EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation) – Telegram
EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)
138K subscribers
38.2K photos
458 videos
80 files
13.1K links
EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation) @etvafaanoromoo1
@ETVkidschannel
@EBCWORLD1
@etventertainment1
Download Telegram
ኢትዮጵያ የተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ፖሊሲ ተግባራዊ በማድረግ ለውጭ ኢንቨስተሮች ምቹ ሁኔታ ፈጥራለች - ፕሬዚዳንት ታየ አጽቀ ሥላሴ
**************************

ኢትዮጵያ ሁለተኛውን የሀገር በቀል ኢኮኖሚ ማሻሻያ እና የተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ፖሊሲ ተግባራዊ በማድረግ ለውጭ ኢንቨስተሮች ምቹ ሁኔታ መፍጠሯን ፕሬዚዳንት ታየ አጽቀ ሥላሴ ተናግረዋል፡፡

ይህም የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ትግበራን ለማቀላጠፍ ወሳኝ እርምጃ መሆኑን አንስተዋል፡፡

ነጻ የንግድ ቀጣናው የአህጉሪቱን ዘላቂ ዕድገት የሚያረጋግጥ እና ወደ ብልፅግና የሚያሸጋግር በመሆኑ ለተግባራዊነቱ መረባረብ እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡

ፕሬዚዳንቱ የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና “የጋራ ራዕያችንን የምናሳካበት የበለጸገች አፍሪካን እውን የምናደርግበት ነው” ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

15ኛው የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና የንግድ ሚኒስትሮች ጉባዔ በአፍሪካ ህብረት እየተካሄደ ይገኛል፡፡
👍296👎4👏1
ከንቲባ አዳነች አቤቤ የተሻለ አፈጻጸም ላስመዘገቡ የከተማዋ ፖሊስ ሠራዊት አባላት ዕውቅና ሰጡ
*************************

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ የተሻለ አፈጻጸም ላስመዘገቡ የመዲናዋ የፖሊስ ሠራዊት አባላት ዕውቅና ሰጥተዋል፡

ከንቲባዋ በማኀበራዊ ትስስር ገጻቸው “ለከተማችን ሰላም ፖሊሳዊ ሥነ-ምግባር በመላበስ፣ የሌሊት ቁር እና የቀትር ጸሐይን በመቋቋም በሰብዓዊነት እና በጀግንነት እስከ ህይወት መስዋዕትነት በማገልገል በተሰራዉ ሥራ እና በተገኘዉ ውጤት የተሻለ አፈጻጸም ላስመዘገቡ የከተማችን ፖሊስ ሠራዊት አባላት ዕውቅና ሰጥተናል” ብለዋል፡፡

ለከተማዋ ሰላም እና ደህንነት መረጋገጥ ከአዲስ አበባ ፖሊስ ጋር በቅርበት እየሰሩ ላሉ የጸጥታ አካላትም ከንቲባ አዳነች አቤቤ ምስጋና አቅርበዋል፡፡
👏20👍1210👎5
በስንዴ ልማት እየታየ ያለው ክንውን የምግብ ዋስትናን በማረጋገጥ ረገድ ትልቅ ሚና በመጫወት ላይ ነው - አቶ ሽመልስ አብዲሳ
***********

በስንዴ ልማት እየታየ ያለው ክንውን የምግብ ዋስትናን በማረጋገጥ ረገድ ትልቅ ሚና በመጫወት ላይ መሆኑን የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ ገለጹ።

ርዕሰ መስተዳድሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባጋሩት መልዕክት፥ የለውጡ መንግሥት የምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥ ባሻገር የክልሉን የኢኮኖሚ መዋቅር ዝንፈት ለማረቅ ሀገሪቱ ያላት ትልቁ አቅም ግብርና መሆኑን ተገንዘቦ ወደ ሥራ መግባቱን አስታውሰዋል።

በዚህ ረገድ የስንዴ ልማት ላይ እየታየ ያለው ክንውን የምግብ ዋስትናን በማረጋገጥ፣ የአገር ውስጥ የኢንዱስትሪ ግብዓት በማስፋት እና ወጪ ንግድን በመጨመር ረገድ ትልቅ ሚና በመጫወት ላይ መሆኑን አንስተዋል።

ጅምሩን ለማስፈንጠር መንግሥት የግብርና ግብዓት እና ቴክኖሎጂ በማቅረብ፣ የአርሶ አደሩን ክህሎት በማሳደግ፣ የኢኮኖሚ መዋቅሩን በማስተካከል እና የንግድ ሥርዓቱን በማመቻቸት ረገድ በስፋት እየሠራ መሆኑን አክለዋል።

ይሁን እንጂ በርዕሰ መስተዳድሩ አስተያየት በስንዴ ልማት ዙሪያ እየታየ ያለው የስኬት ብልጭታ ሀገሪቱ ያላትን እምቅ አቅም ከማስታወስ የዘለለ አይደለም።

በመሆኑም የሴክተሩን ሁለንተናዊ ሽግግር እውን በማድረግ የወል እና የቤተሰብ ብልጽግናን ለማረጋገጥ መንግሥት በግብርናው ዘርፍ መውሰድ የጀመራቸው ስትራቴጂያዊና የተቀናጁ እርምጃዎች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው በየደረጃው ያለ አመራር የሚስተው ጉዳይ አይደለም ብለዋል አቶ ሽመልስ።
👍222