EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation) – Telegram
EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)
138K subscribers
38.3K photos
462 videos
80 files
13.1K links
EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation) @etvafaanoromoo1
@ETVkidschannel
@EBCWORLD1
@etventertainment1
Download Telegram
አትሌት ሞስነት ገረመው የሊዝበን ግማሽ ማራቶንን አሸነፈ
*************

የሊዝበን ግማሽ ማራቶን ዛሬ በፖርቹጋል መዲና ሊዝበን ሲካሄድ አትሌት ሞስነት ገረመው በወንዶች አሸናፊ ሆኗል፡፡

አትሌት ሞስነት 21 ኪሎ ሜትሩን ለመጨረስ 1 ሰዓት ከ3 ደቂቃ ከ8 ሰኮንድ ወስዶበታል፡፡

በውድድሩ ኬንያዊው ፒተር ኪፕሲራትና ዩጋንዳዊው ቪክቶር ክዌምቦይ ሁለተኛና ሶስተኛ ወጥተዋል፡፡

በሴቶች ደግሞ አለም ንጉሴ ውድድሯን በሶስተኛነት ጨርሳለች፡፡

በውድድሩ ኬንያውያኑ ቸፕቸርቸር ኪፕሮቲችና ፌይዝ ቼፕኮች አንደኛና ሁለተኛ ደረጃን ይዘው አጠናቅቀዋል፡፡

በዮሴፍ ሹምዬ
👍32👏63
የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር በመጀመሪያ ዙር የ 2.5 ኪሎ ሜትር የኮሪደር ልማት ማጠናቀቁን ገለፀ
***

የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ለኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ተመራጭ በሆነችው ከተማ በመጀመሪያ ዙር ሁለት ነጥብ አምስት ኪሎ ሜትር የኮሪደር ልማት ማጠናቀቁን አስታውቋል።

ከተማ አስተዳደሩ የሁለተኛ ዙር የኮሪደር ልማት ስራን በመንግስት፣ በልማት ድርጅቶች፣ በባለሀብቱና በህብተሰቡ የጋራ አቅም መጀመሩን ጠቅሷል፡፡

የከተማ አስተዳደሩ የፅዱ፣ ውብና ለማህበረሰብ ምቹ ከተማ ግንባታን ለማረጋገጥ የኮሪደር ልማቱን አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ከከተማ አስተዳደሩ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ያገኘነዉ መረጃ ያመለክታል።
👍354
#etv በአዲስ አበባ አንዳንድ አካባቢዎች የመሬት መንቀጥቀጥ ተከሰተ
https://www.facebook.com/share/v/x5Cwyjsmbnr6t7xG/
👏10👍5
በመዲናዋ የተለያዩ አከባቢዎች የተሰማው የመሬት ንዝረት ፈንታሌ ላይ በደረሰው የመሬት መንቀጥቀጥ የተከሰተ መሆኑ ተገለፀ
************

በአዲስ አበበ ከተማ የተለያዩ አከባቢዎች ዛሬ ምሽት የተሰማው የመሬት ንዝረት ፈንታሌ ላይ በደረሰው የመሬት መንቀጥቀጥ የተከሰተ መሆኑ ተገልጿል፡፡

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጂኦፊዚክስ እና ስፔስ ሳይንስ ዳይሬክተር ዶ/ር ኤሊያስ ሌዊ ለኢቲቪ እንደገለፁት፤ አዋሽ ፈንታሌ አከባቢ የተከሰተ የመሬት መንቀጥቀጥ በመሬት ውስጥ አልፎ በአዲስ አበበ ከተማ የተለያዩ አካባቢዎች መሰማቱን ተናግረዋል፡፡
👍585
በመዲናዋ የተለያዩ አከባቢዎች የተሰማው የመሬት ንዝረት ለከተማዋ ነዋሪዎች አስጊ አይደለም
*************

በአዲስ አበበ ከተማ የተለያዩ አከባቢዎች ዛሬ ምሽት የተሰማው የመሬት ንዝረት ለከተማዋ ነዋሪዎች አስጊ አለመሆኑን በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጂኦፊዚክስ እና ስፔስ ሳይንስ ዳይሬክተር ዶ/ር ኤሊያስ ሌዊ ገልፀዋል፡፡

ዶ/ር ኤሊያስ ሌዊ ለኢቲቪ እንደገለፁት፤ አዋሽ ፈንታሌ አከባቢ የተከሰተ የመሬት መንቀጥቀጥ በመሬት ውስጥ አልፎ በአዲስ አበበ ከተማ የተለያዩ አካባቢዎች መሰማቱን ተናግረዋል፡፡

በፈንታሌ ተራራ ላይ በሬክተር ስኬል 4.9 የተመዘገበ የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱን የገለፁት ዳይሬክተሩ፤ በአዲስ አበባ ከተማ የተከሰተ የመሬት መንቀጥቀጥ አለመኖሩን አረጋግጠዋል፡፡

በአዲስ አበባ ዛሬ ምሽት የመሬት መንቀጥቀጥ ተከሰተ በሚል በማህበራዊ ሚዲያ እየተሰራጨ ያለው መረጃ ትክክለኛ አለመሆኑን ያረጋገጡት ዳይሬክተሩ፤ ለከተማዋ ነዋሪዎች የሚያሰጋ ነገር አለመኖሩንም ገልፀዋል።

ሰሞኑን በአፋር ክልል እየተከሰተ የነበረው የመሬት መንቀሳቀስ ዛሬም የተከሰተ ሲሆን ዛሬ ምሽት በሬክተር ስኬል 4.9 የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱን የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የጂኦ ፊዝክስ ስፔስ ሳይንስና አስትሮኖሚ ተቋም የመሬት መንቀጥቀጥ ተማራማሪ እና መምህር ፕሮፌሰር አታላይ አየለ እንዲሁ ለኢቢሲ ሳይበር ገልፀዋል።

ፕሮፌሰር አታላይ በአዲስ አበባ የመሬት መንቀጥቀጥ አለመከሰቱን ገልጸው፤ በአፋር ፈንታሌ አከባቢ በተከታታይ እየተከሰተ ያለው የመሬት መንቀጥቀጥ አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ አከባቢዎች የተፈጠረ የመሬት ሞገድ (ንዝረት) መሆኑን አረጋግጠዋል።

በላሉ ኢታላ
👍386👏2
ምሽቱን በአዲስ አበባ የተለያዩ አካባቢዎች የተከሰተው የመሬት ንዝረት ለ18 ሰከንድ ያህል የቆየ ነው - ዶ/ር ኤልያስ ሌዊ
*******************

ዛሬ ምሽት በአዲስ አበባ የተለያዩ አካባቢዎች የተከሰተው የመሬት ንዝረት ለ18 ሰከንድ ያህል መቆየቱን በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የጂኦ ፊዚክስ ስፔስ ሳይንስ እና አስትሮኖሚ ተቋም አስታውቋል፡፡

የተቋሙ ዳይሬክተር ዶ/ር ኤልያስ ሌዊ በመዲናዋ የተከሰተው የመሬት ንዝረት በአዋሽ ፈንታሌ ተራራ አካባቢ በተከሰተ የመሬት መንቀጥቀጥ ሞገድ አማካይነት የተፈጠረ መሆኑን ገልጸዋል።

ህብረተሰቡ በአዲስ አበባ የተከሰተው የመሬት ንዝረት መሆኑን አውቆ፤ የእለተ እለት እንቅስቃሴውን በተረጋጋ መንገድ መቀጠል እንዳለበትም አስገንዝበዋል።

በፈንታሌ ተራራ አካባቢ የተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ በሬክተር ስኬል 4.9 ሆኖ የተመዘገበ መሆኑን ዶ/ር ኤልያስ ሌዊ በተለይ ለኢቢሲ ተናግረዋል።
https://www.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid0nFyY73tpx6WGfUzrE8MBYM8H61WPExCNefaaJtT8aRA5khCn5oE9LrQxtU788Wdcl
👍306
የሁለቱ ምክር ቤቶች የጋራ የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ዛሬ ከሰዓት ይካሄዳል
****************

6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና የፌዴሬሽን ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ዛሬ ከሰዓት ከቀኑ 8 ሰዓት ጀምሮ ይካሄዳል።

በኢፌዴሪ ሕገ-መንግስት አንቀፅ 58 ንዑስ አንቀፅ (2) እና በምክር ቤቱ የአሠራርና የአባላት የሥነ-ምግባር ደንብ ቁጥር 6/2008 አንቀፅ 24 ንዑስ አንቀፅ (1) መሰረት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአንድ ዓመት የሥራ ጊዜ ከመስከረም ወር የመጨረሻ ሳምንት ሰኞ ጀምሮ እስከ ሰኔ 30 ቀን ድረስ መሆኑ ተደንግጓል።

በድንጋጌው መሰረት የ6ኛው ምክር ቤት 3ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የተጠናቀቀ ሲሆን 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓትም የሪፐብሊኩ ፕሬዚደንት በተገኙበት እንደሚካሄድ ተገልጿል።https://www.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid026n4JrkzV9FPQbAJzsdvBHCFNbkJQHmQ6xkxwAtRTjxBUS6ymD4htWkijhz1MJxKul
👍224
በእኛ ቤት ውትድርና በፍቅር የሚወረስ ሙያ ሆኗል:- መንትዮቹ ተመራቂ ወታደሮች
*******************

መንትዮቹ ወንድማማቾች ፍቃዱ ማሙሽ ፈይሳ እና ታሪኩ ማሙሽ ፈይሳ ትውልድ እና ዕድገታቸው በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ነው።

ታላቅ እህታቸው በውትድርና ሕይወት ሀገሯን ታገለግላች፤ ይሄ አጋጣሚ ወንድማማቾቹ ልባቸው ወደ ውትድርና እንዲሸፍት አድርጓል ።

ለውትድርና ባላቸው ልዩ ፍቅር ልጆች እያሉ የእህታቸውን ወታደራዊ ልብስ ተደብቀው ይለብሱ እንደነበር ያስታውሳሉ።

መንትዮቹ ዕድሜያቸው ለውትድርና ሲደርስ ወደ ብላቴ ኮማንዶ እና አየር ወለድ ማሰልጠኛ ማዕከል ገብተው ከህልማቸው ጋር ተገናኝተዋል።

የብላቴ ኮማንዶ እና አየር ወለድ ማሰልጠኛ ማዕከል ያስመረቃቸው የሁለተኛ ዙር መስመራዊ ወታደሮች አባል ናቸው።

ሀገርን ማገልገል የቤታችን ልምድ እና የፍላጎታችን መልስ ነውና ሙሉ ሕይወታችንን ለሀገራችን በመቆም እናሳልፋለን ሲሉ ለኢቢሲ ገልጸዋል።

ለእኛ ቤት ውትድርና በፍቅር የሚወረስ እና የሚያኮራ ሙያ በመሆኑ በአደራ መልክ እናስቀጥለዋለን ሲሉም መንትዮቹ ተመራቂ ወታደሮች ተናግረዋል።

በአስረሳው ወገሼ
👍3210👏4