የ"እሳት ወይ አበባ" ተውኔት ወደ መድረክ የሚመለስበት ጊዜ እንደተራዘመ አዘጋጆቹ አስታወቁ
በሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን ግጥሞች ላይ የተመሰረተው "እሳት ወይ አበባ" ግጥማዊ ዳንስ ተውኔት በብሔራዊ ቴአትር ዛሬ ሰኔ 14 2016 ዓ.ም ወደ መድረክ እንደሚመለስ ተገልጾ የነበረ ቢሆንም በአንዳንድ ምክንያቶች ላልተወሰነ ጊዜ እንደተራዘመ አዘጋጆቹ ለኤቨንት አዲስ ድረገፅ ገለጸዋል።
ይህ ሙከራዊ ተውኔት ባሳለፍነው ጥቅምት 2 2016 ዓ.ም ነበር ዘወትር አርብ ሲቀረብበት ከነበረው የአንጋፋው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር መድረክ የተሰናበተው። በምትኩም "የሁለት ጌቶች አሽከር" የተሰኘ ተውኔት ሲቀርብም ቆይቷል።
ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1

#መሰረት_መብራቴ
እልልታ ሪልስቴት አርቲስት መሰረት መብራቴን የብራንድ አምባሳደር አድርጎ እንደሾመ አስታወቀ
እልልታ ሪልስቴት አርቲስት መሰረት መብራቴን የብራንድ አምባሳደር በማድረግ እንደሾመ ዛሬ ሰኔ 14 2016 ዓ.ም በመቄዶንያ የአረጋውያን እና የአእምሮ ህሙማን ማዕከል ውስጥ በተካሄደ የፊልማ ሥነሥርዓት አስታውቋል።
በዕለቱም ከብራንድ አምባሳደር ሹመቱ በተጨማሪም በመቄዶንያ የአረጋውያን እና የአእምሮ ህሙማን ማዕከል ጉብኝት እንዲሁም የአረጋውያን ምገባ ተከናውኗል።
የእልልታ ሪል ስቴት ተወካይ አቶ ቢረሳው ምናሉ እልልታ ከተቋቋመበት ዋና ተግባር በተጓዳኝ ማህበራዊ ኃላፊነቱን በመወጣትም በከተማችን ብሎም በሀገር አቀፍ ደረጃ በርካታ የበጎ አድራጎት ስራዎች በመስራትም ይታወቃል ብለዋል።
የድርጅቱ የብራንድ አምባሳደር አድርጎ ከሾማት ከተወዳጇ ሁለገብ አርቲስት መሰረት መብራቴ ጋር የአረጋውያን ጉብኝትና ምገባ እንዲሁም የፊርማ ሥነ ሥርዓት በማድረጉ ከፍተኛ ክብር ይሰማዋል ብለዋል፡፡
የእልልታ ሪልስቴት የብራንድ አምባሳደር አርቲስት መሰረት መብራቴ ከአረጋዊያን ጋር ማዕድ በማጋራቷ እንዲሁም ከእልልታ ሪልስቴት ጋር ለመስራት እድሉን በማግኘቷ የተሰማትን ክብር ገልጻለች።
ቢአኤካ ጠቅላላ ንግድ (BEAEKA GENERAL BUSINESS) እና የጀር ኃ.የተ.የግ.ማ የሆነው እልልታ ሪልስቴት ፣ በሪል ስቴት ልማት፣ በሲሚንቶ ፋብሪካ እና በተለያዩ ፋብሪካዎች፣ በማዕድን፣ በግንባታ ዕቃዎች አምራችነት፣ በግንባታ ማሽነሪዎች እና ቁሳቁሶች አስመጪ እና የግንባታ እቃዎች የጅምላ ንግድ ላይ የተሰማራ ሀገር በቀል ድርጅት ነው።

የድምፃዊ አብዱ ኪያር አልበም አርብ ይለቀቃል
የድምፃዊ አብዱ ኪያር አዲስ አልበም ቀጣይ ሳምንት ሰኔ 21 2016 ዓ.ም ለአድማጮች እንደሚደርስ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ከድምጻዊው ይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገፅ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
ድምጻዊ አብዱ ኪያር በማህበራዊ ትስስር ገፁ
"አዲሱ አልበም የዛሬ ሳምንት እናንተ ጋር ይደርሳል"ብሏል።
"ከመርካቶ ሰፈሬ" የመጀመሪያ አልበሙ ጀምሮ በተከታታይ የሰራቸው አልበሞቹ ተወዳጅ የሆኑለት አብዱ ኪያር ይህ አምስተኛ አልበሙ ነው።

የደራሲ አሌክስ አብርሃም መጻሕፍት ድጋሚ ታተሙ
የደራሲ አሌክስ አብርሃም ዙቤይዳ ፣ዶክተር አሸብር ከዕለታት ግማሽ ቀን እና አልተዘዋወረችም የተሰኙ አራት መጻሕፍት በድጋሚ እንደታተሙ ደራሲው አስታውቋል።
ዙቤይዳ ለ16ኛ ፣ዶክተር አሸብር ለ15ኛ ፣ከዕለታት ግማሽ ቀን ለ12ኛ ፣አልተዘዋወረችም ለ7ኛ ጊዜ በድጋሚ ታትመው በዚህ ሳምንት በድጋሚ ለገበያ እንደቀረቡ ኤቨንት አዲስ ሰምቷል።
በተጨማሪም በቱባ የመጻሕፍት መተግበሪያ ላይ "ዙቤይዳ" የተሰኘ መጽሐፉ በድምፅ ተተርኮ በአማራጭ ቀርቧል ተብሏል።
እንዲሁም በመላው ዓለም የግጥም መፅሐፎቹን ጨምሮ ደራሲው ያሳተማቸው 6 መጻሕፍት በአማዞን በኩል በየጊዜው እየታተሙ ነው ።

ነገ "ማስታወሻ" መጽሐፍ በድጋሚ ለንባብ ይበቃል
በደራሲ ስብሐት ገ/እግዚአብሔር ህይወትና ስራዎች ላይ የሚያተኩረው "ማስታወሻ " መጽሐፍ በድጋሚ ታትሞ ነገ ቅዳሜ ሰኔ 15 2016 ዓ.ም ለአንባቢያን እንደሚደርስ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ከደራሲ ዘነበ ወላ ሰምቷል።
ደራሲ ዘነበ ወላ "በርካታ ወጣት አንባቢያን በተለያዩ አጋጣሚዎች ስንገናኝ"ማስታወሻ " መጽሐፍን የት ልታገኙት እንደምትችሉ ትጠይቁኝ ነበር።ይህንን ጥያቄአችሁን ከግምት ውስጥ በማስገባት ጥቂት ኮፒዎች ታትሞአል" ብሏል።
በተጨማሪም "ይህንን ከሁለት አስርት ዓመታት በላይ ያስቆጠረ ሥራዬን አትግታችሁ አሻሽዬ ለዳግም ህትመት እንዳበቃው ላተጋችሁኝ ወዳጆቼ ሁሉ ምስጋናዬ ይድረሳችሁ። የገሃዱ ዓለም መምህሬ እና ጓደኛዬን ጋሼ ስብሐት ለአብን በአደባባይ እንዳስበው አድርጋችሁኛል። ለነገሩ ስለ እርሱ እንዳወራ ሰበብ ሆናችሁኝ እንጂ እኔ እንኳን ባለፉት 12 ዓመታት አንዲትም ቀን ሳላስበው ውዬ አላውቅም " ሲል ስሜቱን ተናግሯል።
መጽሐፉ "ጃዕፋር መጻሕፍት መደብር ተወልደ ህንጻ ለገሐር እና ጦብያ መጻሕፍት መደብር መላ ህንጻ ካሳንቺስ" ይገኛል ተብሏል።

በድምጻዊ ኢሳያስ ታምራት ባለቤት የሚመራው የስ የውበት ሙያ ማሰልጠኛ ተቋም ያስልጠናቸውን የመጀመሪያው ዙር ተማሪዎችን አስመረቀ
የድምጻዊት ኢሳያስ ታምራት ባለቤት በሆነችው
በሜክፕ ባለሞያ እና መምህርት ሲትራ ጀማል የሚመራው የስ የውበት ሙያ ማሰልጠኛ ተቋም በፊልም ኢፌክት፣ በቢዩቲ ሜካፕ ፣ በጥፍር ስራ ፣ በፕሮቶኮል እና በአይላሽ ለአንድ ዓመት ያሰለጠናቸውን የመጀመሪያ ዙር ተማሪዎች ዛሬ አርብ ሰኔ 14 2016 ዓ.ም 22 በሚገኘው ትሪፕል ኢ ሆቴል ውስጥ በድምቀት አስመርቋል።
በምርቃት ሥነሥርዓቱ ላይ የተገኘው ድምጻዊ ኢሳያስ ታምራት"እዚህ ዝግጅት ላይ መገኘቴ የባለቤትን ስራ ለማበረታታት ነው" ብሏል።
የስ የውበት ማሰልጠኛ በዋናነት "ሴቶችን በተሻለ ሁኔታ ለመደገፍ ዓላማ "ያለው ተብሏል።
የውበት ማሰልጠኛው በዚህኛው ዙር 20 ተማሪዎችን ያስመረቀ ሲሆን በቀጣይ ለሴቶች ትኩረት በመስጠት እንደሚሰራ አስታውቋል።
በዕለቱ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በምርቃት ሥነሥርዓቱ ላይ ተገኝተዋል።

ዛሬ ሁለት ትልልቅ ኮንሰርቶች በአዲስ አበባ ይካሄዳሉ
#ዮቶር_ኮንሰርት
የተወዳጁ የሙዚቃ ግጥምና ዜማ ደራሲውን አለማየሁ ደመቀን የሩብ ክ/ዘመናት የሙዚቃ ጉዞ የሚያወሳ እና እርሱንም የሚዘክር "ዮቶር ድግስ" የተሰኘ የሙዚቃ ኮንሰርት ዛሬ ቅዳሜ ሰኔ 15 2016 ዓ.ም በማሪዮት ሌግዥሪ ሆቴል ይካሄዳል።
በሙዚቃ ባለሙያው የ25 ዓመታት ጉዞ ውስጥ የእርሱን ተወዳጅ እና ዘመን ተሻጋሪ የግጥምና ዜማ ስራዎች ወስደው ከተጫወቱ ድምፃውያን መካከል ጎሳዬ ተስፋዬ ፣ኃይልዬ ታደሰ ፣ አብነት አጎናፍር ፣ግርማ ተፈራ ካሣ ፣ ሐሊማ አብዱራህማን፣ ሔለን በርሔ ፣ ዳዊት ፅጌ ፣ብስራት ሱራፌል ፣ አዲስ ለገሰ፣አንተነት ምናሉ ፣ አበባው ጌታቸው ፣ ዳግማዊ ታምራት ፣መስከረም ኡስማን በኮንሰርቱ ላይ እንደሚሳተፉ የሙዚቃ ስራቸውንም እንደሚያቀርቡ ተገልጿል።
በዕለቱም በ "ዮቶር ድግስ" ከኮንሰርቱ በተጨማሪም በቅርቡ ለአንባቢያን የደረሰው "ዮቶር ቁጥር 2" መጽሐፍ ይመረቃል ስለመባሉ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ሰምቷል።
የኮንሰርቱ መግቢያ 3000 ብር ሲሆን ትኬቱን በቴሌ ብር ሱፐር አፕ ፣በማርዮት ሆቴል ፣ በአቻሬ ጫማ እንደሚገኝ አዘጋጆቹ አስታውቀዋል።
#Elegance_Concert
ሶስት አንጋፋ ድምጻዊያን የተጣምሩበት ኮንሰርት
ሶስቱ አንጋፋ ድምጻዊያን ዳዊት መለሠ፣ አብርሃም ገብረመድህን እና ጌታቸው ኃ/ማርያም የተጣምሩበት "Elegance" ኮንሰርት ዛሬ ሰኔ 15 2016 ዓ.ም በሸራተን አዲስ ጋዝ ላይት ውስጥ ከምሽቱ 4:00 ጀምሮ ይካሄዳል ተብሏል።
መግቢያው ቅድሚያ 2000 ብር በር ላይ 3000 ብር ሲሆን የትኬት መሸጫ ቦታ ሸራተን አዲስ ፣ ይማና ክትፎ እና አምስተርዳም ሬስቶራንት ነው ።
ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1

የልጆች የንባብ ፌስቲቫል በሀዋሳ ይካሄዳል
የዘንድሮ የትምህርት ዘመን መጠናቀቅን ምክንያት በማድረግ በመጪው ሳምንት ቅዳሜ ሰኔ 22 ቀን 2016 ዓ.ም፣ ዓመታዊው የልጆች የንባብ ፌስቲቫል በሀዋሳ ከተማ በጉዱማሌ ፓርክ ይካሄዳል።
የንባብ ፌስቲቫሉን ያዘጋጀው ሰማይ መልቲ ሚዲያ ከሲዳማ ልማት ማህበር ጋር በመተባበር ሲሆን፤ በዚህ ፌስቲቫል ላይ በርካታ የከተማዋ ልጆች ይሳተፋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ የሰማይ መልቲ ሚዲያ መስራችና ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ኢዮብ ፅጌ ለአዲስ አድማስ በላኩት መግለጫ አስታውቀዋል።
በዚህ የንባብ ፌስቲቫል ላይ በርካታ ዝግጅቶች እንደሚቀርቡ የተገለጸ ሲሆን፤ ከነዚህም መካከል የመፅሐፍት አውደርዕይና ባዛር፣ የልጆች አዝናኝ ጨዋታዎችና አስተማሪ መርሃ ግብሮች ይገኙበታል ተብሏል።
የንባብ ፌስቲቫሉ አላማም ጉዱማሌ ፓርክ ለንባብ ክፍት መሆኑን ለማህበረሰቡ ለማሳወቅ ብሎም ልጆች በንባብ እየዳበሩ ካደጉ የተሻለ አገር መፍጠር እንደሚቻል ለማስገንዘብና የእረፍት ጊዜያቸውን በንባብ እንዲያሳልፉ ለማበረታታት ነው ሲሉ አቶ ኢዮብ ጨምረው ገልፀዋል።
ሰማይ መልቲ ሚዲያ በሀዋሳ ከተማና በአካባቢው በትምህርት፣ በሬዲዮ ፕሮግራም ዝግጅት፣ በንባብ ፌስቲቫል፣ በመፅሐፍት አውደርዕይና በሌሎች በርካታ የኹነት ዝግጅት ዘርፎች ተሰማርቶ ታዳጊዎችን፣ ወጣቶችንና አጠቃላይ ማህበረሰቡን በማንቃትና በማስተማር ተግባር ላይ የተሰማራ ድርጅት መሆኑን ለማወቅ ተችሏል።
📍መረጃው የአዲስ አድማስ ጋዜጣ ነው።

ለቴዲ አፍሮ ኮንሰርት ምን ያክል ትኬት ተቆረጠ ?
17 ሺ ተመልካቾችን በሚያስተናግደው የሙዚቃ እና ሌሎች የመዝናኛ ዘርፎች ማቅረቢያ በሆነው የዱባዩ ኮካኮላ አሬና ስታዲየም ድምጻዊ ቴዲ አፍሮ ሰኔ 23 2016 ዓ.ም ዝግጅቱን ያቀርባል።
በዝግጅቱ ላይ 5431 ቲኬቶች ተዘጋጅተዋል። ከዚህ ውስጥ የመጨረሻ ደረጃ ላይ የሚገኘው 3679 ወንበር ተሽጦ ተጠናቋል። እንዲሁም በሌላ ደረጃ ላይ ካለው 651 በአጠቃላይ እስካሁን 4320 ወንበር ተሽጦ ተጠናቋል።
ለቴዲ አፍሮ አሜሪካን ሀገር ስራዎቹን በርከት ባሉ ከተሞች ላይ ካቀረበ ከዓመት በኋላ የመጀመሪያ ኮንሰርቱ ነው ።
ይህንንም ኮንሰርት ከኢትዮጵያ ወደ ዱባይ ለ3 ቀናት የሆቴል ቆይታን ጨምሮ 49, 999 Danex tour and travel ከሙዚቃው ደጋሹ G power ጋር በመተባበር አዘጋጅቷል።
የመግቢያ ዋጋ 149 ዶላር፣ 122 ዶላር ፣ 95 እና 68 ዶላር ናቸው።ዝቅተኛው ባለ 54 ዶላሩ ተሽጦ ተጠናቋል።
📍መረጃው የሁሉ አዲስ የሬድዮ ፕሮግራም ነው።

የጋዜጠኛ መሰለ ገብረህይወት "መሴ ሾው" የተሰኘ የመዝናኛ ዝግጅት የፊታችን ሰኔ 29 ይጀምራል
በዜና አንባቢነት የሚታወቀው አንጋፋው ጋዜጠኛ መሠለ ገ/ህይወት የሚያዘጋጀው "ሙሴ ሾው" የተሰኘ የመዝናኛ ዝግጅች በዚህ ወር የፊታችን ሰኔ 29 2016 ዓ.ም በአባይ ቲቪ እንደሚጀምር ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ከጋዜጠኛ መሰለ ገብረህይወት ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
መሴ ሾዉ የተሠኘው የምሽት የመዝናኛ ፕሮግራም (late night show) የሠርጌለታ፣ የሙዚቀኞች ብፌ፣ የእንግዳ ቆይታ እንዲሁም እግሬ ሲደርስ የተሰኙ አዝናኝ መሠናዶዎች የተካተቱበት ነው።
ፕሮግራሙ በየሣምንቱ ቅዳሜ ምሽት በአባይ ቲቪ ከመተላለፉ ባሻገር መሴ ሾው በሚል ስያሜ በተከፈተ በራሱ የዩቲዩብ ቻናል ለተመልካች ይደርሳል ተብሏል።
መሴ ሾው ዩቲዩብ:
https://www.youtube.com/@Meseshow

«የመኸር ለሊት ሕልም» የተሰኘ ተውኔት ዛሬን ጨምሮ ለሁለት ቀናት ሊቀረብ እንደሆነ አዘጋጆቹ አስታውቀዋል
በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተመራቂ የማታ ተማሪዎች የተዘጋጀው «የመኸር ለሊት ሕልም» የተሰኘ ተውኔት ዛሬ ሰኔ 17 2016 ዓ.ም እና ሐሙስ ሰኔ 20 2016 ዓ.ም ለሁለት ቀናት 5 ኪሎ በሚገኘው ፋርማ ግቢ ውስጥ ከምሽቱ 11:30 ጀምሮ ለታዳሚያን ይቀርባል ተብሏል።
"የመኸር ለሊት ህልም" ድርሰት ዋሊያም ሼኪስፒር ፣ትርጉም በላይነህ አቡኔ፣ አዘጋጅ ናፖሊዮን አለሙ።
ተዋናኒያን ተስፋአብ ለገሰ ፣ፍቅር ተስፋዬ ፣አድኖን ነጋሽ ፣ትዝታ ማናዬ እና ሌሎችም ናቸው።
በተጠቀሱት ቀናት ተውኔቱ ላይ ለመታደም ትኬቱን በእነዚህ ስልክ ቁጥሮች ያገኛሉ 0900663787 ፣0912647402።

የ"ጃናሞራ"ፊልም ምርቃት ሰኔ 19 እንደሆነ አዘጋጆቹ አስታወቁ
ኤቨንት አዲስ ድረገፅን ጨምሮ በተለያዩ ማህበራዊ ትስስር ገፆች ዛሬ ሰኔ 17 2016 ዓ.ም እንደሚመረቅ ሲዘገብ የቆየው "ጃናሞራ" ፊልም በአዳራሽ እና ተያያዥ ምክያንቶች የፊታችን ረቡዕ ሰኔ 19 2016 ዓ.ም እንደሚመረቅ የጃናሞራ ፊልም ደራሲና ዳይሬክተር ያለው ደስታ ለኤቨንት አዲስ ድረገፅ ተናግሯል።
ፊልሙም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ስታዲየም አካባቢ በሚገኘው የኦሮሚያ የባህል ማዕከል ውስጥ ይመረቃል ተብሏል።
በኪም ፊልምስ ተዘጋጅቶ በከአብ መልቲሚዲያ የቀረበው የያለው ደስታ (ራስ) "ጃናሞራ" የተሰኘ ፊልም ከሰኔ 21 2016 ዓ.ም ጀምሮ በሁሉም ሲኒማ ቤቶች ለተመልካች እንደሚቀረብ ኤቨንት አዲስ ድረገጽ የደረሰው መረጃ ያመለክታል።
በዚህ ሀገርኛ ፊልም ማርታ ጎይቶም፣ ነብዩ እንድሪስ ፣ እንግዳሰው ሀብቴ እና ሌሎችም በተዋናይነት ተሳትፈውበታል።
"ጃናሞራ" ፊልምን በተለያዩ የዓለማችን ከተሞችም ለማሳየት እቅድ እንዳላቸው አዘጋጁ ለድረገጻችን ተናግሯል።

አርቲስት አማኑኤል ሀብታሙ ፣ ከያኒ ዳግማዊ አመለወርቅ ፊይሳ ከእስር እንደተፈቱ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ከቤተሰቦቻቸው ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
ባሳለፍነው ሐሙስ ሰኔ 13 2016 ዓ.ም “ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓትን በትጥቅ ትግል ለመቀየር” በመንቀሳቀስ የተጠረጠሩት አርቲስት አማኑኤል ሀብታሙ፣ የቴአትር አዘጋጅ ዳግማዊ ፈይሳ እና ፍላጎት አብርሃምን ጨምሮ 17 ግለሰቦች እያንዳንዳቸው በ50 ሺህ ብር ዋስትና ከእስር እንዲለቀቁ ፍርድ ቤት እንደወሰነ ይታወቃል።
በዚህም መሰረት አርቲስት አማኑኤል ሀብታሙ ፣ ከያኒ ዳግማዊ አመለወርቅ ፊይሳ ፣ ከእስር እንደተፈቱ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ከቤተሰቦቻቸው ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
በዚሁ መዝገብ ተጠርጥረው የቀረቡት ያሬድ ገ/ጻዲቅ (ያያ ዘ ልደታ)ን ጨምሮ ሌሎች ሶስት ግለሰቦች በአንጻሩ 11 ተጨማሪ የምርመራ ቀናት እንደተወሰነባቸው ይታወሳል።

የ"ማያዬ" አልበም ምርቃት ሰኔ 22 ይካሄዳል
የድምጻዊት ለምለም ኃ/ሚካኤል "ማያዬ" የአልበም ምርቃት የፊታችን ቅዳሜ ሰኔ 22 2016 ዓ.ም አመሸሻ ላይ በማሪዮት ኤክስኪዩቲቭ ሆቴል እንደሚካሄድ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ የደረሰው መረጃ ያመለክታል።
በዚህ የአልበም ምርቃት የሙዚቃ ዝግጅት ላይ ከለምለም ኃ/ሚካኤል በተጨማሪም ድምጻዊያኑ ግርማ ተፈራ ካሣ ፣ ግዛቸው ተሾመ ፣ ኤደን አይሸሹም እና ሌሎችም የሙዚቃ ስራዎቻቸውን ያቀርባሉ ተብሏል።
የድምጻዊት ለምለም ኃ/ሚካኤል "ማያዬ" የተሰኘ የመጀመሪያ አልበም ባሳለፍነው ወር ግንቦት 9 2016 ዓ.ም በናሆም ሪከርድስ የዩቲዩብ ቻናል እና በዓለምአቀፍ የሙዚቃ መተግበሪያዎች በኩል ለአድማጮች እንደደረሰ ይታወሳል።
ለተጨማሪ: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1

"ዶሳይስ" የተሰኘ መጽሐፍ ቅዳሜ ይመረቃል
የደራሲና ገጣሚ ኩሪ አየለ "ዶሳይስ" የተሰኘ የአጫጭር ልቦለዶች ስብስብ መጽሐፍ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት የፊታችን ቅዳሜ ሰኔ 22 2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 3:00 ጀምሮ በአንጋፋው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ውስጥ ይመረቃል።
በምርቃት ሥነሥርዓቱ ላይ ጸሐፊ ተውኔት አያልነህ ሙላቱ ፣ ደራሲ ኃይለመለኮት መዋዕል ፣የሻው ተሰማ ፣ሳሙኤል ተስፋዬ ፣ ሔኖክ በሪሁን እና ሌሎችም ይገኛሉ ተብሏል።
ደራሲና ገጣሚ ኩሪ አየለ ከዚህ ቀደም "ቁርጥራጭ ትንፋሾች" እና "የተሰነቀሩ ጥማቶች" የተሰኙ የግጥም መጻሕፍትን ለአንባቢያን አድርሳለች።
ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
የደራሲና ገጣሚ ኩሪ አየለ "ዶሳይስ" የተሰኘ የአጫጭር ልቦለዶች ስብስብ መጽሐፍ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት የፊታችን ቅዳሜ ሰኔ 22 2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 3:00 ጀምሮ በአንጋፋው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ውስጥ ይመረቃል።
በምርቃት ሥነሥርዓቱ ላይ ጸሐፊ ተውኔት አያልነህ ሙላቱ ፣ ደራሲ ኃይለመለኮት መዋዕል ፣የሻው ተሰማ ፣ሳሙኤል ተስፋዬ ፣ ሔኖክ በሪሁን እና ሌሎችም ይገኛሉ ተብሏል።
ደራሲና ገጣሚ ኩሪ አየለ ከዚህ ቀደም "ቁርጥራጭ ትንፋሾች" እና "የተሰነቀሩ ጥማቶች" የተሰኙ የግጥም መጻሕፍትን ለአንባቢያን አድርሳለች።
ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
የቡና አውደርዕይ በሐዋሳና ጅማ ከተሞች ሊካሄድ ነው
የቡና ላኪዎችና አቅራቢዎች በቀጥታ ትስስር ሊያገናኝ የሚችል የቡና አውደርዕይ ሊያዘጋጅ መሆኑን የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን አስታወቀ።
የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አዱኛ ደበላ (ዶ/ር) እንደገለጹት፤ የቡና አውደርዕይ በሐዋሳ ከተማ ከሰኔ 21 እስከ 22 ቀን 2016 ዓም እንዲሁም በጅማ ከሰኔ 26 እስከ 27 ቀን 2016 ዓ.ም ይካሄዳል።
አውደርዕዩ በዘርፉ የሚገኘውን ጥቅም ይበልጥ ለማሳደግ ያግዛል ያሉት ዶክተር አዱኛ፤ከኤግዚቢሽኑ ጎን ለጎን የተለያዩ ፓናል ውይይት ይደረጋል ብለዋል።
እስካሁን ከ300 በላይ አቅራቢዎች በአውደርዕዩ ለመሳተፍ ተመዝግበው የምርት ናሙና አቅርበዋል። ከመቶ በላይ ላኪዎችም ለመሳተፍ ፍላጎት ማሳየታቸውን ጠቁመዋል።
📍መረጃው የኢፕድ ነው ።

አራት ደራሲያን የተጋበዙበት"ቆይታ ከደራሲያን ጋር" የተሰኘ የመጻሕፍት ውይይት ቅዳሜ ይካሄዳል።
የኢትዮጵያ ቡክ ፎረም በ’ክለብ ሀውስ’ መተግበሪያ የመጻሕፍት ውይይት አራተኛ ዙር መርሐግብር ከደራሲያን እና ተጋባዥ እንግዶች ጋር የፊታችን ቅዳሜ ሰኔ 22 2016 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 እስከ 11:30 ድረስ ፊትለፊት ውይይት እንደሚካሄድ ኤቨንት ድረገፅ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
በዚህ የውይይት መርሐግብር ላይ "የሦስት ትውልዶች ወግ በመጻሕፍት፣ ንባብና ሌሎች ርዕስ ጉዳዮች "በሚል ርዕስ ከደራሲ አለማየሁ ገላጋይ፣ ከዶ/ር ዳዊት ወንድማገኝ ፣ ከደራሲ ይፍቱስራ ምትኩ እና ከፕ/ር ጴጥሮስ ቶጃ ጋር ከቅዱስ እስጢፋኖስ ቤተክርስትያን ፊትለፊት በሚገኘው ከቤት እስከ ከተማ የከተማ ማዕከል ውስጥ ይካሄዳል ተብሏል።
ዝግጅቱ ላይ ለመታደም አስቀድሞ መመዝገብ የሚያስፈልግ ሲሆን ለመመዝገብ ሊንኩን ተጠቀሙ https://cutt.ly/KesyFuqf ተብላችኋል።

"ኦሎምፒክ" የተሰኘ ግዙፍ የሙዚቃ ኮንሰርት በአዲስ አበባ በመስቀል አደባባይ ሊካሄድ ነው
በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ "ኦሎምፒክ" የተሰኘ ግዙፍ ኮንሰርት ሊካሄድ እንደሆነ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ የደረሰው መረጃ ያመለክታል።
ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ከአዘጋጆቹ ሌብል ዋን ኢንተርቴይመንት እንደሰማሁ ከሆነ በዚህ ግዙፍ ኮንሰርት ላይ አንጋፋዎቹ ድምጻዊያን ንዋይ ደበበ ፣ ዳዊት መለሠ፣ ሸዋዳኝ ኃይሉ ፣ታደለ ሮባ ከወጣቶቹ ድምጻዊያን አንዱዓለም ጎሳ ፣ ሔለን በሪሔ እና ሌሎችም ስራዎቻቸውን ያቀርባሉ ተብሏል።
ሐምሌ 9 2016 ዓ.ም በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ይካሄዳል የተባለው ኮንሰርቱ መግቢያው ከ500 ብር ጀምሮ እንደሆነ ድረገጻችን ከአዘጋጆቹ ሰምቷል።
ለረጅም ጊዜያት ከኃይማኖታዊና መንግስታዊ ዝግጅቶች ውጪ ያልተካሄደበት መስቀል አደባባይ ይህንን የሙዚቃ ኮንሰርት በቅርቡ ያስተናግዳል ተብሏል።
የ2024 የፓሪስ ኦሎምፒክ በፈረንሳይ አዘጋጅነት ከሐምሌ 19 2016 ዓ.ም ጀምሮ በፓሪስ ከተማ እንደሚካሄድ ይታወሳል።
📍መረጃውን ሲጠቀሙ ምንጭ ይጠቀሱ!

"ሚዲያ አዋርድ" የተሰኘ ሽልማት ሊካሄድ ነው
በኢትዮጵያ ሚዲያዎች ላይ በቴሌቪዥን፣ በሬዲዮ እና በጋዜጦች ላይ የሚሰሩ የሚዲያ ባለሞያዎችን የሚሸልመዉ "ሚዲያ አዋርድ" በወርሐ ነሐሴ ይካሄዳል ተብሏል።
የአዋርዱ አዘጋጆች ከባለፈዉ ዓመት ሰኔ ወር ጀምሮ የተላለፉ ፕሮግራሞች እና ለሰባት ወራት በስራ ላይ የነበሩ የሚዲያ ባለሞያዎች ብቻ በእጩነት እንደቀረቡ ያነሱ ሲሆን በአዋርዱ ላይ የቀረቡት ሁሉም እጩዎች መስፈርቶችን ያሟሉት ብቻ ናቸዉ ተብሏል።
አሸናፊዎች በዳኞች እና በህዝብ ድምፅ የሚመረጡ ሲሆን ህዝቡ በመጀመሪያ ዙር በኦንላይ ethio-mediaaward.com በመግባት ድምፅ መስጠት ይችላልም ብለዋል።
አንጋፋዋ ጋዜጠኛ መዓዛ ብሩ የመጀመሪያው ‘የሚዲያ አዋርድ’ የህይወት ዘመን ተሸላሚ እንደሆነች አዘጋጆቹ አስታውቀዋል።
የመጀመሪያዉ የሽልማት ፕሮግራም ዘርፎች
1.የዓመቱ ምርጥ የቴሌቪዥን ወንድ ዜና አንባቢ
2. የዓመቱ ምርጥ የቴሌቪዥን ሴት ዜና አንባቢ
3.የዓመቱ ምርጥ የሬዲዮ ሴት ዜና አንባቢ
4. የዓመቱ ምርጥ የሬዲዮ ወንድ ዜና አንባቢ
5.የዓመቱ ምርጥ የስፖርት ፕሮግራም
6.የዓመቱ የህዝብ ምርጫ/ምርጥ ጋዜጠኛ
7.የዓመቱ ምርጥ አይደል ሾዉ
8.የዓመቱ ምርጥ ዶክመንተሪ
9.የዓመቱ ምርጥ የዜና ዘገባ
10.የዓመቱ ምርጥ አርቲክል/ፕሪንት ሚዲያ
11.የዓመቱ ምርጥ ዲጄ
12.የዓመቱ ምርጥ የቴሌቪዥን ጣቢያ
13.የዓመቱ ምርጥ የሬዲዮ ጣቢያ
14.የዓመቱ ምርጥ ጋዜጣ
15.የዓመቱ ምርጥ የቴሌቪዥን የመዝናኛ ፕሮግራም
16.የዓመቱ ምርጥ የሬዲዮ የመዝናኛ ፕሮግራም
17.የዓመቱ ምርጥ የቴሌቪዥን የመዝናኛ ፕሮግራም ወንድ አቅራቢ
18.የዓመቱ ምርጥ የቴሌቪዥን የመዝናኛ ፕሮግራም ሴት አቅራቢ

ጋዜጠኛ ዮሴፍ ኃይሌ አረፈ
የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ባልደረባ የነበረው ጋዜጠኛ ዮሴፍ ኃይሌ ባደረበት ህመም በህክምና ሲረዳ ቆይቶ በዛሬው ዕለት በተወለደ 44 ዓመቱ አርፏል፡፡
ጋዜጠኛ ዮሴፍ ኃይሌ በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን መዝናኛ ቻናል ከሪፖርተር እስከ ረዳት ኤዲተርነት ላለፉት 15 ዓመታት አገልግሏል፡፡
የተለያዩ የመዝናኛ ዝግጅቶችን በማዘጋጀት በርካታ ዓመታትን ያገለገለው ዮሴፍ ኃይሌ፤ በተለይም የብዙዎች ትዝታ የሆነውን እንደ “ታላቅ ፊልም” ያሉ ስራዎችን ለስርጭት እንዲስማሙ አድርጎ በማቅረብ ይታወቃል፡፡
📍መረጃው የኢቢሲ መዝናኛ ቻናል ነው።

የገጣሚና ደራሲ ኤፍሬም ስዩም "ምልኪና ቡና " የተሰኘ አዲስ የግጥም መድብል ገበያ ላይ ውሏል።
“ሶሊያና” በተሰኘው የግጥም መድብሉ ዕውቅናን ያገኘው ደራሲው ዘጠነኛ መፅሐፉን ለንባብ አብቅቷል።
በግጥም መድብሉ ላይ የተካተቱት ግጥምች በ2012 እና ከዛም ቀደም ብለው የተፃፉ ሲሆኑ መፅሐፉ በ216 ገፆች የተቀነበበ ነው።
ደራሲው ከኤፍ ኤም አዲስ 97.1 የመሰንበቻ መሰናዶ ጋር በነበረው ቆይታ ለስድስት ዓመታት መፅሐፍ ከማሳተም ርቆ የቆየ መሆኑን ገልፆል::
አሁን ግን ወደ አራት ስራዎች እጁ ላይ እንዳሉ ተናግሮ "ምልኪና ቡና" የተሰኘው ስራው ከአራቱ አንዱ ሲሆን በቀጣይ ሌሎቹም ለንባብ እንደሚበቁ አሳውቋል።
በግጥም መድብሉ ላይ በርካታ ሃሳቦች እንደተነሱት የሚገልጸው ኤፍሬም የተዋጡ ሃሳቦችን በግጥም መልክ ማውጣት ተችሏል ብሏል።
ደራሲው አያይዞም የግጥም ስራዎቹን በድምፅ በማስቀረፅ ለአንባቢያን እንደሚያቀርብም አስታውቋል።
📍መረጃው የኤፍ ኤም አዲስ 97.1 ነው።