EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation) – Telegram
EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)
137K subscribers
38.4K photos
462 videos
80 files
13.2K links
EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation) @etvafaanoromoo1
@ETVkidschannel
@EBCWORLD1
@etventertainment1
Download Telegram
ከንቲባ አዳነች አቤቤ የተሻለ አፈጻጸም ላስመዘገቡ የከተማዋ ፖሊስ ሠራዊት አባላት ዕውቅና ሰጡ
*************************

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ የተሻለ አፈጻጸም ላስመዘገቡ የመዲናዋ የፖሊስ ሠራዊት አባላት ዕውቅና ሰጥተዋል፡

ከንቲባዋ በማኀበራዊ ትስስር ገጻቸው “ለከተማችን ሰላም ፖሊሳዊ ሥነ-ምግባር በመላበስ፣ የሌሊት ቁር እና የቀትር ጸሐይን በመቋቋም በሰብዓዊነት እና በጀግንነት እስከ ህይወት መስዋዕትነት በማገልገል በተሰራዉ ሥራ እና በተገኘዉ ውጤት የተሻለ አፈጻጸም ላስመዘገቡ የከተማችን ፖሊስ ሠራዊት አባላት ዕውቅና ሰጥተናል” ብለዋል፡፡

ለከተማዋ ሰላም እና ደህንነት መረጋገጥ ከአዲስ አበባ ፖሊስ ጋር በቅርበት እየሰሩ ላሉ የጸጥታ አካላትም ከንቲባ አዳነች አቤቤ ምስጋና አቅርበዋል፡፡
👏20👍1210👎5
በስንዴ ልማት እየታየ ያለው ክንውን የምግብ ዋስትናን በማረጋገጥ ረገድ ትልቅ ሚና በመጫወት ላይ ነው - አቶ ሽመልስ አብዲሳ
***********

በስንዴ ልማት እየታየ ያለው ክንውን የምግብ ዋስትናን በማረጋገጥ ረገድ ትልቅ ሚና በመጫወት ላይ መሆኑን የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ ገለጹ።

ርዕሰ መስተዳድሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባጋሩት መልዕክት፥ የለውጡ መንግሥት የምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥ ባሻገር የክልሉን የኢኮኖሚ መዋቅር ዝንፈት ለማረቅ ሀገሪቱ ያላት ትልቁ አቅም ግብርና መሆኑን ተገንዘቦ ወደ ሥራ መግባቱን አስታውሰዋል።

በዚህ ረገድ የስንዴ ልማት ላይ እየታየ ያለው ክንውን የምግብ ዋስትናን በማረጋገጥ፣ የአገር ውስጥ የኢንዱስትሪ ግብዓት በማስፋት እና ወጪ ንግድን በመጨመር ረገድ ትልቅ ሚና በመጫወት ላይ መሆኑን አንስተዋል።

ጅምሩን ለማስፈንጠር መንግሥት የግብርና ግብዓት እና ቴክኖሎጂ በማቅረብ፣ የአርሶ አደሩን ክህሎት በማሳደግ፣ የኢኮኖሚ መዋቅሩን በማስተካከል እና የንግድ ሥርዓቱን በማመቻቸት ረገድ በስፋት እየሠራ መሆኑን አክለዋል።

ይሁን እንጂ በርዕሰ መስተዳድሩ አስተያየት በስንዴ ልማት ዙሪያ እየታየ ያለው የስኬት ብልጭታ ሀገሪቱ ያላትን እምቅ አቅም ከማስታወስ የዘለለ አይደለም።

በመሆኑም የሴክተሩን ሁለንተናዊ ሽግግር እውን በማድረግ የወል እና የቤተሰብ ብልጽግናን ለማረጋገጥ መንግሥት በግብርናው ዘርፍ መውሰድ የጀመራቸው ስትራቴጂያዊና የተቀናጁ እርምጃዎች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው በየደረጃው ያለ አመራር የሚስተው ጉዳይ አይደለም ብለዋል አቶ ሽመልስ።
👍222
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) ከአልጄሪያ አቻቸው አህመድ አታፍ ጋር ተወያዩ
*************

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) በሶቺ፣ ሩስያ እየተካሄደ ካለው የሩስያ -አፍሪካ የትብብር ፎረም የጋራ የሚኒስትሮች ስብሰባ ጎን ለጎን ከአልጄሪያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አህመድ አታፍ ጋር ተወያይተዋል።

ሚኒስትሮቹ በውይይታቸው በተለያዩ የትብብር መስኮች የሁለቱን አገራት ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር ተስማምተዋል።

የጋራ ተጠቃሚነትን በሚያስከብሩ ቀጣናዊ እና አህጉራዊ ጉዳዮች ዙሪያም መምከራቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።
👍28
በስፔን ላሊጋ ሪያል ማድሪድ ኦሳሱናን 4ለ0 አሸነፈ
***

በስፔን ላሊጋ 12ኛ ሳምንት የጨዋታ መርሃ ግብር ሪያል ማድሪድ ኦሳሱናን 4ለ0 አሸንፏል።

በ2024 የባላንዶር ሽልማት 2ኛ ደረጃ በመያዝ ያጠናቀቀው ቪኒሺየስ ጁኒየር ለማድሪድ 3 ግቦችን በማስቆጠር ሃትሪክ ሲሰራ፤ ቤሊንግሃም አራተኛዋን ግብ ጨምሯል።

ማድሪድ ዛሬ ማሸነፉን ተከትሎ ነጥቡን 27 በማድረስ ላሊጋውን በ33 ነጥብ እየመራ ካለው ባርሴሎና ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት ማጥበብ ችሏል።

የላሊጋው መሪ ባርሴሎና ነገ ምሽት 5 ሰዓት ከሜዳው ውጭ ከሪያል ሶሴዳድ ጋር ይጫወታል።

በላሉ ኢታላ
👍282
የሊጉ መሪ ሊቨርፑል ከአስቶን ቪላ፤ ሻምፒዮኑ ማን ሲቲ ከብራይተን ዛሬ ምሽት የሚያደርጓቸው ጨዋታዎች ተጠባቂ ናቸው
****

በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 11ኛ ሳምንት መርሃ ግብር የሊጉ መሪ ሊቨርፑል በሜዳው ምሽት 5 ሰዓት ከአስቶን ቪላ ጋር ይጫወታል።

በፕሪሚየር ሊጉ 2ኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው ማንቸስተር ሲቲ ከሻምፒዮንስ ሊግ ሽንፈት በኋላ በሊጉ 8ኛ ደረጃ ላይ ከሚገኘው ብራይተን አልቢዮን ጋር ዛሬ ምሽት 2:30 የሚጫወት ይሆናል።

ሲቲ በሻምፒዮንስ ሊጉ ባለፈው ማክሰኞ በስፖርቲንግ ሊዝበን ከደረሰበት ሽንፈት ለማገገም ከጉዳት የተመለሰውን የኬቨን ዴብራይን አገልግሎት እንደሚያገኝ ይጠበቃል።

በሲቲ በኩል ተከላከዩ ጆን ስቶንስ፣ ጃክ ግሪሊሽ፣ ኦስካር ቦብ እና ሩበን ዲያዝ በጉዳት ምክንያት በዛሬው ጨዋታ አይገቡም ተብሏል።

ብራይተን አልቢዮን ከሲቲ ጋር ባደረጋቸው 14 የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ሁለት ጊዜ ማሸነፍ ችሏል።

በ10 ጨዋታዎች በሰበሰበው 25 ነጥብ ፕሪሚየር ሊጉን እየመራ ያለው ሊቨርፑል፣ በሊጉ በ18 ነጥብ 6ኛ ጀረጃ ላይ ከሚገኘው አስቶን ቪላ ጋር በአንፊልድ ምሽት 5፡00 ሰዓት ይጫወታል።

የሊቨርፑል አሰልጣኝነትን ከክሎፕ የተረከቡት አሰልጣኝ አርና ስሎት በሊጉ ባደረጓቸው 16 ጨዋታዎች በ14ቱ በማሸነፍ ምርጥ ጅማሮ ካላቸው አሰልጣኞች መካካል ተጠቃሽ ናቸው።

በሊቨርፑል በኩል አሊሰን ዲያጎ ጆታ፣ ሃርቪ ኤሊዬት እና ፌዴሪኮ ቺዛ በጉዳት፤ አሌክሲስ ማካሊስተር በሁለት ቢጫ ቅጣት በዛሬው ጨዋታ እንደማይሰለፉ ቢቢሲ ዘግቧል።

ሊቨርፑል ሊጉን በ25 ነጥብ እየመራ፤ ሲቲ በ23 ነጥብ በሁለተኛነት እየተከተለ መሆኑ የዛሬዎቹን ጨዋታዎች በስፖርቱ አፍቃሪዎች ዘንድ ተጠባቂ እንዲሆኑ አድርጓቸዋል።

በላሉ ኢታላ
👍17