“ለቴክኖሎጂ የቀረበ ትውልድ ቢያስፈልገንም፤ የሀገርን ባህል በሚበርዝ መልኩ ግን አይደለም“ - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
**********************
ትውልዱ በዲጂታሉ ዓለም የሚኖረው ተሳትፎ ከፍ ያለ እንዲሆን ቢፈለግም የሀገርን ባህል በሚበርዝ መልኩ ሊሆን አይገባውም ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለፁ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030ን ትልም እና ትግበራን በተመለከተ ባደረጉት የእሳት ዳር ወግ ላይ፤ ኢትዮጵያ ያላትን የዳታ ትራንዛክሽን መከላከል የሚያስችል ቁመና ላይ እንደምትገኝ ተናግረዋል፡፡
ይህንንም ከተለዋዋጩ ዓውድ ጋር ማስኬድ ካልተቻለ መልካቸውን ቀይረው ለሚሰነዘሩ ጥቃቶች ተጋላጭነት እንደሚፈጠር አመላክተዋል፡፡
በዚህም የሳይበር ደህንነት ተቋማት ሲስተም እና ዳታን ከጥቃት የመከላከል እንዲሁም ትውልድን የመጠበቅ ኃላፊነት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል፡፡
ትውልድን መጠበቅ ላይ በተለይም የትስስር መተግበሪያዎችን የሚጠቀሙ ዜጎች ቴክኖሎጂውን በምን መልኩ ሊጠቀሙ እንደሚገባ ማስተማር፣ መንገድ ሲስቱ መገሰፅ ወሳኝ ስለመሆኑ አንስተዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ “ለቴክኖሎጂ የቀረበ ትውልድ ቢያስፈልገንም፤ የሀገርን ባህል በሚበርዝ መልኩ ግን አይደለም” ሲሉም አፅዕኖት ሰጥተዋል፡፡
በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያዎች በርካቶች የሚከተሏቸው ተጽዖኖ ፈጣሪዎች ከተቀረው ዓለም የሚወስዱትን ትምህርት መምረጥ እና የሀገርን ባህል ይጣረሳል ወይ የሚለውን ማጤን እንደሚገባቸውም ነው የገለፁት፡፡
ከዚህ ጋር ተያይዞ ታዳጊዎች መተግበሪዎችን እንዳይጠቀሙ የከለከሉ ሀገራት ቢኖሩም እኛ ግን እንዴት መጠቀም እንዳለባቸው የተገነዘቡ ትውልድን መፍጠር ቅድሚያ የምንሰጠው ጉዳይ ነው ሲሉ አክለዋል፡፡
በአፎምያ ክበበው

❤61👍20👏9🆒1
የኢቢሲ ም/ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ አብዱራህማን ሩቤ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ
*****
የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው እያገለገሉ የነበሩት አቶ አብዱራህማን ሩቤ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል::
ባደረባቸው ሕመም ምክንያት በህክምና ሲረዱ ቆይተው ዛሬ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል::
የአቶ አብዱራህማን ሥርዓተ ቀብር ዛሬ ይፈፀማል::
አቶ አብዱራህማን ከሪፖርተርነት እስከ ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚነት በተለያዩ የሚዲያ ተቋማት አገልግለዋል::
በተለይም በኦቢኤን እና በኢቢሲ ከሪፖርተርነት ጀምሮ በኃላፊነት ቦታዎች አገልግለዋል::
ህይወታቸው እስከአለፈበት ቀን ድረስ ደግሞ የኢቢሲ ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው እያገለገሉ ነበር::
አቶ አብዱራህማን ባለትዳር እና የሦስት ልጆች አባት ነበሩ::
የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን በምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚው አቶ አብዱራህማን ሩቤ ህልፈት የተሰማውን ሃዘን እየገለፀ ለቤተሰቦቻቸው ለወዳጆቻቸው እና ለሥራ ባልደረቦቻቸው መፅናናትን ይመኛል::

😢69❤30🙏4🥰2
574 ተጠርጣሪዎች በሳይበር ወንጀል መከላከል ዘመቻ በቁጥጥር ስር ዋሉ
****************
በ19 የአፍሪካ ሀገራት ውስጥ ላለፉት 30 ቀናት ሲካሄድ የቆየው መጠነ-ሰፊ የሳይበር ወንጀል መከላከያ ዘመቻ 574 ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር በማዋል መጠናቀቁን ኢንተርፖል አስታውቋል።
"ኦፕሬሽን ሴንቲነል" በሚል ስያሜ በተካሄደው በዚህ ዘመቻ፣ 3 ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋ የተዘረፈ ገንዘብ ማስመለስ የተቻለ ሲሆን፤ ከ6 ሺህ በላይ ጎጂ የሆኑ የኢንተርኔት ድረ-ገጾችም እንዲዘጉ ተደርጓል።

👍17❤5🔥1
የአቶ አብዱራህማን ሩቤ የቀብር ስነ ስርዓት በዛሬው ዕለት ይፈፀማል
***************
የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ የነበሩት አቶ አብዱራህማን ሩቤ የቀብር ስነ ስርዓት ዛሬ ከቀኑ 7 ሰዓት በኮልፌ የሙስሊም መካነ መቃብር ይፈፀማል።
አቶ አብዱራህማን ሩቤ ባደረባቸው ሕመም ምክንያት በህክምና ሲረዱ ቆይተው ዛሬ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።
አቶ አብዱራህማን ከሪፖርተርነት እስከ ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚነት በተለያዩ የሚዲያ ተቋማት ያገለገሉ ሲሆን፤ በተለይም በኦቢኤን እና በኢቢሲ ከሪፖርተርነት ጀምሮ በተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች ሀገራቸውን አገልግለዋል፡፡
ከመስከረም 27 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ ህይወታቸው እስከአለፈበት ቀን ድረስ ደግሞ የኢቢሲ ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው እያገለገሉ ነበር፡፡
ባለትዳር እና የሦስት ልጆች አባት የነበሩት አቶ አብዱራህማን ሩቤ በመልካም ስብዕናቸው እና በስራ ትጋታቸው ምስጉን ነበሩ፡፡
የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን በምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚው አቶ አብዱራህማን ሩቤ ህልፈት የተሰማውን ኃዘን በድጋሚ እየገለፀ፤ ለቤተሰቦቻቸው ለወዳጆቻቸው እና ለሥራ ባልደረቦቻቸው መፅናናትን ይመኛል::

❤13😢7🕊7🥰1
ሩሲያ ወደ ቻይና በምትልከው የተፈጥሮ ጋዝ አዲስ ክብረወሰን አስመዘገበች
********************
ሩሲያ ወደ ቻይና ከፍተኛ መጠን ያለው የተፈጥሮ ጋዝ በመላክ አዲስ ክብረወሰን አስመዝግባለች።
ሩሲያ ወደ ቻይና የምትልከው ፈሳሽ የተፈጥሮ ጋዝ በ2024 ከነበረው ቁጥር በሁለት እጥፍ በመብለጥ በ2025 1.6 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን በመድረሱ አዲስ ክብረወሰን ሆኖ መመዝገቡ ተነግሯል።
ከዚህ ቀደም አውስትራሊያ እና ኳታር ለቻይና ዋነኛ የተፈጥሮ ጋዝ አቅራቢ ሀገራት እንደነበሩ ተመላክቷል፡፡
ነገር ግን ሩሲያ በ2025 በነበረው የተፈጥሮ ጋዝ አቅርቦቷ አሁን ላይ አውስትራሊያን በመብለጥ እና ከኳታር በመቀጠል ሁለተኛዋ ለቻይና ትልቅ የተፈጥሮ ጋዝ አቅራቢ ሆናለች ነው የተባለው።
በቻይና እና አሜሪካ መካከል በተፈጠረው የንግድ ፍጥጫ ምክንያት ተቀዛቅዞ የነበረው የቻይና የተፈጥሮ ጋዝ ፍላጎት ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ መነቃቃት የታየበት ሲሆን የሩሲያ የጋዝ አቅራቢ ድርጅቶችም ምርታቸውን በማቅረብ ላይ እንደሚገኙ ስፑትኒክ ዘግቧል።
የአውሮፓ ኅብረት ከሩሲያ በሚገባው የጋዝ ምርት ላይ ማዕቀብ ቢጥልም ሩሲያ ወደ ቻይና የምትልከው የጋዝ ምርት በእጥፍ በማደጉ ሩሲያ በገበያው ላይ ተፎካካሪ ሆና መቀጠሏም ተገልጿል።
በሀብተሚካኤል ክፍሉ
#Ebc #Ebcdotstream #Naturalgas #Russia #China

❤30👏8
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለሥራ ጉብኝት ወደ ኢትዮጵያ የመጡትን የኬንያ ፕሬዚዳንት ዊልያም ሩቶን ተቀበሉ
***********
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለአንድ ቀን የሥራ ጉብኝት ወደ ኢትዮጵያ የመጡትን የኬንያ ፕሬዚዳንት ዊልያም ሩቶን ተቀብለዋል።
#PMOEthiopia

❤43👍16🔥8👏3🤣1
የፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ ጉብኝት በሁለቱ ሀገሮቻችን መካከል ያለውን ጥልቅ ግንኙነት የሚያንፀባርቅ ነው፡- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
****************
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከኬንያው ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ ጋር ዛሬ በአዲስ አበባ ውይይት አድርገዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፤ ዛሬ የኬንያ ፕሬዚደንት ዊልያም ሳሞይ ሩቶን ለአንድ ቀን የሥራ ጉብኝት መቀበላቸውን ገልጸዋል።
ጉብኝቱ በሁለቱ ሀገሮቻችን መካከል ያለውን ጥልቅ፣ ታሪካዊ እና ወንድማዊ ግንኙነት የሚያንፀባርቅ ነው ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ።
በውይይቱ የሁለትዮሽ ግንኙነቱ በሚጠናከርበት ሁኔታ ላይ እንዲሁም በአፍሪካ ቀንድ ሰላም እና ፀጥታ ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን አመልክተዋል።
ይህም በሰላም እና መረጋጋት፣ ብሎም በአፍሪካ መር መፍትሔዎች ላይ ያለንን የወል ጽኑ አቋም የሚያሳይ ነበር ሲሉ ገልጸዋል።

❤25👍12🔥2🙏1
የኢቢሲ ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ አብዱራህማን ሩቤ ሥርዓተ ቀብር ተፈፀመ
******
የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ የነበሩት የአቶ አብዱራህማን ሩቤ ሥርዓተ ቀብር በኮልፌ የሙስሊም መካነ መቃብር ተፈፅሟል።
አቶ አብዱራህማን ሩቤ ባደረባቸው ሕመም ምክንያት በሕክምና ሲረዱ ቆይተው በተወለዱ በ40 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።
አቶ አብዱራህማን በኢቢሲ እና በኦቢኤን ከሪፖርተርነት እስከ ከፍተኛ አመራርነት ያገለገሉ ሲሆን ሕይወታቸው እስካለፈበት ቀን ድረስም የኢቢሲ ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው እያገለገሉ ነበር፡፡
አቶ አብዱራህማን ሩቤ ባለትዳር እና የሦስት ልጆች አባት ነበሩ፡፡
በቀብር ሥነ ሥርዓቱ ላይ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ ቤተሰቦቻቸው፣ ታዋቂ ግለሰቦች፣ የሥራ ባልደረቦቻቸው እና ወዳጅ ዘመዶቻቸው ተገኝተዋል።
የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን በምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚው አቶ አብዱራህማን ሩቤ ኅልፈት የተሰማውን ኀዘን እየገለጸ ለቤተሰቦቻቸው፣ ለወዳጆቻቸው እና ለሥራ ባልደረቦቻቸው መፅናናትን ይመኛል።
በላሉ ኢታላ

😢21❤20