Event Addis Media – Telegram
Event Addis Media
9.61K subscribers
6.13K photos
14 videos
4 files
4.75K links
Connect with Addis artistic community!

Website: https://eventaddis.com

Contact: @Tmanaye
Download Telegram
"ዱባይ እንደምን ሠለጠነች?" የተሰኘ አዲስ መጽሐፍ ከሰሞኑ ለንባብ በቅቷል

በዱባዮ ገዢ ሼኽ መሀመድ ቢን ረሺድ አል መክቱም ህይወት ዙሪያ የሚያጠነጥነው"My Story"መጽሐፍ በጋዜጠኛ ናትናኤል ከበደ "ዱባይ እንደምን ሠለጠነች" በሚል ርዕስ ተተርጉሞ ለንባብ በቅቷል።

መፅሀፉ የዱባዩ ገዢ እና የተባበሩት አረብ ኤምሬት ጠቅላይ ሚኒስትር ህይወት ዙሪያ የተፃፈ ቢሆንም ከ ሼኽ መሀመድ ህይወት ባሻገር በውስጡ ብዙ ርዕሰ ጉዳዮች እንደያዘ የሚናገረው ተርጓሚው አያይዞም መፅሀፉ በዋናነት ለሀገራችን ለኢትዮጵያ ትምህርት ሊሆን የሚችል የዱባይ የሀገር ምስረታ ፣አለም ላይ ታዋቂ የሆኑት ተቋማቸውን እንዴት እንደገነቡ ፣ዲፕሎማሲ፣ከነዳጅ ባሻገር ስላለው የአመራር ክህሎት እና ልህቀት እንደሚያወሳ ተናግሯል።

50 ምዕራፎች የያዘው መጽሐፉ በ400 ብር የጀርባ ዋጋ ለአንባቢያን ቀርቧል።

መጻሐፉም ሜክሲኮ ጃፈር መፅሀፍት መደብር እና 4 ኪሎ እነሆ መፅሀፍት መደብር ይገኛል።

Telegram:https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
"እሳት ወይ አበባ" ተውኔት ወደ መድረክ ሊመለስ ነው

በሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን ግጥሞች ላይ የተመሰረተው "እሳት ወይ አበባ" ግጥማዊ ዳንስ ተውኔት በብሔራዊ ቴአትር ከሰኔ 14 2016 ዓ.ም ጀምሮ ወደ መድረክ እንደሚመለስ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ሰምቷል።

"እሳት ወይ አበባ" የሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን ግጥሞች ላይ መሰረት ያደረገ የግጥማዊ ዳንስ የሙከራ (Experimental) ቴአትር ነው።

ይህ ሙከራዊ ተውኔት ባሳለፍነው ጥቅምት 2 2016 ዓ.ም ነበር ዘወትር አርብ ሲቀረብበት ከነበረው የአንጋፋው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር መድረክ የተሰናበትው።በምትኩም "የሁለት አሽከር ጌቶች" የተሰኘ ተውኔት ሲቀርብም ቆይቷል።

ኤቨንት አዲስ ድረገፅ እንዳረጋገጠው በሚቀጥለው ሳምንት ሰኔ 14 2016 ዓ.ም "እሳት ወይ አበባ " ተውኔት ወደ መድረክ ተመልሶ በቋሚነት ዘወትር አርብ በ11:30 መቅረብ ይጀምራል ተብሏል።

ይህ ግጥማዊ ድራማ ከዚህ ቀደም በሀገር ፍቅር ቴአትር ትንሿ አዳራሽ ለታደሚያን ይቀርብ እንደነበር ይታወሳል።

📍መረጃውን ሲጠቀሙ ምንጭ ይጠቀሱ !

ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
በነፃ የተዘጋጀው የሮፍናን ማስተር ክላስ

ሁለገቡ ሙዚቀኛ ሮፍናን ኑሪ በሐዋሳና አካባቢ ለሚገኙ ወጣት የሙዚቃ ባለሞያዎች እና ተያያዥ የስራ መስክ ውስጥ ለሚገኙ ሁሉ "የሮፍናን ማስተር ክላስ" ስልጠና ጥሪ አስተላልፏል።

ሙዚቀኛ ሮፍናን ኑሪ ለሚመለከተው ሁሉ ተከታዩን መልዕክት በማህበራዊ ትስስር ገፁ አስተላልፏል:

"በሐዋሳ እና አካባቢው ምትገኙ የማስተር ክላሱን የትምህርት እና በተግባር የታገዘ ልምድ ልውውጥ ለመካፈል የምትፈልጉ ወጣት ጀማሪ ሙዚቀኞች: አቀናባሪዎች : ድምፃዊያን : የግጥም እና ዜማ ደራሲዎች : ዲጄዎች : የድምፅ ቅጂ እና ማስተሪንግ ኢንጂነሮች : እንዲሁም በኢንተርቴመንት ማርኬቲንግ ስራ ላይ ለተሰማራችሁ የማርኬቲንግ ባለሙያዎች እድሉ ለሚፈቅደው የ150 ሰው ምርጫ ውስጥ ለመግባት ለአጭር ጊዜ ምዝገባ ክፍት ነው::

ይህንንም ስናገር ለሀገራችን የሙዚቃ እና ኪነጥበብ ሚያበረክተውን በጎ አስተዋፆ በማሰብ ትልቅ ደስታ እና እድለኝነት ይሰማኛል:: ምስጋናዬ ለሚመለከተው ሁሉ ይድረስ::

ሊንኩን በመጫን መመዝገብ ትችላላችሁ::

https://rophnanmasterclass.et/ "

ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1

https://news.1rj.ru/str/EventAddis1

https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
እያዩ ፈንገስ ተውኔት አይቀርብም ተባለ

የእያዩ ፈንገስ 10ኛ ዓመት በዓልን አስመልክቶ ነገ ረቡዕ ሰኔ 5 እና አርብ ሰኔ 7 2016 በራስ ሆቴል ሊቀርብ የነበረው ዝግጅት ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት በነገው እለት እንደማይቀርብ አዘጋጆቹ ስለማሳወቃቸው ኤቨንት ድረገፅ ሰምቷል።

የተወኔቱ አዘጋጆች ወደፊት ተለዋጭ ፕሮግራም ሲኖር ለተመልካቹ እንደሚያሳውቁ ጨምረው ገልፀዋል።

በተጨማሪም "ለ10ኛ ዓመት በዓላችን መልካሙን ሁሉ ለተመኛችሁልንና በጠመዝማዛው መንገዳችን አብራችሁን ለነበራችሁ ወገኖቻችን ምስጋናችን ወሰን የለውም" በማለት መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።

"እያዩ ፈንገስ" የአንድ ሰው ተውኔት "አጀንዳዬ"  "ፌስታሌ" እና በቅርቡ ከመድረክ በታገደው "ቧልቲካ" በሚሉ ርዕሶች በተለያዩ መድረኮች ለታደሚያን ሲቀረብ ቆይቷል።

ዘወትር ሐሙስ በዓለም ሲኒማ ሲቀረብ የነበረው የእያዩ ፈንገስ "ቧለቲካ" ቴአትር ባሳለፍነው ጥር 2 2016 ዓ.ም ለህዝብ እንዳይታይ እንደተከለከለ ይታወሳል።

📍መረጃውን ሲጠቀሙ ምንጭ ይጠቀሱ !

ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
የኢትዮጵያ ኤለክትሪሲቲ አውደርዕይ ተከፈተ

አራተኛው የኢትዮጵያ ኤለክትሪሲቲ አውደርዕይ ከዛሬ ሰኔ 05 እስከ ፊታችን ቅዳሜ ሰኔ 08 ቀን 2016 ዓ.ም በሚሊኒየም አዳራሽ እየተካሄደ ይገኛል።

የዘንድሮው አራተኛው የኢትዮጵያ ኤለክትሪሲቲ አውደርዕይ"ኃይል ቁጠባ፣ አረንጓዴ አፍሪካ"በሚል መሪ ቃል የሚከናውን ሲሆን በዚህ አውደርዕይ ላይ አምራቾች ምርቶቻቸውንና አቅርቦቶቻቸውን ይዘው ይገኛል ተብሏል።

ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
ኢትዮ የምግብ እና መጠጥ ፌስቲቫል ተከፈተ

የምግብና መጠጥ ኢንዱስትሪ ምርምር እና ልማት ማዕከል ከአሜዚንግ ፕሮሞሽንና ኢቨንት እና ከዳብ ትሬዲንግ ጋር በመተባበር ከዛሬ ሰኔ 5 እስከ የፊታችን 9 2016 ዓ.ም የሚቆይ ኢትዮ የምግብና መጠጥ ፌስቲቫል በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል ተከፍቷል።

ለ5 ተከታታይ ቀናት በሚቆየው "ኢትዮ የምግብና መጠጥ ፌስቲቫል" በምግብ፣ በመጠጥ፣ በፓኬጂንግ እና ተዛማጅ መስኮች ላይ የተሰማሩ ግብዓት አቅራቢዎች፣ አምራቾች፣ አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶች፣ ከዘርፉ ጋር የተገናኙ አምራች እና አስመጪዎች እንዲሁም የፋይናንስ ተቋማት ይሳተፋሉ ተብሏል።

በፌስቲቫሉ ላይ የዘርፉ ባለሙያዎች የእውቅና አሰጣጥ ፕሮግራም፣ ሽልማት የሚያስገኙ ልዩ ልዩ ውድድሮች እና የመዝናኛ ፕሮግራሞች መካተታቸው ተገልጿል።

ኢትዮ የምግብና መጠጥ ፌስቲቫል የውጪ ሀገራት ዲፕሎማቶችን ጨምሮ በርካታ ኢትዮጵያውያን ሀገራችን በምግብና መጠጥ ረገድ ያላትን የቱሪዝም አቅም በቅርበት እንዲያውቁት የሚያደርግ ፌስቲቫል እንደሆነ ተነግሯል፡፡

የፊስቲቫሉ መግቢያ በነፃ መሆኑን እና ሁሉም ህብረተሰብ መካፈል እንደሚችሉ ተነግሯል ።

ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
የሐሙስ መረጃዎች

የሳምንቱ ኪናዊ መረጃዎች ቀጥሎ ይቀርባሉ!

ቀድመ ማሳሰቢያ: ሚዲያዎች መረጃውን ስትጠቀሙ ምንጭ ጥቀሱ❗️

📍መጽሐፍ

- የገጣሚ ኤፍሬም ስዩም አንድ መጽሐፍ በአንድ ሺህ ብር ቅድመ ክፍያ ለህትመት ሊበቃ እንደሆነ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ሰምቷል። "ቡና እና ምልኪ" የተሰኘውና ከዓመት በፊት ለንባብ ይበቃል ተብሎ የዘገየው መጽሐፍ ከፊታችን ቅዳሜ ጀምሮ በማህበራዊ ትስስር ገፅ በሚደረግ ቅድም ክፍያ እንደሚታተም ገጣሚው አስታውቋል። ገጣሚው በማህበራዊ ትስስር ገፁ"በሀርድ ኮፒ ያጌጠ ምልኪና ቡና ከቅዳሜ ጀምሮ 1000 ኮፒ ህትመት በ1000 ብር ብቻ እጃችሁና የመጻሕፍት ሼልፋችሁ ላይ ለማኖር ዝግጅት አድርጉ" ብሏል።

-የገጣሚ መንበረማርያም ኃይሉ አዲስ መጽሐፍ ለንባብ በቃ። መጽሐፉ "የጊዜ ሠሌዳ" የተሰኘ ርዕስ የተሰጠው የግጥም ስብስብ መጽሐፍ ነው።በ103 ገፆች ተቀንብቡ በ250 የጀርባ ዋጋ ለአንባቢያን የቀረበ ሲሆን ዛሬ በሚካሄደው የመቅረዝ ሥነኪን የኪነጥበብ ዝግጅት ላይ በገጣሚዋ ተፈረሞ ለአንባቢያን ይደርሳል ተብሏል። ገጣሚዋ ከዚህ ቀደም "የቃል ሠሌዳ" የተሰኘ መጽሐፍ ለንባብ ማብቃቷ ይታወሳል።

-የገጣሚና የህግ ባለሞያው ደሱ ፍቅርኤል "እስከ መቅደላ " የተሰኘ መጽሐፍ ለንባብ በቅቷል።ገጣሚ ደሱ ከዚህ ቀደም "ሀገሬን ሰቀሏት" እና "ተይው ፖለቲካን ዝም ብለሽ ሳሚኝ" የተሰኙ መጻሕፍትን ለአንባቢያን አድርሷል። መጽሐፉን በተለያዩ መጻሕፍት መደብሮች ታገናላችሁ ተብላችኋል።

-የጋዜጠኛ መኮንን ወ/አረጋይ "እነሆ ማሟሻ" የተሰኘ አዲስ መጽሐፍ በሳምንቱ መጨረሻ ቀናት ለአንባቢያን ይደርሳል።ከዚህ ቀደም በሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ ላይ በሚያቀርባቸው የስንክሳር፣  የማሟሻ፣ የአርብ ምሽት ቆየት ያሉ ሙዚቃዎች እና አሁን ላይ በኢንቢሲ ቴሌቪዥን በልዩ ልዩ ዝግጅቶች የምናውቀው ጋዜጠኛ መኮንን ወ/አረጋይ "እነሆ ማሟሻ" የተሰኘ የመጀመሪያ ቅጽ አዲስ መጽሐፍ በዚህ ሳምንት መጨረሻ ቀናት ለአንባቢያን ይደርሳል ተብሏል።መጽሐፉ በ200 ገፆች የተነበበ ሲሆን በ250 ብር የጀርባ ዋጋ ለአንባቢያን እንደሚደርስ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ሰምቷል።

📍ሙዚቃ

-የድምጻዊት ሔዋን ገብረወልድ "ያንተን" የተሰኘ ሙዚቃ ነገ አርብ  ለአድማጮች ይደርሳል። በዚህ የሙዚቃ ስራዋ ላይ ገጣሚ ምልእቲ ኪሮስ በግጥም ምረታብ ደስታ በዜማ ተሳትፈዋል።ሙዚቃ ቅንብርና ማስተሪንጉን ስማአገኘሁ ሳሙኤል ሰርቷል።

-የድምጻዊት ሜላት ቀለመወርቅ "ዋይ" የተሰኘ ሙዚቃ ነገ አርብ በናሆም ሪከርድስ በኩል ለአድማጮች ይደርሳል ተብሏል።በዚህ የሙዚቃ ስራዋ ላይ በግጥምና ዜማ ምህረትአብ ደስታ ሲሳተፍ ቅንብር፣ሚክሲንግ፣እና ማስተሪጉን ደግሞ ሔኖክ ድለቃ ሰርቷል።

-ሙዚቀኛ ሮፍናን ኑሪ "የኔ ትውልድ" በተሰኘ የአሜሪካ ጉዞ የሙዚቃ ዝግጅቱን እንደሚያካሄድ በማህበራዊ ትስስር ገፁ አስታውቋል። የሙዚቃ ዝግጅቱን በቅርቡ በአሜሪካ አትላንታ ግዛትን ጨምሮ በተለያዩ ግዛቶች ውስጥ እንደሚያቀርብ ገልጿል። ሮፍናና ከወራት በፊት ዘጠኝ በሚል ርዕስ "ሀራንቤ" እና "ኖር" የተሰኙ ሁለት አልበሞችን በአንድ ቀን ለአድማጮች ማድረሱ ይታወሳል።

📍 ቴአትር

-የ"እያዩ ፈንገስ" 10ኛ ዓመት በዓልን አስመልክቶ  ረቡዕ ሰኔ 5 እና አርብ ሰኔ 7 2016 ዓ.ም በራስ ሆቴል ሊቀርብ የነበረው ዝግጅት ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት  እንደማይቀርብ አዘጋጆቹ ማሳወቃቸው የተሰማው በዚህ ሳምንት ነበር።የተወኔቱ አዘጋጆች ወደፊት ተለዋጭ ፕሮግራም ሲኖር ለተመልካቹ እንደሚያሳውቁ ጨምረው ገልፀዋል።

- "እሳት ወይ አበባ" ተውኔት ወደ መድረክ ሊመለስ ነው። በሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን ግጥሞች ላይ የተመሰረተው "እሳት ወይ አበባ" ግጥማዊ ዳንስ ተውኔት በብሔራዊ ቴአትር ከሰኔ 14 2016 ዓ.ም ጀምሮ ወደ መድረክ እንደሚመለስ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ሰምቷል።ይህ ሙከራዊ ተውኔት ባሳለፍነው ጥቅምት 2 2016 ዓ.ም ነበር ዘወትር አርብ ሲቀረብበት ከነበረው የአንጋፋው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር መድረክ የተሰናበተው። በምትኩም "የሁለት ጌቶች አሽከር" የተሰኘ ተውኔት ሲቀርብም ቆይቷል።

📍ኪነጥበብ ዝግጅት

"መቅረዝ ሥነኪን" የኪነጥበብ ዝግጅት ዛሬ ይካሄዳል። አንጋፋ እና ወጣት የኪነጥበብ ባለሞያዎችን እያጣመር የዘለቀው መቅረዝ ሥነኪን ወርሀዊ የኪነጥበብ  ዝግጅት ሀሙስ ሰኔ 6 2016 ዓ.ም ከምሽቱ 11:00 ጀምሮ በብሔራዊ ቤተመጻሕፍትና ቤተመዛግብት አገልግሎት (ወመዘክር )አዳራሽ ውስጥ ይካሄዳል። በዕለቱም አርቲስት ድርብወርቅ ሰይፉ በክብር እንግድነት ትገኛላች ተብሏል።

📍የሥነጥበብ አውደርዕይ (ሥዕል)

- የሠዓሊ ዮናታን ወንደሰን ሥዕል ስራዎች የሚቀርቡበት "ከአጥሮች ባሻገር" የሥዕል አውደርዕይ ነገ አርብ ሰኔ 7 2016 ዓ.ም ከምሽቱ 12:00 ጀምሮ ካዛንቺስ በሚገኘው ፈንድቃ የባህል ማዕከል ውስጥ ለእይታ ይበቃል። ይህ የሥዕል አወድርዕይ እስከ ሰኔ 21 2016 ዓ.ም ይቆያል ተብሏል።

-የሠዓሊ ኃይለገብርኤል ንጉሴ የሥዕል ስራዎች የሚቀረበብት "The light Path" የሥዕል አውደርዕይ ቅዳሜ ሰኔ 8 2016 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ጀምሮ መስቀል አደባባይ አካባቢ በሚገኘው የአዲስ አበባ ሙዚየም ውስጥ ላይ ለእይታ ይበቃል።ይህም የሥዕል አውደርዕይ እስከ ሰኔ 23 2016 ዓ.ም በእይታ ላይ ይቆያል ተብሏል።

📍ፊልም

"ጃንሞራ" የተሰኘ ፊልም በቅርቡ ለተመልካች ይቀርባል። በኪም ፊልምስ ተዘጋጅቶ በከአብ መልቲሚዲያ የቀረበው የያለው ደስታ (ራስ) "ጃንሞራ" የተሰኘ ፊልም ከሰኔ 21 ጀምሮ በሁሉም ሲኒማ ቤቶች ለተመልካች እንደሚቀረብ ኤቨንት አዲስ ድረገጽ የደረሰው መረጃ ያመለክታል።በዚህ ሀገርኛ ፊልም ማርታ ጎይቶም፣ ነብዩ እንድሪስ ፣ እንግዳሰው ሀብቴ እና ሌሎችም በተዋናይነት ተሳትፈውበታል።

አዘጋጅ: ናቲ ማናዬ

ቀን: ሰኔ 6 2016 ዓ.ም

አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

በድረገጻችን በተሻለ አቀራረብ ያንብቡ:

https://eventaddis.com

ቴሌግራም: @EventAddis1
ሜሊስ ፋሽን እና ትሬድንግ ዓለምአቀፍ ሞዴል ጆዝሳ እስዝተር ኒኮሌቴን የድርጅቱ ብራንድ አምባሳደር አድርጎ ሾመ

ሜሊስ ፋሽን እና ትሬድንግ በሀገራችን ኢትዮጵያ ጥራት ፣ደረጃቸው የተመሰከረላቸው የሜሊስ ፋሽን እና ትሬዲንግ ልዩ ልዩ የፋሽን እና የዲዛይን ምርቶች የሚቀረቡባቸው ሱቆች መከፈቱን በማስመልከት ዓለምአቀፍ እውቅና ያላትን የሃንጋሪይ ተወላጅ ከሆነችው ኢንተርናሽናል ሞዴል ጆዝሳ እስዝተር ኒኮሌቴን ጋር አብሮ ለመስራት የድርጅቱ የብራንድ አምባሳደር ይፋ ማድረጊያ ሥነሥርዓት ሐሙስ ሰኔ 6 2016 ዓ.ም በሀያት ሪጀንሲ አካሄዷል።

ሜሊስ ፋሽን እና ትሬድንግ በኢንተርናሽናል ሞዴል እና ዲዝይነር ሜላት ሚካኤል የተመሰረተ ሲሆን ፤ በቻይና ጉዋንዡ ሆንግኮንግ እና ሻንጋይ ዓለምአቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ ዕውቅ የፋሽንና ዲዛይን ምርቶችን እንዲሁም ብራንዶችን ለዓለም ገበያ የሚያቀርብባቸው ሱቆችን በመክፈት አገልግሎት እየሰጠ እንደሚገኘ ተገልጿል።

ኢንተርናሽናል ሞዴል እና ዲዝይነር ሜላት ሚካኤል በዓለምአቀፉ ፋሽን መድረክ ላይ የእሷን አሻራ ለማሳረፍ ጥረት እያደረገች እንደምትገኝ በኩነቱ ላይ ገልጻለች።

ሜሊስ ፋሽን እና ትሬድንግ በሀገራችን ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ጥራት ደረጃቸው የተመሰከረላቸው የሜሊስ ፋሽን እና ትሬዲንግ ልዩ ልዩ የፋሽን ሱቆች እንደፈከትም ይፋ አድርጓል።

ቴሌግራም: @EventAddis1
ኮሜዲያን ቤቲ ዋኖስ የማይ ሶሮባን ሀገር አቀፍ የሒሳብ ትምህርት ውድድር የበጎ ፍቃድ አምባሳደር ሆና ተሾመች

ማይ ሶሮባን ኢትዮጵያ ኃ/የተ/የግ/ማህበር “ሒሳብ ትምህርት ይከብዳል” የሚል የተሳሳተ አመለካከት በማስወገድ ጉብዝና ያሽልማል › በሚል መሪ ቃል ሀገር አቀፍ የሒሳብ ትምህርት እና የስሌት ውድድር በሀገራችን በሚገኙ ሁለም ትምህርት ቤቶች ለማከናወን የተቋቋመ በኢትዮጵያ ብቸኛው የሒሳብ ትምህርት አወዳዳሪ ተቋም ነው፡፡

በማይ ሶሮባን ኢትዮጵያ የ2016 ዓ.ም ሀገር አቀፍ የሒሳብ ትምህርት ውድድር ከ50 ከተሞች የተውጣጡ ከ2ሺ በላይ ትምህርት ቤቶች እና ከ3መቶ ሺ በላይ ተማሪዎችን አሳትፏል፡፡

ውድድሩ በአጠቃላይ ስድስት ዙሮች ሲኖሩት አምስቱ ዙሮች በየከተሞቹ የተከናወኑ ሲሆን የመጨረሻው ወይም ስድስተኛው ዙር የፍጻሜ ውድድር ከሁሉም ከተሞች የየከተማው አሸናፊ ተማሪዎች በተገኙበት በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኘው የሚሊኒየም አዳራሽ የመጨረሻውን የአሸናፊዎች አሸናፊ ውድድር ለከፍተኛ ሽልማት ይወዳደራሉ፡፡ የዚህ ውድድር አሸናፊ ተማሪዎች በጠቅላላ አራት ሚሊዮን ብር የሚፈጅ የገንዘብና የአይነት ሽልማት ተዘጋጅቶላቸዋል ተብሏል።

በዳኝነት የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ እና የኮተቤ መምህራን ዩኒቨርስቲ መምህራን ሲሳተፉ የየከተማ ተወካዮቻቸውም በታዛቢነት እንደሚሳተፉ ተገልጿል።

የመዝጊያው መርሃግብር በአዲስ አበባ ሚሊኒየም አዳራሽ ከሐምሌ 28 እስከ ነሐሴ 1 2016 ዓ.ም ይከናወናል ተብሏል።

ማይ ሶሮባን ኢትዮጵያ ዛሬ ሰኔ 6 2016 ዓ.ም በሚሊኒየም አዳራሽ በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ኮሜዲያን ቤቲ ዋኖስ የበጎ ፍቃድ አምባሳደር አድርጎ እንደሾመ አስታውቋል።

ቴሌግራም: @EventAddis1
በኢትዮጵያዊው የዜማ ሊቅ በቅዱስ ያሬድ ስም የተሰየመ የድረገጽ አገልግሎት ይፋ ተደረገ

ታሪካዊው በሆነው የደብረ ሐዊ ቅዱስ ያሬድ የአንድነት ገዳም ስያሜ የተሰራው ድረገጽ  ብፁዕ አቡነ ዲሜጥሮስ የምሥራቅ ካናዳ ሊቀ ጳጳስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል በተገኙበት ሰኔ 6 2016 ዓ.ም በራማዳ ሆቴል በተከናወነው መርሐግብር ይፋ ተደርጓል።

በሰሜን ጎንደር ዞን በበየዳ ወረዳ የሚገኘውን ደብረ ሐዊ ቅዱስ ያሬድ አንድነት ገዳም  እየተከናወነ ያለውን የግንባታ ኘሮጀክት ያስተዋውቃል የተባለው ድረገጹ በገዳሙ እየተሰራ ያለውን የአብነት ትምህርት ጥንታዊነቱን ጠብቆ የሚያስተምር የልህቀት ማዕከል ማድረግና ምዕመናን ወደ ገዳሙ እየሔዱ በረከት የሚያገኙበት ከዓለም ዙሪያ ለሚመጡ ጎብኚዎች የቤተክርስቲያኗንና የሀገራችን ቀደምትነት ገናና ባለታሪክ መሆናቸውን የሚረዱበትና ሀገራችንም የውጭ ምንዛሪ የምታገኝበት ማድረግን ዓላማ አድርጎ እየሠራ ይገኛል ተብሏል።

www.kidusyaredzedebrehawi.com በገዳሙ እየተከናወነ ያለውን ፕሮጀክት አስመልክቶ ዝርዝር ማብራሪያ የሚሰጥ ሲሆን ገዳሙን በገንዘብ በቀጥታ ማገዝ እንድችሉ ተደርጎ እንደበለጸገ በመድረኩ ላይ ተገልጿል።

ቅዱስ ያሬድ ከ1500 አመታት በፊት የኖረ፣ የመጀመሪያው የአለማችን  የዜማ አውጭ፣ የመጀመሪያው የመፃሕፍት ደራሲ፣ ታላቅ የፍልስፍና ሰው፣ የብዙ ነገሮች ሊቅ፣ ባለቅኔ የሆነ፣ ኢትዮጵያ ለዓለም ያበረከተችው ግዙፍ ባለጸጋ ነው።

ቅዱስ ያሬድ ባስተማረበት በመጨረሻም በተሰወረበት ስፍራ፣ በሰሜን ተራራ ላይ በደብረ ሐዊ ቅዱስ ያሬድ አንድነት ገዳም በርካታ ልማቶችን በማድረግ ላይ እንደሚገኝ ማህበሩ አስታውቋል።

ቴሌግራም: @EventAddis1
ካውሰር ( ሻሊና ሄልዝ ኬር)የተሰኘ ድርጅት አራት የቆዳ መንከባከቢያ ምርቶችን ያስተዋውቀበትን ኩነት አካሄድ

ካውሰር PLC( ሻሊና ሄልዝ ኬር) በአለም አቀፍ ደረጃ ትልቅ ተቀባይነትን ያተረፈ ድርጅት ሲሆን በኢትዮጵያ ይዟቸው የመጣቸውን አዳዲስ ምርቶች ሰኔ 6 2016 ዓ.ም አስተዋውቋል።

ከነዚህ ምርቶች ውስጥ አንዱ ሞናሊሳ ሲባል ይህም የቆዳ እንክብካቤን ለመጠበቅ የሚያስችል ሎሽንና ክሬም ነው።

ኤፒግሎው የተሰኘው ደግሞ ለአፍሪካ ቆዳ የተዘጋጀ ሲሆን እንደ ጥቁር ነጠብጣቦች እና ዥንጉርጉር ፊትን እና የተለመዱ የቆዳ ስጋቶችን በ28 ቀናት ውስጥ በመቀነስ ብቻ የሚታይ ለውጥ የሚሰጥ የቆዳ መንከባከቢያ እንደሆነ ተገልጿል።

ሌላው ፍሎደንት የተባለው የጥርስ ሳሙና ምርት ሲሆን በፍሎራይድ ለተጠቃ ጥርስ፣ ለአፍ ጤንነት፣ የጥርስ መቦርቦርን የሚታደግ እንደሆነ ተነግሯል።

የመጨረሻው ምርት ጀርሞል የተሰኘ ሳሙና ሲሆን  ሰውነትን ከጀርሞች ለመከላከል የሚረዳ ነው ተብሏል።

ሻሊና ሄልዝ ኬር 40 አመትን ያስቆጠረ ድርጅት ሲሆን እስካሁን በ22  የአፍሪካ ሀገራት ላይ ሰርቷል።

ድርጅቱ በአሁን ሰአት በአዲስ አበባ ላይ 6 ክፍለ ከተሞች ላይ ስራ የጀመረ ሲሆን 1000 ለሚደርሱ ሰዎች የስራ እድል ፈጥሯል።

ቴሌግራም: @EventAddis1
የኔ መኪና እና የኔ ዴልቨሪ አገልግሎቶች ይፋ ሆኑ

ቲዎስ ቴክኖሎጂ "የኔ መኪና" እና "የኔ ዴልቨሪ" የተሰኙ ሶፍትዌሮችን በማበልጸግ ወደ ስራ ማስገባቱን ሰኔ 6 2016 ዓ.ም በሃያት ሪጀንሲ ሆቴል በተሰናዳ ፕሮግራም ይፋ አድርጓል።

"የኔ መኪና" የትራንስፖርት ዘርፉን ከማዘመን አኳያ በርካታ ጥቅሞች እንደሚሰጥ የተነገረ ሲሆን በተለይም በመንገድ እና ትራንስፖርት ባለስልጣንና በተሽከርካሪ ባለንብረቶች መካከል ያለውን ግንኙነት ያለምንም ክፍተት በመናበብ ስራቸውን ምቹ እና ቀልጣፋ እንዲሆን ከማድረግም በላይ የተሽከርካሪ ባለንብረቶችን ማሳደስ ያለባቸውን ነገሮች በማስታወስ ከቅጣት እና አላስፈላጊ እንግልት የሚያድን ሶፍትዌር እንደሆነ ተገልጿል።

ሌላኛው "የኔ ዴሊቨሪ" ሶፍትዌር ሲሆን የተለያዩ ዶክመንቶችን፣ ሰነዶችን፣ እቃዎችን እንዲሁም የተሽከርካሪ መለዋወጫ እቃዎችን ቴከኖሎጂ በመጠቀም ለግለሰቦች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለሆስፒታሎች ለማድረስ የበለጸገ ሶፍትዌር እንደሆነ ተነግሯል።

ቲዎስ ቴክኖሎጂ ሶልሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር የተለያዩ ሶፍትዌር መተግበሪያዎችን በማበልጽግ እየሰራ የሚገኘ ድርጅት ነው።

ቴሌግራም: @EventAddis1
ድምጻዊ ጉቱ አበራ "ጋፊኮ" የተሰኘ አልበሙን በሚቀጥለው ሳምንት ለአድማጮች ያደርሳል

ድምፃዊ ጉቱ አበራ “ጋፊኮ” የተሰኘ የመጀመሪያው አልበሙን ማጠናቀቁን አስታወቀ።

ድምፃዊ ጉቱ አበራ በለቀቃቸው ነጠላ ዜማዎች በርካታ አድናቂዎችን አፍርቷል።

ከ15 ቀን በፊት ኢዮሌ የተሰኘ ቪዲዮ ክሊፕ የተሰራለት ነጠላ ዜማ ለቆ ተወዶለታል።

አልበሙ በሚቀጥለው ሳምንት አርብ ሰኔ 14 2016 ዓ.ም እንደሚለቀቅ ፋስት መረጃ ከድምፃዊው ያገኘው መረጃ ያሳያል።

አልበሙ የራሱን የዩቲዩብ ቻናልን ጨምሮ በሌሎችም ዓለምአቀፍ የሙዚቃ መተግበሪያዎች በላይ ይለቀቃል ተብሏል።

📍መረጃው የፋስት መረጃ ነው።

ቴሌግራም: @EventAddis1
የሠዓሊ ብሩክ የሺጥላ የሥዕል አውደርዕይ ተከፈተ

የእውቁ ሠዓሊ ብሩክ የሺጥላ "የይቅርታ ጉዞ" የተሰኘ የሥዕል አውደርዕይ ሰኔ 6 2016 ዓ.ም ቦሌ አትላስ መብራት አካባቢ በሚገኘው የኢትዮጵያ ሜትሮፖሊታን የሥዕል ማሳያ ውስጥ የሥዕል ወዳጆች በተገኙበት ለእይታ እንደበቃ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ሰምቷል።

ይህ የሥዕል አውደርዕይ እስከ ሰኔ 23 2016 ዓ.ም ለሳምንታት በእይታ ላይ ይቆያል ተብሏል።

ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
"ሜላድ"አውደርዕይ ቅዳሜ እና እሁድ ይካሄዳል

ሜላድ ጥንታዊ የብራና መጻሕፍት ዝግጅት ማዕከል"ሜላድ የብራና ማዕድ" በሚል መሪ ቃል ዛሬ ቅዳሜ ሰኔ 8 እና ነገ እሁድ ሰኔ 9 2016 ዓ.ም አዘጋጅቷል።

ይህ አውደርዕይ ከዛሬ ቅዳሜ ከጠዋት 3፡00 ላይ ተከፍቶ እስከ እሁድ ምሽት ድረስ በቦሌ ደብረ ሳሌም ካቴድራል ትልቁ አዳራሽ ውስጥ ይካሄዳል።

ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
"የአባቶች የአእምሮ ጤና:የቤተሰብ ብርታት" የተሰኘ ተከታታይ የሥነልቦና ውይይት ከእሁድ ጀምሮ ይካሄዳል

የአእምሮ ጤና ተሟጋች የሆነው እና የቤተሰብ የአእምሮ ደህንነት ላይ በመስራት የሚገኘው ሜንታል ሄልዝ አዲስ “የአባቶች የአእምሮ ጤና፡ የቤተሰብ ብርታት” በሚል መሪ ቃል ተከታታይ  መርሐግብር ለማሰናዳት እየተዘጋጀ እንደሆነ አስታውቋል።

ይህም አባቶች ጤናማ እና ብርቱ ቤተሰብ በማጎልበት ረገድ ስለሚጫወቱት ወሳኝ ሚና አፅንዖት ለመስጠትም ያለመ ነው ተብሏል።

ዝግጅቱን በዓለም አቀፍ የአባቶች ቀን እሁድ ሰኔ 9 2016 ዓ.ም ከቀኑ በ9፡00 ሰዓት ጀምሮ በኢሊሊ ኢንተርናሽናል ሆቴል በርካታ አባቶች በተገኙበት አባትነትን በመዘከር የመክፈቻ ፕሮግራም እንደሚደረግ ኤቨንት አዲስ ደስታ ድረገፅ ሰምቷል።

የዚህ መርሐግብር መግቢያ ሁለት መቶ ብር ነው።

ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ሽልማት በዚህ ወር ይካሄዳል

የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ሽልማት የፊታችን ሰኔ 22 ቀን 2016 ዓ.ም እንደሚካሄድ አዘጋጆቹ አስታውቀዋል።

ዘንድሮ ለሶስተኛ ጊዜ የሚካሄደው የሃጫሉ ሽልማት በ11 የሽልማት ዘርፎች፤ በአፋን ኦሮሞ የተሰሩ የዓመቱ ምርጥ አልበም፣ የአመቱ ምርጥ ግጥምና ዜማ ደራሲ፣ የዓመቱ ምርጥ አቀናባሪ፣ ምርጥ የባህል ዘፈን፣ ምርጥ ዘመናዊ ሙዚቃ፣ የዓመቱ ምርጥ ወንድ እና ሴት አርትስቶች፣ የኣመቱ ምርጥ አዲስ ሙዚቀኛ (ሴት እና ወንድ)፣ ምርጥ የአመቱ የሙዚቃ ቪዲዮ፣ ሲኒማቶግራፊ እና ምርጥ ባህላዊ ውዝዋዜ በሚሉ ዘርፎች እንደሚሸለሙ ታውቋል፡፡

በሽልማት ውድድሩ ውስጥ ሚካተቱ የሙዚቃ ስራዎች ከመጋቢት 22 ቀን 2015 ዓ.ም እስከ መጋቢት 21 ቀን 2016 ዓ.ም የወጡ ብቻ ናቸው ተብሏል፡፡

ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
እማዬ እንዳለች ኑ ቡና ጠጡ ብላለች!

በአዲስ አበባ ከተማ መስቀል አደባባይ ከዛሬ ሰኔ 8 እስከ ነገ ሰኔ 9 2016 ዓ.ም ለአዲስ አበባ ህዝብ ቡና በነፃ እየተጋበዘ ነው።

ይህ አዲስ ነገር በአዲስ ዓመት ነፃ ቡና ዝግጅት ሙዚቃ ፣ፋሽን ሾዎችን መዝናኛዎችን እና የተለያዩ አዝናኝ ዝግጅቶችን ማሰናዳታቸውን እና ህብረተሰቡ በነጻ ቡና እየጠጣ እንዲዝናና አዘጋጆቹ ታሜሶል ኮሚዩኒኬሽን አሴቲክስ ሶሉሽን እና ከሊያን ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።

#Ads

ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
የወንዲ ማክ አልበም ሰኔ 14 ይለቀቃል

የድምፃዊ ወንደሰን መኮንን በመድረክ ስሙ (ወንዲ ማክ) "ይንጋልሽ" የተሰኘ አዲስ አልበም የፊታችን ሰኔ 14 2016 ዓ.ም ለአድማጮች እንደሚደርስ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ሰምቷል።

ድምጻዊው በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገፁም "እነሆ አርብ ሠኔ 14 ቁርጥ ቀን ሆነ "ይንጋልሽ " ብለን ከንጋት የተቃጠርንበት አልበማችንን ወደ እናንተ የምናደርስበት ሠላም ያቆየን" ብሏል።

ይህም አልበም ዩቲዩብን ጨምሮ በተለያዩ ዓለምአቀፍ የሙዚቃ መተግበሪያዎች ላይ ይለቀቃል ተብሏል።

ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
ጋዜጠኛ ፀጋዬ ወንድወሰን የ"ቮይስ ኦፍ ሚዲያ" የኢትዮጵያ ተወካይ ሆኖ ተመረጠ፡፡

በፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት የሬድዮ እና ቴሌቪዥን ዜናዎቹ የምናዉቀውና በያዝነው አመት መጀመሪያ አዲስ ዋልታ ቴሌቪዥንን የተቀላቀለው ጋዜጠኛ ፀጋዬ ወንድወሰን የ"ቮይስ ኦፍ ሚዲያ "የኢትዮጵያ ተወካይ ሆኖ እንደተመረጠ በማህበራዊ ትስስር ገፁ አስታውቋል።

ጋዜጠኛ ፀጋዬ በማህበራዊ ትስስር ገፁ ባሰፈረው መረጃ "ቮይስ ኦፍ ሚዲያ" መቀመጫውን በህንድ ሙምባይ ከተማ ያደረገ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ነው።

የጋዜጠኞችን ሙያዊ ክህሎት እና ቤተሰቦቻቸውን  ህይወት ማሻሻል ላይ ትኩረት አድርጎ የሚሰራው ድርጅቱ በመላው ዓለም ያሉ ጋዜጠኞችን "ቮይስ ኦፍ ሚዲያ" በሚል ስያሜ ከፈረንጆቹ 2021 ጀምሮ ለማስተባበር እየሰራ ያለ ተቋም ነው። ዋና ዋና አምስት መርሆችን አሉኝ የሚለው ድርጅቱ ጋዜጠኝነትን ማስፋፋት እና የጋዜጠኞችን አኗኗር ማሻሻል ላይ አልሞ የሚሰራ ነው፡፡ 

ኢቨንት አዲስ ከጋዜጠኛ ፀጋዬ ወንድወሰን ባገኘው መረጃ  "ድርጅቱ በዋናነት የጋዜጠኞችን የመኖሪያ ቤት፣ የጤና፣ የጋዜጠኛ ልጆችን በትምህርት መደገፍን ጨምሮ የጋዜጠኞችን ክህሎት እና የድህረ ጡረታ ፈተናዎች ላይ ትኩረቱ አድርጎ ይሰራል፡፡"

"ቮይስ ኦፍ ሚዲያ" በኢትዮጵያ ለሚያደርጋቸው እንቅስቃሴዎች ጋዜጠኛ ፀጋዬ ወንድወሰንን በበጎ ፍቃደኛ ተወካይነት ሲመርጥ ፤ በዋናነት ለዚሁ ስራ በጎ ፈቃደኛ እና ተነሳሽነት ያላቸውን ሌሎች ኢትዮጵያዊያን ጋዜጠኞችንም የሚያካትት መሆኑንም ሰምተናል፡፡

ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1