የአንጋፋ ሠዓሊያን ስራዎች የሚቀርብበት "የኢትዮጵያ ቀለም 3"የሥዕል አውድርዕይ ዛሬ ይከፈታል
የስምንት አንጋፋ ሠዓሊያን የሥዕል ስራዎች የሚቀርብበት "የኢትዮጵያ ቀለም 3" የሥዕል አውደርዕይ ዛሬ ግንቦት 21 2016 ዓ.ም ከምሽቱ 12:00 ጀምሮ በፈንድቃ ባህል ማዕከል ውስጥ ለእይታ ይበቃል።
በዚህ የሥዕል አውደርዕይ ላይ ስራዎቻቸው የሚቀረብላችው ሠዓሊያን ወርቁ ጎሹ ፣ ባርባራ ጎሹ ፣ገብረክርስቶስ ሰለሞን ፤ዘሪሁን የትምጌታ ፤አሸናፊ ወለደየሱስ ፣ አይናለም ገ/ማርያም ፣ አክሊሉ መንግስቱ ናቸው።
የሥዕል አውድርዕዩ ከግንቦት 21 እስከ ሰኔ 5 2016 ዓ.ም ድረስ በፈንድቃ በእይታ ላይ ይቆያል ተብሏል።
ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1

ደራሲ ሔኖክ በቀለ "ሀገር ያጣ ሞት" ከተሰኘው መጽሐፌ ላይ በቤተልሔም ታፈስ ያለፍቃዴ ጽሑፍ ተወስዶብኛል ሲል ቅሬታውን አቀረበ
ደራሲ ሔኖክ በቀለ "ሀገር ያጣ ሞት" የተሰኘውን የመጀመሪያ መጽሐፉን በ2013 ዓ.ም ነው ለንባብ ያበቃው። በቀድሞ "ኤልቲቪ ሾው" አቅራቢነት የምናውቃት ቤተልሔም ታፈስ ደግሞ ከወራት በፊት "5 ጉዳይ" የተሰኘ መጽሐፏን ለንባብ አብቅታለች።
ደራሲ ሔኖክ በቀለ እንደሚለው ከሆነ "ከሀገር ያጣ ሞት መጽሐፌ ገጽ “132” ላይ ያለው አንቀጽ አንዲትም ቃል ሳይቀየር የአንቺ “5 ጉዳይ” በተሰኘ መጽሐፍ ገጽ 164 ላይ ተጽፏል" ሲል ደራሲው ተናግሯል።
ጸሐፊዋ ይህንን ስታደርግ ምንም አይነት የሌላ መጽሐፍ ሀሳብ መሆኑን አመላካች የሆነ ነገር ያልተጠቀመች እንደሆነ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ተመልክቷል ደራሲውም "መጠቀም ከፈለግሽም በቀላሉ በትምህርተ ጥቅስ አድርገሽ ምንጭ ጠቅሰሽ መጠቀም ትችይ ነበር። ይሄ የአዋቂ ተግባር እንጂ መዋረድ አይደለም። እንዲህ ዓይነቱ ነገር የሥራሽንም የሰብዕናሽንም ንጽሕና ያጎድፋል።" ሲል ቅሬታውን አቅርቧል።
ደራሲው"ከዚህም በተጨማሪ መጽሐፉ ከተጻፈለት አጀንዳ ውጪ ለፖለቲካዊ ዲስኮርስ ጠምዝዞ መጠቀም የፈጠራ ሥራን ጠንቅቆ ያለመረዳት የዋኀነትና ድፍረት ነው። ..ሥራችንን አክብረንና ወደን ዋጋ እንከፍልበታለን። ለጥራቱና ለውበቱ በገንዘብ የማይታመን ዋጋ እናወጣለን። ማንም እንዳሻው ዘግኖና ከታትፎ ሊጠቀመው አይገባም። "ሲል ቅሬታውን ገልጿል።
ኤቨንት አዲስ ድረገፅ የ"5 ጉዳይ" ጽሐፊ ቤተልሔም ታፈሰ በዚህ ጉዳይ ምላሽ እንድትሰጠን ያደረገው ሙከራ ያልተሳካ ሲሆን ምላሽ ለመስጠት ፍቃደኛ በሆነች ጊዜ ሀሳቧን ለማስተናገድ በራችን ክፍት እንደሆነ ለማሳወቅ እንወዳለን።
📍ከላይ የተያያዘውን ፎቶ ይመለከቱ

ጋዜጠኛ መሠለ ገ/ህይወት ከዜናው ዓለም ወደ መዝናኛው ዓለም ሊሸጋገር ነው።
በዜና አንባቢነት የሚታወቀው አንጋፋው ጋዜጠኛ መሠለ ገ/ህይወት በመዝናኛው ዘርፍ ሊመጣ ነው።
ላለፉት 18 ዓመታት በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን በዜና አንባቢነት ሲያገለግል የቆየው መሠለ በቅርቡ "መሴ ሾዉ" የተሠኘ የምሽት መዝናኛ ፕሮግራም በአባይ ቲቪ እንደሚጀምር ታውቋል።
መሴ ሾዉ የተሠኘው የምሽት የመዝናኛ ፕሮግራም (late night show) የሠርጌለታ፣ የሙዚቀኞች ብፌ፣ የእንግዳ ቆይታ እንዲሁም እግሬ ሲደርስ የተሰኙ አዝናኝ መሠናዶዎች የተካተቱበት ነው።
ፕሮግራሙ በየሣምንቱ ቅዳሜ ምሽት በአባይ ቲቪ ከመተላለፉ ባሻገር መሴ ሾው በሚል ስያሜ በተከፈተ በራሱ የዩቲዩብ ቻናል ለተመልካች የሚደርስ ይሆናል።
ጋዜጠኛ መሠለ ከሁለት ዓመታት በፊት የመልካሙ ተበጀንና የንዋይ ደበበን ዘፈኖች በመጫወት የመዝናኛ ተሥጥዖውን ማሣየቱና ተመልካቾችን ማሥደመሙ ይታወሳል።
መረጃው የኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 ነው።

Event Addis Media
ደራሲ ሔኖክ በቀለ "ሀገር ያጣ ሞት" ከተሰኘው መጽሐፌ ላይ በቤተልሔም ታፈስ ያለፍቃዴ ጽሑፍ ተወስዶብኛል ሲል ቅሬታውን አቀረበ ደራሲ ሔኖክ በቀለ "ሀገር ያጣ ሞት" የተሰኘውን የመጀመሪያ መጽሐፉን በ2013 ዓ.ም ነው ለንባብ ያበቃው። በቀድሞ "ኤልቲቪ ሾው" አቅራቢነት የምናውቃት ቤተልሔም ታፈስ ደግሞ ከወራት በፊት "5 ጉዳይ" የተሰኘ መጽሐፏን ለንባብ አብቅታለች። ደራሲ ሔኖክ በቀለ እንደሚለው ከሆነ…
የቤተልሔም ታፈሰ ምላሽ እና ይቅርታ
ደራሲ ሔኖክ በቀለ "ሀገር ያጣ ሞት" ከተሰኘው መጽሐፌ ላይ በቤተልሔም ታፈሰ ያለፍቃዴ ጽሑፍ ተወስዶብኛል ሲል ላቀረበው ቅሬታ የ"5 ጉዳይ" መጽሐፍ ጻፊ ቤተልሔም ታፈሰ ምላሽ እና ይቅርታ ለደራሲው እንዳቀረበች ኤቨንት አዲስ ድረገጽ ተመልክቷል።
የ"5 ጉዳይ" መጽሐፍ ጻፊ ቤተልሔም ታፈሰ የሰጠችው ምላሽ እና ይቅርታ እንደሚከተለው ይቀርባል።
"ታላቅ ይቅርታ "5 ጉዳይ" በተሰኘው መፅሀፌ ላይ ሰፊ ሽፋን ያገኘው "የባሮ ቱምሳ ገዳይ ማነው?" የሚለው ክፍል ብዙ የደበዘዙ እና የተሸፈኑ ታሪኮችን የገለጠ እና የእውነት ክር ብትቀጥንም እንደማትበጠስ ያሳየ በብዙ ልፋት እና ድካም የተዘጋጀ ስራ ነው::
ሆኖም ግን ይህ በታሪክ የምርምር ሰነድነት ደረጃ ሊጠቀስ የሚችል ፅሁፍ፤ ስነፅሁፋዊ ለዛ እንዲኖረው በማሰብ የመግቢያ ክፍል ሲሰናዳለት የመፅሀፌ አርታዒ አንድ አንቀፅ ቃል በቃል እና እንደወረደ ከደራሲ ሄኖክ በቀለ "ሀገር ያጣ ሞት" የተሰኘ መፅሀፍ ስረአተ ነጥብም ሆነ የህዳግ ማስታወሻ ሳይጠቀም እንዳለ ገልብጦ ተጠቅሟል::
ይህ ተግባር መፈፀሙን ያወቅሁት ዛሬ ማለዳ የወንድም ሄኖክን ቅሬታ ካነበብኩ በኃላ ነው:: በተፈፀመው ጉዳይ በተለይም ደግሞ እንደ አንድ ፀሀፊ ይህ ጉዳይ ምን ያህል አስከፊ መሆኑን ስለምረዳ ምንም እንኳን በስልክ ከሄኖክ ጋር ስለተፈጠረው ስህተት አስረድቼው የተግባባን ቢሆንም፤ ደራሲ ሄኖክን በአደባባይ ይቅርታ ማለት እፈልጋለሁ:: ከይቅርታ ባለፈም በቀጣይ ህትመት ላይ አንቀፁ በትምህርተ ጥቅስ ውስጥ ተቀምጦ በህዳግ ምንጩ ተጠቅሶ እንዲወጣ ለማድረግ ቃል እገባለሁ::
በድጋሚ ለተፈጠረው ስህተት በሙሉ ሀላፊነቱን ወስጄ አንባቢዎቼን በሙሉ ይቅርታ እጠይቃለሁ::"
@EventAddis1

የሐሙሰ መረጃዎች ደርሰዋል !
የሳምንቱ የመዝናኛ መረጃዎችን በአጫጭሩ እነሆ:
ተከታዩን ሊንክ https://shorturl.at/uZpnU በመነካት ብቻ የቻናሉን ስፔሻል የሐሙስ መረጃዎችን በድረገጻችን በጥሩ አቀራረብ ማንበብ ትችላላችሁ።
ማሳሰቢያ: የኤቨንት አዲስ ድረገጽ መረጃዎችን በእርሰዎ ሚዲያ ሲጠቀሙ እባክዎ በተገቢው መንገድ ምንጭ ይጠቀሱ።
የEventAddis/ሁነት አዲስ ማኅበራዊ ገፆቻችን:
Telegram:https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
Website: https://eventaddis.com
Facebook:https://facebook.com/groups/2009372275938661/
Facebook Page:https://www.facebook.com/profile.php?id=100083170462851&mibextid=ZbWKwL

የሳምንቱ የመጻሕፍት መረጃዎች (በአጭሩ )
📍መጽሐፍ
- የደራሲና ገጣሚ ምግባር ሲራጅ "እየዳነ ሄደ" መጽሐፍ ነገ አርብ ግንቦት 23 2016 ዓ.ም ከቀኑ 10:30 ጀምሮ አራት ኪሎ በሚገኘው ዋልያ መጻሕፍት ውስጥ ይመረቃል።በምርቃት ሥነሥርዓቱ ላይ ልዩ ልዩ ተጋባዥ እንግዶች የሥነጽሑፍ ስራዎቻቸውን ያቀርባሉ ተብሏል።
-በዶ/ር ወሰን መኮንን የተዘጋጀው "ዚድራር" መጽሐፍ የፊታችን ቅዳሜ ግንቦት 24 2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00 ጀምሮ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በብሔራዊ ቴአትር ይመረቃል።
- በጋዜጠኛ ዮሴፍ ዳሪዮስ የተተረጎመው "ባይተዋሩ ልዑል" የተሰኘው መጽሐፍ የፊታችን ቅዳሜ ግንቦት 24 2016 ዓ.ም ከቀኑ 9:00 ጀምሮ በብሔራዊ ቤተመጻሕፍትና ቤተመዛግብት አግልግሎት (ወመዘክር ) አዳራሽ ውስጥ ይመረቃል።በዕለቱም ደራሲ ኃይለመለኮት መዋዕል ፣ገጣሚ ሀብታሙ ማሞ ፣ ጋዜጠኛ ኃይለየሱስ መኮንን ጨምሮ ሌሎችም ባለሞያዎች ሀሳቦቻቸውን በመድረኩ ያጋራሉ ተብሏል።
-በናትናኤል ከበደ የተዘጋጀው "ዱባይ እንደምን ሰለጠነች?" የተሰኘ መጽሐፍ የፊታችን ቅዳሜ ግንቦት 24 2016 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ጀምሮ በኢሊሊ ሆቴል ውስጥ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ይመረቃል።
-የጋዜጠኛ ታምራት ኃይሉ "ዜሮ የስራ ልምድና ሌሎችም ወጎች" የተሰኘ መጽሐፍ የፊታችን ሰኞ ግንቦት 26 2016 ዓ.ም ከምሽቱ 11:ዐዐ ጀምሮ በግዮን ግሩቭ ጋርድን ውስጥ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ይመረቃል።
-የኤፍ ኤም አዲስ 97.1 የ24ኛው ዓመት የምስረታ በዓልን አስመልክቶ የተዘጋጀው "ለተሻለ ነገ እናንብብ"የተሰኘ የመጻሕፍት አውደርዕይ ከግንቦት 22 እስከ 27 2016 ዓ.ም ሸጎሌ በሚገኘው በአዲሱ የኢቢሲ ሚዲያ ኮምፕሌክስ ግቢ ውስጥ እየተካሄደ ይገኛል።
ለተጨማሪው: @EventAddis1

ልዑል እና ሚኪ የተጣመሩበት "ልዑል" ኮንሰርት
ድምጻዊ ልዑል ሲሳይ እና ድምጻዊ ሚካኤል በላይነህ የተጣመሩበት "ልዑል" ኮንሰርት የፊታችን ሰኔ 1 2016 ዓ.ም በሚሊኒየም አዳራሽ ይካሄዳል። ከሁለቱ ድምጻዊያን በተጨማሪም ድምጻዊ ሳሚ ዳን በኮንሰርቱ ስራውን ያቀርባል ተብሏል ።
ወጣቱ ድምጻዊ ልዑል ሲሳይ ከወራት በፊት "ልዑል" የተሰኘ አልበም ለአድማጮች ያደረሰ ሲሆን በሌላ በኩል ድምጻዊ ሚካኤል በላይነህ ከዓመታት በኃላ በቅርቡ የሙዚቃ አልበሙን ለአድማጮች ያደርሳል ተብሏል።

የድምፃዊት እግቱ ጉዳይ ከምን ደረሰ?
ድምፃዊት ትዕግስት ኃይሉ (እግቱ) የደረሰባትን በፋስት መረጃ ካደረስን በኋላ በርካታ ጥያቄዎች ተነስቷል። ከአዲስ አበባ ከተማ መስተዳደር ከትራንስፖርት ቢሮ፣ ከባህል እና ቱሪዝም ቢሮ መረጃውን ከተመለከቱ በኋላ ነገሩን ለማጣራት ተደውሎልን ነበር ፈጣን እርምጃ ለመውሰድ ላደረጋችሁት ተነሳሽነት ፋስት መረጃ ከልብ ያመሰግናል።
እግቱ ምን ደረጃ እንደደረሰች ፋስት መረጃ ድምፃዊቷን ለማውራት ሞክረን ነበር ከፈረስ ጋር እየተነጋገርኩ ነው የደረስኩበትን ነገር አሳውቃለሁ ብላን ነበር።
አሁን ማምሻውን የደረሰችበትን ነገር አሳውቃናለች።
ሙከራውን አምልጣ ቤት እንደገባች መጀመሪያ ወደ ፈረስ ትራንስፖርት ደውላ የደረሰባን ስትነግራቸው ስትሳፈር ኪሎሜትር ስላላስጀመረች ኤቪደንስ ስለሌለ ነገሩን አክብዶታል ብላለች። (መጀመሪያ ከቤት ሲወስዳት በፈረስ ነበር ደውላ የጠራችው ስትመለስ ግን አላስጀመረችም ነበር።)
ከዛ በኋላስ ምን ተፈጠረ?
ፈረስ ትራንስፖርት እና ድምፃዊቷ በአሁኑ ወቅት በመነጋገር አሽከርካሪው ከስራው እንደታገደ እግቱ ለፋስት መረጃ ገልፃለች፣ አሽከርካሪውም ደውሎ እንዳወሩ እና መጀመሪያ ማመን አልፈለገም ነበር ጉዳዩ ሲሪየስ መሆኑን ሲያውቅ ይቅርታ ጠይቆኛል ብላለች።
እኔ ዋና አላማዬ ከእኔ ስህተት ብዙ ሰው እንዲማር ነበር ይፋ ያደረኩት ብላለች። ኮሜንቶቹን በተመለከተ እኔን በመተባበር እንኳን አተረፈሽ ያሉ በርካታ ሰዎች ከልብ አመስግናለሁ። እኔ አሁን በጣም ደህና ነኝ ብላለች።
በጣም የሚያሳዝን ከሰው የማይጠበቅ ሰው እንዴት ሰው ላይ እንደዚህ ይመኛል የሚያስብሉ ኮሜንቶችን ተመልክቻለሁ፣ ሌሎች ሰዎች የደረሰባቸውን ወጥተው እንዳይናገሩ የሚያደርግ ነው፣ በራቸውን የዘጉ ብዙ ነገር የሆኑ አሉ ለእነሱ እንደዚህ መባሉ ጥሩ አይደለም። እኔ ላይ ምንም ለውጥ አያመጣም በማለት አስተያየት ሰጪዎችን በተመለከተ ሃሳቧን ተናግራለች።
📍መረጃው የፋስት መረጃ ነው

የሳምንቱን የሙዚቃ ሰሞነኛ መረጃዎች ( በአጭሩ )
📍ሙዚቃ
- ድምጻዊ ልዑል ሲሳይ እና ድምጻዊ ሚካኤል በላይነህ የተጣመሩበት "ልዑል" ኮንሰርት የፊታችን ሰኔ 1 2016 ዓ.ም በሚሊኒየም አዳራሽ ይካሄዳል። ከሁለቱ ድምጻዊያን በተጨማሪም ድምጻዊ ሳሚ ዳን በኮንሰርቱ ስራውን ያቀርባል ተብሏል።
-የድምጻዊ ጉቱ አበራ "lyolee" የተሰኘ የኦሮምኛ ነጠላ ሙዚቃ ቪዲዮ ዛሬ አርብ ግንቦት 23 2016 ዓ.ም በድምጻዊው የዩቲዩብ ቻናል ይለቀቃል። የሙዚቃው ግጥም እና ዜማ በራሱ በድምጻዊው ጉቱ አበራ ተሰርቷል።
-የወጣቷ ድምፃዊት አዲስ ጌራ "መስከረሜ" የተሰኘ አዲስ ነጠላ ሙዚቃዋ ዛሬ አርብ ግንቦት 23 አርብ ማታ 2016 ዓ.ም በአዲስ ጌራ ዩቲውብ ቻናል እና ዓለምአቀፍ የሙዚቃ መተግበሪያዎች ላይ ይለቀቃል። የሙዚቃው ግጥምና ዜማው የአዲስ ጌራ እና የህዝብ ሲሆን ሙዚቃ ቅንብሩን አብርሀም ኪዳኔ ሲሰራው ሙሳ ማቲ ሚክስና ማስተር አድርጎታል ፤ ልዋም መሀሪ በቤዝ ጊታር ፣ ዘሪሁን በለጠ በሳክስፎን ተሳትፈውበታል።
-የድምጻዊ ወንዲ ማክ አዲስ አልበም በቅርቡ ለአድማጮች ይደርሳል። ድምፃዊ ወንደሰን መኮንን በመድረክ ስሙ (ወንዲ ማክ) በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገፁም "ፈጣሪ ፈቅዶ እነሆ በአዲስ አልበም መጥተናል በቅርብ ቀን ይጠብቁን" ብሏል።
-የሮፍናን ኑሪ "ሮፍናን ማስተር ክላስ" በቅርቡ በሐዋሳ ከተማ ይካሄዳል። ይህ ዝግጅት ሙዚቀኛው የሙዚቃ ዕውቀቱን መሰረት አድርጎ ከባለሙያ ስነምግባር እስከ የራስን ብራንድ ፈጠራ ድረስ ያለውን ልምድ የሚያካፍልበት ነው።
-አንጋፋዋ ድምጻዊት ማሪቱ ለገሠ ነገ ግንቦት 24 2016 ዓ.ም በቶቶት የባህል ምግብ አዳራሽ ከምሽቱ 1:00 ጀምሮ የሙዚቃ ስራዋን ታቀርባለች።
📍መረጃውን ሲጠቀሙ ምንጭ ይጠቀሱ !

5ኛው ዙር የተስፋ አዲስ ቤተሰቦች የደም ልገሳ
5ኛው ዙር የተስፋ አዲስ ቤተሰቦች የደም ልገሳ መርሃግብር ከተለያዩ ተባባሪ አካላት ጋር በመሆን በሀገራችን በ12 ከተሞች በዚህ ሳምንት መጨረሻ ግንቦት 24 እና 25 2016 ዓ.ም ይካሄዳል።
እነዚህም ከተሞች አርባምንጭ ፣ጎንደር ፣አዳማ ፣መቀሌ ፣ሐዋሳ ፣ጅማ ፣ባህርዳር ፣ድሬዳዋ ፣ጂንካ ፣ሀላባ ፣ሐረር ፣እና መዲናችን አዲስ አበባ ናቸው።
የፕሮግራሙ አስተባባሪ ማስተዋል እያሱ "ከተጠቀሱት ከተሞች በተጨማሪ በሌሎችም ከተሞች ያሉ በጎ ፍቃደኞች ወደ ደም ባንኮች ጎራ ብለው በዕለቱ አብረው ደም ቢለግሱ ደስ ይለናል" ስትል ለኤቨንት አዲስ ድረገፅ ተናግራለች።
በተጨማሪም" ኑ በደማች አዲስ ታሪክ እንስራ። በሚተካው ደም የማይተካውን የሰው ልጅ ህይወት እናድን። ለካንሰር ታማሚ ህፃናት የነገን የማየት ተስፋ ምክንያት እንሁን ።" ብለዋል አዘጋጆቹ ።

የሳምንቱ ጥበባዊ ውይይቶችን (በአጭሩ )
📍ጥበባዊ ውይይቶች
- በዋልያ መጻህፍት የሚዘጋጀው ከደራስያን ጋር የመጨዋወት እና መጽሐፍ የማስፈረም ልዩ ሥነሥርዓት በዚህ ሳምንት "በኢትዮጵያ የውርስ ሕግ መሰረት ሀሳቦች " የተሰኘ መጽሐፍ ላይ ነገ ቅዳሜ ግንቦት 24 2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00 ጀምሮ በዋልያ መጻሕፍት ውይይት ይካሄዳል።በዕለቱም የሕግ ባለሞያው ዳዊት በዛብህ ያወያያል።
- በዘርዓያዕቆብ የፍልስፍና ት/ቤት በየሳምንቱ የሚዘጋጀው የሀሳብ ውይይት በዚህም ሳምንት "ነገረ እኩይ" የተሰኘ ርዕስ መርጧል ይህም ውይይት ቅዳሜ ግንቦት 27 2016 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ጀምሮ 5 ኪሎ በሚገኘው አፄ ናኦድ ት/ቤት ግቢ ውስጥ ይካሄዳል።"ነገረ እኩይ"በሚል ርዕስ በዮናስ ዘውዴ መነሻ ሀሳብ ይቀርባል ተብሏል።
-የብራና ጁፒተር የንባብ ቡድን ነገ ቅዳሜ ግንቦት 24 2016 ዓ.ም በዶ/ር መላኩ አዳል "ለሉሲ ሀገር ሰዎች" መጽሐፍ ላይ ውይይት ያካሄዳል። ይህ ውይይት ከ9:45 እስከ 12:00 ካዛንቺስ በሚገኘው ጁፒተር ሆቴል ውስጥ ይካሄዳል።
-በ"አስተውሎት" ፊልም ላይ ነገ ቅዳሜ ግንቦት 24 2016 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ጀምሮ በኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ውስጥ ሙያዊ ውይይት ይካሄዳል። በፊልሙ ላይ ሰውመሆን ይስማው ፣ ቴዎድሮስ አበበ ፣ ሚካኤል ሚሊዮን ሀሳብ አቅራቢ ባለሞያዎች ናቸው።
- "ስብሐቲዝም" የሀሳብ ውይይት የፊታችን እሁድ ግንቦት 25 2016 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ጀምሮ በኢትዮጵያ ቤተመዛግብት እና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት(ወመዘክር) አዳራሽ ውስጥ ይካሄዳል። በዚህኛው ዙር "ስለ አርምሞ እንነጋገር " የተሰኘ ርዕሰ ጉዳይ የተመረጠ ሲሆን በኤልያስ አእምሮ (ዶ/ር) መነሻ ሀሳብ ይቀርባል ተብሏል።

"ኢትዮ የምግብና መጠጥ ፌስቲቫል"
"ኢትዮ የምግብና መጠጥ ፌስቲቫል" ከሰኔ 5 እስከ 9 2016 ዓ.ም በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል ይካሄዳል።
ለ5 ተከታታይ ቀናት በሚቆየው "ኢትዮ የምግብና መጠጥ ፌስቲቫል" በምግብ፣ በመጠጥ፣ በፓኬጂንግ እና ተዛማጅ መስኮች ላይ የተሰማሩ ግብዓት አቅራቢዎች፣ አምራቾች፣ አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶች፣ ከዘርፉ ጋር የተገናኙ አምራች እና አስመጪዎች እንዲሁም የፋይናንስ ተቋማት ይሳተፋሉ ተብሏል።
በፌስቲቫሉ ላይ የዘርፉ ባለሙያዎች የእውቅና አሰጣጥ ፕሮግራም፣ ሽልማት የሚያስገኙ ልዩ ልዩ ውድድሮች እና የመዝናኛ ፕሮግራሞች መካተታቸው ተገልጿል።
አዘጋጆቹ "ኢትዮ የምግብና መጠጥ ፌስቲቫል" በተሳካ መልኩ ይካሄድ ዘንድ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ምዝገባ እያደረጉ መሆናቸውን ያስታወቁ እስካሁን ያልተመዘገቡ ተቋማትም በቀሩት አጭር ቀናት ምዝገባ አድርገው ይህን ፌስቲቫል እንዲቀላቀሉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ይህን የምግብና መጠጥ ፌስቲቫል ለመታደም ለሚፈልጉ ጎብኚዎች መግቢያው በነፃ ነው ተብሏል።
ፌስቲቫሉ የኢንዱስትሪውን የተለያዩ ባለድርሻ አካላትን በማገናኘትና በማስተሳሰር ረገድ ፋይዳ እንዳለው ተገልጿል።
ፌስቲቫሉን በአምራች ኢንዱስትሪ ኢንስቲትዩት የምግብና መጠጥ ምርምርና ልማት ማዕከል ፣አሜዚንግ ፕሮሞሽንና ኤቨንትስ ፣ ዳብ ትሬዲንግ በጋራ በመሆን አዘጋጅተዋል።

የ"በዓሉ ግርማ ቤርሙዳ" ተውኔት ለአጭር ጊዜ በቋሚነት በብሔራዊ ቴአትር መቅረብ ሊጀምር ነው
በውድነህ ክፍሌ ተደርሶ በተሻለ አሰፍ የተዘጋጀውና በቅርቡ በአንጋፋው የሀገር ፍቅር ቴአትር ቤት ሲቀረብ የነበረው "በዓሉ ግርማ ቤርሙዳ" ተውኔት ከፊታችን ሐሙስ ግንቦት 29 2016 ዓ.ም ጀምሮ ለአጭር ጊዜ በቋሚነት በአንጋፋው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ከምሽቱ 11:30 ጀምሮ መቅረብ እንደሚጀምር ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ሰምቷል።
በበዓሉ ግርማ የሕይወት ታሪክ ላይ ተመሥርቶ የተሠራው "ቤርሙዳ" ተውኔት የበዓሉ ግርማ ወዳጆች በተገኙበት ከወራት በፊት ጥቅምት 17 2016 ዓ.ም ነበረ በሀገር ፍቅር ቴአትር የተመረቀው።
ለወራትም በሀገር ፍቅር ቴአትር ቤት ዘወትር እሁድ ከቀኑ 8:00 ጀምሮ በቋሚነት ለታዳሚያን ሲቀረብ ነበር።
በኮሪደር ልማቱ የተነሳም በሀገር ፍቅር ቴአትር ቤት የትርዒት አቅርቦት እንደተቋረጠ ይታወሳል።

የሳምንቱ የኪነጥበብ ዝግጅቶች ( በአጭሩ )
📍የኪነጥበብ ዝግጅቶች
"ወደ ግጥም" ክፍት የኪነጥበብ ዝግጅት ዛሬ ቅዳሜ ግንቦት 24 2016 ዓ.ም ከቀኑ 8:30 ጀምሮ በፈንድቃ ባህል ማዕከል ውስጥ ይካሄዳል።በዕለቱም ግጥም ፣ ሙዚቃ ፣ጨምሮ ልዩ ልዩ ኪናዊ መሰናዶዎች ይቀርባሉ ተብሏል።
የ "ግራጭ ቃጭሎች" ግጥም በአኩስቲክ የኪነጥበብ ዝግጅት ነገ እሁድ ግንቦት 25 2016 ዓ.ም ከቀኑ 9:00 ጀምሮ በደብረዘይት ቶማይ ሆቴል ውስጥ ይካሄዳል ተብሏል።

የሳምንቱ የሥዕል መረጃዎች (በአጭሩ )
📍ሥነጥበብ
1.የአንጋፋ ሠዓሊያን የሥዕል ስራዎች የሚቀርብበት "የኢትዮጵያ ቀለም 3" የሥዕል አውደርዕይ በዚህ ሳምንት በፈንድቃ ባህል ማዕከል ውስጥ ለእይታ በቅቷል።
በዚህ የሥዕል አውደርዕይ ላይ ስራዎቻቸው የቀረበላቸው ሠዓሊያኑ ወርቁ ጎሹ ፣ ባርባራ ጎሹ ፣ገብረክርስቶስ ሰለሞን ፤ዘሪሁን የትምጌታ ፤አሸናፊ ወለደየሱስ ፣ አይናለም ገ/ማርያም ፣ አክሊሉ መንግስቱ ናቸው።
የሥዕል አውድርዕዩ ከግንቦት 21 እስከ ሰኔ 5 2016 ዓ.ም ድረስ በፈንድቃ በእይታ ላይ ይቆያል ተብሏል።
2.የሠዓሊ ዳዊት ገረሡ "አሁን" የተሰኘ የሥዕል አውድርዕይ ግንቦት 23 2016 ዓ.ም ስድስት ኪሎ በሚገኙ ገብረክርስቶስ ደስታ ዘመናዊ ቤተመዘክር ውስጥ ለእይታ በቅቷል።
ይህ የሥዕል አውደርዕይ እስከ ሰኔ 14 2016 ዓ.ም ድረስ በእይታ ላይ ይቆያል።

የጊፍት ሪል ስቴት መንደር 3 ዘመናዊ ቅንጡ የመኖሪያና የንግድ አፓርትማዎች ምርቃት ሥነሥርዓት ተከናወነ
በሪስ ስቴት ዘርፍ ውስጥ ሀያ ዓመታት በላይ ዘመናዊ የመኖሪያ ቪላ መንደሮችን በመገንባት በቂ ልምድ ያካበተው ጊፍት ሪልስቴት፣ በተለምዶ ፈረስ ቤት ተብሎ በሚጠራው እና ደራርቱ ቱሉ አደባባይ አጠገብ የገነባቸውን ረጃጅም፣ ዘመናዊ የመኖሪያና የንግድ አፓርትማዎችን ዛሬ ግንቦት 24 2016 ዓ.ም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ተመርቋል።
ዛሬ የተመረቀው የጊፍት ሪል ስቴት መንደር ሦስት በ54 ሺህ ሜትር ካሬ ላይ ያረፈ ነው፡፡
የጊፍት መንደር ሦስት 2117 ቤቶችን በውስጡ የያዘ መንደር ሲሆ ከ2 እስከ 24 የሚደርስ ፎቆችን ያካተተ አፓርትማዎች፣ ቪላዎች፣ ታዎን ሃውሶችና ሮው ሃውሶችን ያካተተ መንደር ነው።
ጊፍት ሪልስቴት የካ እና ሲኤምሲ ላይ በተለምዶ የጊፍት መንደር አንድና መንደር ሁለት ተብለው በሚታወቁ የመኖሪያ አካባቢዎች፣ 95 ሺህ ካሬ መሬት ላይ ዘመናዊ መንደሮችን ገንብቶ ለተጠቃሚዎች ማስተላለፉ ይታወሳል።
ባሳለፍነው ሚያዝያ ወር 2016 ዓ.ም ላይ ጊፍት ሪል ስቴት በመንግስትና የግል አጋርነት ልማት ፕሮግራም መሠረት፣ በዓይነቱ የመጀመሪያ የሆነውን የ12 ሺህ ቤቶች ግንባታ ስምምነት የተፈራረመ ሲሆን በመጀመሪያው ዙር የ4 ሺህ ቤቶች ግንባታ ስራ በለገሃር አካባቢ ግንባታቸው እየተፋጠነ ይገኛል ተብሏል።

አርቲስት ሊዲያና ሰለሞን የብሪጅ ብረታብረትና እንጨት ስራ ብራንድ አምባሳደር በመሆን ስምምነት ፈፀመች
ብሪጅ ኃ/ቱ የተወሰነ የግል ማህበር በሞናርክ ሆቴል አርቲስት ሊዲያና ሰለሞንን ይፋዊ ብራንድ አምባሳደር አድርጎ ሾሟል።
አርቲስት ሊዲያና ሰለሞን በሚሊዮን የሚቆጠር ብር ስምምነት እንደፈፀመች የተናገረች ሲሆን ፣ የብሪጅ ኢትዮጵያ ምርቶችና ድርጅቶች ለማስተዋወቅ የበኩሏን ድርሻ እንደምትወጣ ገልፃለች።
የብሪጅ ብረታብረትና እንጨት ስራ ኃ/ቱ የተወሰነ የግል ማህበር ስራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ ደረጄ በላቸው፣ ከአርቲስት ሊዲያና ሰለሞን ጋር የፈፀምነው ስምምነት ድርጅታችን ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ እና ተደራሽነቱን ለማስፋት በማሰብ ነው ሲሉ ተናግረዋል።
ብሪጅ በ 2002 ዓ.ም በ 50 ሺ ብር ካፒታል፣ በአነስተኛና ጥቃቅን ተደራጅቶ ስራውን የጀመረ ሲሆን፣ አሁን ከ25.5 ሚሊየን ብር በላይ ካፒታል ማፍራት ችሏል ሲሉ አቶ ደረጄ በላቸው አክለው ተናግረዋል።
ሊዲያና ሰለሞን፣ ብሪጅ ኢትዮጵያ በስሩ ከሚያስተዳድራቸው ድርጅቶች አንዱ ከሆነው ከዳልማንት ትሬዲንግ ጋር የብራንድ አምባሳደር ውል ተፈራርማለች።