EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation) – Telegram
EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)
137K subscribers
38.4K photos
462 videos
80 files
13.2K links
EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation) @etvafaanoromoo1
@ETVkidschannel
@EBCWORLD1
@etventertainment1
Download Telegram
“ካለፈው መልካም ነገር እንወስዳለን፤ ያለፈው የሚወቀስበትን እያስተካከልን እንዳንወቀስ አድርገን እንሠራለን። የሰውን ልጆችን በእኩል ማየትን ከገዳ እንማራለን”

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
👍33👎87
የሐረሪ ክልላዊ መንግስት ለኢሬቻ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፈ
*******************

የሐረሪ ክልላዊ መንግስት ያስተላለፈው የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ቀርቧል።

የሐረሪ ክልላዊ መንግስት የሰላም፣ የፍቅር፣ የእርቅ፣ የወንድማማችነት፣ የእህትማማችነት እና የአንድነት ማሳያ ለሆነው የኢሬቻ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልእክቱን ያስተላልፋል።

በኦሮሞ ህዝብ ዘንድ በታላቅ በድምቀት የሚከበረው የኢሬቻ በዓል በመስከረም ወር ከክረምት ወደ በጋ ፣ ከጭለማ ወደ ብርሃን መሸጋገርን በማሰብ ለፈጣሪ ምስጋናን ለማቅረብ የሚከበር የአደባባይ በዓል ነው።https://www.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid0ckgWqBrYf3i6ue1tBGyrzS51kkH7X1echSD6Seubu1dRrzNcvP9FSzvE9y28xFEFl
👍143👎3
ኢሬቻ ከልዩነት ይልቅ አንድነት የሚንፀባረቅበት፣የምስጋና፣ የእርቅና ሠላም በዓል ነው፡- ርዕሰ መስተዳድር አለሚቱ ኡሞድ
*************

ኢሬቻ ከልዩነት ይልቅ አንድነት የሚንፀባረቅበት፣የምስጋና፣ የእርቅና ሠላም በዓል ነው ሲሉ የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አለሚቱ ኡሞድ ገለጹ።

ርዕሰ መስተዳድሯ የሰላም፣የፍቅር፣የእርቅ እና የአንድነት ማሳያ ለሆነው የኢሬቻ በዓል እንኳን አደረሳችሁ ብለዋል።

ኢሬቻ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ሀብት ከመሆኑም ባሻገር አንድነትን የሚያጎለብት ታላቅ በዓል እንደሆነ ገልፀዋል።https://www.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid02gGFMUW9BsKawYNSE5GzKbcuJ8ve1ynfpum2bAcdE6ThFKzzGmpVhst5EELgiDeael
👍164👎4👏1
ፍቅር እና መተሳሰብ የሚነግስበት በዓል
📷 በአሰግድ ሲሳይ
#etv #EBC #ኢሬቻ
24👍17👎15
ፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ የኢሬቻ በዓልን ምክንያት በማድረግ የመልካም ምኞት መግለጫ መልዕክት አስተላለፉ
***********
የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ የዘንድሮውን የኢሬቻ በዓል ምክንያት በማድረግ ለመላው የኦሮሞ ህዝብ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፏል።
"ለመላው የኦሮሞ ሕዝብ እንኳን ለ2017 ዓ.ም የኢሬቻ በዓል በሠላም እና በጤና አደረሳችሁ" ብለዋል ፕሬዚዳንቷ በመልካም ምኞት መግለጫ መልዕክታቸው።
https://www.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid0wofp3nGDuK2PHAyvHSw4LxRvaJcX3tub4gDUNuntYjdQDXEVgKgr8usmqKMAq9rgl
👍286👎6
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ቤይሩት እና ወደ ቴልአቪቭ የሚያደርገውን በረራ ማቋረጡን አስታወቀ
**********

በከተሞቹ ባለው ወቅታዊ ሁኔታ ምክንያት ወደ ቤይሩት እና ወደ ቴልአቪቭ የሚያደርገውን በረራ በጊዜያዊነት ማቋረጡን የኢትዮጵያ አየር መንገድ አስታውቋል።

አየር መንገዱ በማህበራዊ ትስስር ገጹ ባጋራው መረጃ፥ ተለዋጭ ማስታወቂያ እስከሚያወጣ ድረስ ወደ ቤይሩት የሚያደርጋቸውን ሁሉንም በረራዎች ማቋረጡን ገልጿል።

ወደ ቴልአቪቭ ደግሞ እስከ መስከረም 27 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ በረራ የማያደርግ መሆኑን ነው አየር መንገዱ የገለጸው።

በተጠቀሱት አካባቢዎች ስላለው ወቅታዊ ሁኔታ በቅርበት እየተከታተለ መሆኑን የጠቀሰው አየር መንገዱ፤ ስለጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር መረጃ እየተለዋወጠ ስለመሆኑም ጠቁሟል።
👍286👎2
በኢሬቻ በዓላት ላይ በስፋት የሚታየው "ጥቁር፣ ቀይ እና ነጭ" ቀለማት ያሉት ባንዲራ ትርጉም ምንድነው??
*********************

ከላይ ወደ ታች ጥቁር፣ ቀይ፣ ነጭ ቀለማት ያሉት የአባገዳ ባንዲራ

በተለይ በአዲስ አበባ እና በቢሾፍቱ በድምቀት በሚከበሩት የኦሮሞ ሕዝብ የኢሬቻ በዓላት ላይ በሚሳተፉ የበዓሉ ታዳሚዎች እጅ ላይ የማይጠፋው ባንዲራ አስገራሚ የቀለማቱ አደራደር እና ትርጓሜ የሚከተለውን ይመስላል፦

👉ጥቁር መደብ፦ ፈጣሪ የበላይ መሆኑን የሚገልጽ ነው። የኦሮሞ ሕዝብ ራሱ ጥቁር እንደሆነው ሁሉ ፈጣሪው /ዋቃ/ ጥቁር ነው ብሎ ያምናል። ጥቁር ቀለምም በኦሮሞ ሕዝብ ዘንድ የቀዳሚነት መገለጫ ነው። ጥቁሩ ፈጣሪ ያለው ከላይ ነው፤ ዝናብ የሚዘንበው ከላይ ባለው ጥቁር ደመና ነው፣ ራሳችን ላይ ያለው ፀጉር እስኪሸብት ድረስ ጥቁር ነው፤ የዓይናችን ብሌን ጥቁር ነው - የሚገኘውም ከላይ ነው። እናም ጥቁር ቀዳሚ የመሆን መገለጫ ነው።

👉ቀይ መደብ፦ የብቃት፣ ብስል የመሆን፣ ሙሉ ሆኖ የመገኘት እና ለሕዝብ ነፃነት መሥዋዕት የመሆን መገለጫ ነው። ሁሉም ነገር በጊዜው ሙሉ ሆኖ የመገኘት ምሳሌ ነው። የኦሮሞ ሕዝብ አንድ ነገር የብቃት ደረጃው ላይ መድረሱን ሲገልጽ “diimate” /ቀላ/ ብሎ ይገልጻል።

👉ነጭ መደብ፦ የነገሮች ፍፃሜ መገለጫ ነው። እንደ ምሳሌ፦ ጠቁሮ ዝናብ የሚሰጠን ደመና ነጭ ሲሆን አይዘንብም ማለት ነው፤ ጥቁር የነበረው የሰው ፀጉር እርጅና ሲደርስ ይሸብታል (ነጭ ይሆናል)፣ ነዶ ያለቀ እንጨት አመዱ ነጭ ነው … ስለዚህ ነጭ የፍፃሜ መገለጫ ነው ብሎ ያምናል - የኦሮሞ ሕዝብ።

#ኢሬቻ #etv #EBC
👍50👎285👏5
ወደ 8 በመቶ ወርዶ የነበረው በሀገር ውስጥ የተመረተ መድሃኒት የአቅርቦት ድርሻ መንግሥት በወሰደው የፖሊሲ ማሻሻያ እርምጃ ወደ 36 በመቶ ከፍ ሊል ችሏል
*****************

የኢትዮጵያ መድኃኒት እና ሕክምና መገልገያ አምራቾች ማህበር 21ኛ ጠቅላላ ዓመታዊ ጉባኤውን አካሂዷል።

በጉባኤው ላይ የተገኙት የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ፥ በመንግሥት ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቷቸው እየተከናወኑ ካሉ ስትራቴጂያዊ ተግባራት መካከል በአምራችነት የተሰማሩ ባለሃብቶችን በመደገፍ እና በማበረታታት ብሎም አዳዲስ አምራቾችን ወደ ዘርፉ በመሳብ የሀገር ውስጥ ምርትን ማሳደግና ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን መተካት ነው ብለዋል።

በዚህ መነሻነት መንግሥት በወሰደው የፖሊሲ ማሻሻያ እርምጃ ምክንያት በየዓመቱ እየቀነስ መጥቶ 8 በመቶ ደርሶ የነበረው በሀገር ውስጥ የተመረተ መድሃኒት የአቅርቦት ድርሻ አሁን ላይ ወደ 36 በመቶ ከፍ ሊል ችሏል ብለዋል።

ከውጭ በሚገቡ ምርቶች ላይ ያለውን ጥገኝነት በመቀነስ ኢኮኖሚያዊ እድገትን ለማፋጠን አምራቾች፣ የፈጠራ ባለሙያዎች፣ ተቆጣጣሪዎች፣ የፋይናንስ ተቋማት እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት በጋራ መረባረብ እንደሚገባቸው ጠቁመዋል።

የፕላንና ልማት ሚኒስትር ዶ/ር ፍጹም አሰፋ፥ መንግሥት እየወሰደው ባለው ወሳኝ የፖሊሲ ማሻሻያ እርምጃ የሀገር ውስጥ የሕክምና ግብዓት ምርቶች እያደጉ መምጣታቸውን ገልጸዋል።

በቀጣይም ዘርፉ ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን መተካት ብቻ ሳይሆን በቀጣናው ብሎም በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ መሆን ይጠበቅበታል ብለዋል።
https://www.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid02dqux1JwtkdSaiGcck8B1L8E6VhuXi16wckjh337W3Xn7k7bbCCQUt8vLh56aCYmfl
👍363👏1