የድምፃዊ መሳይ ተፈራ "የልቤን” የተሰኘ አዲስ አልበም የፊታችን ቅዳሜ ለአድማጮች ይደርሳል
የድምፃዊ መሳይ ተፈራ ካሣ "የልቤን "የተሰኘ የመጀመሪያ አዲስ አልበም የፊታችን ቅዳሜ ሰኔ 1 2016 ዓ.ም በራሱ Mesay Tefera የዩቲዩብ ቻናል እንደሚለቀቅ ኤቨንት አዲስ ድረገጽ ሰምቷል።
በሙዚቃ አልበሙ ላይ ወጣትና አንጋፋ የግጥምና ዜማ ደራሲያን የተሳተፉበት ሲሆን ከእነዚህ መካከል ድምፃዊ ጎሳዬ ተስፋዬ ፣ ሞገስ ተካ ፣ አቤል ሙሉጌታ ፣ ናትናኤል ግርማቸዉ ፣ አቡዲ ፣ምህረታብ ደስታ፣ አንተነህ ምናሉ ፣ወንድወሰን ይሁብ ይገኙበታል።
በቅንብር ሚክሲንግና ማስተሪንግ የሙዚቃ ባለሙያዎች ሚካኤል ኃይሉ (ሚኪ ጃኖ) ታምሩ አማረ (ቶሚ) አቤል ጳውሎስና ኪሩቤል ተስፋዬ ተሳትፈውበታል።
አምስት ዓመታት እንደፈጀ የተገለጸው አልበሙ በውስጡ ቻል ቻል ፣የብቻዬ ፣ቆንጆ ነሽ፤ደህና ይግጠምሽ፤ ማካሪና ፤ ከአባይ ማዶ ፤ውረጅ ካናቴ ፤ የልቤን ፤ግድ የለሽም፤ ኸረ ተይ፤አይ አለማወቋ፤ አወሰድማዬ፤ እሳቱ የተሰኙ ርዕሰ ያላቸው የተለያዩ ጉዳዮችን የሚዳስሱ 12 የሙዚቃ ስራዎችን ይዟል።
ድምጻዊ መሳይ ተፈራ ካሣ ከዚህ ቀደም አሰብኩት ፣ ፋሽን፣ብርቄ ነሽ፣ ደግዬ ፣ በጣም እንጂ በጣም እና ሌሎችንም ነጠላ ሙዚቃዎች ለአድማጮች አድርሷል።
ይህን የሙዚቃ አልበም ጋዜጣዊ መግለጫ ያስተባበረው ቴዲኔት ሚዲያና ኢቨንትስ ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ በታላላቅ ሀገራዊና እንዲሁም ዓለም አቀፋዊ ሁነቶችን በማዘጋጀት በማስተባበር ልዩ ልዩ መድረኮችን በመምራት የሚታወቅና የሚዲያ ኮሙኒኬሽንና የመዝናኛ ኢንተርቴይመንት ዘርፍ ላይ በመሰማራት የተለያዩ ስራዎችን በብቁ ዝግጅት በሃላፊነት በመስራት ላይ የሚገኝ ተቋም ነው።
ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1

ኤፍ ኤም አዲስ 97.1 ‹‹ለተሻለ ነገ እናንብብ›› በሚል መሪ ቃል ሲያካሂደው የቆየው የ100 ቀናት የንባብ ዘመቻ ተጠናቀቀ
ላለፉት አንድ መቶ ቀናት በተካሄደው የንባብ ዘመቻ በቁጥር አንድ መቶ የሚሆኑ ከተለያዩ የሕይወት ዘርፎች የተመረጡ ኢትዮጵያውያን ተካፍለዋል።
የሃይማኖት ሰዎች፣ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች፣ የስፖርት ሰዎች፣ የንግድና ሥራ ፈጣሪዎች፣ ምሁራንና ተመራማሪዎች፣ የገዢ እና ተፎካካሪ ፓርቲ አባላት፣ የሚዲያ ሰዎችና ከሌሎች ዘርፎች የተወከሉ ዝነኞች የንባብ ልምዳቸውን አካፍለዋል፤ የምጊዜም ምርጥ መጽሐፎቻቸውንም ጠቁመዋል።
በመቶ ቀናቱ ቆይታ የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገር መጻሕፍት በዝነኞቹ የምንጊዜም ምርጥ መጽሐፎች እየተባሉ የተጠቆሙ ሲሆን፤ በርካታውን እጅ የሚይዙት የሀገር ውስጥ መጻሕፍት ናቸው።
በብዛት ከተጠቆሙ የሀገር ውስጥ መጽሐፎች፥ ነባር ልቦለዶች እንዲሁም የህይወት ታሪክና ግለ ታሪኮች ቅድሚያውን ወስደዋል።
ከእነዚህም መካከል፦ፍቅር እስከመቃብር፣ በሀዲስ ዓለማየሁ (ብዙ ጊዜ ተደጋሞ የተመረጠ መፅሃፍ)፣ኦሮማይ፣ በበዓሉ ግርማ፣የህይወቴ ታሪክ (ኦቶባዮግራፊ)፣ በፊታውራሪ ተ/ሐዋርያት ተ/ማርያም፣እሳት ወይ አበባ፣ በጸጋዬ ገ/መድኅን፣ የኤርትራ ጉዳይ፣ በአምባሳደር ዘወዴ ረታ፣ መጽሐፈ ትዝታ ዘዓለቃ ለማ ኃይሉ ወልደ ታሪክ፣ በመንግሥቱ ለማ፣ትዝታ፣ በሀዲስ ዓለማየሁ፣ህይወቴ፣ በደጃዝማች ወ/ሰማያት ገ/ወልድ፣የከፍተኛ ትምህርት ዘይቤ፣ በእጓለ ገ/ዮሐንስ፣ ህይወቴና የኢትዮጵያ ርምጃ፣ በግርማዊ ቀዳማዊ ኃ/ሥላሴ፣አደፍርስ፣ በዳኛቸው ወርቁ "የምንጊዜም ምርጥ" ተብለው በተሳታፊዎች በብዛት የተጠቀሱ መጻሕፍት ሲሆኑ፤ ከውጭ ሀገር መጻሕፍት መካከል ደግሞ ዘአልኬሚስትና ሌሎችም ይገኙበታል።

በሚሊኒየም አዳራሽ : የመዝሙር ኮንሰርት
የፊታችን እሁድ ሰኔ 2 ቀን 2016 ዓም በሚሊኒየም አዳራሽ የመዝሙር ኮንሰርት እንደተዘጋጀ ተገልጿል።
ኤልሀዳር ኢንጂነሪንግ ከዘማሪ ጳውሎስ ተገኝ ጋር በመተባበር «ዲልቢ ገለታ የሱሲፍ»የተሰኘውን የመዝሙር ድግስ በሚኒሊየም አዳራሽ የፊታችን እሁድ ሰኔ 2 2016 ዓ.ም ቀኑ ከ7፡00 ጀምሮ ማዘጋጀቱን ዛሬ ግንቦት 27 2016 ዓ.ም በስካይ ላይት ሆቴል በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ተገልጿል።
ዘማሪ ጳውሎስ ተገኝ በዝማሬው ዓለም ውስጥ በመቆየት እና በርካታ የመዝሙር ስራዎችን በመስራት ይታወቃል።ሶስት አልበሞችን እና የተለያዩ መዝሙሮችን ከተለያዩ ዘማሪዎች ጋር በመስራት፣እንዲሁም 'ሙጫ ካዮ' ከተሰኘ የህፃናት ህብረት ጋር በመሆን ሁለት ቪሲዲዎችን በመስራት ለአማኞች አድርሷል።
በዚህ ፕሮግራም ለመሳተፍ የመግቢያ ዋጋው በነፃ ስለሆነ መጨናነቅ እንዳይፈጠር ከጠዋቱ 4:00 ጀምሮ በሚሊኒየም አዳራሽ በሚካሄደው የመዝሙር ድግስ እንዲገኙ ጥሪ ተላልፏል።

"ማለዳ" የተሰኘ ሀገርኛ ፊልም ተመረቀ
በድሮ ፒክቸር ተዘጋጅቶ የቀረበው”ማለዳ” የተሰኘ የሳሙኤል ካሣሁን ፊልም ትላንት ግንቦት 26 2016 ዓ.ም ጥሪ የተደረገላቸው የጥበብ ቤተሰቦች እና እንግዶች በተገኙበት በቀይ ምንጣፍ ሥነ -ሥርዓት ተመርቋል።
በፊልሙ ላይ ታሪኩ ብርሃኑ(ባባ)፣ መታሰቢያ ታደሰ ፣ ዘላለም ይታገሱ እና ሌሎችም በተዋናይነት ተሳትፈዋል።
“ ማለዳ “ፊልም የቤተሰብ ድራማ ዘውግ እንደዳለው የተገለፀ ሲሆን ግንቦት 30 ሰኔ 1,2 እና ሰኔ 7,8 እና 9 በተመረጡ ሲኒማ ቤቶች መታየት ይጀምራል።
የ"ማለዳ" ፊልም አዘጋጅ ሳሙኤል ካሣሁን ከዚህ ቀደም ከተሳተፈባቸው ፊልሞች መካከል አሚን ፣አስርቱ ቀናት፣ የታሰረ ፍቅር ፣ ጊዜ ለኩሉ ፣ ትመጪ እንደሁ ፣ ቁልፉን ስጪኝ ፣ተከፍሏል ፣ ከሽሽት መልስ ይገኙበታል።

አርቲስት ፍቃዱ ከበደ የክብር የእንግዳ የሆነበት አንጋፋው የኪነጥበብ ምሽት ረቡዕ ይካሄዳል
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ባህል ማዕከል የሚዘጋጀው የኪነጥበብ መርሃግብር ነገ ረቡዕ ግንቦት 28 2016 ዓ.ም ይካሄዳል።
በዕለቱ አርቲስት ፍቃዱ ከበደ"የአንድ ግጥም፣ የአንድ ወግ" የክብር እንግዳ ሆኖ ይገኛል።
እንዲሁም ግጥሞች፣ ወግ፣ ሙዚቃና ሞኖሎግ ተሰናድተው እናንተ ውድ ታዳሚዎቻችንን በባህል ማዕከል አዳራሽ ከቀኑ በ11: 30 ጀምሮ ይጠብቃችኃል ብለዋል አዘጋጆቹ ።
ማስታወሻ :— ፕሮግራሙ ላይ ለመታደም የምትፈልጉ በአሁን ሰዓት የዩኒቨርስቲው ተማሪ ያልሆናችሁ የስነ ጽሑፍ አፍቃሪያን መግቢያው በ5ተኛ በር በኩል ነው።
ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ባህል ማዕከል የሚዘጋጀው የኪነጥበብ መርሃግብር ነገ ረቡዕ ግንቦት 28 2016 ዓ.ም ይካሄዳል።
በዕለቱ አርቲስት ፍቃዱ ከበደ"የአንድ ግጥም፣ የአንድ ወግ" የክብር እንግዳ ሆኖ ይገኛል።
እንዲሁም ግጥሞች፣ ወግ፣ ሙዚቃና ሞኖሎግ ተሰናድተው እናንተ ውድ ታዳሚዎቻችንን በባህል ማዕከል አዳራሽ ከቀኑ በ11: 30 ጀምሮ ይጠብቃችኃል ብለዋል አዘጋጆቹ ።
ማስታወሻ :— ፕሮግራሙ ላይ ለመታደም የምትፈልጉ በአሁን ሰዓት የዩኒቨርስቲው ተማሪ ያልሆናችሁ የስነ ጽሑፍ አፍቃሪያን መግቢያው በ5ተኛ በር በኩል ነው።
ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
ተዋናይ አማኑኤል ሐብታሙ ከ42 ቀናት እስር በኋላ ዛሬ ዳይሬክተሩን ዳግማዊ ፈይሳ ጨምሮ ከ20 ተጠርጣሪዎች ጋር ፍርድ ቤት ቀረበ
ተዋናይ አማኑኤል ሐብታሙ እስራኤል አገር "እብደት በሕብረት" የተሰኘ ቴአትሩን ለማሳየት አውሮፕላን ሊሳፈር ሲል ሚያዝያ 15 ቀን 2016 ዓ/ም ከአዲስ አበባ ኤርፖርት በፖሊሶች ተይዞ ወደ አዲስ አበባ ፖሊስ ተወስዶ መታሰሩ ይታወሳል።
አማኑኤል በታሰረ ከ42 ቀናት በኋላ በዛሬው ዕለት ግንቦት 28 ቀን 2016 ዓ/ም ፖሊስ ፍርድ ቤት አቅርቦት የነበረ ሲሆን ፍርድ ቤቱ ፖሊስ የጠየቀውን ተጨማሪ ጊዜ ቀጠሮ በመፍቀድ ለሰኔ 11 ቀን ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።
ተዋናይ አማኑኤል ሐብታሙ በተጨማሪም በቅርቡ በፖሊስ ተይዞ ለእስር የበቃው የ"እብደት በሕብረት" ቴአትር አዘጋጅ አንጋፋው ከያኒ ዳግማዊ ፈይሳን ጨምሮ ሌሎች 20 ሰዎችን በአንድ መዝገብ ለፌደራል መደበኛ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ጊዜ ቀጠሮ ወንጀል ችሎት ቀርበው ሁሉንም ለሰኔ 11 ቀን 2016 ዓ/ም ተለዋጭ ቀጠሮ እንደተሰጣቸው ማረጋገጥ ችያለሁ።
መረጀው የያሬድ ሹመቴ ነው።

የኪናዊ ዲጂታል መጽሔቶች ጥቆማ!
በኪነጥበብ፣ በሥነጥበብ ፣በሥነጽሑፍ፣ ማኅበራዊና ባህላዊ ጉዳዮች ላይ ትኩረታቸውን አድርገው ለአንባቢያን እየደረሱ ከሚገኙ ዲጂታል መጽሔቶች ውስጥ እንደ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ የተወሰኑትን እንነግራችኋለን።
📍ቃላት
ቃላት ዲጂታል መጽሔት ሥነ-ጽሑፍ ፣ ኂስ ፣ ሙዚቃ፣ሲኒማ እና ሌሎችም ጉዳዮች ላይ ትኩረቱን ያደረገ ኪናዊ ዲጂታል መጽሔት ነው።
ቃላት ዲጂታል መጽሔት እስካሁን አስራ አንድ መጽሔቶችን ለአንባቢያን አድርሷል።
የቃላት የዲጂታል መጽሔት የቴሌግራም ገፅ:
https://news.1rj.ru/str/Words2014
📍ባይራ
ባይራ ዲጂታል መጽሔት በሥነጽሐፍ ፣በኪነጥበብና ማህበራዊ ፣ ባህላዊ ጉዳዮች ላይ የሚያተኮር ዲጂታል መጽሔት ነው።
ባይራ ዲጂታል መጽሔት ከስድስት በላይ ዲጂታል መጽሔቶችን ለአንባቢያን አድርሷል።
የባይራ ዲጂታል መጽሔቶች የቴሌግራም ገፅ:
https://news.1rj.ru/str/Bayradigital
📍 መዲና
መዲና ዲጂታል መጽሔት በኪነጥበብ፣ ሥነጽሑፍ እና በሌሎችም ጉዳዮች ላይ ትኩረቱን አድርገው ለአንባቢያን እየደረሰ የሚገኝ ዲጂታል መጽሔት ነው።
የመዲና ዲጂታል መጽሔት የቴሌግራም ገፅ:
https://news.1rj.ru/str/Medinamagazine
ኤቨንት አዲስ ድረገፅ እነዚህን ኪናዊ ዲጂታል መጽሔቶች በየገፆቻቸው እየገባችሁ እንድታነቡ ይጋብዛል።

የአርቲስት ዘሪቱ ከበደ የመጀመሪያ ልጅ አረፈ
የአርቲስት ዘሪቱ ከበደ የ17 ዓመት የመጀመሪያ ልጇ ክርስቲያን ላቃቸው በድንገተኛ ህመም በህክምና ሲረዳ ቆይቶ ዛሬ ግንቦት 28 2016 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱ ተሰምቷል።
ባለቤቷ ( የ3 ልጆቿ አባት ) የተወዳጁ የምንጊዜም የኢትዮጵያ እግር ኳስ ተጫዋች የመንግስቱ ወርቁ ልጅ ላቃቸው መንግስቱ ነው።
በድንገት ያረፈው ክርስቲያን ላቃቸው የ11ኛ ክፍል ተማሪ ነበር።
📍መረጀው የጌጡ ተመስገን ነው።

የሐሙስ መረጃዎች
የሳምንቱ ኪናዊ መረጃዎች ቀጥሎ ይቀርባሉ!
📍በደራሲ ስብሐት ገ/እግዚአብሔር ህይወት ላይ የሚያተኩረው "ማስታወሻ " መጽሐፍ በድጋሚ ታትሞ በቅርቡ ለአንባቢያን እንደሚደረስ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ከደራሲ ዘነበ ወላ ሰምቷል።"በርካታ ወጣት አንባቢያን በተለያዩ አጋጣሚዎች ስንገናኝ"ማስታወሻ " መጽሐፍን የት ልታገኙት እንደምትችሉ ትጠይቁኝ ነበር።ይህንን ጥያቄአችሁን ከግምት ውስጥ በማስገባት ጥቂት ኮፒዎች ታትሞአል። በቅርቡ በሁሉም መጻሕፍት መደብር ታገኙታላችሁ" ሲል ደራሲው አስታውቋል።
📍የድምፃዊ መሳይ ተፈራ ካሣ "የልቤን "የተሰኘ የመጀመሪያ አዲስ አልበም የፊታችን ቅዳሜ ሰኔ 1 2016 ዓ.ም በራሱ Mesay Tefera የዩቲዩብ ቻናል እንደሚለቀቅ ኤቨንት አዲስ ድረገጽ ሰምቷል።በሙዚቃ አልበሙ ላይ ወጣትና አንጋፋ የግጥምና ዜማ ደራሲያን የተሳተፉበት ሲሆን በቅንብር ሚክሲንግና ማስተሪንግ የሙዚቃ ባለሙያዎቹ ሚካኤል ኃይሉ (ሚኪ ጃኖ) ታምሩ አማረ (ቶሚ) አቤል ጳውሎስና ኪሩቤል ተስፋዬ ተሳትፈውበታል።
📍ገጣሚ ምልእቲ ኪሮስ በግጥም የተሳተፈበችበት የድምጻዊት ሔዋን ገብረወልድ "ያንተን" የተሰኘ ሙዚቃ በቅርቡ ለአድማጮች እንደምታደርስ ድምጻዊቷ በማህበራዊ ትስስር ገጿ አስታውቃለች።በዚህ የሙዚቃ ስራዋ ላይ ገጣሚ ምልእቲ ኪሮስ በግጥም ምረታብ ደስታ በዜማ ተሳትፈዋል።ሙዚቃ ቅንብርና ማስተሪንጉን ስማአገኘሁ ሳሙኤል ሰርቷል።
📍ድምጻዊኑ ልዑል ሲሳይ፣ ሚካኤል በላይነህ፣ ሳሚ ዳን የተጣመሩበት "ልዑል" ኮንሰርት የፊታችን ቅዳሜ ሰኔ 1 2016 ዓ.ም በሚሊኒየም አዳራሽ ይካሄዳል።ወጣቱ ድምጻዊ ልዑል ሲሳይ ከወራት በፊት "ልዑል" የተሰኘ አልበም ለአድማጮች ያደረሰ ሲሆን በሌላ በኩል ድምጻዊ ሚካኤል በላይነህ ከዓመታት በኃላ በቅርቡ የሙዚቃ አልበሙን ለአድማጮች ያደርሳል ተብሏል።
📍የ"በዓሉ ግርማ ቤርሙዳ" ተውኔት ለአጭር ጊዜ በቋሚነት በብሔራዊ ቴአትር ከዛሬ ጀምሮ መቅረብ ይጀምራል።በውድነህ ክፍሌ ተደርሶ በተሻለ አሰፍ የተዘጋጀውና በቅርቡ በአንጋፋው የሀገር ፍቅር ቴአትር ቤት ሲቀረብ የነበረው "በዓሉ ግርማ ቤርሙዳ" ተውኔት ከዛሬ ሐሙስ ግንቦት 29 2016 ዓ.ም ጀምሮ ለአጭር ጊዜ በቋሚነት በአንጋፋው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ከምሽቱ 11:30 ጀምሮ መቅረብ እንደሚጀምር ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ሰምቷል።
📍ተዋናይ አማኑኤል ሀብታሙ በታሰረ ከ42 ቀናት በኋላ በትላንትናው ዕለት ግንቦት 28 ቀን 2016 ዓ.ም ፖሊስ ፍርድ ቤት አቅርቦት የነበረ ሲሆን ፍርድ ቤቱ ፖሊስ የጠየቀውን ተጨማሪ ጊዜ ቀጠሮ በመፍቀድ ለሰኔ 11 ቀን ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቷል።በተጨማሪም በቅርቡ በፖሊስ ተይዞ ለእስር የበቃው የ"እብደት በሕብረት" ቴአትር አዘጋጅ አንጋፋው ከያኒ ዳግማዊ ፈይሳን ጨምሮ ሌሎች 20 ሰዎችን በአንድ መዝገብ ለፌደራል መደበኛ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ጊዜ ቀጠሮ ወንጀል ችሎት ቀርበው ሁሉም ለሰኔ 11 ቀን 2016 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ እንደተሰጣቸው ተነግሯል።
📍የሠዓሊ በኃይሉ በዛብህ "ድመት ዘጠኝ ነፍስ አላት" የሥዕል አውደርዕይ ግንቦት 27 2016 ዓ.ም በሐያት ሪጀንሲ ለእይታ እንደቀረበ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ተመልክቷል። ይህ የሥዕል አውደርዕይ እስከ ሰኔ 8 2016 ዓ.ም በእይታ ላይ ይቆያል ተብሏል።
📍"ማለዳ" ፊልም ከነገ ጀምሮ በሲኒማ ቤቶች መታየት ይጀምራል።በድሮ ፒክቸር ተዘጋጅቶ የቀረበው”ማለዳ” የተሰኘ የሳሙኤል ካሣሁን ፊልም ከነገ ግንቦት 30 ጀምሮ ሰኔ 1 ፣ 2 እና ሰኔ 7 ፣8 እና 9 በተመረጡ ሲኒማ ቤቶች መታየት ይጀምራል።በፊልሙ ላይ ታሪኩ ብርሃኑ(ባባ)፣ መታሰቢያ ታደሰ ፣ ዘላለም ይታገሱ እና ሌሎችም በተዋናይነት ተሳትፈዋል። ፊልሙ ባሳለፍነው ሰኞ ግንቦት 26 2016 ዓ.ም መመረቁ ይታወሳል።
📍አላቲኖስ ኢትዮጵያዊ ፊልም ሰሪዎች ማሕበር ፒያሳ በሚገኘው የሩሲያ ሳይንስና ባህል ማዕከል (ፑሽኪን) አዳራሽ ውስጥ በሚያዘጋጀው የፊልም ውይይት መርሐግብር ዛሬ ሐሙስ ግንቦት 29 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 10:30 ጀምሮ" ሙዚቃዊ ፊልም: በቺካጎ ፊልም አስረጂነት" በሚል ርዕስ እይታ እና ውይይት ያካሄዳል።
📍በዘርዓያዕቆብ የፍልስፍና ት/ቤት በየሳምንቱ የሚዘጋጀው የሀሳብ ውይይት በዚህም ሳምንት "የኢትዮጵያ ፍልስፍና: ሰሙነ ህማማት ወይንስ ትንሣኤ"የተሰኘ ርዕስ መርጧል ይህም ውይይት ቅዳሜ ሰኔ 1 2016 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ጀምሮ 5 ኪሎ በሚገኘው አፄ ናኦድ ት/ቤት ግቢ ውስጥ ይካሄዳል።
አዘጋጅ: ናቲ ማናዬ
ቀን: ግንቦት 29 2016 ዓ.ም
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
በድረገጻችን በተሻለ አቀራረብ ያንብቡ:
https://eventaddis.com
ቴሌግራም: @EventAddis1

ኤቨንት አዲስ/ሁነት አዲስ ዛሬ ሁለት ዓመት ሞላው
ሚዲያችን Event Addis/ሁነት አዲስ የኩነት እና መዝናኛ መረጃዎች ምንጭ መሆን ከጀመረ ዛሬ ግንቦት 29 2016 ዓ.ም ሁለተኛ ዓመቱን አስቆጠረ።
እንኳን አደረሰን ፣ እንኳን አደረሳችሁ !
በእነዚህ ሁለት ዓመታት ያለማቋረጥ በየዕለቱ የሥነጽሑፍ ፣ የኪነጥበብ ፣ የሥነጥበብ፣ የኩነት እና ሚዲያ መረጃዎችን ለተከታዮቹ በፍጥነት እና በጥራት እያቀረበ ነው።
ሚዲያዎችን ኤቨንት አዲስ/ሁነት አዲስ በኢትዮጵያ ለሚገኙ የቴሌቪዥን ጣቢያዎች፣ የሬድዮ ጣቢያዎች እና ዝግጅቶች ፣ የማህበራዊ ትስስር ገፆችና ጋዜጦች ሁነኛ የመዝናኛ መረጃዎች ምንጭ በመሆን እያገለገለ ይገኛል።
በእነዚህም ሁለት ዓመታት በኢትዮጵያ የሁነት (Event) እና ኪነት( Art) መረጃዎች ላይ የሚታየውን ክፍተት ለመድፈን እጅግ ጥቂትም ቢሆንም ጥረት እያደረገን እንገኛለን።ይህም ጥረታችን ይቀጥላል።
በቀጣይም እንኑር ያኑርን እያለን በተለያዩ የሚዲያ አማራጮች በጥራት እና በተሻለ አቀራረብ እኛን እኛን የሚሸቱ ፕሮግራሞች ይዘን እንመጣለን።
በቅርቡም ሚዲያችን በዩቲዩብ ፣ በቲክቶክ ፣ እና በሬድዮ ፕሮግራም አማራጮች ልዩ ልዩ ዝግጅቶችን ማቅረብ እንደሚጀምር ስናበስራችሁ በታላቅ ደስታ ነው።
መልካም በዓል ለኤቨንት አዲስ
📍ኪነት እና ኩነት
ለሃሳብና አስተያየት: @Tmanaye
የEventAddis/ሁነት አዲስ ማኅበራዊ ገፆቻችን
Telegram:https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
Website: https://eventaddis.com
Facebook:https://facebook.com/groups/2009372275938661/
Facebook Page:https://www.facebook.com/profile.php?id=100083170462851&mibextid=ZbWKwL

ግንቦት 30 ሀገር አቀፍ የምስጋና ቀን
በጣፋጭ ህይወት መልቲሚዲያ በየዓመቱ የሚዘጋጅው "የጣፋጭ ህይወት የምስጋና ሽልማት" ዘንድሮ ለአራተኛ ጊዜ ነገ ግንቦት 30 2016 ዓ.ም በስካይላት ሆቴል ይካሄዳል።
በሀገር አቀፍ ደረጃም ግንቦት 30 የምስጋና ቀን ሆኖ እንዲቀጥል ለ4ተኛ ዙርም በሀገር አቀፍ ደረጃ ነገ ግንቦት 30 2016 ዓ.ም የምስጋና ቀን ሆኖ ይውላል።
የዚህም ቀን አንዱ አካል የሆነው"እኔም የማመሰግነው ሰው አለኝ" የተሰኘ የማኅበራዊ ትስስር ገፅ ንቅናቄ (ቻሌንጅ) በይፋ ተጀምሮአል።በዚህም "ቻሌንጅ" በተለያየ መንገድ መልካም ስራ የሰሩ ሰዎች ይመሰገኑበታል።
ግንቦት 30 ከጠዋት ጀምሮ እስከ አመሻሽ ድረስ የምንመሰጋገንበት ቀን ሆኖ እንደሚውልም የተገለፀ ሲሆን የተያዘውን እቅድም ለማሳካት ሁሉም የማኀበረሰብ ክፍል በጋራ መስራት አለበት ተብሏል።
የ"ጣፋጭ ህይወት የምስጋና ሽልማት" አመሻሽ ላይ የሚካሄድ ሲሆን ይህም የሽልማት ሥነሥርዓት በሀገሬ ቴሌቪዥን በቀጥታ ስርጭት ይተላለፋል።

የዓለማችን ተጠቃሽ የኤሌክትሪክ መኪኖች አምራች የ"ሆን ዞ" አውቶ ፋክተሪ የኢትዮጵያና ምስራቅ አፍሪካ ብቸኛ ወኪል ኢትዮፒካር ብራንድ የኤሌክትሪክ መኪኖችን በብድር አስረከበ።
መኪኖቹ የግሎባል የገንዘብ ቁጠባና ብድር ተቋም አባል የሆኑና 30% ቁጠባን ለቆጠቡ ነው የተሰጠው።
በኤሌክትሪክ የሚሰሩ መኪኖች በበርካታ ሃገራት ተመራጭነታቸው ከዕለት ወደ ዕለት እየጨመረ ይገኛል ኢትዮጵያም እንደ ሃገር የውጭ ምንዛሬ እጥረትን ብሎም የአየር ንብረትን ለመጠበቅ ይረዳ ዘንድ የኤሌክትሪክ መኪናን እንደ አማራጭ የመጠቀም ፓሊሲን ከመተግበር ባለፈ በሃገራችን የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ፍላጎት ከፍተኛ እየሆነ መጥቷል።
የዜጎችን ኑሮ ባማከለ መልኩ በባንክ ብድር አማራጭ እየቀረቡ የሚገኙት እነዚህ የኤሌክት መኪኖች የፋብሪካ ዋስትና ያላቸውም ናቸው።
ለዚህም በዛሬው ዕለት ግንቦት 29 ቀን 2016 ዓ.ም ኢትዮፒካር ብራንድ ከግሎባል የገንዘብ ቁጠባና ብድር ተቋም ጋር የኤሌክትሪክ መኪኖችን ለተቋሙ አባላት በብድር መስጠት የሚያስችል ስምምነት ፈፅሟል፡፡
በዚህ ስምምነት መሰረትም የ"ሆን ዞ" አውቶ ፋክተሪ የኢትዮጵያና ምስራቅ አፍሪካ ብቸኛ ወኪል ኢትዮፒካር የግሎባል የገንዘብ ቁጠባና ብድር ተቋም አባላት የሚፈልጓቸውን የኤሌክትሪክ መኪኖች ምቹ እና ቀልጣፋ በሆነ መልኩ በብድር እንደሚሰጥ ''የኢቲዮፒካር'' ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሳሙኤል አዲስአለም ገልፀዋል።
በተጨማሪም ዛሬ ግንቦት 29/2016 ዓም ኢትዮፒካር የግሎባል የገንዘብ ቁጠባና ብድር ተቋም አባላት ለሆኑና የብድር መስፈርቱን አሟልተው 30 በመቶ ቁጠባ ለፈፀሙ አባላት የኤሌክትሪክ መኪኖችን አስረክቧል።

ኤም ኤን ጂ ፊልም ፕሮዳክሽንና ኢንቨስትመንት የአፍሪካ ጽህፈት ቤቱን ሰኞ ያስመርቃል
ከቴክኖሎጂ ጋር ዝምድና የፈጠረ፣ ዓለም አቀፍ የፊልም ማህበረሰብን የመፍጠር ግብ የሰነቀው ኤም ኤን ጂ የፊልም ኩባንያ በኢትዮጵያ ሥራውን በይፋ ሊጀምር ነው።
ኤም ኤን ጂ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከሚታወቁ የፊልም አምራቾች የተወሰነውን ገበያ በመግዛት መልሶ በስቶክ ማርኬት የሚሸጥ ኩባንያ ነው፡፡
ይህ የፊልም ኩባንያ፣ ሲኒማቶግራፊን ከዘመኑ ቴክኖሎጂ ጋር እንዴት ማቆራኘት እንደሚቻልና የፊልም ኢንዱስትሪንም ለማሳደግ የሚያስችሉ ዘዴዎችን የሚቀይስ ነው ተብሏል።
ኤም ኤን ጂ ኩባንያ በአፍሪካ በይፋ የከፈተውን የኢትዮጵያ ጽህፈት ቤቱን ሰኞ ሰኔ 3 2016 ከቀኑ 9:00 ጀምሮ በማዶ ሆቴል ያስመርቃል፡፡
በዚህ ዕለትም ከፊልም ሙያ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ያላቸው ባለሙያዎችና የሚዲያ ሰዎች ይታደማሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ተወዳጅ ሚዲያ እና ኮሚኒኬሽን ከፓፓራዚ ማስታወቂያ ጋር በትብብር ያዘጋጁት እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል፡፡
📍መረጃው የተወዳጅ ሚዲያ ነው

ሔሎ ኢትዮጵያ የሬድዮ ፕሮግራም እውቅና ተሰጠው
በዳጉ ኮምኒኬሽን ፒኤልሲ እየተዘጋጀ በአንጋፋው ኤፍ ኤም አዲስ 97.1 የሚተላለፈው "ሔሎ ኢትዮጵያ" የሬድዮ ፕሮግራም ከአርማወር ሐንሰን የምርምር ኢንስቲትዩት እውቅና ተሰጥቶታል።
54 ዓመታትን ያስቆጠረው አርማወር ሐንሰን የምርምር ኢንስቲትዩት በርካታ የምርምር ውጤቶችን በማውጣትና ለሀገራችን ብሎም ለዓለም አስተዋፅኦ በማድረግ ላይ የሚገኝ ተቋም ነው።
ግንቦት 29 እና 30 2016 ዓ.ም በአዲስ አበባ አህሪ አለርት የጤና መንደር እና በአዳማ በሚገኘው የወባና ትኩረት የሚሹ ቆላማ በሽታዎች የምርምርና ስልጠና ማዕከል ውስጥ በተካሄደው ጉባኤ ላይ የአርማወር ሐንሰን የምርምር ኢንስቲትዩት (አህሪ) ላለፉት 54 ዓመታት በጤናው ዘርፍ የምርምር ልማትን ለማሳደግ እንዲያስችል በርካታ የምርምር ውጤቶችን በማውጣትና ለሀገራችን ብሎም ለአለም አስተዋፅኦ በማድረግ ላይ እንደሚገኝ ተገልጿል።
በኢንስቲትዩቱ መድኃኒት የተላመደ የቲቢ ሕክምናን ከ24 ወራት ወደ 9 ወራት ዝቅ የሚያደርግ የምርምር ውጤት መገኘቱ የተገለፀ ሲሆን የምርምር ውጤቱ በዓለም ጤና ድርጅት እውቅና ተሰጥቶታል።
በዚህ ጉባኤ ላይ ለሚዲያ ተቋማት እውቅና የተሰጠ ሲሆን ከእነዚህም የሚዲያ ተቋማት መካከል ሔሎ ኢትዮጵያ የሬድዮ ፕሮግራም አንደኛው ነው።
እውቅናውን በቦታው በመገኘት የሔሎ ኢትዮጵያ ባልደረባ ጋዜጠኛ ናትናኤል ደበና በክብር ተቀብሏል።

"ጣፋጭ ህይወት የምስጋና ሽልማት" በድምቀት ተካሄደ
በጣፋጭ ህይወት መልቲሚዲያ በየዓመቱ የሚዘጋጅው "የጣፋጭ ህይወት የምስጋና ሽልማት" ዘንድሮ ለአራተኛ ጊዜ ግንቦት 30 2016 ዓ.ም በስካይላት ሆቴል ተካሄዷል።
አርብ አመሻሽ ላይ የተካሄደው"የጣፋጭ ህይወት የምስጋና ሽልማት" በስድስት ዘርፎች ልዩ ልዩ ተሸላሚዎችን ሸልሟል።
የዘንድሮው የአራተኛው የጣፋጭ ህይወት የምስጋና ሽልማት የተሸላሚዎች ዝርዝር የሚከተለውን እንደሚመለስ ኤቨንት አዲስ ድረገጽ ተመልክቷል።
1.ስራ ፈጠራን ተግባር ዘርፍ ተሸላሚ: ኢ/ር ቢጃይ ናይከር
2. ተስፋ የሚጣልበት/የሚጣልባት ስራ ፈጣሪ ዘርፍ ተሸላሚ: ቤተልሔም ደሴ
3.በበጎ አድራጎት ተቋማት ዘርፍ ተሸላሚ: ይመለከተኛል የበጎ አድራጎት ተቋም
4. በበጎ አድራጎት ተቋማት ዘርፍ (በግል): ሚኪያስ ለገሰ
5.የህይወት ክህሎት አሰልጣኝ (በተግባር ዘርፍ ) ተሸላሚ: ሔኖክ ሐ/ማርያም (ኒው ላይፍ )
6.ተስፋ የሚጣልበት/የሚጣልባት የህይወት ክህሎት አሰልጣኝ ተሸላሚ: ሰላም አታላይ (ቡና ፖድካስት)
7.ዝናን ለመልካም ምግባር በመጠቀም ዘርፍ ተሸላሚ: አርቲስት መቅደስ ፀጋዬ
8.ሚዲያውን ለሥነልቦና ግንባታ ዘርፍ ተሸላሚ: መጽሔተጥበብ የሬድዮ ፕሮግራም
9.ማህበራዊ ሚዲያውን ለበጎ ምግባር በመጠቀም በቲክቶክ ዘርፍ ተሸላሚ : መምህርት ዙፋን ታምር (ሚስ ዙፋን)
10.ማህበራዊ ሚዲያን በበጎ በመጠቀም በዩቲዩብ ዘርፍ ተሸላሚ: መሪ ፖድካስት
11. ልዩ ተሸላሚ: ማስተር ካርድ ፋውንዴሽን
ለተጨማሪው: @EventAddis1

ወጣቷ ድምጻዊት ሀና ግርማ ''ባንተ ላይ'' በተሰኘ ስራዋ የናሆም ሪከርድስን ሪከርድ ሰብራለች
ድምፃዊት ሀና ግርማ ከ9 ወራት በፊት በሰራችው ስራ ከሰሞኑ የናሆም ሪከርድስን ሪከርድ ሰብራለች ።
የተለያዩ ቪዲዮ ክሊፖችን እና ፊልሞችን ዳይሬክት እያደረገች የምትገኘው አዩ ግርማ ቪድዮውን ሰርተዋለች። አቡዱ ግጥምና ዜማውን ሰርቶ ታምሩ አማረ ሙዚቃውን አቀናብሮታል ። ሃና ግርማ ደግሞ በነሀሴ ወር 2015 ላይ አቀንቅናው በአንድ ግዜ በሙዚቃ አፍቃሪው ተወዳጅነትን አግኝቶላታል ።
''ባንተ ላይ''ሙዚቃው በናሆም ሪከርድስ በተለቀቀ 9 ወሩ 20 ሚሊዮን እይታ አግኝቷል።ይህም ኩባንያው ቪድዮዎችን መልቀቅ ከጀመረ ጊዜ አንስቶ በአጭር ጊዜ ውስጥ ከፍተኛ ተመልካች በማግኘት ቀዳሚ ሆኗል።
ናሆም ሪከርድስ በዩቲዩብ ከለቀቃቸው ስራዎች በቀዳሚነት ላይ የሚገኘው የታሪኩ ጋንኪሳ ዲሽታ ጊና ሲሆን 35 ሚሊዮን ጊዜ ታይቷል። ይህ ስራ በዚህ ቁጥር የታየው በ3 አመት ውስጥ ነው። የሃና ግን በ9 ወራት ነው 20,000,000 የታየው። የቬሮኒካ አዳነ "ጥፍጥ አለኝ" ከሁለት አመት በፊት ተለቆ 18 ሚሊየን ጊዜ ታይቶ ናሆም ከለቀቃቸው ስራዎች ብዙ እይታ በማግኘት 3ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።
📍መረጃው የሁሉ አዲስ ነው።

የድምፃዊ መሳይ ተፈራ "የልቤን" አልበም ተለቀቀ
የድምፃዊ መሳይ ተፈራ ካሣ "የልቤን "የተሰኘ የመጀመሪያ አዲስ አልበም ዛሬ ቅዳሜ ሰኔ 1 2016 ዓ.ም በራሱ Mesay Tefera የዩቲዩብ ቻናል እና በዓለማቀፍ መተግበሪያዎች ላይ ተለቋል።
በሙዚቃ አልበሙ ላይ ወጣትና አንጋፋ የግጥምና ዜማ ደራሲያን የተሳተፉበት ሲሆን ከእነዚህ መካከል ድምፃዊ ጎሳዬ ተስፋዬ ፣ ሞገስ ተካ ፣ አቤል ሙሉጌታ ፣ ናትናኤል ግርማቸዉ ፣ አቡዲ ፣ምህረታብ ደስታ፣ አንተነህ ምናሉ ፣ወንድወሰን ይሁብ ይገኙበታል።
በቅንብር ሚክሲንግና ማስተሪንግ የሙዚቃ ባለሙያዎች ሚካኤል ኃይሉ (ሚኪ ጃኖ) ታምሩ አማረ (ቶሚ) አቤል ጳውሎስና ኪሩቤል ተስፋዬ ተሳትፈውበታል።
ኤቨንት ድረገፅ እንደተመለከተው አምስት ዓመታት የፈጀው አልበሙ በውስጡ ቻል ቻል ፣የብቻዬ ፣ቆንጆ ነሽ፤ደህና ይግጠምሽ፤ ማካሪና ፤ ከአባይ ማዶ ፤ውረጅ ካናቴ ፤ የልቤን ፤ግድ የለሽም፤ ኸረ ተይ፤አይ አለማወቋ፤ አወሰድማዬ፤ እሳቱ የተሰኙ ርዕሰ ያላቸው የተለያዩ ጉዳዮችን የሚዳስሱ 12 የሙዚቃ ስራዎችን ይዟል።
ድምጻዊ መሳይ ተፈራ ካሣ ከዚህ ቀደም አሰብኩት ፣ ፋሽን፣ብርቄ ነሽ፣ ደግዬ ፣ በጣም እንጂ በጣም እና ሌሎችንም ነጠላ ሙዚቃዎች ለአድማጮች አድርሷል።
ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
የድምፃዊ መሳይ ተፈራ ካሣ "የልቤን "የተሰኘ የመጀመሪያ አዲስ አልበም ዛሬ ቅዳሜ ሰኔ 1 2016 ዓ.ም በራሱ Mesay Tefera የዩቲዩብ ቻናል እና በዓለማቀፍ መተግበሪያዎች ላይ ተለቋል።
በሙዚቃ አልበሙ ላይ ወጣትና አንጋፋ የግጥምና ዜማ ደራሲያን የተሳተፉበት ሲሆን ከእነዚህ መካከል ድምፃዊ ጎሳዬ ተስፋዬ ፣ ሞገስ ተካ ፣ አቤል ሙሉጌታ ፣ ናትናኤል ግርማቸዉ ፣ አቡዲ ፣ምህረታብ ደስታ፣ አንተነህ ምናሉ ፣ወንድወሰን ይሁብ ይገኙበታል።
በቅንብር ሚክሲንግና ማስተሪንግ የሙዚቃ ባለሙያዎች ሚካኤል ኃይሉ (ሚኪ ጃኖ) ታምሩ አማረ (ቶሚ) አቤል ጳውሎስና ኪሩቤል ተስፋዬ ተሳትፈውበታል።
ኤቨንት ድረገፅ እንደተመለከተው አምስት ዓመታት የፈጀው አልበሙ በውስጡ ቻል ቻል ፣የብቻዬ ፣ቆንጆ ነሽ፤ደህና ይግጠምሽ፤ ማካሪና ፤ ከአባይ ማዶ ፤ውረጅ ካናቴ ፤ የልቤን ፤ግድ የለሽም፤ ኸረ ተይ፤አይ አለማወቋ፤ አወሰድማዬ፤ እሳቱ የተሰኙ ርዕሰ ያላቸው የተለያዩ ጉዳዮችን የሚዳስሱ 12 የሙዚቃ ስራዎችን ይዟል።
ድምጻዊ መሳይ ተፈራ ካሣ ከዚህ ቀደም አሰብኩት ፣ ፋሽን፣ብርቄ ነሽ፣ ደግዬ ፣ በጣም እንጂ በጣም እና ሌሎችንም ነጠላ ሙዚቃዎች ለአድማጮች አድርሷል።
ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
የጋዜጠኛ መኮንን ወ/አረጋይ "እነሆ ማሟሻ" የተሰኘ አዲስ መጽሐፍ በሚቀጥለው ሳምንት ለንባብ ይበቃል
ከዚህ ቀደም በሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ ላይ በሚያቀርባቸው የስንክሳር፣ የማሟሻ፣ የሃኪሞ መልዕክት፣ የአርብ ምሽት ቆየት ያሉ ሙዚቃዎች እና አሁን ላይ በኢንቢሲ ቴሌቪዥን በልዩ ልዩ ዝግጅቶች የምናውቀው ጋዜጠኛ መኮንን ወ/አረጋይ "እነሆ ማሟሻ" የተሰኘ የመጀመሪያ ቅጽ አዲስ መጽሐፍ በሚቀጥለው ሳምንት ለንባብ ያበቃል።
ጋዜጠኛ መኮንን ወልደአረጋይ ስለመጽሐፉ በመግቢያው "በተለይም በራዲዮና በቴሌቪዥን የቀረበ መሰናዶዎቹን ያደመጡና የተመለከቱ ወዳጆቼ ይህ ቁም ነገር ተሰንዶ በህትመት ቢቀርብ እጅግ ጠቃሚ እንደሆነ ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ ሳያስገነዘበ ቦዝነው አያውቁም፡፡ እናም ዛሬ ጊዜው ደርሶ የመጀመሪያውን ቅጽና ለሌሎች ሥራዎች ዓይን ገላጭ የሆነውን "እነሆ ሟሟሻ" እንካችሁ ብያለሁ" ብሏል።
መጽሐፉ በ200 ገፆች የተነበበ ሲሆን በ250 ብር የጀርባ ዋጋ ለአንባቢያን እንደሚደርስ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ሰምቷል።