Event Addis Media – Telegram
Event Addis Media
9.61K subscribers
6.13K photos
14 videos
4 files
4.75K links
Connect with Addis artistic community!

Website: https://eventaddis.com

Contact: @Tmanaye
Download Telegram
ኤቨንት አዲስ/ሁነት አዲስ ዛሬ ሁለት ዓመት ሞላው

ሚዲያችን Event Addis/ሁነት አዲስ የኩነት እና መዝናኛ መረጃዎች ምንጭ መሆን ከጀመረ ዛሬ ግንቦት 29 2016 ዓ.ም ሁለተኛ ዓመቱን አስቆጠረ።

እንኳን አደረሰን ፣ እንኳን አደረሳችሁ !

በእነዚህ ሁለት ዓመታት ያለማቋረጥ በየዕለቱ የሥነጽሑፍ ፣ የኪነጥበብ ፣ የሥነጥበብ፣ የኩነት እና ሚዲያ መረጃዎችን ለተከታዮቹ በፍጥነት እና በጥራት እያቀረበ ነው።

ሚዲያዎችን ኤቨንት አዲስ/ሁነት አዲስ በኢትዮጵያ ለሚገኙ የቴሌቪዥን ጣቢያዎች፣ የሬድዮ ጣቢያዎች እና ዝግጅቶች ፣ የማህበራዊ ትስስር ገፆችና ጋዜጦች ሁነኛ የመዝናኛ መረጃዎች ምንጭ በመሆን እያገለገለ ይገኛል።

በእነዚህም ሁለት ዓመታት በኢትዮጵያ የሁነት (Event) እና ኪነት( Art) መረጃዎች ላይ የሚታየውን ክፍተት ለመድፈን እጅግ ጥቂትም ቢሆንም ጥረት እያደረገን እንገኛለን።ይህም ጥረታችን ይቀጥላል።

በቀጣይም እንኑር ያኑርን እያለን በተለያዩ የሚዲያ አማራጮች በጥራት እና በተሻለ አቀራረብ እኛን እኛን የሚሸቱ ፕሮግራሞች ይዘን እንመጣለን።

በቅርቡም ሚዲያችን በዩቲዩብ ፣ በቲክቶክ ፣ እና በሬድዮ ፕሮግራም አማራጮች ልዩ ልዩ ዝግጅቶችን ማቅረብ እንደሚጀምር ስናበስራችሁ በታላቅ ደስታ ነው።

መልካም በዓል ለኤቨንት አዲስ

📍ኪነት እና ኩነት

ለሃሳብና አስተያየት: @Tmanaye

የEventAddis/ሁነት አዲስ ማኅበራዊ ገፆቻችን

Telegram:https://news.1rj.ru/str/EventAddis1

Website: https://eventaddis.com

Facebook:https://facebook.com/groups/2009372275938661/

Facebook Page:https://www.facebook.com/profile.php?id=100083170462851&mibextid=ZbWKwL
ግንቦት 30 ሀገር አቀፍ የምስጋና ቀን

በጣፋጭ ህይወት መልቲሚዲያ በየዓመቱ የሚዘጋጅው "የጣፋጭ ህይወት የምስጋና ሽልማት" ዘንድሮ ለአራተኛ ጊዜ ነገ ግንቦት 30 2016 ዓ.ም በስካይላት ሆቴል ይካሄዳል።

በሀገር አቀፍ ደረጃም ግንቦት 30 የምስጋና ቀን ሆኖ እንዲቀጥል ለ4ተኛ ዙርም በሀገር አቀፍ ደረጃ ነገ ግንቦት 30 2016 ዓ.ም የምስጋና ቀን ሆኖ ይውላል።

የዚህም ቀን አንዱ አካል የሆነው"እኔም የማመሰግነው ሰው አለኝ" የተሰኘ የማኅበራዊ ትስስር ገፅ ንቅናቄ (ቻሌንጅ) በይፋ ተጀምሮአል።በዚህም "ቻሌንጅ" በተለያየ  መንገድ መልካም ስራ የሰሩ ሰዎች ይመሰገኑበታል።

ግንቦት 30 ከጠዋት ጀምሮ እስከ አመሻሽ ድረስ የምንመሰጋገንበት ቀን ሆኖ እንደሚውልም የተገለፀ ሲሆን የተያዘውን እቅድም ለማሳካት ሁሉም የማኀበረሰብ ክፍል በጋራ መስራት አለበት ተብሏል።

የ"ጣፋጭ ህይወት የምስጋና ሽልማት" አመሻሽ ላይ የሚካሄድ ሲሆን ይህም የሽልማት ሥነሥርዓት በሀገሬ ቴሌቪዥን በቀጥታ ስርጭት ይተላለፋል።

Telegram:https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
የዓለማችን ተጠቃሽ የኤሌክትሪክ መኪኖች አምራች የ"ሆን ዞ" አውቶ ፋክተሪ የኢትዮጵያና ምስራቅ አፍሪካ ብቸኛ ወኪል ኢትዮፒካር ብራንድ የኤሌክትሪክ መኪኖችን በብድር አስረከበ።

መኪኖቹ የግሎባል የገንዘብ ቁጠባና ብድር ተቋም አባል የሆኑና 30% ቁጠባን ለቆጠቡ ነው የተሰጠው።

በኤሌክትሪክ የሚሰሩ መኪኖች በበርካታ ሃገራት ተመራጭነታቸው ከዕለት ወደ ዕለት እየጨመረ ይገኛል ኢትዮጵያም እንደ ሃገር የውጭ ምንዛሬ እጥረትን ብሎም የአየር ንብረትን ለመጠበቅ ይረዳ ዘንድ የኤሌክትሪክ መኪናን እንደ አማራጭ የመጠቀም ፓሊሲን ከመተግበር ባለፈ በሃገራችን የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ፍላጎት ከፍተኛ እየሆነ መጥቷል።

የዜጎችን ኑሮ ባማከለ መልኩ በባንክ ብድር አማራጭ እየቀረቡ የሚገኙት እነዚህ የኤሌክት መኪኖች የፋብሪካ ዋስትና ያላቸውም ናቸው።

ለዚህም በዛሬው ዕለት ግንቦት 29 ቀን 2016 ዓ.ም ኢትዮፒካር ብራንድ ከግሎባል የገንዘብ ቁጠባና ብድር ተቋም ጋር የኤሌክትሪክ መኪኖችን ለተቋሙ አባላት በብድር መስጠት የሚያስችል ስምምነት ፈፅሟል፡፡
 
በዚህ ስምምነት መሰረትም የ"ሆን ዞ" አውቶ ፋክተሪ የኢትዮጵያና ምስራቅ አፍሪካ ብቸኛ ወኪል ኢትዮፒካር የግሎባል የገንዘብ ቁጠባና ብድር ተቋም አባላት የሚፈልጓቸውን የኤሌክትሪክ መኪኖች ምቹ እና ቀልጣፋ በሆነ መልኩ በብድር  እንደሚሰጥ ''የኢቲዮፒካር'' ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሳሙኤል አዲስአለም  ገልፀዋል።

በተጨማሪም ዛሬ ግንቦት 29/2016 ዓም  ኢትዮፒካር የግሎባል የገንዘብ ቁጠባና ብድር ተቋም አባላት ለሆኑና የብድር መስፈርቱን አሟልተው 30 በመቶ ቁጠባ ለፈፀሙ አባላት የኤሌክትሪክ መኪኖችን አስረክቧል።

Telegram:https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
ኤም ኤን ጂ ፊልም ፕሮዳክሽንና ኢንቨስትመንት የአፍሪካ ጽህፈት ቤቱን ሰኞ ያስመርቃል

ከቴክኖሎጂ ጋር ዝምድና የፈጠረ፣ ዓለም አቀፍ  የፊልም ማህበረሰብን የመፍጠር ግብ የሰነቀው  ኤም ኤን ጂ የፊልም ኩባንያ በኢትዮጵያ ሥራውን በይፋ ሊጀምር ነው።

ኤም  ኤን ጂ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከሚታወቁ የፊልም አምራቾች የተወሰነውን ገበያ በመግዛት መልሶ በስቶክ ማርኬት የሚሸጥ ኩባንያ ነው፡፡ 

ይህ የፊልም ኩባንያ፣ ሲኒማቶግራፊን ከዘመኑ ቴክኖሎጂ ጋር እንዴት ማቆራኘት እንደሚቻልና  የፊልም ኢንዱስትሪንም ለማሳደግ የሚያስችሉ ዘዴዎችን የሚቀይስ ነው ተብሏል።

ኤም ኤን ጂ ኩባንያ በአፍሪካ በይፋ የከፈተውን የኢትዮጵያ ጽህፈት ቤቱን ሰኞ ሰኔ 3 2016 ከቀኑ 9:00  ጀምሮ በማዶ ሆቴል ያስመርቃል፡፡

በዚህ ዕለትም ከፊልም ሙያ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ያላቸው ባለሙያዎችና የሚዲያ ሰዎች ይታደማሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ተወዳጅ ሚዲያ እና ኮሚኒኬሽን ከፓፓራዚ ማስታወቂያ ጋር በትብብር ያዘጋጁት እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል፡፡

📍መረጃው የተወዳጅ ሚዲያ ነው

Telegram:https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
ሔሎ ኢትዮጵያ የሬድዮ ፕሮግራም እውቅና ተሰጠው

በዳጉ ኮምኒኬሽን ፒኤልሲ እየተዘጋጀ በአንጋፋው ኤፍ ኤም አዲስ 97.1 የሚተላለፈው "ሔሎ ኢትዮጵያ" የሬድዮ ፕሮግራም ከአርማወር ሐንሰን የምርምር ኢንስቲትዩት እውቅና ተሰጥቶታል።

54 ዓመታትን ያስቆጠረው አርማወር ሐንሰን የምርምር ኢንስቲትዩት በርካታ የምርምር ውጤቶችን በማውጣትና ለሀገራችን ብሎም ለዓለም አስተዋፅኦ በማድረግ ላይ የሚገኝ ተቋም ነው።

ግንቦት 29 እና 30 2016 ዓ.ም በአዲስ አበባ አህሪ አለርት የጤና መንደር እና በአዳማ በሚገኘው የወባና ትኩረት የሚሹ ቆላማ በሽታዎች የምርምርና ስልጠና ማዕከል ውስጥ በተካሄደው ጉባኤ ላይ የአርማወር ሐንሰን የምርምር ኢንስቲትዩት (አህሪ) ላለፉት 54 ዓመታት በጤናው ዘርፍ የምርምር ልማትን ለማሳደግ እንዲያስችል በርካታ የምርምር ውጤቶችን በማውጣትና ለሀገራችን ብሎም ለአለም አስተዋፅኦ በማድረግ ላይ እንደሚገኝ ተገልጿል።

በኢንስቲትዩቱ መድኃኒት የተላመደ የቲቢ ሕክምናን ከ24 ወራት ወደ 9 ወራት ዝቅ የሚያደርግ የምርምር ውጤት መገኘቱ የተገለፀ ሲሆን የምርምር ውጤቱ በዓለም ጤና ድርጅት እውቅና ተሰጥቶታል።

በዚህ ጉባኤ ላይ ለሚዲያ ተቋማት እውቅና የተሰጠ ሲሆን ከእነዚህም የሚዲያ ተቋማት መካከል ሔሎ ኢትዮጵያ የሬድዮ ፕሮግራም አንደኛው ነው።

እውቅናውን በቦታው በመገኘት የሔሎ ኢትዮጵያ ባልደረባ ጋዜጠኛ ናትናኤል ደበና በክብር ተቀብሏል።

Telegram:https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
"ጣፋጭ ህይወት የምስጋና ሽልማት" በድምቀት ተካሄደ

በጣፋጭ ህይወት መልቲሚዲያ በየዓመቱ የሚዘጋጅው "የጣፋጭ ህይወት የምስጋና ሽልማት" ዘንድሮ ለአራተኛ ጊዜ  ግንቦት 30 2016 ዓ.ም በስካይላት ሆቴል ተካሄዷል።

አርብ አመሻሽ ላይ የተካሄደው"የጣፋጭ ህይወት የምስጋና ሽልማት" በስድስት ዘርፎች ልዩ ልዩ ተሸላሚዎችን ሸልሟል።

የዘንድሮው የአራተኛው የጣፋጭ ህይወት የምስጋና ሽልማት የተሸላሚዎች ዝርዝር የሚከተለውን እንደሚመለስ ኤቨንት አዲስ ድረገጽ ተመልክቷል።

1.ስራ ፈጠራን ተግባር ዘርፍ ተሸላሚ: ኢ/ር ቢጃይ ናይከር

2. ተስፋ የሚጣልበት/የሚጣልባት ስራ ፈጣሪ ዘርፍ ተሸላሚ: ቤተልሔም ደሴ

3.በበጎ አድራጎት ተቋማት ዘርፍ ተሸላሚ: ይመለከተኛል የበጎ አድራጎት ተቋም

4. በበጎ አድራጎት ተቋማት ዘርፍ (በግል): ሚኪያስ ለገሰ

5.የህይወት ክህሎት አሰልጣኝ (በተግባር ዘርፍ ) ተሸላሚ: ሔኖክ ሐ/ማርያም (ኒው ላይፍ )

6.ተስፋ የሚጣልበት/የሚጣልባት የህይወት ክህሎት አሰልጣኝ ተሸላሚ: ሰላም አታላይ (ቡና ፖድካስት)

7.ዝናን ለመልካም ምግባር በመጠቀም ዘርፍ ተሸላሚ: አርቲስት መቅደስ ፀጋዬ

8.ሚዲያውን ለሥነልቦና ግንባታ ዘርፍ ተሸላሚ: መጽሔተጥበብ የሬድዮ ፕሮግራም

9.ማህበራዊ ሚዲያውን ለበጎ ምግባር በመጠቀም  በቲክቶክ ዘርፍ ተሸላሚ : መምህርት ዙፋን ታምር (ሚስ ዙፋን)

10.ማህበራዊ ሚዲያን በበጎ በመጠቀም በዩቲዩብ ዘርፍ ተሸላሚ: መሪ ፖድካስት

11. ልዩ ተሸላሚ: ማስተር ካርድ ፋውንዴሽን

ለተጨማሪው: @EventAddis1
ወጣቷ ድምጻዊት ሀና ግርማ ''ባንተ ላይ'' በተሰኘ ስራዋ የናሆም ሪከርድስን ሪከርድ ሰብራለች

ድምፃዊት ሀና ግርማ ከ9 ወራት በፊት በሰራችው ስራ ከሰሞኑ የናሆም ሪከርድስን ሪከርድ ሰብራለች ።

የተለያዩ ቪዲዮ ክሊፖችን እና ፊልሞችን ዳይሬክት እያደረገች የምትገኘው አዩ ግርማ ቪድዮውን ሰርተዋለች። አቡዱ ግጥምና ዜማውን ሰርቶ ታምሩ አማረ  ሙዚቃውን አቀናብሮታል ። ሃና ግርማ ደግሞ በነሀሴ ወር 2015 ላይ አቀንቅናው በአንድ ግዜ በሙዚቃ አፍቃሪው ተወዳጅነትን አግኝቶላታል ።

''ባንተ ላይ''ሙዚቃው በናሆም ሪከርድስ በተለቀቀ 9 ወሩ 20 ሚሊዮን እይታ አግኝቷል።ይህም ኩባንያው ቪድዮዎችን መልቀቅ ከጀመረ ጊዜ አንስቶ በአጭር ጊዜ ውስጥ ከፍተኛ ተመልካች በማግኘት ቀዳሚ ሆኗል።

ናሆም ሪከርድስ በዩቲዩብ ከለቀቃቸው ስራዎች በቀዳሚነት ላይ የሚገኘው የታሪኩ ጋንኪሳ ዲሽታ ጊና ሲሆን 35 ሚሊዮን ጊዜ ታይቷል። ይህ ስራ በዚህ ቁጥር የታየው በ3 አመት ውስጥ ነው። የሃና ግን በ9 ወራት ነው 20,000,000 የታየው። የቬሮኒካ አዳነ "ጥፍጥ አለኝ" ከሁለት አመት በፊት ተለቆ 18 ሚሊየን ጊዜ ታይቶ ናሆም ከለቀቃቸው ስራዎች ብዙ እይታ በማግኘት 3ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

📍መረጃው የሁሉ አዲስ ነው።

ለተጨማሪው: @EventAddis1
የድምፃዊ መሳይ ተፈራ "የልቤን" አልበም ተለቀቀ

የድምፃዊ መሳይ ተፈራ ካሣ "የልቤን "የተሰኘ የመጀመሪያ አዲስ አልበም ዛሬ ቅዳሜ ሰኔ 1 2016 ዓ.ም በራሱ Mesay Tefera የዩቲዩብ ቻናል እና በዓለማቀፍ መተግበሪያዎች ላይ ተለቋል።

በሙዚቃ አልበሙ ላይ ወጣትና አንጋፋ የግጥምና ዜማ ደራሲያን የተሳተፉበት ሲሆን ከእነዚህ መካከል ድምፃዊ ጎሳዬ ተስፋዬ ፣ ሞገስ ተካ ፣ አቤል ሙሉጌታ ፣ ናትናኤል ግርማቸዉ ፣ አቡዲ ፣ምህረታብ ደስታ፣ አንተነህ ምናሉ ፣ወንድወሰን ይሁብ ይገኙበታል።

በቅንብር ሚክሲንግና ማስተሪንግ የሙዚቃ ባለሙያዎች ሚካኤል ኃይሉ (ሚኪ ጃኖ) ታምሩ አማረ (ቶሚ) አቤል ጳውሎስና ኪሩቤል ተስፋዬ ተሳትፈውበታል።

ኤቨንት ድረገፅ እንደተመለከተው አምስት ዓመታት የፈጀው  አልበሙ በውስጡ ቻል ቻል ፣የብቻዬ ፣ቆንጆ ነሽ፤ደህና ይግጠምሽ፤ ማካሪና ፤ ከአባይ ማዶ ፤ውረጅ ካናቴ ፤ የልቤን ፤ግድ የለሽም፤ ኸረ ተይ፤አይ አለማወቋ፤ አወሰድማዬ፤ እሳቱ የተሰኙ ርዕሰ ያላቸው የተለያዩ ጉዳዮችን የሚዳስሱ 12 የሙዚቃ ስራዎችን ይዟል።

ድምጻዊ መሳይ ተፈራ ካሣ ከዚህ ቀደም  አሰብኩት ፣ ፋሽን፣ብርቄ ነሽ፣ ደግዬ ፣ በጣም እንጂ በጣም እና ሌሎችንም ነጠላ ሙዚቃዎች ለአድማጮች አድርሷል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
የጋዜጠኛ መኮንን ወ/አረጋይ "እነሆ ማሟሻ" የተሰኘ አዲስ መጽሐፍ በሚቀጥለው ሳምንት ለንባብ ይበቃል

ከዚህ ቀደም በሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ ላይ በሚያቀርባቸው የስንክሳር፣  የማሟሻ፣ የሃኪሞ መልዕክት፣ የአርብ ምሽት ቆየት ያሉ ሙዚቃዎች እና አሁን ላይ በኢንቢሲ ቴሌቪዥን በልዩ ልዩ ዝግጅቶች የምናውቀው ጋዜጠኛ መኮንን ወ/አረጋይ "እነሆ ማሟሻ" የተሰኘ የመጀመሪያ ቅጽ አዲስ መጽሐፍ በሚቀጥለው ሳምንት ለንባብ ያበቃል።

ጋዜጠኛ መኮንን ወልደአረጋይ ስለመጽሐፉ በመግቢያው "በተለይም በራዲዮና በቴሌቪዥን የቀረበ መሰናዶዎቹን ያደመጡና የተመለከቱ ወዳጆቼ ይህ ቁም ነገር ተሰንዶ በህትመት ቢቀርብ እጅግ ጠቃሚ እንደሆነ ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ ሳያስገነዘበ ቦዝነው አያውቁም፡፡ እናም ዛሬ ጊዜው ደርሶ የመጀመሪያውን ቅጽና ለሌሎች ሥራዎች ዓይን ገላጭ የሆነውን "እነሆ ሟሟሻ" እንካችሁ ብያለሁ" ብሏል።

መጽሐፉ በ200 ገፆች የተነበበ ሲሆን በ250 ብር የጀርባ ዋጋ ለአንባቢያን እንደሚደርስ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ሰምቷል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
የተስፋ የኪነ-ጥበብ ኢንተርፕራይዝ 25ተኛ ዓመት ክብረበዓል የመዝጊያ ዝግጅት በሚቀጥለው ሳምንት ይካሄዳል

የተስፋ የኪነ-ጥበብ ኢንተርፕራይዝ 25ተኛ ዓመት ክብረበዓል የመዝጊያ ዝግጅት በሚቀጥለው ሳምንት ሰኔ 13 ቀን 2016 ዓ.ም በኢንተር ሌግዤሪ ሆቴል በልዩ ልዩ ሥነሥርዓት ይካሄዳል።

በመዝጊያ ዝግጅቱም አንጋፋና ወጣት የኪነጥበብ ባለሙያዎች በተስፋ የኪነጥበብ ኢንተርፕራዝ ይሸለማሉ።ከተስፋ ጋር አብረው የሰሩ ድርጅቶችም እውቅና ይሰጣቸዋል ተብሏል።

ተስፋ የኪነ-ጥበብ ኢንተርፕራይዝ 25ተኛ ዓመት ክብረ በዓሉን አስመልክቶ በጎ ስራዎችን የጀመረው ከታህሳስ 1-29 ከሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ ጋር “በሊፍት ከፍዬ እሳፈራለሁ የጎዳና ልጅ አነሳለሁ” በሚል የገቢ ማሰባሰቢያ ስራ ነበር።

ጥር 10  ቀን 2016 ዓ.ም በኢትዮጵያ በብሔራዊ ቴአትር “ቤርሙዳ” የተሰኘውን ቴአትር፤ ሚያዚያ 28  ቀን “ሀሁ ወይም ፐፑ” ቴአትርን በልዩ ፕሮግራም ለኪነ-ጥበብ አፍቃሪው አቅርቧል፡፡

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
አርቲስት ድርብወርቅ ሰይፉ የክብር እንግዳ የሆነችበት "መቅረዝ ሥነኪን" የኪነጥበብ ዝግጅት ሀሙስ ይካሄዳል

አንጋፋ እና ወጣት የኪነጥበብ ባለሞያዎችን እያጣመር የዘለቀው መቅረዝ ሥነኪን ወርሀዊ የኪነጥበብ  ዝግጅት ሀሙስ ሰኔ 6 2016 ዓ.ም ከምሽቱ 11:00 ጀምሮ በብሔራዊ ቤተመጻሕፍትና ቤተመዛግብት አገልግሎት (ወመዘክር )አዳራሽ ውስጥ ይካሄዳል።

በዕለቱም እረኛዬን ጨምሮ በተለያዩ ፊልሞቿና ድራማዎቿ የምናውቃት አርቲስት ድርብወርቅ ሰይፉ የክብር እንግዳ ሆና የምትገኝ ሲሆን በተጨማሪም ወጣት የኪነጥበብ ባለሞያዎች የግጥም ፣የሙዚቃ እና  የዳንስ ስራዎቻቸውን ያቀርባሉ።

የዚህ ዝግጅት መግቢያ በነፃ ነው።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
የያሬድ የሙዚቃ ት/ቤት የመጀመሪያው ዳይሬክተር በሆኑት ፕ/ር አሸናፊ ከበደ ስም የተሰየመው የጥበብ ማዕከል ተመረቀ

ፕ/ር አሸናፊ ከበደ በመጀመርያ ዳሬክተርነት ባገለገሉበት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሚገኘው የያሬድ ሙዚቃ ትምህርት ቤት  በስማቸው የተሰየመው ፕሮፌሰር "አሸናፊ ከበደ የሙዚቃዊ ጥበባት ማዕከል" ባሳለፍነው ቅዳሜ ሰኔ 1 2016 ዓ.ም ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆኗል።

ይህም የሙዚቃዊ ጥበባት ማዕከል በርካታ ሙዚቀኞችን እና የሙዚቃ ታዳሚያንን መያዝ የሚችል ሲሆን በሀገራችን ለሙዚቃ ማቅረቢያ የተሰራ ግዙፍና የመጀመሪያው ማዕከል እንደሆነ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ሰምቷል።

የሙዚቃ ሊቁ ፕ/ር አሸናፊ ከበደ በኢትዮጵያ ዘመናዊ ሙዚቃ ውስጥ ትልቅ አሻራ ያሳረፉ እና ዘመን አይሽሬ የሙዚቃ ሥራዎችን ያበረከቱ የሙዚቃ ሊቅ እንደነበሩ ይነገራል።

እረኛው ባለዋሽንት፣ የኢትዮጵያ ሰላም፣ የፍቅር አንሰር ፣ የእሳት እራት፣ የተማሪ ፍቅር ፣ የሀገራችን ሕይወት ፣ ኒርቫኒክ ፋንታሲ የተሰኙ ረቂቅ ሙዚቃዎችን ለአድማጭ ጆሮ  ያደረሱ የሙዚቃ ደራሲ አቀናባሪና ኮንዳክተር ናቸው።

በተጨማሪም የሙዚቃ ሰዋሰው የመማርያ መፅሀፍ በአማርኛ፣ ኮንፌንሽን ልቦለድ እንዲሁም Root of Black Music የተሰኙ መጽሐፍትም ለአንባቢያን አድርሰዋል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
"እያዩ ፈንገስ" ለሁለት ቀናት ብቻ ሊታይ ነው

በበረከት በላይነህ ተደርሶ በግሩም ዘነበ የሚተውነው "እያዩ ፈንገስ" የአንድ ሰው  ተውኔት መድረክ ላይ መቅረብ ከጀመረ ዘንድሮ አስር ዓመት እንደሚሞላው አዘጋጆቹ አስታውቀዋል።

ይህንን የአስርኛ ዓመት ክብረበዓል በማሰብ ረቡዕ ሰኔ 5 እና አርብ ሰኔ 7 2016 ዓ.ም ከምሽቱ 12:00 ጀምሮ በራስ ሆቴል ለሁለት ቀናት ብቻ "እያዩ ፈንገስ" የአንድ ሰው ተውኔት ለታዳሚያን እንደሚቀረብ ኤቨንት አዲስ ድረገጽ ሰምቷል።

"እያዩ ፈንገስ" የአንድ ሰው ተውኔት "አጀንዳዬ"  "ፌስታሌ" እና በቅርቡ ከመድረክ በታገደው "ቧልቲካ" በሚሉ ርዕሶች በተለያዩ መድረኮች ለታደሚያን ሲቀረብ ቆይቷል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
"ምን ሆኛለሁ?" መጽሐፍ በቅርቡ ለንባብ ይበቃል

የሥነልቦና ባለሞያዋ ትዕግስት ዋልተንጉስ እና ጋዜጠኛና ደራሲ ቴዎድሮስ ተክለአረጋይ የተጣመሩበት 'ምን ሆኛለሁ?' መፅሀፍ በጣም በቅርቡ ታትሞ ይወጣል ተብሏል።

"የምታደርጉት ድርጊት ግራ አጋብቷችሁ 'ምን ሆኛለሁ?' ብላችሁ ከጠየቃችሁ ይሄ መፅሀፍ ልጅነታችሁን በመመርመር ራሳችሁን በተሻለ እንድትረዱ ያግዛችኋል"።

በተጨማሪም "በዙሪያችሁ ያሉ ሰዎች ወይም በቲቪ የምታውቋቸው ነጋዴዎች፣ ፖለቲከኞች፣ ታዋቂ ሰዎች የሚያደርጉት ድርጊት አልገባ ብሏችሁ 'ምን ሆኖ ነው?' ወይም 'ምን ሆና ነው?' የሚል ጥያቄ ከፈጠረባችሁ ይሄ መፅሀፍ ጥሩ የፅንሰ ሀሳብ መነፅር ይሰጣችኋል " ስለመባሉ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ሰምቷል።

"ምን ሆኛለሁ" የተሰኘውን መጽሐፍ ብዙዎች መፅሀፉን ቀድመው እየገዙ እንደሆነም ተመልክተናል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
በእስር ላይ የሚገኘው መራሔ ተውኔት ዳግማዊ አመለወርቅ ፈይሳ በጽኑ ስለመታመሙ ተሰምቷል

ከመጋረጃ ጀርባ ፣እብድት በህብረት  የተሰኙ ተውኔቶችን ጨምሮ የተለያዩ ተውኔቶች ሲያዘጋጅ የምናውቀው መራሔ ተውኔት ዳግማዊ አመለወርቅ ፈይሳ ከሰሞኑ በታሰረበት ሦስተኛ ፖሊስ ጣቢያ በፅኑ ህመም ላይ እንደሚገኝ እና ዛሬ ሰኔ 2 2016 ዓ.ም ወደ ህክምና ቦታ እንደተወሰደ ኤቨንት አዲስ ድረገጽ ከቅርብ ምንጮች ሰምቷል።

አንጋፋው ከያኒ ዳግማዊ አመለወርቅ ፈይሳ ለረጅም ጊዜ የስኳር ህመምተኛ እንደሆነ የተገለፀ ሲሆን ክሱን ከእስር ቤት ውጪ ሆኖ እንዲከታተል ቤተሰቦቹ ለፖሊስ ጥያቄ ማቅረባቸው ተነግሯል።

በቅርቡ በፖሊስ ተይዞ ለእስር የበቃው የ"እብደት በሕብረት" ቴአትር አዘጋጅ አንጋፋው ከያኒ ዳግማዊ ፈይሳ ባለፈው ሳምንት ግንቦት 28 2016 ዓ.ም ለመጀመሪያ ጊዜ ፍርድ ቤት የቀረብ ሲሆን አርቲስት አማኑኤል ሀብታሙን ጨምሮ ሌሎች 20 ሰዎችን በአንድ መዝገብ ለፌደራል መደበኛ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ  ቀጠሮ ወንጀል ችሎት ቀርበው ሁሉም ለሰኔ 11 ቀን 2016 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ እንደተሰጣቸው ይታወሳል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
"እውቀትን ፍለጋ መጻሕፍት መደብር"

እውቀትን ፍለጋ መጻሕፍት መደብር አዳዲስና ቆየት ያሉ የአማርኛ እና እንግሊዝኛ መጻሕፍትን አቅርቦላቸዋል።

የፍልስፍና ፣ የታሪክ ፣ የልቦለድ ፣ የትምህርት መማሪያ ፣የልጆች እና የሙያ መጻሕፍትን በብዛትና እጅግ በተመጣጣኝ ዋጋ ታገኛላችሁ።

አድራሻቸው: ገርጂ ታክሲ ተራ (ዓለም ጋለሪ አካባቢ )

ስልክ : 0913624488
ወይም :0913825404

የቴሌግራም ገጻቸው:
https://news.1rj.ru/str/book1219
"ዱባይ እንደምን ሠለጠነች?" የተሰኘ አዲስ መጽሐፍ ከሰሞኑ ለንባብ በቅቷል

በዱባዮ ገዢ ሼኽ መሀመድ ቢን ረሺድ አል መክቱም ህይወት ዙሪያ የሚያጠነጥነው"My Story"መጽሐፍ በጋዜጠኛ ናትናኤል ከበደ "ዱባይ እንደምን ሠለጠነች" በሚል ርዕስ ተተርጉሞ ለንባብ በቅቷል።

መፅሀፉ የዱባዩ ገዢ እና የተባበሩት አረብ ኤምሬት ጠቅላይ ሚኒስትር ህይወት ዙሪያ የተፃፈ ቢሆንም ከ ሼኽ መሀመድ ህይወት ባሻገር በውስጡ ብዙ ርዕሰ ጉዳዮች እንደያዘ የሚናገረው ተርጓሚው አያይዞም መፅሀፉ በዋናነት ለሀገራችን ለኢትዮጵያ ትምህርት ሊሆን የሚችል የዱባይ የሀገር ምስረታ ፣አለም ላይ ታዋቂ የሆኑት ተቋማቸውን እንዴት እንደገነቡ ፣ዲፕሎማሲ፣ከነዳጅ ባሻገር ስላለው የአመራር ክህሎት እና ልህቀት እንደሚያወሳ ተናግሯል።

50 ምዕራፎች የያዘው መጽሐፉ በ400 ብር የጀርባ ዋጋ ለአንባቢያን ቀርቧል።

መጻሐፉም ሜክሲኮ ጃፈር መፅሀፍት መደብር እና 4 ኪሎ እነሆ መፅሀፍት መደብር ይገኛል።

Telegram:https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
"እሳት ወይ አበባ" ተውኔት ወደ መድረክ ሊመለስ ነው

በሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን ግጥሞች ላይ የተመሰረተው "እሳት ወይ አበባ" ግጥማዊ ዳንስ ተውኔት በብሔራዊ ቴአትር ከሰኔ 14 2016 ዓ.ም ጀምሮ ወደ መድረክ እንደሚመለስ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ሰምቷል።

"እሳት ወይ አበባ" የሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን ግጥሞች ላይ መሰረት ያደረገ የግጥማዊ ዳንስ የሙከራ (Experimental) ቴአትር ነው።

ይህ ሙከራዊ ተውኔት ባሳለፍነው ጥቅምት 2 2016 ዓ.ም ነበር ዘወትር አርብ ሲቀረብበት ከነበረው የአንጋፋው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር መድረክ የተሰናበትው።በምትኩም "የሁለት አሽከር ጌቶች" የተሰኘ ተውኔት ሲቀርብም ቆይቷል።

ኤቨንት አዲስ ድረገፅ እንዳረጋገጠው በሚቀጥለው ሳምንት ሰኔ 14 2016 ዓ.ም "እሳት ወይ አበባ " ተውኔት ወደ መድረክ ተመልሶ በቋሚነት ዘወትር አርብ በ11:30 መቅረብ ይጀምራል ተብሏል።

ይህ ግጥማዊ ድራማ ከዚህ ቀደም በሀገር ፍቅር ቴአትር ትንሿ አዳራሽ ለታደሚያን ይቀርብ እንደነበር ይታወሳል።

📍መረጃውን ሲጠቀሙ ምንጭ ይጠቀሱ !

ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
በነፃ የተዘጋጀው የሮፍናን ማስተር ክላስ

ሁለገቡ ሙዚቀኛ ሮፍናን ኑሪ በሐዋሳና አካባቢ ለሚገኙ ወጣት የሙዚቃ ባለሞያዎች እና ተያያዥ የስራ መስክ ውስጥ ለሚገኙ ሁሉ "የሮፍናን ማስተር ክላስ" ስልጠና ጥሪ አስተላልፏል።

ሙዚቀኛ ሮፍናን ኑሪ ለሚመለከተው ሁሉ ተከታዩን መልዕክት በማህበራዊ ትስስር ገፁ አስተላልፏል:

"በሐዋሳ እና አካባቢው ምትገኙ የማስተር ክላሱን የትምህርት እና በተግባር የታገዘ ልምድ ልውውጥ ለመካፈል የምትፈልጉ ወጣት ጀማሪ ሙዚቀኞች: አቀናባሪዎች : ድምፃዊያን : የግጥም እና ዜማ ደራሲዎች : ዲጄዎች : የድምፅ ቅጂ እና ማስተሪንግ ኢንጂነሮች : እንዲሁም በኢንተርቴመንት ማርኬቲንግ ስራ ላይ ለተሰማራችሁ የማርኬቲንግ ባለሙያዎች እድሉ ለሚፈቅደው የ150 ሰው ምርጫ ውስጥ ለመግባት ለአጭር ጊዜ ምዝገባ ክፍት ነው::

ይህንንም ስናገር ለሀገራችን የሙዚቃ እና ኪነጥበብ ሚያበረክተውን በጎ አስተዋፆ በማሰብ ትልቅ ደስታ እና እድለኝነት ይሰማኛል:: ምስጋናዬ ለሚመለከተው ሁሉ ይድረስ::

ሊንኩን በመጫን መመዝገብ ትችላላችሁ::

https://rophnanmasterclass.et/ "

ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1

https://news.1rj.ru/str/EventAddis1

https://news.1rj.ru/str/EventAddis1