EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation) – Telegram
EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)
138K subscribers
38.3K photos
462 videos
80 files
13.2K links
EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation) @etvafaanoromoo1
@ETVkidschannel
@EBCWORLD1
@etventertainment1
Download Telegram
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የጌዴኦ ዞን የቡና ምርት
👍5113
የጊኒ ጠቅላይ ሚኒስትር አማዱ ኡሪ ባህ አዲስ አበባ ገቡ
**********************

የጊኒ ጠቅላይ ሚኒስትር አማዱ ኡሪ ባህ ዛሬ ማለዳ አዲስ አበባ ሲገቡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ተገኝተው አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው "የጊኒ ጠቅላይ ሚኒስትር አማዱ ኡሪ ባህ እንኳን ወደ ኢትዮጵያ መጡ እላለሁ" ብለዋል።

#etv #ኢቲቪ #ኢቢሲ #ዐቢይአሕመድ #Guinea #TheRepublicofGuinea
https://web.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid02xA7Jsts1NpT1sB3yWUU3WYHBV6JnzRFSXLF5kBcWC3N6eMuCgBzTkW5XYaF56zrrl
👍183
ትራምፕ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫውን እየመሩ ነው
******************

የአለም ፖለቲካ ዘዋሪዋ ሀገር አሜሪካ 47ተኛውን ፕሬዝዳንቷን በመምረጥ ላይ ትገኛለች።

ፉክክሩ የጋለው እና እጩዎቹ አንገት ለአንገት የተያያዙበት ምርጫ ውጤት በዚህ ሰዐት የሪፐብሊካኑ ዶናልድ ትራምፕ እየመሩ ይገኛሉ።

የዲሞክራቷ እጩ ካማላ ሀሪስም ሆኑ ሪፐብሊካኑ ዶናልድ ትራምፕ ለሀገራቸው ይበጃል ብለው የያዟቸው ፖሊሲዎች አሜሪካውያንና የቀረውን አለም ቀልብ ስቦ የምርጫውን ውጤት አለም በጉጉት እንዲከታተል አድርጎታል።

እስከመጨረሻ ውጤቱን ለመገመት አስቸጋረ የሚሆነው 47ተኛው የአሜሪካ ምርጫ ፉክክር ማንን ፕሬዝዳንት ያደርግ ይሆን?
አሁንም የሁለቱን ፉክክር እና ውጤት ለማወቅ "ስዊንግ ስቴት" የሚባሉትን 7 ግዛቶች የምርጫ ውጤት መጠበቅ አስገዳጅ ነው።

ካማላ ሀሪስ እስካሁን በብዙ ሴቶች በመመረጥ ቅድሚያውን ቢይዙም በአጠቃላይ የምርጫ ሂደቱ በሪፐብሊካኑ እጩ ዶናልድ ትራምፕ እየተመሩ ይገኛሉ።

አሁን ላይ ባለው መረጃ ትራምፕ ምርጫውን የማሸነፍ ዕድላቸው ወደ 89% ከፋ ማለቱ እየተዘገበ ነው::

በናርዶስ አዳነ
https://web.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid0KCyGkjCneLH2FSW7h6aXeDNFwHm7QowbrpUpHpdEwvETxZVeREkDa2XDxp9Vnxfql
👍368👏3
እንግዶች በቤተ- መንግሥት