EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation) – Telegram
EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)
137K subscribers
38.4K photos
462 videos
80 files
13.2K links
EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation) @etvafaanoromoo1
@ETVkidschannel
@EBCWORLD1
@etventertainment1
Download Telegram
ሞስኮ ከዋሽንግተን ጋር ለመነጋገር ዝግጁ ነች፦ ፕሬዚዳንት ፑቲን
***********************************

የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን በአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ዶናልድ ትራምፕ ማሸነፋቸውን ተከትሎ የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላልፈዋል።

ፕሬዚዳንቱ በመልዕክታቸው ሞስኮ ከተመራጩ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ጋር ለመነጋገር ዝግጁ መሆኗን ገልፀዋል።

ፑቲን በሶቺ በሚገኘው የቫልዳይ ዓለም አቀፍ የውይይት መድረክ ላይ “በአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ስላሸነፍክ ትራምፕ እንኳን ደስ አለህ ለማለት እወዳለሁ” ስለማለታቸው አልጀዚራ ዘግቧል።

ፑቲን ከትራምፕ ድል በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ይፋዊ መግለጫቸውን የሰጡ ሲሆን ሀገራቸው ከአዲሱ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ጋር ለመነጋገር ዝግጁ ስለመሆኗ ጠቁመዋል።

አሜሪካ ከሩሲያ ጋር ያላትን ግንኙነት ለማሻሻል እና የሩሲያ ዩክሬን ግጭትን ለመፍታት ትራምፕ ያላቸውን ፍላጎት ያነሱት ፑቲን አሁንም ለጉዳዮቹ ከፍተኛ ትኩረት እንደሚሰጡ ጠቁመዋል።

ይህ በንዲህ እንዳለ የዩክሬን ፕሬዚዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ ከምርጫው ውጤት በኋላ ትራምፕን ካነጋገሩት መሪዎች መካከል አንዱ ሲሆኑ የዩክሬን እና የአሜሪካን ቀጣይ ትብብር አስፈላጊነት ላይ አፅንዖት ስለመስጠታቸው ተሰምቷል።

"ጠንካራ እና የማይናወጥ የአሜሪካ አመራር ለዓለም ፍትሃዊ ሰላምን ለማምጣት አስፈላጊ ነው" ሲሉ ዘለንስኪ በኤክስ መልዕክታችን አጋርተዋል ሲል የዘገበው አልጀዚራ ነው።

በናርዶስ አዳነ
👍30
ርዕሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ የመገጭ መስኖ ግድብ ፕሮጀክትን ጎበኙ
*************

የአማራ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ የመገጭ መስኖ ግድብ ፕሮጀክትን የግንባታ እንቅስቃሴ ጎብኝተዋል።

ጉብኝቱን ተከትሎ ርዕሰ መሥተዳድሩ የግድቡ ግንባታ በአጭር ጊዜ እንዲጠናቀቅ አቅጣጫ ያመላክታሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ርዕሰ መሥተዳድሩ በቆይታቸው በከተማዋ እና በአካባቢው እየተከናወኑ ያሉ ሌሎች ትላልቅ የልማት ፕሮጀክቶችን ተዘዋውረው እንደሚጎበኙ ይጠበቃል።
👍23
በ"ከረሃብ ነጻ ዓለም" ጉባዔ የተካፈሉ መሪዎች ወደየሀገራቸው ተመለሱ
*********

ባለፉት ቀናት በአዲስ አበባ በተካሄደው "ከረሃብ ነጻ ዓለም" ጉባዔ የተሳተፉ መሪዎች ወደየሀገራቸው ተመልሰዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴዔታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ በቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ለመሪዎቹ አሸኛኘት አደርገውላቸዋል።
👍33👎75👏4
ሦስት ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን ለመገንባት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ተፈረመ
***************

ትምህርት ሚኒስቴር ከሰዎች ለሰዎች ፋውዴሽን ጋር ሦስት ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን ለመገንባት የሚያስችለውን የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ተፈራርሟል።

የስምምነት ሰንዱን የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እና የሰዎች ለሰዎች ፋውንዴሽን ቦርድ ሰብሳቢ ዶ/ር ሴባስቲያን ብራንዲስ ተፈራርመዋል።

በመግባቢያ ስምምነቱም ሰዎች ለሰዎች ፋውንዴሽን ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ለመገንባት ካቀዳቸው 13 ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መካከል ሦስቱን የሚገነባ መሆኑ ተጠቅሷል።
https://web.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid02gKDYGMSbbSjMk2EhwBk9hWo78UNDrxKHQoLAbXWZ2dwxi3o8tGn2G2Ao14hAjbXcl
👍231👎1
የመንግስት አግልግሎትና አስተዳደር ሪፎርም አመራር አብይ ኮሚቴ የመጀመሪያው ዙር የቀዳሚ ምዕራፍ ሥራዎችን ገመገመ
*************

የመንግስት አግልግሎትና አስተዳደር ሪፎርም አመራር አብይ ኮሚቴ ሁለተኛ መደበኛ ስብሰባውን ዛሬ አካሂዷል።

አብይ ኮሚቴው በስብሰባው የመጀመሪያው ዙር የቀዳሚ ምዕራፍ ሥራዎችን በዚህ ምዕራፍ የተካተቱ ስምንት ተቋማት በተገኙበት መገምገሙን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው አስታውቀዋል።

በቀጣይም መልካም ጅምሮች ተጠናክረው የሚቀጥሉበት እና በሪፎርሙ የታቀፉ ተቋማትም ያላቸውን ልምድ የሚቀያየሩበት አውድ መፍጠር መቻሉን ጠቅሰዋል።

ተቋማት ያከናወኗቸውን ተግባራት በዝርዝር በመቃኘት እንዲሁም ጥንካሬዎችንና ውስንነቶችን በመለየት በቀጣይ ትኩረት ሊደረግባቸው የሚገባቸው ጉዳዮች ላይ አብይ ኮሚቴው አቅጣጫ ማስቀመጡንም ገልፀዋል።

አብይ ኮሚቴ ከስብሰባው ጎን ለጎን በሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን የተከናወኑ የሪፎርም ስራዎችንም ጎብኝቷል።

በመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ዘርፍ የሚታዩ ችግሮችን በመሰረታዊነት ለመፍታት ሪፎርም መጀመሩ ይታወቃል።
👍10
ርዕሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ የአጼ ፋሲል ቤተ መንግሥትን የእድሳት ሥራ ጎበኙ
***********

የአማራ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ በጎንደር ከተማ የተለያዩ ልማቶችን የሥራ እንቅስቃሴ ተዘዋውረው ተመልክተዋል።

ርዕሰ መሥተዳድሩ የመገጭ መስኖ ግድብ ፕሮጀክት አፈፃፀምን እና የአጼ ፋሲል ቤተ መንግሥት የእድሳት ሥራ ሂደትን ጎብኝተዋል።

በተጨማሪም የመገጭ መስኖ ግድብ ፕሮጀክትን በተቋራጭነት ከሚሠራው ቢአይካ ድርጅት የሥራ ኃላፊዎች ጋር በቀጣይ የስራ አቅጣጫዎች ዙሪያ መወያየታቸውን አሚኮ ዘግቧል።
👍17👏2