EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation) – Telegram
EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)
138K subscribers
38.2K photos
458 videos
80 files
13.1K links
EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation) @etvafaanoromoo1
@ETVkidschannel
@EBCWORLD1
@etventertainment1
Download Telegram
የመስቀል ደመራ በዓል ድባብ በደብረ ማርቆስ ከተማ
14👍13👎1
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለመስቀል በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላለፉ
***********

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለ2017 ዓመት የመስቀል በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለበዓሉ ያስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ይቀርባል፡-

የመስቀል በዓል የሕልም ጉልበት የታየበት በዓል ነው፡፡

ንግሥት ዕሌኒ መስቀሉን ለማውጣት ያለመችው ምንም አመቺ ነገር ባልነበረበት ጊዜ ነው፡፡ ዙሪያዋ ጨለማ ነበር፡፡ መንገዶች ሁሉ ዝግ ነበሩ፡፡ ነገሮች ሁሉ አስቸጋሪ ነበሩ፡፡ ማንም በማያስበው ጊዜ፤ አይቻልም አይሞከርም በሚባልበት ወቅት፤ አንድ ቀን፤ ፈጣሪዋ ሲፈቅድ፤ መስቀሉን ከተቀበረበት ሥፍራ ለማውጣት ሕልም ነበራት፡፡

ሕልሟ እንዲሳካ ሠራች፤ ታገለች፡፡ ጨለማውን እየገፈፈች፤ አስቸጋሪውን ጎዳና እየጠረገች፤ ከውስብስብ ችግሮች ጋር እየተጋፈጠች ወደ ፊት ተጓዘች፡፡ በመጨረሻም ኢየሩሳሌም ተሻግራ፣ መስቀሉን ከተቀበረበት ሥፍራ ለማውጣት በቃች፡፡ ሕልሟ እውን ሆነ፡፡ ታሪክን ቀየረች፡፡ ልዕልናን ዐወጀች፡፡ ደመራ ለሚታገል፤ ተስፋ ለማይቆርጥና እስከ መጨረሻው ለሚጸና ሰው ሕልሙ አንድ ቀን እውን እንደሚሆን የሚያሳይ ትእምርት ነው፡፡
https://www.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid0fhvFHPF476JMQQZc67nK5sHuGbERdXmS1so9mfrh8xLXkdBwhQKYcLnyB5y4Xwxnl
👍2916👏6
"እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ አደረሳችሁ" - ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
****************

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ለመስቀል በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለበዓሉ ያስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ይቀርባል፡-

የመስቀል በዓል ከሰሜን እስከ ደቡብ፣ ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ በኢትዮጵያውያን የሚከበር በዓል ነው። አከባበሩ ኅብራዊ ነው። የየአካባቢው ቀለም ይጨመርበታል። የሚከበረው ግን በተመሳሳይ ወቅት ነው። ከግላዊ ይልቅ ቤተሰባዊና ማኅበራዊ በዓል ነው።

መስቀል ነባር ኅብረ ብሔራዊ አንድነታችንን ያሳያል። በብዙ አካባቢዎች የዘመን መለወጫ በዓላት በመስከረም ወር፣ ከመስቀል በዓል ጋር ተያይዘው መከበራቸው ጥንታዊ ማኅበራዊ ትሥሥራችንን ሳያመለክት አይቀርም።
https://www.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid02fDXJHU7VJFrK1EP91aj97ZFgMrev2yGDVYD7K3H17hNyq8u7A5LmpcWPKaAGF2xbl
👍21👏5
የሀረሪ ክልል መንግስት ለመስቀል በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፈ
******************

የሀረሪ ክልላዊ መንግስት ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች ለደመራና ለመስቀል በዓል የአንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላልፏል፡፡

የክልሉ መንግስት በመልእክቱ፤ ህዝበ ክርስትያኑ የደመራ በዓል አከባበር እሴቱን ጠብቆ እንዲከበር በማድረግ የተቸገሩ ወገኖችን በማብላትና የተጠሙትን በማጠጣት እንዲሁም የተለመደ የመተዛዘንና የመረዳዳት ባህሉን በመተግበር በዓሉን እንዲያከብር ጥሪ አቅርቧል።

ህዝበ ክርስትያኑን ጨምሮ መላው የክልሉ ነዋሪ ሰላምን፣ አብሮነትን፣ መተባበርንና ወንድማማችነት እና እህትማማችነትን በማጎልበት እንዲሁም በክልሉ የተጀመሩ ሁሉን አቀፍ የልማት ተግባራት እንዲጠናከርም ጠይቋል።

የክልሉ መንግስት ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች ለደመራና ለመስቀል በዓል የአንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላልፎ፤ በዓሉ የሰላም፣ የአንድነት፣ የመተሳሰብ፣ የደስታና የፍቅር እንዲሆን ተመኘቷል።
7👍6
ርዕሰ መስተዳደር ሽመልስ አብዲሳ በኦሮሚያ ክልል የተጀመረውን አዲስ የቀበሌ አደረጃጀት የስራ እንቅስቃሴ ጎበኙ
********************

የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ሽመልስ አብዲሳ እና የብልፅግና ፓርቲ የኦሮሚያ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ኃላፊ ከፍያለው ተፈራ በክልሉ የተጀመረውን አዲስ የቀበሌ አደረጃጀት በምስራቅ ሸዋ ዞን ሉሜ ወረዳ ጠዴ ድልዲማ በመገኘት ጎብኝተዋል፡፡

በምስራቅ ሸዋ ዞን 302 ቀበሌዎች በአዲሱ አደረጃጀት የተዋቀሩ ሲሆን 281 የሚሆኑት ወደ ስራ መግባታቸዉን የዞኑ አስተዳደር አቶ አባቦ ማሞ ገልፀዋል::

በሉሜ ወረደ የጠዴ ድልዲማ ቀበሌ አስተዳደር ወ/ሮ ትግስት ኢብራህም የህዝብ አገልግሎት በቀበሌ ደረጃ እንዲሰጥ መደረጉ የበለጠ አመራሩ እራሱን ሰጥቶ ህዝቡን በንቃት እንዲገለግል አድርጎታል ብለዋል::

ነዋሪዎችም አገልግሎት በቅርበት ማግኘታቸው እንዳስደታቸው እና ግዜያቸዉን እንደቆጠበላቸዉ ገልፀዋል::

በዓሊ ደደፎ
👍18👎5
የመስከረም ስጦታው የሙዚቃ ንጉሥ፦ ክቡር ዶክተር አርቲስት ጥላሁን ገሠሠ
********************

ለግማሽ ምዕተ ዓመት በኢትዮጵያ ሙዚቃ ግንባር ቀደም ሆኖ ካለፉት ኮከቦች መካከል አንዱ ነበር፤ ለዚህም ነው "የኢትዮጵያ ሙዚቃ ንጉሥ" የሚል መጠሪያ የተሰጠው፡፡

"በፀሐይ ብርሃን ደምቃ፣ ክረምትና በጋ፤

የትውልድ አገር ያላት፣ የአስራ ሦስት ወር ጸጋ፤…" በሚለው እና ከመስከረም ጀምሮ እስከ ቡሄ በሚዘልቀው ዜማው የኢትዮጵያውያንን ውብ የዓውደ ዓመት አከባበር ባህል በአእምሮአችን የሚስልልን ባለዜማን መስከረም ለኢትዮጵያ የለገሰችው እንዲህ እንደሚንቆለጳጵሳት አውቃ ይሆን ያስብላል! ጥላሁን፦

"አቤት በአዲሱ ዓመት - ዘመኑ ሲለወጥ፣

ያበቦቹ ሽታ - መዓዛው ሲመስጥ፤

ኮበሌውም ሲጨፍር - ሲል መስከረም ጠባዬ፤

ኮረዳዋም ባቅሟ - ስትዞር በራሷ ቀዬ፤…" እያለ ነው ኢትዮጵያውያን አዲስ ዓመትን ለአዲስ ህይወት እና አዲስ ተስፋ ጅማሮ እንደ ንጋት የሚቀበሏትን መስከረም ያወሳት፡፡
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ፡- https://ebc.et/newsdetails.aspx?newsid=7879
👍196
ምስጢረኞቹ ቀጠሮ የማያዛንፉት የመስቀል ስጦታዎች
የመስቀል ወፍ እና አደይ አበባ የት ነው የሚደበቁት?
*******

የኢትዮጵያ አዲስ ዓመት የብሩህ ተስፋ ተምሳሌት ነው፡፡ ከጨለማ ወደ ብርሃን መውጫ፣ ከአሮጌ ወደ አዲስ መሸጋገሪያ ነው፡፡ መስከረም ላይ በሚጀመረው የኢትዮጵያ አዲስ ዓመት ብዙዎች ተስፋቸው እንደ ብራው ሰማይ ይፈካል፣ ከከርሞ ህልማቸው ጋር ይቀጣጠራሉ፡፡

በአሮጌው ዘመን ያሰለቻቸውን አሮጌ አስተሳሰብ ትተው በአዲስ መንፈስ ለአዲስ ስኬት ይዘጋጃሉ፤ የመስቀሏ ወፍ ላባዋን እንደምትቀይረው ኢትዮጵያውያንም ራሳቸውን አንጽተው ለቀጣዩ ፍሬያማ ጉዞ ይዘጋጃሉ፡፡ ምድር በዐደይ አበባ እንደምታጌጠው ኢትዮጵያውያንም በፀዓዳ ልብሳቸው ያጌጣሉ፡፡

መስከረም እንደ ሀገር የዘመን መቁጠሪያ ሆኖ በአንድነት የሚከበር ሲሆን፣ በኢትዮጵያ የሚገኙ አብዛኛዎቹ ብሔሮችም እንደ አዲስ ዘመን መባቻቸው አድርገው በተለያዩ ስያሜዎች ያከብሩታል፡፡ ደመራ ደምረው ሕብራቸውን ያደምቁበታል፤ ችቦ አብርተው መጻኢ ብርሃናቸውን ያዩበታል፡፡ ይህ ተፈጥሮን የተከተለ አከባበር በውስጡ በርካታ ምሥጢሮችን የያዘ የኢትዮጵያውያን ብቻ ሀብት ነው፡፡

መስቀል ሲመጣ ቀጠሮአቸውን የማያዛንፉት የመስቀል ወፍ እና ዐደይ አበባ ደግሞ የኢትዮጵያ ተስፋ ብስራት አድማቂዎች ናቸው፡፡
https://www.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid0ovWdqpuXWcUeyGuFangBugRf8Rn7oJgU8Q9HupVmyrY5w8VK1oGJC6ogHehkKF5bl
👍1710
እንኳን ለመስቀል በዓል በሠላም አደረሳችሁ!! - የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት
*****************

የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ለመስቀል በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላልፏል፡፡

አገልግሎቱ በዓሉን አስመልክቶ ያስተላለፈው የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ይቀርባል፡-

ኢትዮጵያ ካላት ሃይማኖታዊና ባህላዊ በዓላቶቻችን አንዱ የመስቀልና የደመራ በዓል ነው፡፡ በመላዉ ኢትዮጵያ መስከረም 16 የደመራ በዓል ተብሎ እንዲሁም መስከረም 17 ቀን የሚከበረዉ የመስቀል በዓል ጥንታዊነቱን ይዞ የቀጠለ የዐደባባይ በዓል በመሆኑ ኢትዮጵያ በዩኔስኮ ካስመዘገበቻቸዉ ቀርሶቻችን አንዱ ነው፡፡ የዐደባባይ በዓላቶቻችን የአብሮነት እሴቶቻችንን የሚያጎሉ፣ የብዝኃነታችን ጌጥነት ማሳያዎች ከመሆን ባሻገር የበርካታ ጎብኝዎችን ቀልብ የሚስቡ ሀብቶቻችን እየሆኑ መጥተዋል፡፡

መስከረም በርከት ያሉ በዓለት የምናከብርበት ወር ነው፤ ዛሬ እንኳ የመስቀል በዓልን ስናከብር የዓለም የቱሪዝም ቀንን ጭምር እያከበርን ነው፡፡ የዓለም ቱሪዝም ቀን በ1980 (እ.አ.አ) በተባበሩት መንግሥታት የዓለም ቱሪዝም ድርጅት ሐውልት መቆምን ምክንያት ተደርጎ የተመረጠ የቱሪዝም መታሰቢያ ቀን ነው፡፡
https://www.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid0ZFexyc8JkA9T3VV5XN7gWhvoB3kbuKwYyL3Jgnm5vebfgbcqd6NqKQ5kfKLdDMhKl
👍1514