጋር ጉዳዮች በስፋት የሚዳሱበትና ውይይት የሚደረግበት ሳምንታዊ ፕሮግራም እነሆ ዛሬ ይጀምራል።

የዛሬይቱ ኢትዮጵያ - ነገን ዛሬ በየሳምንቱ ረቡዕ ከምሽቱ 3 ሰዓት ጀምሮ ወደ እናንተ እናደርሳለን።

ዛሬ ምሽት 3 ሰዓት ላይ በኢቲቪ ዜና ብቻ ይጠብቁን
የዛሬይቱ ኢትዮጵያ
ነገን ዛሬ
ትርክት ትናንት ፤ ዛሬና ነገ
#etv #EBC #የዛሬይቱ_ኢትዮጵያ
👍296👎2
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የመስቀል ደመራ በዓልን በሰላም ለማክበር ከሃይማኖት አባቶች ጋር ውይይት አደረገ
*************

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የመስቀል ደመራ በዓልን በሰላም ለማክበር ከሃይማኖት አባቶች ጋር በዋና መሥሪያ ቤቱ ውይይት አድርጓል።

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል፥ ኅብረተሰቡ የመስቀል ደመራ በዓልን በሰላም እንዲያከብር፤ ከውጭ ሀገራት የሚመጡ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን፣ ቱሪስቶች፣ የሃይማኖት መሪዎች እና ሌሎች ታዳሚዎችም በዓሉን በሰላም አክብረው ወደ መጡበት እንዲመለሱ በቂ የሰው ኃይል እና አነፍናፊ ውሾችን በመጠቀም የተጠናከረ ፍተሻ በማካሄድ አካባቢዎቹን የማጥራት ሥራ እየተሠራ መሆኑን ገልፀዋል።

ፖሊስ የተለያዩ አደረጃጀቶችን በመፍጠር ኦሬንቴሽን በመስጠት ወደ ሥራ መግባቱን እና የፖሊስ ሠራዊቱ በፖሊሳዊ ሥነ-ምግባር በጨዋነት ፍተሻውን እንደሚያካሄድ የገለፁት ኮሚሽነር ጀነራል፤ ሕዝቡም ፍተሻው ለጋራ ጥቅም መሆኑን በመገንዘብ ቀና ትብብር እንዲያደርግ መልዕክት አስተላልፈዋል።

የሃይማኖት አባቶች በበኩላቸው፥ የፀጥታና ደኅንነት አካላት በዓሉ በሰላም እንዲከበር ተግተው መሥራታቸውን አንስተው ለሠሩት የቅድመ ወንጀል መከላከል ተግባር ምስጋና አቅርበዋል።

የተከለከሉና የተፈቀዱ ነገሮችን በመለየት ለምዕመናን ግንዛቤ የማስጨበጥ ሥራ ማከናወናቸውንም ተናግረዋል።

ሁላችንም የየድርሻችንን በመወጣት፤ ችግሮቻችንን በመቀራረብና በሰላማዊ መንገድ በመፍታት፤ ሰላምን አንግሶ ጥላቻን በማስወገድ በዓሉን በሰላም፣ በደስታ እና በፍቅር ማክበር ይጠበቅብናል ሲሉ የሃይማኖት አባቶች መልዕክት ማስተላለፋቸውን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ መረጃ ያመለክታል።
👍223👏3
በ8 የተለያዩ ቋንቋዎች የተከናወነው የመስቀል ደመራ መዝሙር የመጨረሻው ጥናትና ልምምድ
*********

በ2017 ዓ.ም የመስቀል ደመራ በዓል ከሚቀርቡ ኃይማኖታዊ ሥርዓቶች አንዱ ለበዓሉ የሚስማማ መዝሙር ነው።

ይህ መዝሙር የሰንበት ትምህርት ቤት መዘምራን ጊዜ ወስደው የሚዘጋጁበት ነው።

የማኅበረ ቅዱሳን ዋና ማዕከል ለ2017 ዓ.ም የመስቀል ደመራ በዓል ሲያደርገው የነበረውን የመዝሙር ጥናት ያጠናቀቀውም ዛሬ ነው።

በዛሬው ዕለትም ነገ በሚከናወነው የመስቀል ደመራ የሚቀርብ መዝሙር የመጨረሻ ጥናትና ልምምድ ተከናውኗል።

ዕለቱን የሚያወድሱ እና ሌሎች የምስጋና መዝሙራትን ጨምሮ የማዕከሉ ዘማሪያን ከ80 በላይ መዝሙራትን ሲያጠኑ ቆይተዋል።

የመዝሙር ጥናቱ በ8 የተለያዩ ቋንቋዎች ማለትም በግዕዝ፣ በአማርኛ፣ በአፋን ኦሮሞ፣ በትግርኛ፣ በወላይትኛ፣ በጉራግኛ እና በክስታንኛ ተከናውኗል።

ማዕከሉ የዘንድሮውን የመስቀል ደመራ በዓል በደመቀ እና ኃይማኖታዊ ሥርዓቱን በጠበቀ መልኩ ለማሳለፍ እንደተዘጋጀም ተገልጿል።

በአሰግድ ሲሳይ
👍5515👎10👏2
ቅኝት ስፖርት ኤፍ ኤም አዲስ 97.1

ማንቸስተር ዩናይትድ ከትዌንቴ የዩሮፓ ሊግ

https://www.facebook.com/share/v/YBKyx6SqqbdSmnv6/?mibextid=oFDknk
👍86
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የ2025 የአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ የምድብ 3ኛ እና 4ኛ ጨዋታዎቹን በኮትዲቯር ያደርጋል
*************

ዋልያዎቹ ከጊኒ ጋር የሚያደርጓቸው እነዚህ የደርሶ መልስ መረሐ ግብሮች በኮትዲቯር እንደሚደረጉ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን አስታውቋል።

የሁለቱ ሀገራት የመጀመሪያ ጨዋታ ጊኒ የሜዳዋ ጨዋታዋን ለማድረግ ባስመዘገበችውና በያሞሱክሩ በሚገኘው ስታድ ኮናን ባኒ ስታዲየም ጥቅምት 1/2017 ከምሽቱ 1፡00 ላይ ይከናወናል።

ሁለተኛው ጨዋታ ደግሞ ኢትዮጵያ ባስመዘገበችውና አቢጃን በሚገኘው ስታድ ደ ኢቢምፔ ስታዲየም ጥቅምት 4/2017 ምሸት 4፡00 ላይ ይደረጋል።

ሞሮኮ በ2025 ለምታሰናዳው የአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ እስካሁን ሁለት ጨዋታዎችን ያደረጉት ዋልያዎቹ አንድ ነጥብ በመያዝ ሶስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል።

ጊኒ በአንጻሩ እስካሁን ምንም ነጥብ አላስመዘገበችም።

በዮሴፍ ሹምዬ
👍313👎3
ፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ የተ.መ.ድ. ዋና ጸሐፊ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ሀና ቴቴን አሰናበቱ
**************

ፕሬዚዳንቷ በዚሁ ወቅት ልዩ መልዕክተኛዋ ለኢትዮጵያና ለአፍሪካ ቀንድ ላበረከቱት ከፍተኛ ድጋፍ ማመስገናቸውን የፕሬዚዳንት ጽሕፈት ቤት መረጃ ያመለክታል።
👍4412