EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation) – Telegram
EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)
137K subscribers
38.4K photos
462 videos
80 files
13.2K links
EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation) @etvafaanoromoo1
@ETVkidschannel
@EBCWORLD1
@etventertainment1
Download Telegram
በመዲናዋ የተለያዩ አከባቢዎች የተሰማው የመሬት ንዝረት ፈንታሌ ላይ በደረሰው የመሬት መንቀጥቀጥ የተከሰተ መሆኑ ተገለፀ
************

በአዲስ አበበ ከተማ የተለያዩ አከባቢዎች ዛሬ ምሽት የተሰማው የመሬት ንዝረት ፈንታሌ ላይ በደረሰው የመሬት መንቀጥቀጥ የተከሰተ መሆኑ ተገልጿል፡፡

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጂኦፊዚክስ እና ስፔስ ሳይንስ ዳይሬክተር ዶ/ር ኤሊያስ ሌዊ ለኢቲቪ እንደገለፁት፤ አዋሽ ፈንታሌ አከባቢ የተከሰተ የመሬት መንቀጥቀጥ በመሬት ውስጥ አልፎ በአዲስ አበበ ከተማ የተለያዩ አካባቢዎች መሰማቱን ተናግረዋል፡፡
👍585
በመዲናዋ የተለያዩ አከባቢዎች የተሰማው የመሬት ንዝረት ለከተማዋ ነዋሪዎች አስጊ አይደለም
*************

በአዲስ አበበ ከተማ የተለያዩ አከባቢዎች ዛሬ ምሽት የተሰማው የመሬት ንዝረት ለከተማዋ ነዋሪዎች አስጊ አለመሆኑን በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጂኦፊዚክስ እና ስፔስ ሳይንስ ዳይሬክተር ዶ/ር ኤሊያስ ሌዊ ገልፀዋል፡፡

ዶ/ር ኤሊያስ ሌዊ ለኢቲቪ እንደገለፁት፤ አዋሽ ፈንታሌ አከባቢ የተከሰተ የመሬት መንቀጥቀጥ በመሬት ውስጥ አልፎ በአዲስ አበበ ከተማ የተለያዩ አካባቢዎች መሰማቱን ተናግረዋል፡፡

በፈንታሌ ተራራ ላይ በሬክተር ስኬል 4.9 የተመዘገበ የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱን የገለፁት ዳይሬክተሩ፤ በአዲስ አበባ ከተማ የተከሰተ የመሬት መንቀጥቀጥ አለመኖሩን አረጋግጠዋል፡፡

በአዲስ አበባ ዛሬ ምሽት የመሬት መንቀጥቀጥ ተከሰተ በሚል በማህበራዊ ሚዲያ እየተሰራጨ ያለው መረጃ ትክክለኛ አለመሆኑን ያረጋገጡት ዳይሬክተሩ፤ ለከተማዋ ነዋሪዎች የሚያሰጋ ነገር አለመኖሩንም ገልፀዋል።

ሰሞኑን በአፋር ክልል እየተከሰተ የነበረው የመሬት መንቀሳቀስ ዛሬም የተከሰተ ሲሆን ዛሬ ምሽት በሬክተር ስኬል 4.9 የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱን የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የጂኦ ፊዝክስ ስፔስ ሳይንስና አስትሮኖሚ ተቋም የመሬት መንቀጥቀጥ ተማራማሪ እና መምህር ፕሮፌሰር አታላይ አየለ እንዲሁ ለኢቢሲ ሳይበር ገልፀዋል።

ፕሮፌሰር አታላይ በአዲስ አበባ የመሬት መንቀጥቀጥ አለመከሰቱን ገልጸው፤ በአፋር ፈንታሌ አከባቢ በተከታታይ እየተከሰተ ያለው የመሬት መንቀጥቀጥ አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ አከባቢዎች የተፈጠረ የመሬት ሞገድ (ንዝረት) መሆኑን አረጋግጠዋል።

በላሉ ኢታላ
👍386👏2
ምሽቱን በአዲስ አበባ የተለያዩ አካባቢዎች የተከሰተው የመሬት ንዝረት ለ18 ሰከንድ ያህል የቆየ ነው - ዶ/ር ኤልያስ ሌዊ
*******************

ዛሬ ምሽት በአዲስ አበባ የተለያዩ አካባቢዎች የተከሰተው የመሬት ንዝረት ለ18 ሰከንድ ያህል መቆየቱን በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የጂኦ ፊዚክስ ስፔስ ሳይንስ እና አስትሮኖሚ ተቋም አስታውቋል፡፡

የተቋሙ ዳይሬክተር ዶ/ር ኤልያስ ሌዊ በመዲናዋ የተከሰተው የመሬት ንዝረት በአዋሽ ፈንታሌ ተራራ አካባቢ በተከሰተ የመሬት መንቀጥቀጥ ሞገድ አማካይነት የተፈጠረ መሆኑን ገልጸዋል።

ህብረተሰቡ በአዲስ አበባ የተከሰተው የመሬት ንዝረት መሆኑን አውቆ፤ የእለተ እለት እንቅስቃሴውን በተረጋጋ መንገድ መቀጠል እንዳለበትም አስገንዝበዋል።

በፈንታሌ ተራራ አካባቢ የተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ በሬክተር ስኬል 4.9 ሆኖ የተመዘገበ መሆኑን ዶ/ር ኤልያስ ሌዊ በተለይ ለኢቢሲ ተናግረዋል።
https://www.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid0nFyY73tpx6WGfUzrE8MBYM8H61WPExCNefaaJtT8aRA5khCn5oE9LrQxtU788Wdcl
👍306
የሁለቱ ምክር ቤቶች የጋራ የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ዛሬ ከሰዓት ይካሄዳል
****************

6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና የፌዴሬሽን ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ዛሬ ከሰዓት ከቀኑ 8 ሰዓት ጀምሮ ይካሄዳል።

በኢፌዴሪ ሕገ-መንግስት አንቀፅ 58 ንዑስ አንቀፅ (2) እና በምክር ቤቱ የአሠራርና የአባላት የሥነ-ምግባር ደንብ ቁጥር 6/2008 አንቀፅ 24 ንዑስ አንቀፅ (1) መሰረት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአንድ ዓመት የሥራ ጊዜ ከመስከረም ወር የመጨረሻ ሳምንት ሰኞ ጀምሮ እስከ ሰኔ 30 ቀን ድረስ መሆኑ ተደንግጓል።

በድንጋጌው መሰረት የ6ኛው ምክር ቤት 3ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የተጠናቀቀ ሲሆን 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓትም የሪፐብሊኩ ፕሬዚደንት በተገኙበት እንደሚካሄድ ተገልጿል።https://www.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid026n4JrkzV9FPQbAJzsdvBHCFNbkJQHmQ6xkxwAtRTjxBUS6ymD4htWkijhz1MJxKul
👍224
በእኛ ቤት ውትድርና በፍቅር የሚወረስ ሙያ ሆኗል:- መንትዮቹ ተመራቂ ወታደሮች
*******************

መንትዮቹ ወንድማማቾች ፍቃዱ ማሙሽ ፈይሳ እና ታሪኩ ማሙሽ ፈይሳ ትውልድ እና ዕድገታቸው በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ነው።

ታላቅ እህታቸው በውትድርና ሕይወት ሀገሯን ታገለግላች፤ ይሄ አጋጣሚ ወንድማማቾቹ ልባቸው ወደ ውትድርና እንዲሸፍት አድርጓል ።

ለውትድርና ባላቸው ልዩ ፍቅር ልጆች እያሉ የእህታቸውን ወታደራዊ ልብስ ተደብቀው ይለብሱ እንደነበር ያስታውሳሉ።

መንትዮቹ ዕድሜያቸው ለውትድርና ሲደርስ ወደ ብላቴ ኮማንዶ እና አየር ወለድ ማሰልጠኛ ማዕከል ገብተው ከህልማቸው ጋር ተገናኝተዋል።

የብላቴ ኮማንዶ እና አየር ወለድ ማሰልጠኛ ማዕከል ያስመረቃቸው የሁለተኛ ዙር መስመራዊ ወታደሮች አባል ናቸው።

ሀገርን ማገልገል የቤታችን ልምድ እና የፍላጎታችን መልስ ነውና ሙሉ ሕይወታችንን ለሀገራችን በመቆም እናሳልፋለን ሲሉ ለኢቢሲ ገልጸዋል።

ለእኛ ቤት ውትድርና በፍቅር የሚወረስ እና የሚያኮራ ሙያ በመሆኑ በአደራ መልክ እናስቀጥለዋለን ሲሉም መንትዮቹ ተመራቂ ወታደሮች ተናግረዋል።

በአስረሳው ወገሼ
👍3210👏4
የአፋር ክልል የሕብረተሰብ ተወካዮች አጀንዳቸውን ለኮሚሽኑ አስረከቡ
************************

የአፋር ክልል የሕብረተሰብ ተወካዮች አጀንዳቸውን ለይተው ለኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አስረክበዋል።

ባለፉት ቀናት በአፋር ክልል ሲካሄድ የቆየው የአጀንዳ ማሰባሰብና ልየታ መርሐ ግብር በዛሬው ዕለት ተጠናቅቋል።

ከመስከረም 21 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ከ49 ወረዳዎች የተውጣጡ የተለያዩ ማህበረሰብ ክፍሎች አጀንዳቸውን አጠናክረው ለመረጧቸው 54 ተወካዮች ማስረከባቸው ይታወሳል።

ካለፈው ቅዳሜ ጀምሮ የክልል ባለድርሻዎች ከፖለቲካ ፓርቲዎችና ከሲቪክ ማህበራት፣ ከታዋቂ ግለሰቦችና የማህበረሰቡ ተወካይ የሆኑ 54 ሰዎችን ያማከለው የአጀንዳ ማሰባሰብ፣ ትናንት አጀንዳቸውን የሚያደራጁላቸው 25 ሰዎችን መርጠው አጀንዳቸውን ሲያደራጁ ቆይተዋል።https://www.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid0BrNyYwGAh6qyBry1FppASANi5vWXZEFQLLcJmQ86GYSD2wGtCEhdqMzMtsNzGF54l
👍15
ከንቲባ አዳነች አቤቤ የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች የማበረታቻ ሽልማት አበረከቱ
*********************

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በ2016 የትምህርት ዘመን በ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች የማበረታቻ ሽልማት አበርክተዋል።

በ2016 ትምህርት ዘመን በ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች፣ ትምህርት ቤቶች እና ክፍለ ከተሞች የእውቅና እና ሽልማት መርሐ ግብር በዓድዋ ድል መታሰቢያ እየተካሄደ ነው።

ከንቲባዋ በመርሐ ግብሩ ለትምህርት ዘርፉ የተሰጠው ትኩረት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸው፤በቀጣይ የተሻለ ውጤት እንጠብቃለን ብለዋል።https://www.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid0zfzsoi99NM97zy6Wk5uuk2LPYKez9J3VVK9sHFH27aC9BesSkkp2EG7conNexgE7l
👍164👎3👏3
የፌዴሬሽን ምክር ቤት የድጎማ በጀትና የጋራ ገቢዎች ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ ለምክር ቤቱ በሚቀርቡ የውሳኔ ሃሳቦች ላይ መከረ
*****************

በፌዴሬሽን ምክር ቤት የድጎማ በጀትና የጋራ ገቢዎች ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ፤ ምክር ቤቱ መስከረም 28 ቀን 2017 ዓ.ም ለሚያካሂደው 6ኛ የፓርላማ ዘመን 4ኛ የሥራ ጊዜ፣ 1ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ቀርበው በሚፀድቁ የውሳኔ ሃሳቦች ላይ መክሯል።https://www.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid07eJ4yyRsnVA7qvzHzPzCLJsMGpG6AsCAzwXfDqzEtSmPwaAhpduXNVNayDe4BvSwl
👍129
የኢቲቪ ፓርላማ ቻናል ስርጭትን ለመከታተል፦
በFreqyency......11545
SR....44997
POL....H ኢቲዮ ሳት ላይ እንድትከታተሉ እንጋብዛለን።
ከደቂቃዎች በኋላ የሚጀመረውን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና የፌዴሬሽን ምክር ቤት የጋራ የመክፈቻ ስብሰባ በዚሁ ቻናል በቀጥታ ይከታተሉ።
#etv #EBC #HOPR
👍25
ዘላቂ ሰላም፣ኢኮኖሚ እና የመንግስት አገልግሎትን ማዘመን የምክር ቤቱ ዋነኛ ትኩረቶች ናቸው፡- አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ
*****************

ከመስከረም ወር የመጨረሻ ሳምንት ሰኞ ጀምሮ እስከ ሰኔ 30 ቀን የአንድ ዓመት የሥራ ጊዜው አድርጎ የደነገገው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፤ዘላቂ ሰላም ማስፈን፣ፈጣን የሆነውን የኢኮኖሚ እድገትን ማስቀጠል እና የመንግስት አገልግሎትን ማዘመን የ2017 የስራ ዘመን ዋነኛ የትኩረት አቅጣጫዎቹ መሆናቸውን አስታውቋል፡፡

የምክር ቤቱ አፈ ጉባዔ ታገሰ ጫፎ ከኢቢሲ ጋር በነበራቸው ቆይታ፤ ለዘላቂ ሰላም ማጣት የሚነሱ ቅሬታዎች እንዲፈቱ ከበጀት ማፅደቅ ጀምሮ ያሉ ስራዎች ፍትሃዊ እና ሁሉን አካታች አንዲሆኑ እየተሰራ ስለመሆኑ ጠቁመዋል፡፡

ይህንንም ሊያጠናክሩ የሚችሉ የሕግ ማሻሻያዎችን ማድረግ እና ተግባራዊነታቸውን የመከታተል ስራ እንደሚቀጥል ተናግረዋል፡፡
👍30👎63
ለኢፌዲሪ እጩ ፕሬዚዳንት አምባሳደር ታዬ አጽቀ ሥላሴ ቀርበዋል
👏34👍7👎1
አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ የኢፌዲሪ ፕሬዚዳንት ሆነው ተሰየሙ
*******************
አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ በህዝብ ተወካዮች እና ፌዴሬሽን ምክር ቤቶች የጋራ ስብሰባ ላይ ፕሬዚዳንት ሆነው ተሰይመዋል።
በምከርቤቱ በአምስት ድምጽ ተአቅቦ በአብላጫ ድምጽ ነው ፕሬዚዳንት ሆነው የተሰየሙት
38👍15👎7👏4
የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሆነው የተሰየሙት አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ ቃለ መሐላ ፈጸሙ
27👏12👍7
የቀድሞ ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ እና አዲስ የተሰየሙት ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ የስልጣን ርክክብ አድርገዋል፡፡
58👏21👍16👎4