የኢቢሲ ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ አብዱራህማን ሩቤ ሥርዓተ ቀብር ተፈፀመ
******
የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ የነበሩት የአቶ አብዱራህማን ሩቤ ሥርዓተ ቀብር በኮልፌ የሙስሊም መካነ መቃብር ተፈፅሟል።
አቶ አብዱራህማን ሩቤ ባደረባቸው ሕመም ምክንያት በሕክምና ሲረዱ ቆይተው በተወለዱ በ40 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።
አቶ አብዱራህማን በኢቢሲ እና በኦቢኤን ከሪፖርተርነት እስከ ከፍተኛ አመራርነት ያገለገሉ ሲሆን ሕይወታቸው እስካለፈበት ቀን ድረስም የኢቢሲ ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው እያገለገሉ ነበር፡፡
አቶ አብዱራህማን ሩቤ ባለትዳር እና የሦስት ልጆች አባት ነበሩ፡፡
በቀብር ሥነ ሥርዓቱ ላይ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ ቤተሰቦቻቸው፣ ታዋቂ ግለሰቦች፣ የሥራ ባልደረቦቻቸው እና ወዳጅ ዘመዶቻቸው ተገኝተዋል።
የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን በምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚው አቶ አብዱራህማን ሩቤ ኅልፈት የተሰማውን ኀዘን እየገለጸ ለቤተሰቦቻቸው፣ ለወዳጆቻቸው እና ለሥራ ባልደረቦቻቸው መፅናናትን ይመኛል።
በላሉ ኢታላ

😢21❤20
ኢትዮጵያ እና አሜሪካ በጤናው ዘርፍ በአጋርነት መሥራት የሚያስችል የ1.6 ቢሊዮን ዶላር ስምምነት ተፈራረሙ
**************
የኢትዮጵያ እና የአሜሪካ መንግሥታት በጤናው ዘርፍ ያላቸውን ትብብር የሚያጠናክር የ 1 ነጥብ 6 ቢሊዮን ዶላር የጤና ትብብር ማዕቀፍ ተፈራርመዋል።
የትብብር ስምምነቱ በዘላቂ ልማት፣ በጋራ ኢንቨስትመንትና የጤና ሥርዓትን በማጠናከር ላይ ያተኮረ የኢትዮ-አሜሪካ አዲስ የጤና አጋርነት ምዕራፍ መሆኑ ተመላክቷል።
የትብብር ስምምነቱን የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሽዴ፣ የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ እና በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ ፈርመውታል።
የኢትዮጵያና የአሜሪካ የጤና የአጋርነት ስምምነት ለ5 ዓመታት የሚቆይ ሲሆን፣ የትብብር ማዕቀፉ በኤችአይቪ/ኤድስ፣ ቲቢ፣ ወባ፣ የእናቶች እና ህጻናት ጤና፣ የወረርሽኝ ምላሽ እና ዝግጁነትን የነበረውን ድጋፍ ለማስቀጠል እንዲሁም የኢትዮጵያን የጤና ሥርዓት የበለጠ ለማጠናከር ድጋፍ ለማድረግ ያቀደ ነው።
በኤዶሚያስ ንጉሴ

❤39👍13🔥3👏3
ማስታወቂያ
*******
የልጅነት ሕልምዎን እና የወጣትነት አላማዎ የተሳካ እንዲሆን የሲንቄ ባንክ የአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች የብድር አገልግሎት በመጠቀም የኖሩለትን ራዕይ እውን ያድርጉ።
#Siinqee_Bank #Baankii_Siinqee #ሲንቄ_ባንክ #Siinqee_Digital #Siinqee_Ihsan #Financial_Inclusion #EMPOWERED_TOGETHER

❤15
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ከሚሊዮኖች ጋር ትውውቅ የሚፈጥሩበትን ልዩ አጋጣሚ ይጠቀሙ
************
በኢቢሲ አዝናኝ የገና በዓል ዝግጅቶቻችን ላይ ምርትና አገልግሎትዎን ያስተዋውቁ።
ለበለጠ መረጃ ወደ
📲 0968979797
📲 0947959595
ይደውሉ

❤7
ሀድያ ሆሳዕና ወላይታ ድቻን 2 ለ 1 አሸነፈ
******************
በሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 11ኛ ሳምንት መርኃ ግብር ሀድያ ሆሳዕና ወላይታ ድቻን 2 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፏል።
በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩንቨርስቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ የሀድያ ሆሳዕናን የማሸነፊያ ግቦች እዮብ አለማየሁ እና ሄኖክ አርፍጮ ከመረብ አሳርፈዋል፡፡
ወላይታ ድቻን ከሽንፈት ያልታደገች ብቸኛ ግብ ደግሞ መልካሙ ቦጋለ በፍጹም ቅጣት ምት አስቆጥሯል።

❤22🤣5👏4🙏2👍1
ከህብረተሰቡ ባህል፣ ሞራልና እሴት ተቃራኒ የሆኑ መልዕክቶችን በማህበራዊ ሚዲያ ሲያሰራጭ የነበረ ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ
************
ከህብረተሰቡ ባህል፣ ሞራልና እሴት ተቃራኒ የሆኑ መልዕክቶችን በማህበራዊ ሚዲያ ሲያሰራጭ የነበረን ግለሰብ በቁጥጥር ስር ማዋሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡
በማህበራዊ ሚዲያ የሚተላለፉ መልዕክቶች ተደራሽነታቸው የበዛ በመሆኑ በትውልዱ ላይ የሚያሳድሩት አዎንታዊም ሆነ አሉታዊ ተፅዕኖ ከፍተኛ መሆኑን የገለጸው የአዲስ አበባ ፖሊስ፤ ማህበራዊ ሚዲያን በአግባብና በኃላፊነት መንፈስ ከተጠቀሙበት ትውልድን በስነ ምግባር ለማነፅና ለማፅናት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው አመልክቷል፡፡
ነገር ግን ከዚህ በተፃራሪ የተሰለፉ አንዳንድ ግለሰቦች ለማየትና ለመስማት አጸያፊ የሆኑ የማህበራዊ ሚዲያ ይዘቶችን ሲሰሩ እንደሚታዩ ፖሊስ ገልጿል፡፡
በዚህም መሰረት ከህብረተሰቡ ባህል፣ ሞራልና እሴት ተቃራኒ የሆኑ መልዕክቶችን በማህበራዊ ሚዲያ ሲያሰራጭ ከነበሩ ግለሰቦች አንዱ የሆነውን ነዋሪነቱ በን/ስ/ላፍቶ ክ/ከተማ ወረዳ 6 የሚገኝ ናትናኤል ባደግ ገብሬ የተባለን ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር መዋሉን ነው የአዲስ አበባ ፖሊስ የገለፀው፡፡
ተጠርጣሪው የማህበራዊ ሚዲያን በተለይም ዩቱዩብ እና ቲክቶክን በመጠቀም በንግግር ልቅ ፆታዊ ግንኙነትን የሚያበረታታና የሚያስፋፋ አፀያፊ መልዕክቶችን ሲያሰራጭ መቆየቱ ተጠቁሟል።
ተጠርጣሪው በተለምዶአዊው ንግግር ሊገለፁ የማይችሉ አስፀያፊ ቃላትን በመጠቀም በትውልዱ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ሲያሳድር እንደነበርና መሰል ይዘቶችን በተደጋጋሚ ጊዜ በመስራት በማህበራዊ ሚዲያ በመጠቀም ሲያሰራጭ እንደነበርም ፖሊስ አብራርቷል፡፡
ፖሊስ በቁጥጥር ስር በዋለው ናትናኤል ባደግ ላይ ምርመራ መጀመሩን ጠቅሷል።

👍49❤30👏19🔥1
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለመላው ዓለም ክርስቲያኖች የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላለፉ
***********
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለፈረንጆቹ የገና በዓል የእኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፍዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒሰትሩ በዓሉን አስመልክተው በማህበራዊ ሚድያ ባስተላለፉት መልዕክት " መልካም የገና በዓል ለዓለም አቀፍ ቤተሰቦቻችን፡፡
ይህ ወቅት የሚያስታውሰን መልካምነት ድንበር ተሻጋሪ መሆኑን እና ተስፋን በጋራ መገንባት እንደምንችል ነው" ብለዋል።
#ebcdotstream #EBC #AbiyAhmed #xmas2025

❤43👍10🤣5👏1
"የኢትዮጵያ የኃይል መሠረተ ልማት በመስፋቱ ትላልቅ ኢንዱስትሪዎች ወደ ሀገር ቤት ገብተዋል"፦ ፍሰሃ ይታገሱ (ዶ/ር)
**************
ታላቁ ኅዳሴ ግድብን ጨምሮ የመደመር መንግስት ባለፉት ዓመታት የኃይል መሠረተ ልማትን በማስፋቱ ምክንያት ትላልቅ ኢንዱስትሪዎች ወደ ሀገር ቤት ገብተዋል ሲሉ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሰሃ ይታገሱ (ዶ/ር) ተናገሩ።
በኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት አዘጋጅነት የሚካሄደው ስለ ሀገር የውይይት መድረክ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት በጉባ እየተካሄደ ነው።
ኅዳሴ ግድብ ለኢንዱስትሪ ዕድገት ያለውን ፋይዳ በተመለከተ ማብራሪያ የሰጡት የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሰሃ ይታገሱ (ዶ/ር) የኢንዱስትሪ ልማት ከሀይል ውጪ የሚታሰብ አለመሆኑን ተናግረዋል።
በኢትዮጵያ ትርጉም ያለው የኢንዱስትሪ ልማት ለማምጣት የተሰሩ ስራዎችን የጠቆሙት ዋና ሥራ አስፈጻሚው ባለፈው 1 ዓመት ብቻ ግዙፍ ኢንቨስትመንቶችን መሳብ መቻሉን ጠቁመዋል።
ይህንን ለማስቀጠልና የኢትዮጵያን የአፍሪካ የብልጽግና ተምሳሌት ጉዞ እውን ለማድረግ ከፍተኛ ኃይልና ከፍተኛ ቴክኖሎጂ የሚጠቀሙ ብዙ ኅዳሴ ግድቦችን የመሰሉ ፕሮጀክቶች ያስፈልጉናልም ብለዋል።
በአሸናፊ እንዳለ
#ebcdotstream #ኢትዮጵያ #ጉባ #ኢንዱስትሪ

❤31👏6👍5