የመስቀል ደመራ ስነ-ስርዓት የመስቀሉ ክብር በአደባባይ የሚዘከርበት ልዩ በዓል ነው - ቀሲስ መዝገቡ ካሳ (ዶ/ር)
*************
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ- ክርስቲያን መገናገኛ ብዙሃን አገልግሎት ዋና ስራ አስኪያጅ እና በቅድስት ስላሴ ዩኒቨርስቲ መምህር የሆኑት ቀሲስ መዝገቡ ካሳ (ዶ/ር) ከኢቲቪ ጋር በነበራቸው ቆይታ፤ የመስቀል ደመራ ስነ-ስርዓት የመስቀሉ ክብር በአደባባይ የሚዘከርበት ልዩ በዓል ነው ብለዋል፡፡
መስቀል ወንበዴዎች የሚቀጡበት መሳሪያ ነበር ያሉት መምህሩ፤ እየሱስ ክርስቶስም እንደ ወንበዴ ተቆጥሮ በመስቀል ላይ መሰቀሉን ተናግረዋል፡፡
እንደ አይሁድ እሳቤ ክርስቶስን በመስቀል መግደላቸው ማዋረዳቸው የነበረ ቢሆንም ከክርስቶስ ሞት በኋላ ግን መስቀል ዓለም የዳነበት ሊሆን ችሏል ብለዋል፡፡
መስቀል ባህል ሳይሆን ከመሰረታዊ የሰው ልጆች ህልውና ጋር የተያያዘ ነው የሚሉት መምህሩ፤ መስቀልን ስናስብ የአዳም እና የክርስቶስ ሞት የምናስብበት፣ የአዳም ሞት በህይወት የቀየረውን ክርስቶስ የምንዘክርበት ነው ብለዋል፡፡
መስቀል ሞታችን በህይወት መቀየሩን ያሳየል ሲሉም አንስተዋል፡፡
https://www.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid0xtu2uYDdCBhArymupk979p7PduoTzpXCaY8SFnwQe2oW5zb7f2hQ7ZxWxiSPqv5Jl

👍26❤10👏4
የደመራ ማብራት ሥነ-ስርአት
በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ እየተከበረ የሚገኘው የደመራ በዓል በፎቶ
በናርዶስ ሲሳይ
#etv #EBC #ደመራ
https://www.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid0sHLpmPMTiw3osoDVibsFFezMn4XMViPwGZiAGm3uWDfkyYpzjQicvGRikyDERmBCl

Facebook
Ethiopian Broadcasting Corporation
የደመራ ማብራት ሥነ-ስርአት
በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ እየተከበረ የሚገኘው የደመራ በዓል በፎቶ
በናርዶስ አዳነ
#etv #EBC #ደመራ
በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ እየተከበረ የሚገኘው የደመራ በዓል በፎቶ
በናርዶስ አዳነ
#etv #EBC #ደመራ
👍21❤7
"የብሪክስ ማዕቀፍ በዓለም አቀፍ ተቋማት ፍትሀዊ ውክልና እንዲሰፍን ጉልህ ሚና መጫወት ይጠበቅበታል" - አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ
****************
በኒውዮርክ እየተካሄደ ከሚገኘው 79ኛው የተመድ ጠቅላላ ጉባዔ ጎን ለጎን የብሪክስ አባል አገራት ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባ ተካሂዷል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ በስብሰባው ላይ ባደረጉት ንግግር፥ በዓለም አቀፍ ተቋማት አስተዳደር እና በዓለም አቀፍ ጉዳዮች ዙሪያ ፍትሀዊ ውክልና እና ተሰሚነት እንዲሰፍን በሚደረገው የማሻሻያ ጥረት የብሪክስ ማዕቀፍ ከፍተኛ ሚና ይኖረዋል የሚል ተስፋ እየጨመረ መምጣቱን ገልጸዋል።
አምባሳደር ታዬ የባለብዙወገን ዓለም አቀፍ ተቋማቱ አሳታፊ እና ጠንካራ እንዲሆኑ የተጀመሩ የማሻሻያ ጥረቶች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው አንስተዋል።
ሚኒስትሩ የተመድ የጸጥታው ምክር ቤት ማሻሻያን በተመለከተ ባደረጉት ንግግር፥ ማሻሻያው ቅድሚያ ለአፍሪካ ውክልና መስጠት እንደሚገባው እና ታማኝ እና ፍትሃዊ ሆኖ መቀጠል እንዳለበት ጠቁመዋል።
አምባሳደር ታዬ በጸጥታው ምክር ቤት ማሻሻያ ላይ ኢትዮጵያ የምታራምደው አቋም የአፍሪካን አቋም ነው፤ ለአፍሪካ ሕጋዊ ጥያቄ እና ታሪካዊ ኢ-ፍትሀዊነት ግማሻ ምላሽ ሊሰጠው አይገባም ብለዋል።
ሚኒስትሩ ውክልናው መልከዓ ምድርን፣ የብሪክስን የጋራ ዕሴቶችን እና በብሪክስ ማዕቀፍ አባል አገራት መካከል ያለውን ግንኙነት እንዲሁም የተመድን ቻርተር ባማከለ መልኩ መከናወን እንዳለበትም ጠቁመዋል።
እነዚህ መርሆዎች ብሪክስ በዓለም አቀፍ ተቋማት ማሻሻያ እና ፍትሀዊ ውክልና እንዲኖር የሚጫወተውን ሚና የበለጠ ያጠናክሩለታል ማለታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።

👍53❤3
የሀዲያ የዘመን መለወጫ (ያሆዴ) በደቡብ አፍሪካ ተከበረ
********************
በደቡብ አፍሪካ ደርባን በሚኖሩ የብሔሩ ተወላጆች የዳያስፖራ አባላት የሀዲያ የዘመን መለወጫ (ያሆዴ) በድምቀትአከበሩ።
በበዓሉ ላይ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ተወካዮች እና የአካባቢው ነዋሪ የሆኑ የዳያስፖራ አባላት ተገኝተውዋል።
#etv #EBC
https://www.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid02Fd1do5AjjpxJkewe58gsz1cDiUzVKe5FUxugM39LBouf329A7RBz9odHGgxTxsqBl

በበዓሉ ላይ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ተወካዮች እና የአካባቢው ነዋሪ የሆኑ የዳያስፖራ አባላት ተገኝተውዋል።...

👍15❤5👏1
አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ ከዴንማርክ አቻቸው እና ከተባበሩት አረብ ኢምሬቶች የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ጋር ተወያዩ
**********
በኒውዮርክ እየተካሄደ ከሚገኘው 79ኛው የተመድ ጉባዔ ጎን ለጎን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ ከዴንማርክ አቻቸው ላርስ ሎክ ራስምሰን ጋር ተወያይተዋል።
አምባሳደር ታዬ በውይይቱ ላይ ዴንማርክ የተመድ የጸጥታው ምክር ቤት አባል ሆና በመመረጧ የተሰማቸውን ደስታ በመግለጽ፤ በወቅታዊ የአፍሪካ ቀንድ ጉዳዮች እና ኢትዮጵያ ሽብርተኝነትን በመዋጋት ረገድ ባላት ቁርጠኝነት ዙሪያ ገለጻ አድርገዋል።
በተያያዘ አምባሳደር ታዬ ከተባበሩት አረብ ኢምሬቶች የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ሼህ ሻክቡት ናህያን አል ናህያን ጋር በሁለትዮሽ እና በአፍሪካ ቀንድ ሰላም እና ደኀንነት ዙሪያ መክረዋል።
ሶማሊያን በተመለከተ ባደረጉት ውይይት አምባሳደር ታዬ የቀጣናው አገራት ዋጋ የከፈሉበት እና የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ከፍተኛ ወጪ ያወጣበት የሶማሊያ ደህንነት እንዲቀጥል ማድረግ ወሳኝ ጉዳይ መሆኑን ተናግረዋል።
ሚኒስትሩ ከድህረ አትሚስ በኋላ የሚኖረው የኃይል ሥምሪት ጊዜ ተወስዶ በጥንቃቄ መከናወን እንዳለበት መግለፃቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።

👍31❤3👎1👏1
በፕሪሚየር ሊጉ ቅዱስ ጊዮርጊስ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲን 2 ለ 1 አሸነፈ
******************
በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 2ኛ ሳምንት መርሃ ግብር ቅዱስ ጊዮርጊስ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲን 2 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡
ለቅዱስ ጊዮርጊስ የማሸነፊያ ግቦቹን ፍፁም ጥላሁን በ7ኛው እንዲሁም አማኑኤል ኤርቦ በ71ኛው ደቂቃ አስቆጥረዋል፡፡
ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲን ከሽንፈት ያልታደገቸውን ብቸኛ ግብ ኪሩቤል ወንድሙ በ13ኛው ደቂቃ ከመረብ አሳርፏል፡፡
በሌላኛው የፕሪሚየር ሊግ የሁለተኛ ሳምንት መርሃ ግብር ምሽት 1 ሰዓት ባህር ዳር ከተማ እና አዳማ ከተማ ጨዋታቸውን የሚያደርጉ ይሆናል።

👍24❤3
አቶ አገኘሁ ተሻገር በካናዳ የስራ ጉብኝት አደረጉ
***************
የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አገኘሁ ተሻገር በካናዳ ለሁለት ቀናት የስራ ጉብኝት አደረጉ።
በጉብኝታቸው ከካናዳ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ጌርግ ፈርጉሰን እና ከሌሎች የመንግስት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ጋር በሁለቱ አገራት ግንኙነት ዙሪያ ውይይት አድርገዋል።
በውይይቱ፤ በኢትዮጵያ እና ካናዳ የፌዴራል ስርአት እና አሰራር ዙሪያ ምክክር የተደረገ ሲሆን፤ በሁለቱ አገራት ምክር ቤቶች መካከል ያለውን ትብብር ማጠናከር እንደሚገባ ተጠቁሟል።
ካናዳ በኢኮኖሚ ልማት እና ሰብአዊ መስኮች ለኢትዮጵያ እያደረገች ለሚገኘው ድጋፍ አቶ አገኘሁ ምስጋና ያቀረቡ ሲሆን በቀጣይ በቴክኖሎጂ ፣ በንግድ እና ኢንቬስትመንት የአገራቱ ግንኙነት ለማስፋት እንደሚሰራም መናገራቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።
አዳዲስ የትብብር መስኮችን ለመለየት 8ኛው የኢትዮ-ካናዳ የፓለቲካ ምክክር መድረክ በቅርብ ጊዜ ማካሄድ አስፈላጊ መሆኑም ተጠቅሷል።

👍20❤8