EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation) – Telegram
EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)
138K subscribers
38.2K photos
458 videos
80 files
13.1K links
EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation) @etvafaanoromoo1
@ETVkidschannel
@EBCWORLD1
@etventertainment1
Download Telegram
ሩሲያ ወደ ቻይና በምትልከው የተፈጥሮ ጋዝ አዲስ ክብረወሰን አስመዘገበች
********************

ሩሲያ ወደ ቻይና ከፍተኛ መጠን ያለው የተፈጥሮ ጋዝ በመላክ አዲስ ክብረወሰን አስመዝግባለች።

ሩሲያ ወደ ቻይና የምትልከው ፈሳሽ የተፈጥሮ ጋዝ በ2024 ከነበረው ቁጥር በሁለት እጥፍ በመብለጥ በ2025 1.6 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን በመድረሱ አዲስ ክብረወሰን ሆኖ መመዝገቡ ተነግሯል።

ከዚህ ቀደም አውስትራሊያ እና ኳታር ለቻይና ዋነኛ የተፈጥሮ ጋዝ አቅራቢ ሀገራት እንደነበሩ ተመላክቷል፡፡

ነገር ግን ሩሲያ በ2025 በነበረው የተፈጥሮ ጋዝ አቅርቦቷ አሁን ላይ አውስትራሊያን በመብለጥ እና ከኳታር በመቀጠል ሁለተኛዋ ለቻይና ትልቅ የተፈጥሮ ጋዝ አቅራቢ ሆናለች ነው የተባለው።

በቻይና እና አሜሪካ መካከል በተፈጠረው የንግድ ፍጥጫ ምክንያት ተቀዛቅዞ የነበረው የቻይና የተፈጥሮ ጋዝ ፍላጎት ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ መነቃቃት የታየበት ሲሆን የሩሲያ የጋዝ አቅራቢ ድርጅቶችም ምርታቸውን በማቅረብ ላይ እንደሚገኙ ስፑትኒክ ዘግቧል።

የአውሮፓ ኅብረት ከሩሲያ በሚገባው የጋዝ ምርት ላይ ማዕቀብ ቢጥልም ሩሲያ ወደ ቻይና የምትልከው የጋዝ ምርት በእጥፍ በማደጉ ሩሲያ በገበያው ላይ ተፎካካሪ ሆና መቀጠሏም ተገልጿል።

በሀብተሚካኤል ክፍሉ

#Ebc #Ebcdotstream #Naturalgas #Russia #China
26👏7
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለሥራ ጉብኝት ወደ ኢትዮጵያ የመጡትን የኬንያ ፕሬዚዳንት ዊልያም ሩቶን ተቀበሉ
***********

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለአንድ ቀን የሥራ ጉብኝት ወደ ኢትዮጵያ የመጡትን የኬንያ ፕሬዚዳንት ዊልያም ሩቶን ተቀብለዋል።
#PMOEthiopia
41👍16🔥7👏3🤣1
የፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ ጉብኝት በሁለቱ ሀገሮቻችን መካከል ያለውን ጥልቅ ግንኙነት የሚያንፀባርቅ ነው፡- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
****************

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከኬንያው ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ ጋር ዛሬ በአዲስ አበባ ውይይት አድርገዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፤ ዛሬ የኬንያ ፕሬዚደንት ዊልያም ሳሞይ ሩቶን ለአንድ ቀን የሥራ ጉብኝት መቀበላቸውን ገልጸዋል።

ጉብኝቱ በሁለቱ ሀገሮቻችን መካከል ያለውን ጥልቅ፣ ታሪካዊ እና ወንድማዊ ግንኙነት የሚያንፀባርቅ ነው ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ።

በውይይቱ የሁለትዮሽ ግንኙነቱ በሚጠናከርበት ሁኔታ ላይ እንዲሁም በአፍሪካ ቀንድ ሰላም እና ፀጥታ ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን አመልክተዋል።

ይህም በሰላም እና መረጋጋት፣ ብሎም በአፍሪካ መር መፍትሔዎች ላይ ያለንን የወል ጽኑ አቋም የሚያሳይ ነበር ሲሉ ገልጸዋል።
23👍11🔥2
የኢቢሲ ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ አብዱራህማን ሩቤ ሥርዓተ ቀብር ተፈፀመ
******

የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ የነበሩት የአቶ አብዱራህማን ሩቤ ሥርዓተ ቀብር በኮልፌ የሙስሊም መካነ መቃብር ተፈፅሟል።

አቶ አብዱራህማን ሩቤ ባደረባቸው ሕመም ምክንያት በሕክምና ሲረዱ ቆይተው በተወለዱ በ40 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።

አቶ አብዱራህማን በኢቢሲ እና በኦቢኤን ከሪፖርተርነት እስከ ከፍተኛ አመራርነት ያገለገሉ ሲሆን ሕይወታቸው እስካለፈበት ቀን ድረስም የኢቢሲ ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው እያገለገሉ ነበር፡፡

አቶ አብዱራህማን ሩቤ ባለትዳር እና የሦስት ልጆች አባት ነበሩ፡፡

በቀብር ሥነ ሥርዓቱ ላይ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ ቤተሰቦቻቸው፣ ታዋቂ ግለሰቦች፣ የሥራ ባልደረቦቻቸው እና ወዳጅ ዘመዶቻቸው ተገኝተዋል።

የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን በምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚው አቶ አብዱራህማን ሩቤ ኅልፈት የተሰማውን ኀዘን እየገለጸ ለቤተሰቦቻቸው፣ ለወዳጆቻቸው እና ለሥራ ባልደረቦቻቸው መፅናናትን ይመኛል።

በላሉ ኢታላ
18😢18
ኢትዮጵያ እና አሜሪካ በጤናው ዘርፍ በአጋርነት መሥራት የሚያስችል የ1.6 ቢሊዮን ዶላር ስምምነት ተፈራረሙ
**************

የኢትዮጵያ እና የአሜሪካ መንግሥታት በጤናው ዘርፍ ያላቸውን ትብብር የሚያጠናክር የ 1 ነጥብ 6 ቢሊዮን ዶላር የጤና ትብብር ማዕቀፍ ተፈራርመዋል።

የትብብር ስምምነቱ በዘላቂ ልማት፣ በጋራ ኢንቨስትመንትና የጤና ሥርዓትን በማጠናከር ላይ ያተኮረ የኢትዮ-አሜሪካ አዲስ የጤና አጋርነት ምዕራፍ መሆኑ ተመላክቷል።

የትብብር ስምምነቱን የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሽዴ፣ የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ እና በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ ፈርመውታል።

የኢትዮጵያና የአሜሪካ የጤና የአጋርነት ስምምነት ለ5 ዓመታት የሚቆይ ሲሆን፣ የትብብር ማዕቀፉ በኤችአይቪ/ኤድስ፣ ቲቢ፣ ወባ፣ የእናቶች እና ህጻናት ጤና፣ የወረርሽኝ ምላሽ እና ዝግጁነትን የነበረውን ድጋፍ ለማስቀጠል እንዲሁም የኢትዮጵያን የጤና ሥርዓት የበለጠ ለማጠናከር ድጋፍ ለማድረግ ያቀደ ነው።

በኤዶሚያስ ንጉሴ
35👍7🔥3👏2
ማስታወቂያ
*******

የልጅነት ሕልምዎን እና የወጣትነት አላማዎ የተሳካ እንዲሆን የሲንቄ ባንክ የአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች የብድር አገልግሎት በመጠቀም የኖሩለትን ራዕይ እውን ያድርጉ።

#Siinqee_Bank    #Baankii_Siinqee    #ሲንቄ_ባንክ  #Siinqee_Digital #Siinqee_Ihsan   #Financial_Inclusion  #EMPOWERED_TOGETHER
12
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ከሚሊዮኖች ጋር ትውውቅ የሚፈጥሩበትን ልዩ አጋጣሚ ይጠቀሙ
************

በኢቢሲ አዝናኝ የገና በዓል ዝግጅቶቻችን ላይ ምርትና አገልግሎትዎን ያስተዋውቁ።

ለበለጠ መረጃ ወደ

📲 0968979797
📲 0947959595

ይደውሉ
6