የድምፃዊ መሳይ ተፈራ "የልቤን" አልበም ተለቀቀ
የድምፃዊ መሳይ ተፈራ ካሣ "የልቤን "የተሰኘ የመጀመሪያ አዲስ አልበም ዛሬ ቅዳሜ ሰኔ 1 2016 ዓ.ም በራሱ Mesay Tefera የዩቲዩብ ቻናል እና በዓለማቀፍ መተግበሪያዎች ላይ ተለቋል።
በሙዚቃ አልበሙ ላይ ወጣትና አንጋፋ የግጥምና ዜማ ደራሲያን የተሳተፉበት ሲሆን ከእነዚህ መካከል ድምፃዊ ጎሳዬ ተስፋዬ ፣ ሞገስ ተካ ፣ አቤል ሙሉጌታ ፣ ናትናኤል ግርማቸዉ ፣ አቡዲ ፣ምህረታብ ደስታ፣ አንተነህ ምናሉ ፣ወንድወሰን ይሁብ ይገኙበታል።
በቅንብር ሚክሲንግና ማስተሪንግ የሙዚቃ ባለሙያዎች ሚካኤል ኃይሉ (ሚኪ ጃኖ) ታምሩ አማረ (ቶሚ) አቤል ጳውሎስና ኪሩቤል ተስፋዬ ተሳትፈውበታል።
ኤቨንት ድረገፅ እንደተመለከተው አምስት ዓመታት የፈጀው አልበሙ በውስጡ ቻል ቻል ፣የብቻዬ ፣ቆንጆ ነሽ፤ደህና ይግጠምሽ፤ ማካሪና ፤ ከአባይ ማዶ ፤ውረጅ ካናቴ ፤ የልቤን ፤ግድ የለሽም፤ ኸረ ተይ፤አይ አለማወቋ፤ አወሰድማዬ፤ እሳቱ የተሰኙ ርዕሰ ያላቸው የተለያዩ ጉዳዮችን የሚዳስሱ 12 የሙዚቃ ስራዎችን ይዟል።
ድምጻዊ መሳይ ተፈራ ካሣ ከዚህ ቀደም አሰብኩት ፣ ፋሽን፣ብርቄ ነሽ፣ ደግዬ ፣ በጣም እንጂ በጣም እና ሌሎችንም ነጠላ ሙዚቃዎች ለአድማጮች አድርሷል።
ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1

የጋዜጠኛ መኮንን ወ/አረጋይ "እነሆ ማሟሻ" የተሰኘ አዲስ መጽሐፍ በሚቀጥለው ሳምንት ለንባብ ይበቃል
ከዚህ ቀደም በሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ ላይ በሚያቀርባቸው የስንክሳር፣ የማሟሻ፣ የሃኪሞ መልዕክት፣ የአርብ ምሽት ቆየት ያሉ ሙዚቃዎች እና አሁን ላይ በኢንቢሲ ቴሌቪዥን በልዩ ልዩ ዝግጅቶች የምናውቀው ጋዜጠኛ መኮንን ወ/አረጋይ "እነሆ ማሟሻ" የተሰኘ የመጀመሪያ ቅጽ አዲስ መጽሐፍ በሚቀጥለው ሳምንት ለንባብ ያበቃል።
ጋዜጠኛ መኮንን ወልደአረጋይ ስለመጽሐፉ በመግቢያው "በተለይም በራዲዮና በቴሌቪዥን የቀረበ መሰናዶዎቹን ያደመጡና የተመለከቱ ወዳጆቼ ይህ ቁም ነገር ተሰንዶ በህትመት ቢቀርብ እጅግ ጠቃሚ እንደሆነ ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ ሳያስገነዘበ ቦዝነው አያውቁም፡፡ እናም ዛሬ ጊዜው ደርሶ የመጀመሪያውን ቅጽና ለሌሎች ሥራዎች ዓይን ገላጭ የሆነውን "እነሆ ሟሟሻ" እንካችሁ ብያለሁ" ብሏል።
መጽሐፉ በ200 ገፆች የተነበበ ሲሆን በ250 ብር የጀርባ ዋጋ ለአንባቢያን እንደሚደርስ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ሰምቷል።

የተስፋ የኪነ-ጥበብ ኢንተርፕራይዝ 25ተኛ ዓመት ክብረበዓል የመዝጊያ ዝግጅት በሚቀጥለው ሳምንት ይካሄዳል
የተስፋ የኪነ-ጥበብ ኢንተርፕራይዝ 25ተኛ ዓመት ክብረበዓል የመዝጊያ ዝግጅት በሚቀጥለው ሳምንት ሰኔ 13 ቀን 2016 ዓ.ም በኢንተር ሌግዤሪ ሆቴል በልዩ ልዩ ሥነሥርዓት ይካሄዳል።
በመዝጊያ ዝግጅቱም አንጋፋና ወጣት የኪነጥበብ ባለሙያዎች በተስፋ የኪነጥበብ ኢንተርፕራዝ ይሸለማሉ።ከተስፋ ጋር አብረው የሰሩ ድርጅቶችም እውቅና ይሰጣቸዋል ተብሏል።
ተስፋ የኪነ-ጥበብ ኢንተርፕራይዝ 25ተኛ ዓመት ክብረ በዓሉን አስመልክቶ በጎ ስራዎችን የጀመረው ከታህሳስ 1-29 ከሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ ጋር “በሊፍት ከፍዬ እሳፈራለሁ የጎዳና ልጅ አነሳለሁ” በሚል የገቢ ማሰባሰቢያ ስራ ነበር።
ጥር 10 ቀን 2016 ዓ.ም በኢትዮጵያ በብሔራዊ ቴአትር “ቤርሙዳ” የተሰኘውን ቴአትር፤ ሚያዚያ 28 ቀን “ሀሁ ወይም ፐፑ” ቴአትርን በልዩ ፕሮግራም ለኪነ-ጥበብ አፍቃሪው አቅርቧል፡፡

አርቲስት ድርብወርቅ ሰይፉ የክብር እንግዳ የሆነችበት "መቅረዝ ሥነኪን" የኪነጥበብ ዝግጅት ሀሙስ ይካሄዳል
አንጋፋ እና ወጣት የኪነጥበብ ባለሞያዎችን እያጣመር የዘለቀው መቅረዝ ሥነኪን ወርሀዊ የኪነጥበብ ዝግጅት ሀሙስ ሰኔ 6 2016 ዓ.ም ከምሽቱ 11:00 ጀምሮ በብሔራዊ ቤተመጻሕፍትና ቤተመዛግብት አገልግሎት (ወመዘክር )አዳራሽ ውስጥ ይካሄዳል።
በዕለቱም እረኛዬን ጨምሮ በተለያዩ ፊልሞቿና ድራማዎቿ የምናውቃት አርቲስት ድርብወርቅ ሰይፉ የክብር እንግዳ ሆና የምትገኝ ሲሆን በተጨማሪም ወጣት የኪነጥበብ ባለሞያዎች የግጥም ፣የሙዚቃ እና የዳንስ ስራዎቻቸውን ያቀርባሉ።
የዚህ ዝግጅት መግቢያ በነፃ ነው።
ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
አንጋፋ እና ወጣት የኪነጥበብ ባለሞያዎችን እያጣመር የዘለቀው መቅረዝ ሥነኪን ወርሀዊ የኪነጥበብ ዝግጅት ሀሙስ ሰኔ 6 2016 ዓ.ም ከምሽቱ 11:00 ጀምሮ በብሔራዊ ቤተመጻሕፍትና ቤተመዛግብት አገልግሎት (ወመዘክር )አዳራሽ ውስጥ ይካሄዳል።
በዕለቱም እረኛዬን ጨምሮ በተለያዩ ፊልሞቿና ድራማዎቿ የምናውቃት አርቲስት ድርብወርቅ ሰይፉ የክብር እንግዳ ሆና የምትገኝ ሲሆን በተጨማሪም ወጣት የኪነጥበብ ባለሞያዎች የግጥም ፣የሙዚቃ እና የዳንስ ስራዎቻቸውን ያቀርባሉ።
የዚህ ዝግጅት መግቢያ በነፃ ነው።
ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
የያሬድ የሙዚቃ ት/ቤት የመጀመሪያው ዳይሬክተር በሆኑት ፕ/ር አሸናፊ ከበደ ስም የተሰየመው የጥበብ ማዕከል ተመረቀ
ፕ/ር አሸናፊ ከበደ በመጀመርያ ዳሬክተርነት ባገለገሉበት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሚገኘው የያሬድ ሙዚቃ ትምህርት ቤት በስማቸው የተሰየመው ፕሮፌሰር "አሸናፊ ከበደ የሙዚቃዊ ጥበባት ማዕከል" ባሳለፍነው ቅዳሜ ሰኔ 1 2016 ዓ.ም ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆኗል።
ይህም የሙዚቃዊ ጥበባት ማዕከል በርካታ ሙዚቀኞችን እና የሙዚቃ ታዳሚያንን መያዝ የሚችል ሲሆን በሀገራችን ለሙዚቃ ማቅረቢያ የተሰራ ግዙፍና የመጀመሪያው ማዕከል እንደሆነ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ሰምቷል።
የሙዚቃ ሊቁ ፕ/ር አሸናፊ ከበደ በኢትዮጵያ ዘመናዊ ሙዚቃ ውስጥ ትልቅ አሻራ ያሳረፉ እና ዘመን አይሽሬ የሙዚቃ ሥራዎችን ያበረከቱ የሙዚቃ ሊቅ እንደነበሩ ይነገራል።
እረኛው ባለዋሽንት፣ የኢትዮጵያ ሰላም፣ የፍቅር አንሰር ፣ የእሳት እራት፣ የተማሪ ፍቅር ፣ የሀገራችን ሕይወት ፣ ኒርቫኒክ ፋንታሲ የተሰኙ ረቂቅ ሙዚቃዎችን ለአድማጭ ጆሮ ያደረሱ የሙዚቃ ደራሲ አቀናባሪና ኮንዳክተር ናቸው።
በተጨማሪም የሙዚቃ ሰዋሰው የመማርያ መፅሀፍ በአማርኛ፣ ኮንፌንሽን ልቦለድ እንዲሁም Root of Black Music የተሰኙ መጽሐፍትም ለአንባቢያን አድርሰዋል።

"እያዩ ፈንገስ" ለሁለት ቀናት ብቻ ሊታይ ነው
በበረከት በላይነህ ተደርሶ በግሩም ዘነበ የሚተውነው "እያዩ ፈንገስ" የአንድ ሰው ተውኔት መድረክ ላይ መቅረብ ከጀመረ ዘንድሮ አስር ዓመት እንደሚሞላው አዘጋጆቹ አስታውቀዋል።
ይህንን የአስርኛ ዓመት ክብረበዓል በማሰብ ረቡዕ ሰኔ 5 እና አርብ ሰኔ 7 2016 ዓ.ም ከምሽቱ 12:00 ጀምሮ በራስ ሆቴል ለሁለት ቀናት ብቻ "እያዩ ፈንገስ" የአንድ ሰው ተውኔት ለታዳሚያን እንደሚቀረብ ኤቨንት አዲስ ድረገጽ ሰምቷል።
"እያዩ ፈንገስ" የአንድ ሰው ተውኔት "አጀንዳዬ" "ፌስታሌ" እና በቅርቡ ከመድረክ በታገደው "ቧልቲካ" በሚሉ ርዕሶች በተለያዩ መድረኮች ለታደሚያን ሲቀረብ ቆይቷል።

"ምን ሆኛለሁ?" መጽሐፍ በቅርቡ ለንባብ ይበቃል
የሥነልቦና ባለሞያዋ ትዕግስት ዋልተንጉስ እና ጋዜጠኛና ደራሲ ቴዎድሮስ ተክለአረጋይ የተጣመሩበት 'ምን ሆኛለሁ?' መፅሀፍ በጣም በቅርቡ ታትሞ ይወጣል ተብሏል።
"የምታደርጉት ድርጊት ግራ አጋብቷችሁ 'ምን ሆኛለሁ?' ብላችሁ ከጠየቃችሁ ይሄ መፅሀፍ ልጅነታችሁን በመመርመር ራሳችሁን በተሻለ እንድትረዱ ያግዛችኋል"።
በተጨማሪም "በዙሪያችሁ ያሉ ሰዎች ወይም በቲቪ የምታውቋቸው ነጋዴዎች፣ ፖለቲከኞች፣ ታዋቂ ሰዎች የሚያደርጉት ድርጊት አልገባ ብሏችሁ 'ምን ሆኖ ነው?' ወይም 'ምን ሆና ነው?' የሚል ጥያቄ ከፈጠረባችሁ ይሄ መፅሀፍ ጥሩ የፅንሰ ሀሳብ መነፅር ይሰጣችኋል " ስለመባሉ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ሰምቷል።
"ምን ሆኛለሁ" የተሰኘውን መጽሐፍ ብዙዎች መፅሀፉን ቀድመው እየገዙ እንደሆነም ተመልክተናል።

በእስር ላይ የሚገኘው መራሔ ተውኔት ዳግማዊ አመለወርቅ ፈይሳ በጽኑ ስለመታመሙ ተሰምቷል
ከመጋረጃ ጀርባ ፣እብድት በህብረት የተሰኙ ተውኔቶችን ጨምሮ የተለያዩ ተውኔቶች ሲያዘጋጅ የምናውቀው መራሔ ተውኔት ዳግማዊ አመለወርቅ ፈይሳ ከሰሞኑ በታሰረበት ሦስተኛ ፖሊስ ጣቢያ በፅኑ ህመም ላይ እንደሚገኝ እና ዛሬ ሰኔ 2 2016 ዓ.ም ወደ ህክምና ቦታ እንደተወሰደ ኤቨንት አዲስ ድረገጽ ከቅርብ ምንጮች ሰምቷል።
አንጋፋው ከያኒ ዳግማዊ አመለወርቅ ፈይሳ ለረጅም ጊዜ የስኳር ህመምተኛ እንደሆነ የተገለፀ ሲሆን ክሱን ከእስር ቤት ውጪ ሆኖ እንዲከታተል ቤተሰቦቹ ለፖሊስ ጥያቄ ማቅረባቸው ተነግሯል።
በቅርቡ በፖሊስ ተይዞ ለእስር የበቃው የ"እብደት በሕብረት" ቴአትር አዘጋጅ አንጋፋው ከያኒ ዳግማዊ ፈይሳ ባለፈው ሳምንት ግንቦት 28 2016 ዓ.ም ለመጀመሪያ ጊዜ ፍርድ ቤት የቀረብ ሲሆን አርቲስት አማኑኤል ሀብታሙን ጨምሮ ሌሎች 20 ሰዎችን በአንድ መዝገብ ለፌደራል መደበኛ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ቀጠሮ ወንጀል ችሎት ቀርበው ሁሉም ለሰኔ 11 ቀን 2016 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ እንደተሰጣቸው ይታወሳል።

"እውቀትን ፍለጋ መጻሕፍት መደብር"
እውቀትን ፍለጋ መጻሕፍት መደብር አዳዲስና ቆየት ያሉ የአማርኛ እና እንግሊዝኛ መጻሕፍትን አቅርቦላቸዋል።
የፍልስፍና ፣ የታሪክ ፣ የልቦለድ ፣ የትምህርት መማሪያ ፣የልጆች እና የሙያ መጻሕፍትን በብዛትና እጅግ በተመጣጣኝ ዋጋ ታገኛላችሁ።
አድራሻቸው: ገርጂ ታክሲ ተራ (ዓለም ጋለሪ አካባቢ )
ስልክ : 0913624488
ወይም :0913825404
የቴሌግራም ገጻቸው:
https://news.1rj.ru/str/book1219

"ዱባይ እንደምን ሠለጠነች?" የተሰኘ አዲስ መጽሐፍ ከሰሞኑ ለንባብ በቅቷል
በዱባዮ ገዢ ሼኽ መሀመድ ቢን ረሺድ አል መክቱም ህይወት ዙሪያ የሚያጠነጥነው"My Story"መጽሐፍ በጋዜጠኛ ናትናኤል ከበደ "ዱባይ እንደምን ሠለጠነች" በሚል ርዕስ ተተርጉሞ ለንባብ በቅቷል።
መፅሀፉ የዱባዩ ገዢ እና የተባበሩት አረብ ኤምሬት ጠቅላይ ሚኒስትር ህይወት ዙሪያ የተፃፈ ቢሆንም ከ ሼኽ መሀመድ ህይወት ባሻገር በውስጡ ብዙ ርዕሰ ጉዳዮች እንደያዘ የሚናገረው ተርጓሚው አያይዞም መፅሀፉ በዋናነት ለሀገራችን ለኢትዮጵያ ትምህርት ሊሆን የሚችል የዱባይ የሀገር ምስረታ ፣አለም ላይ ታዋቂ የሆኑት ተቋማቸውን እንዴት እንደገነቡ ፣ዲፕሎማሲ፣ከነዳጅ ባሻገር ስላለው የአመራር ክህሎት እና ልህቀት እንደሚያወሳ ተናግሯል።
50 ምዕራፎች የያዘው መጽሐፉ በ400 ብር የጀርባ ዋጋ ለአንባቢያን ቀርቧል።
መጻሐፉም ሜክሲኮ ጃፈር መፅሀፍት መደብር እና 4 ኪሎ እነሆ መፅሀፍት መደብር ይገኛል።
Telegram:https://news.1rj.ru/str/EventAddis1

"እሳት ወይ አበባ" ተውኔት ወደ መድረክ ሊመለስ ነው
በሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን ግጥሞች ላይ የተመሰረተው "እሳት ወይ አበባ" ግጥማዊ ዳንስ ተውኔት በብሔራዊ ቴአትር ከሰኔ 14 2016 ዓ.ም ጀምሮ ወደ መድረክ እንደሚመለስ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ሰምቷል።
"እሳት ወይ አበባ" የሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን ግጥሞች ላይ መሰረት ያደረገ የግጥማዊ ዳንስ የሙከራ (Experimental) ቴአትር ነው።
ይህ ሙከራዊ ተውኔት ባሳለፍነው ጥቅምት 2 2016 ዓ.ም ነበር ዘወትር አርብ ሲቀረብበት ከነበረው የአንጋፋው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር መድረክ የተሰናበትው።በምትኩም "የሁለት አሽከር ጌቶች" የተሰኘ ተውኔት ሲቀርብም ቆይቷል።
ኤቨንት አዲስ ድረገፅ እንዳረጋገጠው በሚቀጥለው ሳምንት ሰኔ 14 2016 ዓ.ም "እሳት ወይ አበባ " ተውኔት ወደ መድረክ ተመልሶ በቋሚነት ዘወትር አርብ በ11:30 መቅረብ ይጀምራል ተብሏል።
ይህ ግጥማዊ ድራማ ከዚህ ቀደም በሀገር ፍቅር ቴአትር ትንሿ አዳራሽ ለታደሚያን ይቀርብ እንደነበር ይታወሳል።
📍መረጃውን ሲጠቀሙ ምንጭ ይጠቀሱ !
ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1

በነፃ የተዘጋጀው የሮፍናን ማስተር ክላስ
ሁለገቡ ሙዚቀኛ ሮፍናን ኑሪ በሐዋሳና አካባቢ ለሚገኙ ወጣት የሙዚቃ ባለሞያዎች እና ተያያዥ የስራ መስክ ውስጥ ለሚገኙ ሁሉ "የሮፍናን ማስተር ክላስ" ስልጠና ጥሪ አስተላልፏል።
ሙዚቀኛ ሮፍናን ኑሪ ለሚመለከተው ሁሉ ተከታዩን መልዕክት በማህበራዊ ትስስር ገፁ አስተላልፏል:
"በሐዋሳ እና አካባቢው ምትገኙ የማስተር ክላሱን የትምህርት እና በተግባር የታገዘ ልምድ ልውውጥ ለመካፈል የምትፈልጉ ወጣት ጀማሪ ሙዚቀኞች: አቀናባሪዎች : ድምፃዊያን : የግጥም እና ዜማ ደራሲዎች : ዲጄዎች : የድምፅ ቅጂ እና ማስተሪንግ ኢንጂነሮች : እንዲሁም በኢንተርቴመንት ማርኬቲንግ ስራ ላይ ለተሰማራችሁ የማርኬቲንግ ባለሙያዎች እድሉ ለሚፈቅደው የ150 ሰው ምርጫ ውስጥ ለመግባት ለአጭር ጊዜ ምዝገባ ክፍት ነው::
ይህንንም ስናገር ለሀገራችን የሙዚቃ እና ኪነጥበብ ሚያበረክተውን በጎ አስተዋፆ በማሰብ ትልቅ ደስታ እና እድለኝነት ይሰማኛል:: ምስጋናዬ ለሚመለከተው ሁሉ ይድረስ::
ሊንኩን በመጫን መመዝገብ ትችላላችሁ::
https://rophnanmasterclass.et/ "
ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
https://news.1rj.ru/str/EventAddis1

እያዩ ፈንገስ ተውኔት አይቀርብም ተባለ
የእያዩ ፈንገስ 10ኛ ዓመት በዓልን አስመልክቶ ነገ ረቡዕ ሰኔ 5 እና አርብ ሰኔ 7 2016 በራስ ሆቴል ሊቀርብ የነበረው ዝግጅት ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት በነገው እለት እንደማይቀርብ አዘጋጆቹ ስለማሳወቃቸው ኤቨንት ድረገፅ ሰምቷል።
የተወኔቱ አዘጋጆች ወደፊት ተለዋጭ ፕሮግራም ሲኖር ለተመልካቹ እንደሚያሳውቁ ጨምረው ገልፀዋል።
በተጨማሪም "ለ10ኛ ዓመት በዓላችን መልካሙን ሁሉ ለተመኛችሁልንና በጠመዝማዛው መንገዳችን አብራችሁን ለነበራችሁ ወገኖቻችን ምስጋናችን ወሰን የለውም" በማለት መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።
"እያዩ ፈንገስ" የአንድ ሰው ተውኔት "አጀንዳዬ" "ፌስታሌ" እና በቅርቡ ከመድረክ በታገደው "ቧልቲካ" በሚሉ ርዕሶች በተለያዩ መድረኮች ለታደሚያን ሲቀረብ ቆይቷል።
ዘወትር ሐሙስ በዓለም ሲኒማ ሲቀረብ የነበረው የእያዩ ፈንገስ "ቧለቲካ" ቴአትር ባሳለፍነው ጥር 2 2016 ዓ.ም ለህዝብ እንዳይታይ እንደተከለከለ ይታወሳል።

የኢትዮጵያ ኤለክትሪሲቲ አውደርዕይ ተከፈተ
አራተኛው የኢትዮጵያ ኤለክትሪሲቲ አውደርዕይ ከዛሬ ሰኔ 05 እስከ ፊታችን ቅዳሜ ሰኔ 08 ቀን 2016 ዓ.ም በሚሊኒየም አዳራሽ እየተካሄደ ይገኛል።
የዘንድሮው አራተኛው የኢትዮጵያ ኤለክትሪሲቲ አውደርዕይ"ኃይል ቁጠባ፣ አረንጓዴ አፍሪካ"በሚል መሪ ቃል የሚከናውን ሲሆን በዚህ አውደርዕይ ላይ አምራቾች ምርቶቻቸውንና አቅርቦቶቻቸውን ይዘው ይገኛል ተብሏል።

ኢትዮ የምግብ እና መጠጥ ፌስቲቫል ተከፈተ
የምግብና መጠጥ ኢንዱስትሪ ምርምር እና ልማት ማዕከል ከአሜዚንግ ፕሮሞሽንና ኢቨንት እና ከዳብ ትሬዲንግ ጋር በመተባበር ከዛሬ ሰኔ 5 እስከ የፊታችን 9 2016 ዓ.ም የሚቆይ ኢትዮ የምግብና መጠጥ ፌስቲቫል በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል ተከፍቷል።
ለ5 ተከታታይ ቀናት በሚቆየው "ኢትዮ የምግብና መጠጥ ፌስቲቫል" በምግብ፣ በመጠጥ፣ በፓኬጂንግ እና ተዛማጅ መስኮች ላይ የተሰማሩ ግብዓት አቅራቢዎች፣ አምራቾች፣ አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶች፣ ከዘርፉ ጋር የተገናኙ አምራች እና አስመጪዎች እንዲሁም የፋይናንስ ተቋማት ይሳተፋሉ ተብሏል።
በፌስቲቫሉ ላይ የዘርፉ ባለሙያዎች የእውቅና አሰጣጥ ፕሮግራም፣ ሽልማት የሚያስገኙ ልዩ ልዩ ውድድሮች እና የመዝናኛ ፕሮግራሞች መካተታቸው ተገልጿል።
ኢትዮ የምግብና መጠጥ ፌስቲቫል የውጪ ሀገራት ዲፕሎማቶችን ጨምሮ በርካታ ኢትዮጵያውያን ሀገራችን በምግብና መጠጥ ረገድ ያላትን የቱሪዝም አቅም በቅርበት እንዲያውቁት የሚያደርግ ፌስቲቫል እንደሆነ ተነግሯል፡፡
የፊስቲቫሉ መግቢያ በነፃ መሆኑን እና ሁሉም ህብረተሰብ መካፈል እንደሚችሉ ተነግሯል ።

የሐሙስ መረጃዎች
የሳምንቱ ኪናዊ መረጃዎች ቀጥሎ ይቀርባሉ!
ቀድመ ማሳሰቢያ: ሚዲያዎች መረጃውን ስትጠቀሙ ምንጭ ጥቀሱ❗️
📍መጽሐፍ
- የገጣሚ ኤፍሬም ስዩም አንድ መጽሐፍ በአንድ ሺህ ብር ቅድመ ክፍያ ለህትመት ሊበቃ እንደሆነ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ሰምቷል። "ቡና እና ምልኪ" የተሰኘውና ከዓመት በፊት ለንባብ ይበቃል ተብሎ የዘገየው መጽሐፍ ከፊታችን ቅዳሜ ጀምሮ በማህበራዊ ትስስር ገፅ በሚደረግ ቅድም ክፍያ እንደሚታተም ገጣሚው አስታውቋል። ገጣሚው በማህበራዊ ትስስር ገፁ"በሀርድ ኮፒ ያጌጠ ምልኪና ቡና ከቅዳሜ ጀምሮ 1000 ኮፒ ህትመት በ1000 ብር ብቻ እጃችሁና የመጻሕፍት ሼልፋችሁ ላይ ለማኖር ዝግጅት አድርጉ" ብሏል።
-የገጣሚ መንበረማርያም ኃይሉ አዲስ መጽሐፍ ለንባብ በቃ። መጽሐፉ "የጊዜ ሠሌዳ" የተሰኘ ርዕስ የተሰጠው የግጥም ስብስብ መጽሐፍ ነው።በ103 ገፆች ተቀንብቡ በ250 የጀርባ ዋጋ ለአንባቢያን የቀረበ ሲሆን ዛሬ በሚካሄደው የመቅረዝ ሥነኪን የኪነጥበብ ዝግጅት ላይ በገጣሚዋ ተፈረሞ ለአንባቢያን ይደርሳል ተብሏል። ገጣሚዋ ከዚህ ቀደም "የቃል ሠሌዳ" የተሰኘ መጽሐፍ ለንባብ ማብቃቷ ይታወሳል።
-የገጣሚና የህግ ባለሞያው ደሱ ፍቅርኤል "እስከ መቅደላ " የተሰኘ መጽሐፍ ለንባብ በቅቷል።ገጣሚ ደሱ ከዚህ ቀደም "ሀገሬን ሰቀሏት" እና "ተይው ፖለቲካን ዝም ብለሽ ሳሚኝ" የተሰኙ መጻሕፍትን ለአንባቢያን አድርሷል። መጽሐፉን በተለያዩ መጻሕፍት መደብሮች ታገናላችሁ ተብላችኋል።
-የጋዜጠኛ መኮንን ወ/አረጋይ "እነሆ ማሟሻ" የተሰኘ አዲስ መጽሐፍ በሳምንቱ መጨረሻ ቀናት ለአንባቢያን ይደርሳል።ከዚህ ቀደም በሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ ላይ በሚያቀርባቸው የስንክሳር፣ የማሟሻ፣ የአርብ ምሽት ቆየት ያሉ ሙዚቃዎች እና አሁን ላይ በኢንቢሲ ቴሌቪዥን በልዩ ልዩ ዝግጅቶች የምናውቀው ጋዜጠኛ መኮንን ወ/አረጋይ "እነሆ ማሟሻ" የተሰኘ የመጀመሪያ ቅጽ አዲስ መጽሐፍ በዚህ ሳምንት መጨረሻ ቀናት ለአንባቢያን ይደርሳል ተብሏል።መጽሐፉ በ200 ገፆች የተነበበ ሲሆን በ250 ብር የጀርባ ዋጋ ለአንባቢያን እንደሚደርስ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ሰምቷል።
📍ሙዚቃ
-የድምጻዊት ሔዋን ገብረወልድ "ያንተን" የተሰኘ ሙዚቃ ነገ አርብ ለአድማጮች ይደርሳል። በዚህ የሙዚቃ ስራዋ ላይ ገጣሚ ምልእቲ ኪሮስ በግጥም ምረታብ ደስታ በዜማ ተሳትፈዋል።ሙዚቃ ቅንብርና ማስተሪንጉን ስማአገኘሁ ሳሙኤል ሰርቷል።
-የድምጻዊት ሜላት ቀለመወርቅ "ዋይ" የተሰኘ ሙዚቃ ነገ አርብ በናሆም ሪከርድስ በኩል ለአድማጮች ይደርሳል ተብሏል።በዚህ የሙዚቃ ስራዋ ላይ በግጥምና ዜማ ምህረትአብ ደስታ ሲሳተፍ ቅንብር፣ሚክሲንግ፣እና ማስተሪጉን ደግሞ ሔኖክ ድለቃ ሰርቷል።
-ሙዚቀኛ ሮፍናን ኑሪ "የኔ ትውልድ" በተሰኘ የአሜሪካ ጉዞ የሙዚቃ ዝግጅቱን እንደሚያካሄድ በማህበራዊ ትስስር ገፁ አስታውቋል። የሙዚቃ ዝግጅቱን በቅርቡ በአሜሪካ አትላንታ ግዛትን ጨምሮ በተለያዩ ግዛቶች ውስጥ እንደሚያቀርብ ገልጿል። ሮፍናና ከወራት በፊት ዘጠኝ በሚል ርዕስ "ሀራንቤ" እና "ኖር" የተሰኙ ሁለት አልበሞችን በአንድ ቀን ለአድማጮች ማድረሱ ይታወሳል።
📍 ቴአትር
-የ"እያዩ ፈንገስ" 10ኛ ዓመት በዓልን አስመልክቶ ረቡዕ ሰኔ 5 እና አርብ ሰኔ 7 2016 ዓ.ም በራስ ሆቴል ሊቀርብ የነበረው ዝግጅት ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት እንደማይቀርብ አዘጋጆቹ ማሳወቃቸው የተሰማው በዚህ ሳምንት ነበር።የተወኔቱ አዘጋጆች ወደፊት ተለዋጭ ፕሮግራም ሲኖር ለተመልካቹ እንደሚያሳውቁ ጨምረው ገልፀዋል።
- "እሳት ወይ አበባ" ተውኔት ወደ መድረክ ሊመለስ ነው። በሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን ግጥሞች ላይ የተመሰረተው "እሳት ወይ አበባ" ግጥማዊ ዳንስ ተውኔት በብሔራዊ ቴአትር ከሰኔ 14 2016 ዓ.ም ጀምሮ ወደ መድረክ እንደሚመለስ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ሰምቷል።ይህ ሙከራዊ ተውኔት ባሳለፍነው ጥቅምት 2 2016 ዓ.ም ነበር ዘወትር አርብ ሲቀረብበት ከነበረው የአንጋፋው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር መድረክ የተሰናበተው። በምትኩም "የሁለት ጌቶች አሽከር" የተሰኘ ተውኔት ሲቀርብም ቆይቷል።
📍ኪነጥበብ ዝግጅት
"መቅረዝ ሥነኪን" የኪነጥበብ ዝግጅት ዛሬ ይካሄዳል። አንጋፋ እና ወጣት የኪነጥበብ ባለሞያዎችን እያጣመር የዘለቀው መቅረዝ ሥነኪን ወርሀዊ የኪነጥበብ ዝግጅት ሀሙስ ሰኔ 6 2016 ዓ.ም ከምሽቱ 11:00 ጀምሮ በብሔራዊ ቤተመጻሕፍትና ቤተመዛግብት አገልግሎት (ወመዘክር )አዳራሽ ውስጥ ይካሄዳል። በዕለቱም አርቲስት ድርብወርቅ ሰይፉ በክብር እንግድነት ትገኛላች ተብሏል።
📍የሥነጥበብ አውደርዕይ (ሥዕል)
- የሠዓሊ ዮናታን ወንደሰን ሥዕል ስራዎች የሚቀርቡበት "ከአጥሮች ባሻገር" የሥዕል አውደርዕይ ነገ አርብ ሰኔ 7 2016 ዓ.ም ከምሽቱ 12:00 ጀምሮ ካዛንቺስ በሚገኘው ፈንድቃ የባህል ማዕከል ውስጥ ለእይታ ይበቃል። ይህ የሥዕል አወድርዕይ እስከ ሰኔ 21 2016 ዓ.ም ይቆያል ተብሏል።
-የሠዓሊ ኃይለገብርኤል ንጉሴ የሥዕል ስራዎች የሚቀረበብት "The light Path" የሥዕል አውደርዕይ ቅዳሜ ሰኔ 8 2016 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ጀምሮ መስቀል አደባባይ አካባቢ በሚገኘው የአዲስ አበባ ሙዚየም ውስጥ ላይ ለእይታ ይበቃል።ይህም የሥዕል አውደርዕይ እስከ ሰኔ 23 2016 ዓ.ም በእይታ ላይ ይቆያል ተብሏል።
📍ፊልም
"ጃንሞራ" የተሰኘ ፊልም በቅርቡ ለተመልካች ይቀርባል። በኪም ፊልምስ ተዘጋጅቶ በከአብ መልቲሚዲያ የቀረበው የያለው ደስታ (ራስ) "ጃንሞራ" የተሰኘ ፊልም ከሰኔ 21 ጀምሮ በሁሉም ሲኒማ ቤቶች ለተመልካች እንደሚቀረብ ኤቨንት አዲስ ድረገጽ የደረሰው መረጃ ያመለክታል።በዚህ ሀገርኛ ፊልም ማርታ ጎይቶም፣ ነብዩ እንድሪስ ፣ እንግዳሰው ሀብቴ እና ሌሎችም በተዋናይነት ተሳትፈውበታል።
አዘጋጅ: ናቲ ማናዬ
ቀን: ሰኔ 6 2016 ዓ.ም
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
በድረገጻችን በተሻለ አቀራረብ ያንብቡ:
https://eventaddis.com
ቴሌግራም: @EventAddis1

ሜሊስ ፋሽን እና ትሬድንግ ዓለምአቀፍ ሞዴል ጆዝሳ እስዝተር ኒኮሌቴን የድርጅቱ ብራንድ አምባሳደር አድርጎ ሾመ
ሜሊስ ፋሽን እና ትሬድንግ በሀገራችን ኢትዮጵያ ጥራት ፣ደረጃቸው የተመሰከረላቸው የሜሊስ ፋሽን እና ትሬዲንግ ልዩ ልዩ የፋሽን እና የዲዛይን ምርቶች የሚቀረቡባቸው ሱቆች መከፈቱን በማስመልከት ዓለምአቀፍ እውቅና ያላትን የሃንጋሪይ ተወላጅ ከሆነችው ኢንተርናሽናል ሞዴል ጆዝሳ እስዝተር ኒኮሌቴን ጋር አብሮ ለመስራት የድርጅቱ የብራንድ አምባሳደር ይፋ ማድረጊያ ሥነሥርዓት ሐሙስ ሰኔ 6 2016 ዓ.ም በሀያት ሪጀንሲ አካሄዷል።
ሜሊስ ፋሽን እና ትሬድንግ በኢንተርናሽናል ሞዴል እና ዲዝይነር ሜላት ሚካኤል የተመሰረተ ሲሆን ፤ በቻይና ጉዋንዡ ሆንግኮንግ እና ሻንጋይ ዓለምአቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ ዕውቅ የፋሽንና ዲዛይን ምርቶችን እንዲሁም ብራንዶችን ለዓለም ገበያ የሚያቀርብባቸው ሱቆችን በመክፈት አገልግሎት እየሰጠ እንደሚገኘ ተገልጿል።
ኢንተርናሽናል ሞዴል እና ዲዝይነር ሜላት ሚካኤል በዓለምአቀፉ ፋሽን መድረክ ላይ የእሷን አሻራ ለማሳረፍ ጥረት እያደረገች እንደምትገኝ በኩነቱ ላይ ገልጻለች።
ሜሊስ ፋሽን እና ትሬድንግ በሀገራችን ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ጥራት ደረጃቸው የተመሰከረላቸው የሜሊስ ፋሽን እና ትሬዲንግ ልዩ ልዩ የፋሽን ሱቆች እንደፈከትም ይፋ አድርጓል።

ኮሜዲያን ቤቲ ዋኖስ የማይ ሶሮባን ሀገር አቀፍ የሒሳብ ትምህርት ውድድር የበጎ ፍቃድ አምባሳደር ሆና ተሾመች
ማይ ሶሮባን ኢትዮጵያ ኃ/የተ/የግ/ማህበር “ሒሳብ ትምህርት ይከብዳል” የሚል የተሳሳተ አመለካከት በማስወገድ ጉብዝና ያሽልማል › በሚል መሪ ቃል ሀገር አቀፍ የሒሳብ ትምህርት እና የስሌት ውድድር በሀገራችን በሚገኙ ሁለም ትምህርት ቤቶች ለማከናወን የተቋቋመ በኢትዮጵያ ብቸኛው የሒሳብ ትምህርት አወዳዳሪ ተቋም ነው፡፡
በማይ ሶሮባን ኢትዮጵያ የ2016 ዓ.ም ሀገር አቀፍ የሒሳብ ትምህርት ውድድር ከ50 ከተሞች የተውጣጡ ከ2ሺ በላይ ትምህርት ቤቶች እና ከ3መቶ ሺ በላይ ተማሪዎችን አሳትፏል፡፡
ውድድሩ በአጠቃላይ ስድስት ዙሮች ሲኖሩት አምስቱ ዙሮች በየከተሞቹ የተከናወኑ ሲሆን የመጨረሻው ወይም ስድስተኛው ዙር የፍጻሜ ውድድር ከሁሉም ከተሞች የየከተማው አሸናፊ ተማሪዎች በተገኙበት በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኘው የሚሊኒየም አዳራሽ የመጨረሻውን የአሸናፊዎች አሸናፊ ውድድር ለከፍተኛ ሽልማት ይወዳደራሉ፡፡ የዚህ ውድድር አሸናፊ ተማሪዎች በጠቅላላ አራት ሚሊዮን ብር የሚፈጅ የገንዘብና የአይነት ሽልማት ተዘጋጅቶላቸዋል ተብሏል።
በዳኝነት የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ እና የኮተቤ መምህራን ዩኒቨርስቲ መምህራን ሲሳተፉ የየከተማ ተወካዮቻቸውም በታዛቢነት እንደሚሳተፉ ተገልጿል።
የመዝጊያው መርሃግብር በአዲስ አበባ ሚሊኒየም አዳራሽ ከሐምሌ 28 እስከ ነሐሴ 1 2016 ዓ.ም ይከናወናል ተብሏል።
ማይ ሶሮባን ኢትዮጵያ ዛሬ ሰኔ 6 2016 ዓ.ም በሚሊኒየም አዳራሽ በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ኮሜዲያን ቤቲ ዋኖስ የበጎ ፍቃድ አምባሳደር አድርጎ እንደሾመ አስታውቋል።

በኢትዮጵያዊው የዜማ ሊቅ በቅዱስ ያሬድ ስም የተሰየመ የድረገጽ አገልግሎት ይፋ ተደረገ
ታሪካዊው በሆነው የደብረ ሐዊ ቅዱስ ያሬድ የአንድነት ገዳም ስያሜ የተሰራው ድረገጽ ብፁዕ አቡነ ዲሜጥሮስ የምሥራቅ ካናዳ ሊቀ ጳጳስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል በተገኙበት ሰኔ 6 2016 ዓ.ም በራማዳ ሆቴል በተከናወነው መርሐግብር ይፋ ተደርጓል።
በሰሜን ጎንደር ዞን በበየዳ ወረዳ የሚገኘውን ደብረ ሐዊ ቅዱስ ያሬድ አንድነት ገዳም እየተከናወነ ያለውን የግንባታ ኘሮጀክት ያስተዋውቃል የተባለው ድረገጹ በገዳሙ እየተሰራ ያለውን የአብነት ትምህርት ጥንታዊነቱን ጠብቆ የሚያስተምር የልህቀት ማዕከል ማድረግና ምዕመናን ወደ ገዳሙ እየሔዱ በረከት የሚያገኙበት ከዓለም ዙሪያ ለሚመጡ ጎብኚዎች የቤተክርስቲያኗንና የሀገራችን ቀደምትነት ገናና ባለታሪክ መሆናቸውን የሚረዱበትና ሀገራችንም የውጭ ምንዛሪ የምታገኝበት ማድረግን ዓላማ አድርጎ እየሠራ ይገኛል ተብሏል።
www.kidusyaredzedebrehawi.com በገዳሙ እየተከናወነ ያለውን ፕሮጀክት አስመልክቶ ዝርዝር ማብራሪያ የሚሰጥ ሲሆን ገዳሙን በገንዘብ በቀጥታ ማገዝ እንድችሉ ተደርጎ እንደበለጸገ በመድረኩ ላይ ተገልጿል።
ቅዱስ ያሬድ ከ1500 አመታት በፊት የኖረ፣ የመጀመሪያው የአለማችን የዜማ አውጭ፣ የመጀመሪያው የመፃሕፍት ደራሲ፣ ታላቅ የፍልስፍና ሰው፣ የብዙ ነገሮች ሊቅ፣ ባለቅኔ የሆነ፣ ኢትዮጵያ ለዓለም ያበረከተችው ግዙፍ ባለጸጋ ነው።
ቅዱስ ያሬድ ባስተማረበት በመጨረሻም በተሰወረበት ስፍራ፣ በሰሜን ተራራ ላይ በደብረ ሐዊ ቅዱስ ያሬድ አንድነት ገዳም በርካታ ልማቶችን በማድረግ ላይ እንደሚገኝ ማህበሩ አስታውቋል።

ካውሰር ( ሻሊና ሄልዝ ኬር)የተሰኘ ድርጅት አራት የቆዳ መንከባከቢያ ምርቶችን ያስተዋውቀበትን ኩነት አካሄድ
ካውሰር PLC( ሻሊና ሄልዝ ኬር) በአለም አቀፍ ደረጃ ትልቅ ተቀባይነትን ያተረፈ ድርጅት ሲሆን በኢትዮጵያ ይዟቸው የመጣቸውን አዳዲስ ምርቶች ሰኔ 6 2016 ዓ.ም አስተዋውቋል።
ከነዚህ ምርቶች ውስጥ አንዱ ሞናሊሳ ሲባል ይህም የቆዳ እንክብካቤን ለመጠበቅ የሚያስችል ሎሽንና ክሬም ነው።
ኤፒግሎው የተሰኘው ደግሞ ለአፍሪካ ቆዳ የተዘጋጀ ሲሆን እንደ ጥቁር ነጠብጣቦች እና ዥንጉርጉር ፊትን እና የተለመዱ የቆዳ ስጋቶችን በ28 ቀናት ውስጥ በመቀነስ ብቻ የሚታይ ለውጥ የሚሰጥ የቆዳ መንከባከቢያ እንደሆነ ተገልጿል።
ሌላው ፍሎደንት የተባለው የጥርስ ሳሙና ምርት ሲሆን በፍሎራይድ ለተጠቃ ጥርስ፣ ለአፍ ጤንነት፣ የጥርስ መቦርቦርን የሚታደግ እንደሆነ ተነግሯል።
የመጨረሻው ምርት ጀርሞል የተሰኘ ሳሙና ሲሆን ሰውነትን ከጀርሞች ለመከላከል የሚረዳ ነው ተብሏል።
ሻሊና ሄልዝ ኬር 40 አመትን ያስቆጠረ ድርጅት ሲሆን እስካሁን በ22 የአፍሪካ ሀገራት ላይ ሰርቷል።
ድርጅቱ በአሁን ሰአት በአዲስ አበባ ላይ 6 ክፍለ ከተሞች ላይ ስራ የጀመረ ሲሆን 1000 ለሚደርሱ ሰዎች የስራ እድል ፈጥሯል።