EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation) – Telegram
EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)
137K subscribers
38.4K photos
462 videos
80 files
13.2K links
EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation) @etvafaanoromoo1
@ETVkidschannel
@EBCWORLD1
@etventertainment1
Download Telegram
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በብሪክስ ማዕቀፍ የሩስያ አፍሪካ ኔትዎርክ ዩኒቨርሲቲዎችን እንዲቀላቀል ጥሪ ቀረበለት
*************

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዚዳንት ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር) ከሩስያ ሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ምክትል ሚኒስትር ቆስጠንጢኖስ ሞግሌብስኪ ጋር ተወያይተዋል።

የብሪክስ ዩኒቨርሲቲዎች ህብረት አባል የሆነው አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከሩስያ ሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ጋር በቴክኖሎጂ፣ በሕክምና፣ በጠፈር ሳይንስ፣ በፊዚክስ እንዲሁም በማዕድን እና ኢነርጂ ዘርፎች ያለውን ትብብር ወደ ላቀ ደረጀ ለማድረስ ያተኮረ ምክክር ተደርጓል።

በዚሁ ወቅት አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በብሪክስ ማዕቀፍ የሩስያ አፍሪካ ኔትዎርክ ዩኒቨርሲቲዎችን እንዲቀላቀል በሩሲያ ሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ጥሪ ቀርቦለታል።

ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት አዲስ አበባ የገቡት ሚኒስትሩ እና ልዑካቸው አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲን የጐበኙ ሲሆን፤ ዩኒቨርሲቲው ወደ ሙሉ ራስገዝነት የሚያደረገውን የሽግግር ሂደት እንደሚደግፉ በዚሁ ወቅት መግለጻቸውን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተገኘው መረጃ ያመላክታል።
👍227
472 ሺህ 500 ኩንታል ዩሪያ የአፈር ማዳበሪያ የጫነች የመጀመሪያዋ መርከብ ጂቡቲ ወደብ ደረሰች
***************

በ2017/18 የምርት ዘመን ከውጭ ከሚገዛው 23 ሚሊዮን ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ውስጥ 472 ሺህ 500 ኩንታል ዩሪያ የጫነች የመጀመሪያዋ ኤም ቪ አባይ ሁለት የተሰኘች የኢትዮጵያ መርከብ ጂቡቲ ወደብ ደርሳለች።

በቀጣይ ቀናት ወደ ሀገር ውስጥ የማጓጓዝ ሥራውም በፍጥነት እንደሚጀመር ይጠበቃል።

ለ2017/18 የምርት ዘመን የ23 ሚሊዮን ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ግዢ ለመፈጸም 1 ነጥብ 3 ቢሊዮን ዶላር ተመድቧል።

መንግሥት አዲስ የግዢ መመሪያ በማውጣቱ ባለፈው የምርት ዘመን 21 ቢሊዮን ብር ለማዳን መቻሉን የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን መረጃ ያመለክታል።
👍452
ማስታወቂያ
**********
የባንካችን የተሟላ ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት “ሲንቄ ኢህሳንን” ምርጫዎ ያድርጉ!
መልካም ጁምዓ!
Siinqee IHSAN
Tajaajila Baankii dhalarraa bilisaa baankii keenyaa 'Siinqee IHSAN' filannoo keessan jalqabaa taasifadhaa.
Jumahaa Gaarii !
#Siinqee_Bank #Baankii_Siinqee #ሲንቄ_ባንክ #Siinqee_Ihsan
#EMPOWERED_TOGETHER
👍11
የኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ አየር መንገድን በ1 ወር ውስጥ ወደ ስራ ለማስገባት ዝግጅት ተጠናቋል - አቶ መስፍን ጣሰው
***********

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ አየር መንገድን በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ወደ ስራ እንደሚያስገባ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ መስፍን ጣሰው ገለጹ።

ዋና ስራ አስፈጻሚው ለኢዜአ እንደገለጹት፥ አየር መንገዱ በራዕዩ መሰረት ሊደርስበት ያቀደው ደረጃ ላይ ለመድረስ በሁሉም አቅጣጫ በፈጣን የእድገት መንገድ ላይ ይገኛል።

በተለይ የአፍሪካ አየር መንገዶችን በማቋቋም ረገድ አየር መንገዱ ሰፊ ተሞክሮ እንዳለውና በቅርቡም በኮንጎ ኪንሻሳ አዲስ አየር መንገድ ለማቋቋም ከሀገሪቱ መንግስት ጋር ስምምነት ላይ መድረሱን ገልጸዋል።
https://web.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid02ZW6TH6ozkg3b3zU2Br5QvT8sHKs7f1hytVhJaAaDud4iCHaDgHJavwQrz1anhaNAl
👍143👏1
ኢትዮጵያ በባህልና ስፖርት ዘርፍ ያላትን እምቅ ሀብት ለዓለም በመሸጥ ከውጤቱ ተጠቃሚ እንድትሆን በትጋት መስራት ይገባል
*********

ባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ከክልልና ከተማ አስተዳደር አመራሮች ጋር በፖሊሲና ስትራቴጂክ ጉዳዮች ዙሪያ ምክክር እያደረገ ነው።

በምክክር መድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ሸዊት ሸንካ፥ ኢትዮጵያ በባህልና ስፖርት ዘርፍ ያላትን እምቅ ሀብት ለዓለም በመሸጥ ከውጤቱ ተጠቃሚ እንድትሆን በትጋት መስራት ይገባል ብለዋል።

ግጭትን ለመፍታትና ሰላምን ለማስፈን የጥበብ ሚና ከፍተኛ ነው ያሉት ሚኒስትሯ፤ ኪነ ጥበብን፣ ስነ ጥበብን እና ባህላዊ እሴቶችን ለሀገር ገፅታና ለትውልድ ግንባታ እንደ ትልቅ መሳሪያ መጠቀምን አዳብረን እንቀጥላለን ብለዋል።

መድረኩ በሃገር አቀፍ ስፖርት ልማት አንፃር የሚታዩ ችግሮችን ለመፍታት በተከለሰ የስፖርት ፖሊሲና ረቂቅ የስፖርት አዋጅ፣ በ2017 አንደኛ ሩብ ዓመት አፈፃፃም እና በሌሎች ስትራቴጂያዊ ጉዳዮች ዙሪያ እንደሚመክር ተገልጿል።

ባህል፣ ኪነ ጥበብና ስነ ጥበብን ለህዝቦች አብሮነትና ገፅታ ግንባታ ለመጠቀም ያለመ የ3 ወር ንቅናቄ ማስጀመርም ሌላው የመድረኩ ዓላማ መሆኑን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመለክታል።
👍8
ሞስኮ ከዋሽንግተን ጋር ለመነጋገር ዝግጁ ነች፦ ፕሬዚዳንት ፑቲን
***********************************

የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን በአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ዶናልድ ትራምፕ ማሸነፋቸውን ተከትሎ የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላልፈዋል።

ፕሬዚዳንቱ በመልዕክታቸው ሞስኮ ከተመራጩ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ጋር ለመነጋገር ዝግጁ መሆኗን ገልፀዋል።

ፑቲን በሶቺ በሚገኘው የቫልዳይ ዓለም አቀፍ የውይይት መድረክ ላይ “በአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ስላሸነፍክ ትራምፕ እንኳን ደስ አለህ ለማለት እወዳለሁ” ስለማለታቸው አልጀዚራ ዘግቧል።

ፑቲን ከትራምፕ ድል በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ይፋዊ መግለጫቸውን የሰጡ ሲሆን ሀገራቸው ከአዲሱ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ጋር ለመነጋገር ዝግጁ ስለመሆኗ ጠቁመዋል።

አሜሪካ ከሩሲያ ጋር ያላትን ግንኙነት ለማሻሻል እና የሩሲያ ዩክሬን ግጭትን ለመፍታት ትራምፕ ያላቸውን ፍላጎት ያነሱት ፑቲን አሁንም ለጉዳዮቹ ከፍተኛ ትኩረት እንደሚሰጡ ጠቁመዋል።

ይህ በንዲህ እንዳለ የዩክሬን ፕሬዚዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ ከምርጫው ውጤት በኋላ ትራምፕን ካነጋገሩት መሪዎች መካከል አንዱ ሲሆኑ የዩክሬን እና የአሜሪካን ቀጣይ ትብብር አስፈላጊነት ላይ አፅንዖት ስለመስጠታቸው ተሰምቷል።

"ጠንካራ እና የማይናወጥ የአሜሪካ አመራር ለዓለም ፍትሃዊ ሰላምን ለማምጣት አስፈላጊ ነው" ሲሉ ዘለንስኪ በኤክስ መልዕክታችን አጋርተዋል ሲል የዘገበው አልጀዚራ ነው።

በናርዶስ አዳነ
👍30
ርዕሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ የመገጭ መስኖ ግድብ ፕሮጀክትን ጎበኙ
*************

የአማራ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ የመገጭ መስኖ ግድብ ፕሮጀክትን የግንባታ እንቅስቃሴ ጎብኝተዋል።

ጉብኝቱን ተከትሎ ርዕሰ መሥተዳድሩ የግድቡ ግንባታ በአጭር ጊዜ እንዲጠናቀቅ አቅጣጫ ያመላክታሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ርዕሰ መሥተዳድሩ በቆይታቸው በከተማዋ እና በአካባቢው እየተከናወኑ ያሉ ሌሎች ትላልቅ የልማት ፕሮጀክቶችን ተዘዋውረው እንደሚጎበኙ ይጠበቃል።
👍23
በ"ከረሃብ ነጻ ዓለም" ጉባዔ የተካፈሉ መሪዎች ወደየሀገራቸው ተመለሱ
*********

ባለፉት ቀናት በአዲስ አበባ በተካሄደው "ከረሃብ ነጻ ዓለም" ጉባዔ የተሳተፉ መሪዎች ወደየሀገራቸው ተመልሰዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴዔታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ በቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ለመሪዎቹ አሸኛኘት አደርገውላቸዋል።
👍33👎75👏4
ሦስት ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን ለመገንባት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ተፈረመ
***************

ትምህርት ሚኒስቴር ከሰዎች ለሰዎች ፋውዴሽን ጋር ሦስት ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን ለመገንባት የሚያስችለውን የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ተፈራርሟል።

የስምምነት ሰንዱን የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እና የሰዎች ለሰዎች ፋውንዴሽን ቦርድ ሰብሳቢ ዶ/ር ሴባስቲያን ብራንዲስ ተፈራርመዋል።

በመግባቢያ ስምምነቱም ሰዎች ለሰዎች ፋውንዴሽን ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ለመገንባት ካቀዳቸው 13 ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መካከል ሦስቱን የሚገነባ መሆኑ ተጠቅሷል።
https://web.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid02gKDYGMSbbSjMk2EhwBk9hWo78UNDrxKHQoLAbXWZ2dwxi3o8tGn2G2Ao14hAjbXcl
👍231👎1
የመንግስት አግልግሎትና አስተዳደር ሪፎርም አመራር አብይ ኮሚቴ የመጀመሪያው ዙር የቀዳሚ ምዕራፍ ሥራዎችን ገመገመ
*************

የመንግስት አግልግሎትና አስተዳደር ሪፎርም አመራር አብይ ኮሚቴ ሁለተኛ መደበኛ ስብሰባውን ዛሬ አካሂዷል።

አብይ ኮሚቴው በስብሰባው የመጀመሪያው ዙር የቀዳሚ ምዕራፍ ሥራዎችን በዚህ ምዕራፍ የተካተቱ ስምንት ተቋማት በተገኙበት መገምገሙን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው አስታውቀዋል።

በቀጣይም መልካም ጅምሮች ተጠናክረው የሚቀጥሉበት እና በሪፎርሙ የታቀፉ ተቋማትም ያላቸውን ልምድ የሚቀያየሩበት አውድ መፍጠር መቻሉን ጠቅሰዋል።

ተቋማት ያከናወኗቸውን ተግባራት በዝርዝር በመቃኘት እንዲሁም ጥንካሬዎችንና ውስንነቶችን በመለየት በቀጣይ ትኩረት ሊደረግባቸው የሚገባቸው ጉዳዮች ላይ አብይ ኮሚቴው አቅጣጫ ማስቀመጡንም ገልፀዋል።

አብይ ኮሚቴ ከስብሰባው ጎን ለጎን በሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን የተከናወኑ የሪፎርም ስራዎችንም ጎብኝቷል።

በመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ዘርፍ የሚታዩ ችግሮችን በመሰረታዊነት ለመፍታት ሪፎርም መጀመሩ ይታወቃል።
👍10