EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation) – Telegram
EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)
137K subscribers
38.4K photos
462 videos
80 files
13.2K links
EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation) @etvafaanoromoo1
@ETVkidschannel
@EBCWORLD1
@etventertainment1
Download Telegram
ኢቲቪ ፓርላማ ቻናል ስርጭት ጀምሯል

የኢትዮጰያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን የይዘት ተደራሽነቱን ለማስፋት እና በአዋጅ የተሰጠውን ተልዕኮ ለማሳካት በተቋማዊ የሪፎርም ሥራ ውስጥ ይገኛል። ከሁለት ዓመታት ወዲህ በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችን ውሳኔ የተጀመረው የመሰረተ ልማት ለውጥ የፈጠረውን አቅም በመጠቀም በቅርቡ "ኢቢሲ ወደ ይዘት" በሚል መርኅ ሰፋፊ የይዘት እና የአቀራረብ ለውጥ እያደረግን እንገኛለን።

የዚሁ ለውጥ አካል የሆነውን የሕዝብ ድምጽ የሚሰማበት ብሎም ለሀገር ግንባታ መረጃ የምንለዋወጥበት መድረክ እንዲሆን የሚያስችለውን የኢቲቪ ፓርላማ ቻናል የሙከራ ስርጭት ዛሬ ጀምረናል። ቻናሉ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ስብሰባዎችን ፣ ውሳኔዎችን እና የሕዝብ ውክልና ሥራዎችን በቀጥታ እና በትንታኔ በሙሉ አቅም ለሕዝብ ተደራሽ የሚያደርግ ይሆናል።

የኢቲቪ ፓርላማ ቻናልን በFreqyency..11545
SR....44997
POL....H ኢቲዮ ሳት ላይ እንድትከታተሉ እንጋብዛለን።

ነገ ከሰዓት ጥቅምት 27 ቀን 2017 ዓ.ም የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና የፌዴሬሽን ምክር ቤት የጋራ የመክፈቻ ስብሰባ በዚሁ ቻናል በቀጥታ እናስተላልፋለን።

ለኢትዮጵያ ልዕልና
👍493
የአፋር ክልልን አጀንዳዎች የሚያደራጁ 25 ወኪሎች ተመረጡ
****************

በአፋር ክልል የምክክር መድረክ ሲሳተፉ የነበሩ ባለድርሻ አካላት የክልሉን አጀንዳዎች የሚያደራጁ 25 ወኪሎችን መርጠዋል።

በአፋር ክልል እየተከናወነ ባለው የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር መድረክ የሀይማኖት አባቶች፣ የቀድሞ ሰራዊት አባላት፣ የመንግስት አካላት፣ የተለያዩ ማህበረሰብ ክፍል ተወካዮች፣ ተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የሲቪክ ማህበራት እና ተፅፅኖ ፈጣሪ ግለሰቦች ተሳትፈውበታል።

ለተከታታይ ቀናት ሲወያዩ የነበሩት የክልሉ ባለድርሻ አካላት ዛሬ መስከረም 26/2017 የክልሉን አጀንዳዎች የሚያደራጁ 25 ወኪሎችን መርጠዋል።

ከ700 በላይ የሚሆኑት እነዚህ ተሳታፊዎች በሀገር ደረጃ መግባባት ሊደረግባቸው ያስፈልጋል ያሏቸውን አጀንዳዎች በስፋት ተመካክረው ለይተዋል።

በአፋር ክልል የአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት እነዚህ የተመረጡ 25 ወኪሎች የአፋር ክልል አጀንዳዎችን አደራጅተው መስከረም 27/2017 አጀንዳቸውን ለኮሚሽኑ ያስረክባሉ።

በወይንሸት ደጀኔ
👍14👏62
አትሌት ሞስነት ገረመው የሊዝበን ግማሽ ማራቶንን አሸነፈ
*************

የሊዝበን ግማሽ ማራቶን ዛሬ በፖርቹጋል መዲና ሊዝበን ሲካሄድ አትሌት ሞስነት ገረመው በወንዶች አሸናፊ ሆኗል፡፡

አትሌት ሞስነት 21 ኪሎ ሜትሩን ለመጨረስ 1 ሰዓት ከ3 ደቂቃ ከ8 ሰኮንድ ወስዶበታል፡፡

በውድድሩ ኬንያዊው ፒተር ኪፕሲራትና ዩጋንዳዊው ቪክቶር ክዌምቦይ ሁለተኛና ሶስተኛ ወጥተዋል፡፡

በሴቶች ደግሞ አለም ንጉሴ ውድድሯን በሶስተኛነት ጨርሳለች፡፡

በውድድሩ ኬንያውያኑ ቸፕቸርቸር ኪፕሮቲችና ፌይዝ ቼፕኮች አንደኛና ሁለተኛ ደረጃን ይዘው አጠናቅቀዋል፡፡

በዮሴፍ ሹምዬ
👍32👏63
የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር በመጀመሪያ ዙር የ 2.5 ኪሎ ሜትር የኮሪደር ልማት ማጠናቀቁን ገለፀ
***

የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ለኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ተመራጭ በሆነችው ከተማ በመጀመሪያ ዙር ሁለት ነጥብ አምስት ኪሎ ሜትር የኮሪደር ልማት ማጠናቀቁን አስታውቋል።

ከተማ አስተዳደሩ የሁለተኛ ዙር የኮሪደር ልማት ስራን በመንግስት፣ በልማት ድርጅቶች፣ በባለሀብቱና በህብተሰቡ የጋራ አቅም መጀመሩን ጠቅሷል፡፡

የከተማ አስተዳደሩ የፅዱ፣ ውብና ለማህበረሰብ ምቹ ከተማ ግንባታን ለማረጋገጥ የኮሪደር ልማቱን አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ከከተማ አስተዳደሩ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ያገኘነዉ መረጃ ያመለክታል።
👍354
#etv በአዲስ አበባ አንዳንድ አካባቢዎች የመሬት መንቀጥቀጥ ተከሰተ
https://www.facebook.com/share/v/x5Cwyjsmbnr6t7xG/
👏10👍5
በመዲናዋ የተለያዩ አከባቢዎች የተሰማው የመሬት ንዝረት ፈንታሌ ላይ በደረሰው የመሬት መንቀጥቀጥ የተከሰተ መሆኑ ተገለፀ
************

በአዲስ አበበ ከተማ የተለያዩ አከባቢዎች ዛሬ ምሽት የተሰማው የመሬት ንዝረት ፈንታሌ ላይ በደረሰው የመሬት መንቀጥቀጥ የተከሰተ መሆኑ ተገልጿል፡፡

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጂኦፊዚክስ እና ስፔስ ሳይንስ ዳይሬክተር ዶ/ር ኤሊያስ ሌዊ ለኢቲቪ እንደገለፁት፤ አዋሽ ፈንታሌ አከባቢ የተከሰተ የመሬት መንቀጥቀጥ በመሬት ውስጥ አልፎ በአዲስ አበበ ከተማ የተለያዩ አካባቢዎች መሰማቱን ተናግረዋል፡፡
👍585
በመዲናዋ የተለያዩ አከባቢዎች የተሰማው የመሬት ንዝረት ለከተማዋ ነዋሪዎች አስጊ አይደለም
*************

በአዲስ አበበ ከተማ የተለያዩ አከባቢዎች ዛሬ ምሽት የተሰማው የመሬት ንዝረት ለከተማዋ ነዋሪዎች አስጊ አለመሆኑን በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጂኦፊዚክስ እና ስፔስ ሳይንስ ዳይሬክተር ዶ/ር ኤሊያስ ሌዊ ገልፀዋል፡፡

ዶ/ር ኤሊያስ ሌዊ ለኢቲቪ እንደገለፁት፤ አዋሽ ፈንታሌ አከባቢ የተከሰተ የመሬት መንቀጥቀጥ በመሬት ውስጥ አልፎ በአዲስ አበበ ከተማ የተለያዩ አካባቢዎች መሰማቱን ተናግረዋል፡፡

በፈንታሌ ተራራ ላይ በሬክተር ስኬል 4.9 የተመዘገበ የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱን የገለፁት ዳይሬክተሩ፤ በአዲስ አበባ ከተማ የተከሰተ የመሬት መንቀጥቀጥ አለመኖሩን አረጋግጠዋል፡፡

በአዲስ አበባ ዛሬ ምሽት የመሬት መንቀጥቀጥ ተከሰተ በሚል በማህበራዊ ሚዲያ እየተሰራጨ ያለው መረጃ ትክክለኛ አለመሆኑን ያረጋገጡት ዳይሬክተሩ፤ ለከተማዋ ነዋሪዎች የሚያሰጋ ነገር አለመኖሩንም ገልፀዋል።

ሰሞኑን በአፋር ክልል እየተከሰተ የነበረው የመሬት መንቀሳቀስ ዛሬም የተከሰተ ሲሆን ዛሬ ምሽት በሬክተር ስኬል 4.9 የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱን የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የጂኦ ፊዝክስ ስፔስ ሳይንስና አስትሮኖሚ ተቋም የመሬት መንቀጥቀጥ ተማራማሪ እና መምህር ፕሮፌሰር አታላይ አየለ እንዲሁ ለኢቢሲ ሳይበር ገልፀዋል።

ፕሮፌሰር አታላይ በአዲስ አበባ የመሬት መንቀጥቀጥ አለመከሰቱን ገልጸው፤ በአፋር ፈንታሌ አከባቢ በተከታታይ እየተከሰተ ያለው የመሬት መንቀጥቀጥ አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ አከባቢዎች የተፈጠረ የመሬት ሞገድ (ንዝረት) መሆኑን አረጋግጠዋል።

በላሉ ኢታላ
👍386👏2
ምሽቱን በአዲስ አበባ የተለያዩ አካባቢዎች የተከሰተው የመሬት ንዝረት ለ18 ሰከንድ ያህል የቆየ ነው - ዶ/ር ኤልያስ ሌዊ
*******************

ዛሬ ምሽት በአዲስ አበባ የተለያዩ አካባቢዎች የተከሰተው የመሬት ንዝረት ለ18 ሰከንድ ያህል መቆየቱን በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የጂኦ ፊዚክስ ስፔስ ሳይንስ እና አስትሮኖሚ ተቋም አስታውቋል፡፡

የተቋሙ ዳይሬክተር ዶ/ር ኤልያስ ሌዊ በመዲናዋ የተከሰተው የመሬት ንዝረት በአዋሽ ፈንታሌ ተራራ አካባቢ በተከሰተ የመሬት መንቀጥቀጥ ሞገድ አማካይነት የተፈጠረ መሆኑን ገልጸዋል።

ህብረተሰቡ በአዲስ አበባ የተከሰተው የመሬት ንዝረት መሆኑን አውቆ፤ የእለተ እለት እንቅስቃሴውን በተረጋጋ መንገድ መቀጠል እንዳለበትም አስገንዝበዋል።

በፈንታሌ ተራራ አካባቢ የተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ በሬክተር ስኬል 4.9 ሆኖ የተመዘገበ መሆኑን ዶ/ር ኤልያስ ሌዊ በተለይ ለኢቢሲ ተናግረዋል።
https://www.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid0nFyY73tpx6WGfUzrE8MBYM8H61WPExCNefaaJtT8aRA5khCn5oE9LrQxtU788Wdcl
👍306