EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation) – Telegram
EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)
138K subscribers
38.3K photos
462 videos
80 files
13.1K links
EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation) @etvafaanoromoo1
@ETVkidschannel
@EBCWORLD1
@etventertainment1
Download Telegram
የመስቀል በዓል በወልድያ ከተማ
የወልድያ ከተማ ነዋሪዎች የመስቀል በዓል ለማክበር ወደ መስቀል ማክበሪያው ስፍራ ከተለያዩ አጥቢያዎች በመነሳት ተመዋል።
በወልድያ መስቀል አደባባይ ካህናት፣ ዲያቆናት እና የሰንበት ተማሪዎች መስቀልን የሚያወድሱ ወረብ እና ዝማሬዎች እያቀረቡ ነው።
አሚኮ
#etv #EBC #ደመራ
https://www.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid02DajgnM9iUWUkw7iprryza4YYi8nhrNb8ieGEo4NnXRiyqQqiAhiUH3f5JtPzKnMDl
8
Live stream finished (6 days)
የመስቀል ደመራ ስነ-ስርዓት የመስቀሉ ክብር በአደባባይ የሚዘከርበት ልዩ በዓል ነው - ቀሲስ መዝገቡ ካሳ (ዶ/ር)
*************

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ- ክርስቲያን መገናገኛ ብዙሃን አገልግሎት ዋና ስራ አስኪያጅ እና በቅድስት ስላሴ ዩኒቨርስቲ መምህር የሆኑት ቀሲስ መዝገቡ ካሳ (ዶ/ር) ከኢቲቪ ጋር በነበራቸው ቆይታ፤ የመስቀል ደመራ ስነ-ስርዓት የመስቀሉ ክብር በአደባባይ የሚዘከርበት ልዩ በዓል ነው ብለዋል፡፡

መስቀል ወንበዴዎች የሚቀጡበት መሳሪያ ነበር ያሉት መምህሩ፤ እየሱስ ክርስቶስም እንደ ወንበዴ ተቆጥሮ በመስቀል ላይ መሰቀሉን ተናግረዋል፡፡

እንደ አይሁድ እሳቤ ክርስቶስን በመስቀል መግደላቸው ማዋረዳቸው የነበረ ቢሆንም ከክርስቶስ ሞት በኋላ ግን መስቀል ዓለም የዳነበት ሊሆን ችሏል ብለዋል፡፡

መስቀል ባህል ሳይሆን ከመሰረታዊ የሰው ልጆች ህልውና ጋር የተያያዘ ነው የሚሉት መምህሩ፤ መስቀልን ስናስብ የአዳም እና የክርስቶስ ሞት የምናስብበት፣ የአዳም ሞት በህይወት የቀየረውን ክርስቶስ የምንዘክርበት ነው ብለዋል፡፡

መስቀል ሞታችን በህይወት መቀየሩን ያሳየል ሲሉም አንስተዋል፡፡
https://www.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid0xtu2uYDdCBhArymupk979p7PduoTzpXCaY8SFnwQe2oW5zb7f2hQ7ZxWxiSPqv5Jl
👍2610👏4
"የብሪክስ ማዕቀፍ በዓለም አቀፍ ተቋማት ፍትሀዊ ውክልና እንዲሰፍን ጉልህ ሚና መጫወት ይጠበቅበታል" - አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ
****************

በኒውዮርክ እየተካሄደ ከሚገኘው 79ኛው የተመድ ጠቅላላ ጉባዔ ጎን ለጎን የብሪክስ አባል አገራት ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባ ተካሂዷል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ በስብሰባው ላይ ባደረጉት ንግግር፥ በዓለም አቀፍ ተቋማት አስተዳደር እና በዓለም አቀፍ ጉዳዮች ዙሪያ ፍትሀዊ ውክልና እና ተሰሚነት እንዲሰፍን በሚደረገው የማሻሻያ ጥረት የብሪክስ ማዕቀፍ ከፍተኛ ሚና ይኖረዋል የሚል ተስፋ እየጨመረ መምጣቱን ገልጸዋል።

አምባሳደር ታዬ የባለብዙወገን ዓለም አቀፍ ተቋማቱ አሳታፊ እና ጠንካራ እንዲሆኑ የተጀመሩ የማሻሻያ ጥረቶች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው አንስተዋል።

ሚኒስትሩ የተመድ የጸጥታው ምክር ቤት ማሻሻያን በተመለከተ ባደረጉት ንግግር፥ ማሻሻያው ቅድሚያ ለአፍሪካ ውክልና መስጠት እንደሚገባው እና ታማኝ እና ፍትሃዊ ሆኖ መቀጠል እንዳለበት ጠቁመዋል።

አምባሳደር ታዬ በጸጥታው ምክር ቤት ማሻሻያ ላይ ኢትዮጵያ የምታራምደው አቋም የአፍሪካን አቋም ነው፤ ለአፍሪካ ሕጋዊ ጥያቄ እና ታሪካዊ ኢ-ፍትሀዊነት ግማሻ ምላሽ ሊሰጠው አይገባም ብለዋል።

ሚኒስትሩ ውክልናው መልከዓ ምድርን፣ የብሪክስን የጋራ ዕሴቶችን እና በብሪክስ ማዕቀፍ አባል አገራት መካከል ያለውን ግንኙነት እንዲሁም የተመድን ቻርተር ባማከለ መልኩ መከናወን እንዳለበትም ጠቁመዋል።

እነዚህ መርሆዎች ብሪክስ በዓለም አቀፍ ተቋማት ማሻሻያ እና ፍትሀዊ ውክልና እንዲኖር የሚጫወተውን ሚና የበለጠ ያጠናክሩለታል ማለታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።
👍533
የሀዲያ የዘመን መለወጫ (ያሆዴ) በደቡብ አፍሪካ ተከበረ
********************
በደቡብ አፍሪካ ደርባን በሚኖሩ የብሔሩ ተወላጆች የዳያስፖራ አባላት የሀዲያ የዘመን መለወጫ (ያሆዴ) በድምቀትአከበሩ።
በበዓሉ ላይ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ተወካዮች እና የአካባቢው ነዋሪ የሆኑ የዳያስፖራ አባላት ተገኝተውዋል።
#etv #EBC
https://www.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid02Fd1do5AjjpxJkewe58gsz1cDiUzVKe5FUxugM39LBouf329A7RBz9odHGgxTxsqBl
👍155👏1
👍193👎3👏2
አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ ከዴንማርክ አቻቸው እና ከተባበሩት አረብ ኢምሬቶች የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ጋር ተወያዩ
**********

በኒውዮርክ እየተካሄደ ከሚገኘው 79ኛው የተመድ ጉባዔ ጎን ለጎን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ ከዴንማርክ አቻቸው ላርስ ሎክ ራስምሰን ጋር ተወያይተዋል።

አምባሳደር ታዬ በውይይቱ ላይ ዴንማርክ የተመድ የጸጥታው ምክር ቤት አባል ሆና በመመረጧ የተሰማቸውን ደስታ በመግለጽ፤ በወቅታዊ የአፍሪካ ቀንድ ጉዳዮች እና ኢትዮጵያ ሽብርተኝነትን በመዋጋት ረገድ ባላት ቁርጠኝነት ዙሪያ ገለጻ አድርገዋል።

በተያያዘ አምባሳደር ታዬ ከተባበሩት አረብ ኢምሬቶች የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ሼህ ሻክቡት ናህያን አል ናህያን ጋር በሁለትዮሽ እና በአፍሪካ ቀንድ ሰላም እና ደኀንነት ዙሪያ መክረዋል።

ሶማሊያን በተመለከተ ባደረጉት ውይይት አምባሳደር ታዬ የቀጣናው አገራት ዋጋ የከፈሉበት እና የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ከፍተኛ ወጪ ያወጣበት የሶማሊያ ደህንነት እንዲቀጥል ማድረግ ወሳኝ ጉዳይ መሆኑን ተናግረዋል።

ሚኒስትሩ ከድህረ አትሚስ በኋላ የሚኖረው የኃይል ሥምሪት ጊዜ ተወስዶ በጥንቃቄ መከናወን እንዳለበት መግለፃቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።
👍313👎1👏1