Event Addis Media – Telegram
Event Addis Media
9.61K subscribers
6.13K photos
14 videos
4 files
4.75K links
Connect with Addis artistic community!

Website: https://eventaddis.com

Contact: @Tmanaye
Download Telegram
የአርአያ ሰው ሽልማት ሥነሥርዓት ዛሬ ይካሄዳል

ተቀማጭነቱን በሀገረ አሜሪካ ዳላስ ቴክሳስ ያደረገው ዓድዋ የባህልና የታሪክ ኅብረት ለትርፍ ያልተቋቋመ ግብረ ሰናይ ድርጅት ሲሆን በዋናነትም ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያውያን አርአያ የሚሆን ሥራ ለሚሠሩ ግለሰቦችና ተቋማት"የአርአያ ሰው ሽልማት" በሚል ዕውቅና ይሰጣል፡፡

ተቋሙ የሚያዘጋጀው አርአያ ሰው ሽልማት ባለፉት ስድስት ዓመታት ባህል፣ ቅርስና ታሪክ ለተተኪው ትውልድ እንዲተላለፍ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ በማድረግ ላይ ለሚገኙ ኢትዮጵያውያን አጋርነት፣ ድጋፍና ዕውቅና ሲሰጥ ቆይቷል፡፡

ዘንድሮም ለ8ኛ ግዜ በአዲስ አበባ ዮድ አቢሲኒያ የባህል አዳራሽ ዛሬ ሰኔ 13 ቀን 2016 ዓ.ም በተመሳሳይ መልኩ ለሀገር ባለውለታዎች በተለይም በባህል ልማት፣ በተፈጥሮ ጥበቃ፣ በቱሪዝም እና ቅርስ እንዲሁም በታሪክ መስኮች ለሀገራቸው አስተዋጽኦ ላበረከቱ ግለሰቦችና ተቋማት ሽልማት ይሰጣል፡፡

ዛሬ የሚካሄደው የአርዓያ ሰው የሽልማት ሥነሥርዓት በሀገሬ ቴሌቪዥን  የቀጥታ ስርጭት  ሽፋን ያገኛል ተብሏል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
ተወዳጇ ተዋናይት ሙላለም ታደሰ ልትሸልም በተጠራችበት መድረክ ተሸልማ ወረደች::

ተስፋ የኪነ ጥበብ ኢተርፕራይዝ ባዘጋጀውና 25ኛ አመቱን ለማክበረ ለ25 የቴአትር ባለሙያዎች እውቅና ሽልማት የሚሰጥበት  መድረክ በመካሄድ ላይ ነው::

በርካቶች በተሸለሙበት ስነ ስርአት ባለፋት 25 ዓመታት ከበርካታ የኪነ ጥበብ ሙያተኞች ጀርባ በመሆን ላበረከተው አስተዎፅኦ ልዩ ተሸላሚ የሆነው የማስታወቂያ ባለሞያ ሳምሶን ማሞ "ልዩ ተሸላሚ" ሆኖ ቢቀርብም የሽልማት ዋንጫውን ለእኔ አይገባኝም በሚል ሽልማቱን ለአርቲስት ሙሉዓለም ታደሰ አስረክቧል::

ሳምሶን " ሙሉዓለም ለቴያትር በሰራችው ስራ ልክ ያልተከበረች ክፍያው በቂ ሳይሆን ሙያውን አክብራ የሰራች በመሆኗ ለኔ ሳይሆን ክብሩ ለሷ ይሁን " ሲል  ስሜቱን ለታዳሚው  ገልፃል::

ነገሩ እንግዳ የሆነባ ተወዳጇ አርቲስት ሙሉዓለም ታደሰ " ሳምሶን ለኔ ባገኝው መድረክ ሁሉ የሚሟገት ነው ይህን ያልጠበኩትን በማድረጉም ብደነግጥም አመሰግነዋለው" ስትል ለኤፍ ኤም አዲስ 97.1 ተናግራለች::

📍መረጃው የአሸናፊ ደምሴ (FM 97.1) ነው።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
ዛሬ ሶስት ሙሉ አልበሞች ለአድማጮች ይደርሳሉ

ዛሬ ሰኔ 14 2016 ዓ.ም የኢትዮጵያ ሙዚቃ  ላይ  "ጋፊኮ"  "ይንጋልሽ" እና "አያዳላም" የሚል ርዕስ የተሰጣቸው ሶስት ሙሉ አልበሞች ይጨምራሉ።

ዛሬ ከሚለቀቁ አልበሞች አንደኛው የድምፃዊ ጉቱ አበራ “ጋፊኮ” የተሰኘ የመጀመሪያ አልበም ሲሆን ዛሬ አርብ ሰኔ 14 2016 ዓ.ም የድምጻዊው ዩቲዩብ ቻናልን ጨምሮ በተለያዩ ዓለምአቀፍ የሙዚቃ መተግበሪያዎች ላይ ይለቀቃል ተብሏል። "ጋፊኮ" አልበም ስምንት የሙዚቃ ስራዎችን ይዟል። ጉቱ አበራ ከዚህ ቀደም ሀዋንሀዋ፣ ዴሚ፣ አነቱ፣ኢዮሌ የተሰኙ ሙዚቃዎችን ለአድማጮች ማድረሱ አይዘነጋም።

በሌላ በኩል የድምፃዊ ወንደሰን መኮንን በመድረክ ስሙ (ወንዲ ማክ) "ይንጋልሽ" የተሰኘ አዲስ አልበም ዛሬ አርብ ሰኔ 14 2016 ዓ.ም ለአድማጮች እንደሚደርስ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ሰምቷል።14 ሙዚቃዎችን የያዘው አልበሙ ግጥም እና ዜማው በራሱ በወንዲ ማክ ተሰርቷል። በፍቅር፣ በማህበራዊ እና ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ የሚያጠነጥን እንደሆነ ተነግሯል።ይህም አልበም ዩቲዩብን ጨምሮ በተለያዩ ዓለምአቀፍ የሙዚቃ መተግበሪያዎች ላይ ይለቀቃል ተብሏል።

ሶስተኛው አልበም የድምጻዊ ፍፁም ቲ "አያዳላም" የተሰኘ አዲስ አልበም ሲሆን ዛሬ አርብ ሰኔ 14 2016 ዓ.ም በፍፁም ቲ የዩቲዩብ ቻናል እና በሌሎችም የሙዚቃ መተግበሪያዎች ላይ ይለቀቃል።አልበሙን ወንድወሰን ይሁብ በሪኮርዲንግ ፕሮዲዩሰርነት ያዘጋጀው ሲሆን በርካታ የሙዚቃ ባለሞያዎች ተሳትፈውበታል ተብሏል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
የ"እሳት ወይ አበባ" ተውኔት ወደ መድረክ የሚመለስበት ጊዜ እንደተራዘመ አዘጋጆቹ አስታወቁ

በሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን ግጥሞች ላይ የተመሰረተው "እሳት ወይ አበባ" ግጥማዊ ዳንስ ተውኔት በብሔራዊ ቴአትር ዛሬ ሰኔ 14 2016 ዓ.ም ወደ መድረክ እንደሚመለስ ተገልጾ የነበረ ቢሆንም በአንዳንድ ምክንያቶች ላልተወሰነ ጊዜ እንደተራዘመ አዘጋጆቹ ለኤቨንት አዲስ ድረገፅ ገለጸዋል።

ይህ ሙከራዊ ተውኔት ባሳለፍነው ጥቅምት 2 2016 ዓ.ም ነበር ዘወትር አርብ ሲቀረብበት ከነበረው የአንጋፋው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር መድረክ የተሰናበተው። በምትኩም "የሁለት ጌቶች አሽከር" የተሰኘ ተውኔት ሲቀርብም ቆይቷል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
#መሰረት_መብራቴ

እልልታ ሪልስቴት አርቲስት መሰረት መብራቴን የብራንድ አምባሳደር አድርጎ እንደሾመ አስታወቀ

እልልታ ሪልስቴት አርቲስት መሰረት መብራቴን የብራንድ አምባሳደር  በማድረግ እንደሾመ ዛሬ ሰኔ 14 2016 ዓ.ም በመቄዶንያ የአረጋውያን እና የአእምሮ ህሙማን ማዕከል ውስጥ በተካሄደ የፊልማ ሥነሥርዓት አስታውቋል።

በዕለቱም ከብራንድ አምባሳደር ሹመቱ በተጨማሪም በመቄዶንያ የአረጋውያን እና የአእምሮ ህሙማን ማዕከል ጉብኝት እንዲሁም የአረጋውያን ምገባ ተከናውኗል።

የእልልታ ሪል ስቴት ተወካይ አቶ ቢረሳው ምናሉ እልልታ ከተቋቋመበት ዋና ተግባር በተጓዳኝ ማህበራዊ ኃላፊነቱን በመወጣትም በከተማችን ብሎም በሀገር አቀፍ ደረጃ በርካታ የበጎ አድራጎት ስራዎች በመስራትም ይታወቃል ብለዋል።

የድርጅቱ የብራንድ አምባሳደር አድርጎ ከሾማት ከተወዳጇ ሁለገብ አርቲስት መሰረት መብራቴ ጋር የአረጋውያን ጉብኝትና ምገባ እንዲሁም የፊርማ ሥነ ሥርዓት በማድረጉ ከፍተኛ ክብር ይሰማዋል ብለዋል፡፡

የእልልታ ሪልስቴት የብራንድ አምባሳደር አርቲስት መሰረት መብራቴ ከአረጋዊያን ጋር ማዕድ በማጋራቷ እንዲሁም ከእልልታ ሪልስቴት ጋር ለመስራት እድሉን በማግኘቷ የተሰማትን ክብር ገልጻለች።

ቢአኤካ ጠቅላላ ንግድ (BEAEKA GENERAL BUSINESS) እና የጀር ኃ.የተ.የግ.ማ የሆነው እልልታ ሪልስቴት ፣ በሪል ስቴት ልማት፣ በሲሚንቶ ፋብሪካ እና በተለያዩ ፋብሪካዎች፣ በማዕድን፣ በግንባታ ዕቃዎች አምራችነት፣ በግንባታ ማሽነሪዎች እና ቁሳቁሶች አስመጪ እና የግንባታ እቃዎች የጅምላ ንግድ ላይ የተሰማራ ሀገር በቀል ድርጅት ነው።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
የድምፃዊ አብዱ ኪያር አልበም አርብ ይለቀቃል

የድምፃዊ አብዱ ኪያር አዲስ አልበም ቀጣይ ሳምንት ሰኔ 21 2016 ዓ.ም  ለአድማጮች እንደሚደርስ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ከድምጻዊው ይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገፅ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

ድምጻዊ አብዱ ኪያር በማህበራዊ ትስስር ገፁ
"አዲሱ አልበም የዛሬ ሳምንት እናንተ ጋር ይደርሳል"ብሏል።

"ከመርካቶ ሰፈሬ" የመጀመሪያ አልበሙ ጀምሮ በተከታታይ የሰራቸው አልበሞቹ ተወዳጅ የሆኑለት አብዱ ኪያር ይህ አምስተኛ አልበሙ ነው።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
የደራሲ አሌክስ አብርሃም መጻሕፍት ድጋሚ ታተሙ

የደራሲ አሌክስ አብርሃም ዙቤይዳ ፣ዶክተር አሸብር ከዕለታት ግማሽ ቀን እና አልተዘዋወረችም የተሰኙ አራት መጻሕፍት በድጋሚ እንደታተሙ ደራሲው አስታውቋል።

ዙቤይዳ ለ16ኛ  ፣ዶክተር አሸብር ለ15ኛ ፣ከዕለታት ግማሽ ቀን ለ12ኛ ፣አልተዘዋወረችም ለ7ኛ ጊዜ በድጋሚ ታትመው በዚህ ሳምንት በድጋሚ ለገበያ እንደቀረቡ ኤቨንት አዲስ ሰምቷል።

በተጨማሪም በቱባ የመጻሕፍት መተግበሪያ ላይ  "ዙቤይዳ" የተሰኘ መጽሐፉ በድምፅ ተተርኮ በአማራጭ ቀርቧል ተብሏል።

እንዲሁም በመላው ዓለም የግጥም መፅሐፎቹን ጨምሮ ደራሲው ያሳተማቸው 6 መጻሕፍት በአማዞን በኩል በየጊዜው እየታተሙ ነው ።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
ነገ "ማስታወሻ" መጽሐፍ በድጋሚ ለንባብ ይበቃል

በደራሲ ስብሐት ገ/እግዚአብሔር ህይወትና ስራዎች ላይ የሚያተኩረው "ማስታወሻ " መጽሐፍ በድጋሚ ታትሞ ነገ ቅዳሜ ሰኔ 15 2016 ዓ.ም  ለአንባቢያን እንደሚደርስ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ከደራሲ ዘነበ ወላ ሰምቷል።

ደራሲ ዘነበ ወላ "በርካታ ወጣት አንባቢያን በተለያዩ አጋጣሚዎች ስንገናኝ"ማስታወሻ " መጽሐፍን የት ልታገኙት እንደምትችሉ  ትጠይቁኝ ነበር።ይህንን ጥያቄአችሁን ከግምት ውስጥ በማስገባት ጥቂት ኮፒዎች ታትሞአል" ብሏል።

በተጨማሪም "ይህንን ከሁለት አስርት ዓመታት በላይ ያስቆጠረ ሥራዬን አትግታችሁ አሻሽዬ  ለዳግም ህትመት እንዳበቃው ላተጋችሁኝ ወዳጆቼ ሁሉ ምስጋናዬ ይድረሳችሁ። የገሃዱ ዓለም መምህሬ እና ጓደኛዬን ጋሼ ስብሐት ለአብን በአደባባይ እንዳስበው አድርጋችሁኛል። ለነገሩ ስለ እርሱ እንዳወራ ሰበብ ሆናችሁኝ እንጂ እኔ እንኳን ባለፉት 12 ዓመታት አንዲትም ቀን ሳላስበው ውዬ አላውቅም " ሲል ስሜቱን ተናግሯል።

መጽሐፉ "ጃዕፋር መጻሕፍት መደብር ተወልደ ህንጻ ለገሐር  እና ጦብያ መጻሕፍት መደብር መላ ህንጻ ካሳንቺስ" ይገኛል ተብሏል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
በድምጻዊ ኢሳያስ ታምራት ባለቤት የሚመራው የስ የውበት ሙያ ማሰልጠኛ ተቋም ያስልጠናቸውን የመጀመሪያው ዙር ተማሪዎችን አስመረቀ

የድምጻዊት ኢሳያስ ታምራት ባለቤት በሆነችው 
በሜክፕ ባለሞያ እና መምህርት ሲትራ ጀማል የሚመራው የስ የውበት ሙያ ማሰልጠኛ ተቋም በፊልም ኢፌክት፣ በቢዩቲ ሜካፕ ፣ በጥፍር ስራ ፣ በፕሮቶኮል እና በአይላሽ ለአንድ ዓመት ያሰለጠናቸውን የመጀመሪያ ዙር ተማሪዎች ዛሬ አርብ ሰኔ 14 2016 ዓ.ም 22 በሚገኘው ትሪፕል ኢ ሆቴል ውስጥ በድምቀት  አስመርቋል።

በምርቃት ሥነሥርዓቱ ላይ የተገኘው ድምጻዊ ኢሳያስ ታምራት"እዚህ ዝግጅት ላይ መገኘቴ የባለቤትን ስራ ለማበረታታት ነው" ብሏል።

የስ የውበት ማሰልጠኛ በዋናነት "ሴቶችን በተሻለ ሁኔታ ለመደገፍ ዓላማ "ያለው ተብሏል።

የውበት ማሰልጠኛው በዚህኛው ዙር 20 ተማሪዎችን ያስመረቀ ሲሆን በቀጣይ ለሴቶች ትኩረት በመስጠት እንደሚሰራ አስታውቋል።

በዕለቱ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በምርቃት ሥነሥርዓቱ ላይ ተገኝተዋል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
ዛሬ ሁለት ትልልቅ ኮንሰርቶች በአዲስ አበባ ይካሄዳሉ

#ዮቶር_ኮንሰርት

የተወዳጁ የሙዚቃ ግጥምና ዜማ ደራሲውን አለማየሁ ደመቀን የሩብ ክ/ዘመናት የሙዚቃ ጉዞ የሚያወሳ እና እርሱንም የሚዘክር "ዮቶር ድግስ" የተሰኘ የሙዚቃ ኮንሰርት ዛሬ ቅዳሜ ሰኔ 15 2016 ዓ.ም በማሪዮት ሌግዥሪ ሆቴል ይካሄዳል።

በሙዚቃ ባለሙያው የ25 ዓመታት ጉዞ ውስጥ የእርሱን ተወዳጅ እና ዘመን ተሻጋሪ የግጥምና ዜማ ስራዎች ወስደው ከተጫወቱ ድምፃውያን መካከል ጎሳዬ ተስፋዬ ፣ኃይልዬ ታደሰ ፣ አብነት አጎናፍር ፣ግርማ ተፈራ ካሣ ፣ ሐሊማ አብዱራህማን፣ ሔለን በርሔ ፣ ዳዊት ፅጌ ፣ብስራት ሱራፌል ፣ አዲስ ለገሰ፣አንተነት ምናሉ ፣ አበባው ጌታቸው ፣ ዳግማዊ ታምራት ፣መስከረም ኡስማን በኮንሰርቱ ላይ እንደሚሳተፉ የሙዚቃ ስራቸውንም እንደሚያቀርቡ ተገልጿል።

በዕለቱም በ "ዮቶር ድግስ" ከኮንሰርቱ በተጨማሪም በቅርቡ ለአንባቢያን የደረሰው  "ዮቶር ቁጥር 2" መጽሐፍ ይመረቃል ስለመባሉ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ሰምቷል።

የኮንሰርቱ መግቢያ 3000 ብር ሲሆን ትኬቱን በቴሌ ብር ሱፐር አፕ ፣በማርዮት ሆቴል ፣ በአቻሬ ጫማ እንደሚገኝ አዘጋጆቹ አስታውቀዋል።

#Elegance_Concert

ሶስት አንጋፋ ድምጻዊያን የተጣምሩበት ኮንሰርት

ሶስቱ አንጋፋ ድምጻዊያን ዳዊት መለሠ፣ አብርሃም ገብረመድህን እና ጌታቸው ኃ/ማርያም የተጣምሩበት  "Elegance" ኮንሰርት ዛሬ ሰኔ 15 2016 ዓ.ም በሸራተን አዲስ ጋዝ ላይት ውስጥ ከምሽቱ 4:00 ጀምሮ ይካሄዳል ተብሏል።

መግቢያው ቅድሚያ 2000 ብር በር ላይ 3000 ብር ሲሆን የትኬት መሸጫ ቦታ  ሸራተን አዲስ ፣ ይማና ክትፎ እና አምስተርዳም ሬስቶራንት ነው ።

ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
የልጆች የንባብ ፌስቲቫል በሀዋሳ ይካሄዳል

የዘንድሮ  የትምህርት ዘመን መጠናቀቅን ምክንያት በማድረግ በመጪው ሳምንት ቅዳሜ ሰኔ 22 ቀን 2016 ዓ.ም፣ ዓመታዊው የልጆች የንባብ ፌስቲቫል በሀዋሳ ከተማ በጉዱማሌ ፓርክ ይካሄዳል።

የንባብ ፌስቲቫሉን ያዘጋጀው ሰማይ መልቲ ሚዲያ ከሲዳማ ልማት ማህበር ጋር በመተባበር ሲሆን፤ በዚህ ፌስቲቫል ላይ በርካታ የከተማዋ ልጆች ይሳተፋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ የሰማይ መልቲ ሚዲያ መስራችና ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ኢዮብ ፅጌ ለአዲስ አድማስ በላኩት መግለጫ አስታውቀዋል።

በዚህ የንባብ ፌስቲቫል ላይ በርካታ ዝግጅቶች እንደሚቀርቡ የተገለጸ ሲሆን፤ ከነዚህም መካከል የመፅሐፍት አውደርዕይና ባዛር፣ የልጆች አዝናኝ ጨዋታዎችና አስተማሪ መርሃ ግብሮች ይገኙበታል ተብሏል።

የንባብ ፌስቲቫሉ አላማም ጉዱማሌ ፓርክ ለንባብ ክፍት መሆኑን ለማህበረሰቡ ለማሳወቅ ብሎም ልጆች በንባብ እየዳበሩ ካደጉ የተሻለ አገር መፍጠር እንደሚቻል ለማስገንዘብና የእረፍት ጊዜያቸውን በንባብ እንዲያሳልፉ ለማበረታታት ነው ሲሉ አቶ ኢዮብ ጨምረው ገልፀዋል።

ሰማይ መልቲ ሚዲያ በሀዋሳ ከተማና በአካባቢው በትምህርት፣ በሬዲዮ ፕሮግራም ዝግጅት፣ በንባብ ፌስቲቫል፣ በመፅሐፍት አውደርዕይና በሌሎች በርካታ የኹነት ዝግጅት ዘርፎች ተሰማርቶ ታዳጊዎችን፣ ወጣቶችንና አጠቃላይ ማህበረሰቡን በማንቃትና በማስተማር ተግባር ላይ የተሰማራ ድርጅት መሆኑን ለማወቅ ተችሏል።

📍መረጃው የአዲስ አድማስ ጋዜጣ ነው።

ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
ለቴዲ አፍሮ ኮንሰርት ምን ያክል ትኬት ተቆረጠ ?

17 ሺ ተመልካቾችን በሚያስተናግደው የሙዚቃ እና ሌሎች የመዝናኛ ዘርፎች ማቅረቢያ በሆነው የዱባዩ ኮካኮላ አሬና ስታዲየም ድምጻዊ ቴዲ አፍሮ ሰኔ 23 2016 ዓ.ም ዝግጅቱን ያቀርባል።

በዝግጅቱ ላይ 5431 ቲኬቶች ተዘጋጅተዋል። ከዚህ ውስጥ የመጨረሻ ደረጃ ላይ የሚገኘው 3679 ወንበር ተሽጦ ተጠናቋል። እንዲሁም በሌላ ደረጃ ላይ ካለው 651 በአጠቃላይ እስካሁን 4320 ወንበር ተሽጦ ተጠናቋል።

ለቴዲ አፍሮ አሜሪካን ሀገር ስራዎቹን በርከት ባሉ ከተሞች ላይ ካቀረበ ከዓመት በኋላ የመጀመሪያ ኮንሰርቱ ነው ።

ይህንንም ኮንሰርት ከኢትዮጵያ ወደ ዱባይ ለ3 ቀናት የሆቴል ቆይታን ጨምሮ 49, 999 Danex tour and travel ከሙዚቃው ደጋሹ G power ጋር በመተባበር አዘጋጅቷል።

የመግቢያ ዋጋ 149 ዶላር፣ 122 ዶላር ፣ 95 እና 68 ዶላር ናቸው።ዝቅተኛው ባለ 54 ዶላሩ ተሽጦ ተጠናቋል።

📍መረጃው የሁሉ አዲስ የሬድዮ ፕሮግራም ነው።

ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
የጋዜጠኛ መሰለ ገብረህይወት "መሴ ሾው" የተሰኘ የመዝናኛ ዝግጅት የፊታችን ሰኔ 29 ይጀምራል

በዜና አንባቢነት የሚታወቀው  አንጋፋው ጋዜጠኛ መሠለ ገ/ህይወት የሚያዘጋጀው "ሙሴ ሾው"  የተሰኘ የመዝናኛ ዝግጅች በዚህ ወር የፊታችን ሰኔ 29 2016 ዓ.ም በአባይ ቲቪ እንደሚጀምር ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ከጋዜጠኛ መሰለ ገብረህይወት ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

መሴ ሾዉ የተሠኘው የምሽት የመዝናኛ ፕሮግራም (late night show) የሠርጌለታ፣ የሙዚቀኞች ብፌ፣ የእንግዳ ቆይታ እንዲሁም እግሬ ሲደርስ የተሰኙ አዝናኝ መሠናዶዎች የተካተቱበት ነው።

ፕሮግራሙ በየሣምንቱ ቅዳሜ ምሽት በአባይ ቲቪ ከመተላለፉ ባሻገር መሴ ሾው  በሚል ስያሜ በተከፈተ በራሱ የዩቲዩብ ቻናል ለተመልካች ይደርሳል ተብሏል።

መሴ ሾው ዩቲዩብ:
https://www.youtube.com/@Meseshow

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
«የመኸር ለሊት ሕልም» የተሰኘ ተውኔት ዛሬን ጨምሮ ለሁለት ቀናት ሊቀረብ እንደሆነ አዘጋጆቹ አስታውቀዋል

በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተመራቂ የማታ ተማሪዎች የተዘጋጀው «የመኸር ለሊት ሕልም» የተሰኘ ተውኔት ዛሬ ሰኔ 17 2016 ዓ.ም እና ሐሙስ ሰኔ 20 2016 ዓ.ም ለሁለት ቀናት 5 ኪሎ በሚገኘው ፋርማ ግቢ ውስጥ ከምሽቱ 11:30 ጀምሮ ለታዳሚያን ይቀርባል ተብሏል።

"የመኸር ለሊት ህልም" ድርሰት ዋሊያም ሼኪስፒር ፣ትርጉም በላይነህ አቡኔ፣ አዘጋጅ ናፖሊዮን አለሙ።

ተዋናኒያን ተስፋአብ ለገሰ ፣ፍቅር ተስፋዬ ፣አድኖን ነጋሽ ፣ትዝታ ማናዬ እና ሌሎችም ናቸው።

በተጠቀሱት ቀናት ተውኔቱ ላይ ለመታደም ትኬቱን በእነዚህ ስልክ ቁጥሮች ያገኛሉ 0900663787 ፣0912647402።

ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
የ"ጃናሞራ"ፊልም ምርቃት ሰኔ 19 እንደሆነ አዘጋጆቹ አስታወቁ

ኤቨንት አዲስ ድረገፅን ጨምሮ በተለያዩ ማህበራዊ ትስስር ገፆች ዛሬ ሰኔ 17 2016 ዓ.ም እንደሚመረቅ ሲዘገብ የቆየው "ጃናሞራ" ፊልም በአዳራሽ እና ተያያዥ ምክያንቶች የፊታችን ረቡዕ ሰኔ 19 2016 ዓ.ም እንደሚመረቅ የጃናሞራ ፊልም ደራሲና ዳይሬክተር ያለው ደስታ ለኤቨንት አዲስ ድረገፅ ተናግሯል።

ፊልሙም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ስታዲየም አካባቢ በሚገኘው የኦሮሚያ የባህል ማዕከል ውስጥ ይመረቃል ተብሏል።

በኪም ፊልምስ ተዘጋጅቶ በከአብ መልቲሚዲያ የቀረበው የያለው ደስታ (ራስ) "ጃናሞራ" የተሰኘ ፊልም ከሰኔ 21 2016 ዓ.ም ጀምሮ በሁሉም ሲኒማ ቤቶች  ለተመልካች እንደሚቀረብ ኤቨንት አዲስ ድረገጽ የደረሰው መረጃ ያመለክታል።

በዚህ ሀገርኛ ፊልም ማርታ ጎይቶም፣ ነብዩ እንድሪስ ፣ እንግዳሰው ሀብቴ እና ሌሎችም በተዋናይነት ተሳትፈውበታል።

"ጃናሞራ" ፊልምን በተለያዩ የዓለማችን ከተሞችም ለማሳየት እቅድ እንዳላቸው አዘጋጁ ለድረገጻችን ተናግሯል።

ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
አርቲስት አማኑኤል ሀብታሙ ፣ ከያኒ ዳግማዊ አመለወርቅ ፊይሳ ከእስር እንደተፈቱ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ከቤተሰቦቻቸው ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

ባሳለፍነው ሐሙስ ሰኔ 13 2016 ዓ.ም “ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓትን በትጥቅ ትግል ለመቀየር” በመንቀሳቀስ የተጠረጠሩት አርቲስት አማኑኤል ሀብታሙ፣ የቴአትር አዘጋጅ ዳግማዊ ፈይሳ እና ፍላጎት አብርሃምን ጨምሮ 17 ግለሰቦች እያንዳንዳቸው በ50 ሺህ ብር ዋስትና ከእስር እንዲለቀቁ ፍርድ ቤት እንደወሰነ ይታወቃል።

በዚህም መሰረት አርቲስት አማኑኤል ሀብታሙ ፣ ከያኒ ዳግማዊ አመለወርቅ ፊይሳ ፣ ከእስር እንደተፈቱ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ከቤተሰቦቻቸው ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

በዚሁ መዝገብ ተጠርጥረው የቀረቡት ያሬድ ገ/ጻዲቅ (ያያ ዘ ልደታ)ን ጨምሮ ሌሎች ሶስት ግለሰቦች በአንጻሩ 11 ተጨማሪ የምርመራ ቀናት እንደተወሰነባቸው ይታወሳል።

ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
የ"ማያዬ" አልበም ምርቃት ሰኔ 22 ይካሄዳል

የድምጻዊት ለምለም ኃ/ሚካኤል "ማያዬ" የአልበም ምርቃት የፊታችን ቅዳሜ ሰኔ 22 2016 ዓ.ም አመሸሻ ላይ በማሪዮት ኤክስኪዩቲቭ ሆቴል እንደሚካሄድ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ የደረሰው መረጃ ያመለክታል።

በዚህ የአልበም ምርቃት የሙዚቃ ዝግጅት ላይ ከለምለም ኃ/ሚካኤል በተጨማሪም ድምጻዊያኑ ግርማ ተፈራ ካሣ ፣ ግዛቸው ተሾመ ፣ ኤደን አይሸሹም እና ሌሎችም የሙዚቃ ስራዎቻቸውን ያቀርባሉ ተብሏል።

የድምጻዊት ለምለም ኃ/ሚካኤል "ማያዬ" የተሰኘ  የመጀመሪያ አልበም ባሳለፍነው ወር ግንቦት 9 2016 ዓ.ም በናሆም ሪከርድስ የዩቲዩብ ቻናል እና በዓለምአቀፍ የሙዚቃ መተግበሪያዎች በኩል ለአድማጮች እንደደረሰ ይታወሳል።

ለተጨማሪ: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
"ዶሳይስ" የተሰኘ መጽሐፍ ቅዳሜ ይመረቃል 

የደራሲና ገጣሚ ኩሪ አየለ "ዶሳይስ" የተሰኘ የአጫጭር ልቦለዶች ስብስብ መጽሐፍ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት የፊታችን ቅዳሜ ሰኔ 22 2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 3:00 ጀምሮ በአንጋፋው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ውስጥ ይመረቃል።

በምርቃት ሥነሥርዓቱ ላይ ጸሐፊ ተውኔት አያልነህ ሙላቱ ፣ ደራሲ ኃይለመለኮት መዋዕል ፣የሻው ተሰማ ፣ሳሙኤል ተስፋዬ ፣ ሔኖክ በሪሁን እና ሌሎችም ይገኛሉ ተብሏል።

ደራሲና ገጣሚ ኩሪ አየለ ከዚህ ቀደም "ቁርጥራጭ ትንፋሾች" እና "የተሰነቀሩ ጥማቶች" የተሰኙ የግጥም መጻሕፍትን ለአንባቢያን አድርሳለች።

ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
የቡና አውደርዕይ በሐዋሳና ጅማ ከተሞች ሊካሄድ ነው

የቡና ላኪዎችና አቅራቢዎች በቀጥታ ትስስር ሊያገናኝ የሚችል የቡና አውደርዕይ ሊያዘጋጅ መሆኑን የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን አስታወቀ።

የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አዱኛ ደበላ (ዶ/ር) እንደገለጹት፤ የቡና አውደርዕይ በሐዋሳ ከተማ ከሰኔ 21 እስከ 22 ቀን 2016 ዓም እንዲሁም በጅማ ከሰኔ 26 እስከ 27 ቀን 2016 ዓ.ም ይካሄዳል።

አውደርዕዩ በዘርፉ የሚገኘውን ጥቅም ይበልጥ ለማሳደግ ያግዛል ያሉት ዶክተር አዱኛ፤ከኤግዚቢሽኑ ጎን ለጎን የተለያዩ ፓናል ውይይት ይደረጋል ብለዋል።

እስካሁን ከ300 በላይ አቅራቢዎች በአውደርዕዩ ለመሳተፍ ተመዝግበው የምርት ናሙና አቅርበዋል። ከመቶ በላይ ላኪዎችም ለመሳተፍ ፍላጎት ማሳየታቸውን ጠቁመዋል።

📍መረጃው የኢፕድ ነው ።

ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
አራት ደራሲያን የተጋበዙበት"ቆይታ ከደራሲያን ጋር" የተሰኘ የመጻሕፍት ውይይት ቅዳሜ ይካሄዳል።

የኢትዮጵያ ቡክ ፎረም በ’ክለብ ሀውስ’ መተግበሪያ የመጻሕፍት ውይይት አራተኛ ዙር መርሐግብር ከደራሲያን እና ተጋባዥ እንግዶች ጋር የፊታችን ቅዳሜ ሰኔ 22 2016 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 እስከ 11:30 ድረስ ፊትለፊት ውይይት እንደሚካሄድ ኤቨንት ድረገፅ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

በዚህ የውይይት መርሐግብር ላይ "የሦስት ትውልዶች ወግ በመጻሕፍት፣ ንባብና ሌሎች ርዕስ ጉዳዮች "በሚል ርዕስ ከደራሲ አለማየሁ ገላጋይ፣ ከዶ/ር ዳዊት ወንድማገኝ ፣ ከደራሲ ይፍቱስራ ምትኩ እና ከፕ/ር ጴጥሮስ ቶጃ ጋር ከቅዱስ እስጢፋኖስ ቤተክርስትያን ፊትለፊት በሚገኘው ከቤት እስከ ከተማ  የከተማ ማዕከል ውስጥ ይካሄዳል ተብሏል።

ዝግጅቱ ላይ ለመታደም አስቀድሞ መመዝገብ የሚያስፈልግ ሲሆን ለመመዝገብ ሊንኩን ተጠቀሙ https://cutt.ly/KesyFuqf  ተብላችኋል።

ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
"ኦሎምፒክ" የተሰኘ ግዙፍ የሙዚቃ ኮንሰርት በአዲስ አበባ በመስቀል አደባባይ ሊካሄድ ነው

በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ "ኦሎምፒክ" የተሰኘ ግዙፍ ኮንሰርት ሊካሄድ እንደሆነ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ የደረሰው መረጃ ያመለክታል።

ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ከአዘጋጆቹ ሌብል ዋን ኢንተርቴይመንት እንደሰማሁ ከሆነ በዚህ ግዙፍ ኮንሰርት ላይ አንጋፋዎቹ ድምጻዊያን ንዋይ ደበበ ፣ ዳዊት መለሠ፣ ሸዋዳኝ ኃይሉ ፣ታደለ ሮባ  ከወጣቶቹ ድምጻዊያን አንዱዓለም ጎሳ ፣ ሔለን በሪሔ እና ሌሎችም ስራዎቻቸውን ያቀርባሉ ተብሏል።

ሐምሌ 9 2016 ዓ.ም በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ይካሄዳል የተባለው ኮንሰርቱ መግቢያው ከ500 ብር ጀምሮ እንደሆነ ድረገጻችን ከአዘጋጆቹ ሰምቷል።

ለረጅም ጊዜያት ከኃይማኖታዊና መንግስታዊ ዝግጅቶች ውጪ  ያልተካሄደበት መስቀል አደባባይ ይህንን የሙዚቃ ኮንሰርት በቅርቡ ያስተናግዳል ተብሏል።

የ2024 የፓሪስ ኦሎምፒክ በፈረንሳይ አዘጋጅነት ከሐምሌ 19 2016 ዓ.ም ጀምሮ በፓሪስ ከተማ እንደሚካሄድ ይታወሳል።

📍መረጃውን ሲጠቀሙ ምንጭ ይጠቀሱ!

ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1