Event Addis Media
Photo
የሐሙስ መረጃዎች
የሳምንቱ ኪናዊ መረጃዎች ቀጥሎው ይቀርባሉ!
📍መረጃውን ሲጠቀሙ ምንጭ ይጠቀሱ!
1.የድምጻዊ ቴዎድሮስ ካሣሁን(ቴዲ አፍሮ) የሙዚቃ ኮንሰርት የፊታችን እሁድ ሰኔ 23 2016 ዓ.ም 17 ሺ ተመልካቾችን በሚያስተናግደው የሙዚቃ እና ሌሎች የመዝናኛ ዘርፎች ማቅረቢያ በሆነው በዱባዩ ኮካኮላ አሬና ስታዲየም ውስጥ ይካሄዳል። ድምጻዊው ለዚህ የሙዚቃ ዝግጅቱ ከቀናት በፊት ዱባይ መግባቱ ይታወሳል።
2. የድምጻዊ አብዱ ኪያር "ፓፓፓ" የተሰኘ አልበም ነገ ሰኔ 21 2016 ዓ.ም በራሱ ዩቲዩብ ቻናል እና በዓለምአቀፍ የሙዚቃ መተግበሪያዎች ላይ ይለቀቃል። በአልበሙ ላይ በቅንብር ስማገኘሁ ሳሙኤል፣ ኪሩቤል ተስፋዬ፣ ካሙዙ ካሳ እና ዳዊት ቦስኮ ተሳትፈዋል። ሚክሲንጉን የሰሩት ስማገኘሁ ሳሙኤል እና ኪሩቤል ተስፋዬ ሲሆኑ ማስተሪንግ ደግሞ በአበጋዝ ክብረወርቅ ተሰርቷል።
3.የድምጻዊት ለምለም ኃ/ሚካኤል "ማያዬ" የአልበም ምርቃት የፊታችን ቅዳሜ ሰኔ 22 2016 ዓ.ም አመሸሻ ላይ በማሪዮት ኤክስኪዩቲቭ ሆቴል እንደሚካሄድ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ የደረሰው መረጃ ያመለክታል።
በዚህ የአልበም ምርቃት የሙዚቃ ዝግጅት ላይ ከለምለም ኃ/ሚካኤል በተጨማሪም ድምጻዊያኑ ግርማ ተፈራ ካሣ ፣ ግዛቸው ተሾመ ፣ ኤደን አይሸሹም እና ሌሎችም የሙዚቃ ስራዎቻቸውን ያቀርባሉ ተብሏል።
4.በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ "ኦሎምፒክ" የተሰኘ ግዙፍ ኮንሰርት የፊታችን ሐምሌ 9 2016 ዓ.ም ሊካሄድ እንደሆነ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ የደረሰው መረጃ ያመለክታል።ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ከአዘጋጆቹ ሌብል ዋን ኢንተርቴይመንት እንደሰማሁ ከሆነ በዚህ ግዙፍ ኮንሰርት ላይ አንጋፋዎቹ ድምጻዊያን ንዋይ ደበበ፣ዳዊት መለሠ፣ ሸዋንዳኝ ኃይሉ፣ታደለ ሮባ ከወጣቶቹ ድምጻዊያን አንዱዓለም ጎሳ፣ሔለን በሪሔ እና ሌሎችም ስራዎቻቸውን ያቀርባሉ ተብሏል።
5.የድምጻዊ ማስተዋል እያዩ "እመጣለሁ " የተሰኘ የሙዚቃ ቪዲዮ በቅርቡ ለተመልካቾች ይደርሳል። የሙዚቃ ቪዲዮው ዳይሬክተር ነፃዓለም አብዲ ሲሆን የሙዚቃው ግጥምና ዜማ በአቡዲ ተሰርቷል።የሙዚቃ ቅንብሩ ደግሞ በሚካኤል ኃይሉ ተከውኗል።
6.የኢትዮጵያ ቡክ ፎረም በ’ክለብ ሀውስ’ መተግበሪያ የመጻሕፍት ውይይት አራተኛ ዙር መርሐግብር ከደራሲያን እና ተጋባዥ እንግዶች ጋር የፊታችን ቅዳሜ ሰኔ 22 2016 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 እስከ 11:30 ድረስ በአካል ውይይት ይካሄዳል።በዚህ የውይይት መርሐግብር ላይ "የሦስት ትውልዶች ወግ በመጻሕፍት፣ ንባብና ሌሎች ርዕስ ጉዳዮች"በሚል ርዕስ ከደራሲ አለማየሁ ገላጋይ፣ ከዶ/ር ዳዊት ወንድማገኝ፣ ከደራሲ ይፍቱስራ ምትኩ እና ከፕ/ር ጴጥሮስ ቶጃ ጋር ከእስጢፋኖስ ቤተክርስትያን ፊትለፊት በሚገኘው ከቤት እስከ ከተማ የከተማ ማዕከል ውስጥ ይካሄዳል ተብሏል።
7.በዛጎል መጻሕፍት ባንክ የሚዘጋጀው "ነገረ መጻሕፍት" የመጽሐፍ ውይይት የፊታችን ቅዳሜ በኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ይካሄዳል። በዚህ ሳምንት ከዶ/ር ስንታየሁ ካሣ እና ከደራሲ በሁሉም አለበል ጋር "ታሪክ የምትስመክርልን ካሣ ገብረማርያም " እና "የተዳፈነዉ ታሪክ: ራስ ጉግሳ ወሌ" በተሰኙ መጻሕፍት ላይ ውይይት ይካሄዳል።የዕለቱ አወያይ ደራሲ እንዳለጌታ ከበደ ነው። ይህ መርሐግብር ቅዳሜ ሰኔ 22 2016 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 እስከ 10:30 ይካሄዳል።
8.የደራሲና ገጣሚ ኩሪ አየለ "ዶሳይስ" የተሰኘ የአጫጭር ልቦለዶች ስብስብ መጽሐፍ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት የፊታችን ቅዳሜ ሰኔ 22 2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 3:00 ጀምሮ በአንጋፋው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ውስጥ ይመረቃል።በምርቃት ሥነሥርዓቱ ላይ ጸሐፊ ተውኔት አያልነህ ሙላቱ ፣ ደራሲ ኃይለመለኮት መዋዕል ፣መምህር የሻው ተሰማ ፣ አርቲስት ሳሙኤል ተስፋዬ ፣ አርቲስት ሔኖክ በሪሁን እና ሌሎችም ይገኛሉ ተብሏል።
9.የደራሲ ዓላማውም ታዬ " communication coach" የተሰኘ መጽሐፍ የፊታችን ቅዳሜ ሰኔ 22 2016 ዓ.ም ከቀኑ 7:00 ጀምሮ በልደታ ክ/ከተማ አዳራሽ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ይመረቃል። መጽሐፉ በ100 ገፆች የተቀነበበ ሲሆን ከተመረቀ በኃላ በጃፋር መጻሕፍት መደብር እና በሌሎችም አማራጮች ለአንባቢያን ይደርሳል ተብሏል።
10.በሠዓሊ ዳዊት ገረሱ "አሁን " በተሰኘው የሥዕል አውደርዕይ ላይ ነገ አርብ ሰኔ 21 2016 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ጀምሮ ስድሰት ኪሎ በሚገኘው በገብረክርስቶስ ደስታ ዘመናዊ ሙዚየም ውስጥ ውይይት ይካሄዳል። በዕለቱም መምህር በቀለ መኮንን፣ሐሌታ ይረጋ ፣ ነፃነት ገብረሚካኤል ሀሳቦቻቸውን ያቀርባሉ ተብሏል።
አዘጋጅ: ናቲ ማናዬ
ቀን: ሰኔ 20 2016 ዓ.ም
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
በድረገጻችን በተሻለ አቀራረብ ያንብቡ:
https://eventaddis.com
ቴሌግራም: @EventAddis1

«የመኸር ለሊት ሕልም» የተሰኘ ተውኔት ዛሬ ይቀርባል
በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተመራቂ የማታ ተማሪዎች የተዘጋጀው «የመኸር ለሊት ሕልም» የተሰኘ ተውኔት ዛሬ ሰኔ 20 2016 ዓ.ም 5 ኪሎ በሚገኘው ፋርማ ግቢ ውስጥ ከምሽቱ 11:30 ጀምሮ ለታዳሚያን ይቀርባል ተብሏል።
"የመኸር ለሊት ህልም" ድርሰት ዋሊያም ሼኪስፒር ፣ትርጉም በላይነህ አቡኔ፣ አዘጋጅ ናፖሊዮን አለሙ።
ተዋናኒያን ተስፋአብ ለገሰ ፣ፍቅር ተስፋዬ ፣አድኖን ነጋሽ ፣ትዝታ ማናዬ እና ሌሎችም ናቸው።
በዝግጅቱ ላይ ጥሪ የተደረገላቸው የክብር እንግዶች ይገኛሉ ተብሏል።
ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1

አርቲስት ትዕግሥት ግርማ የኢትዮጵያ ኦሮቶዶክስ ተዋሕዶ ሕክምና ማህበር የበጎ ፍቃድ አምባሳደር ሆና ተሾመች
አለምአቀፋዊ ማህበር የሆነው የኢትዮጵያ ኦሮቶዶክስ ተዋሕዶ ሕክምና ማህበር አርቲስት ትዕግሥት ግርማን የበጎ ፍቃድ አምባሳደር አድርጎ እንደሾመ ዛሬ ሰኔ 20 2016 ዓ.ም በቤስት ዌስተርን ፕላስ ሆቴል በተካሄደ የፊርማ ሥነሥርዓት ወቅት ገልጿል።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሕክምና ማህበር ምስረታውን ካደረገበት ጊዜ እንስቶ ዘር፣ ቀለም ሀይማኖትም ሆነ ማንነት ያልገደበው ሰብዓዊ ድጋፍ እና አገልግሎትን በኢትዮጵያ የተለያዩ አከባቢዎች እየተዘዋወር በመስጠት ላይ የሚገኝ ማህበር ነው ተብሏል።
ማህበሩ አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች 35 የሚሆኑ የህክምና ጉዞዎችን በማድረግ ሰብዓዊነትን ባስቀደመ ተግባሩ ከ25 ሺህ በላይ ዜጎችን ተጠቃሚ ያደረገ ሲሆን ከ150 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ሰብዓዊ ግልጋሎት ሰጥቷል።
በቀጣይም ማህበሩ አቅም ለሌላቸው ዜጎችን ታሳቢ ያደረገ እና የሕክምና አገልግሎት ባልተዳረሰባቸው አካባቢዎች ሙያዊ ፍቅር እና አክብሮት የታነጸ የሕክምና አገልግሎት ለመስጠት፤ የህክምና አገልግሎት ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመቅረፍ የሚያስችሉ የድጋፍ ስራዎችን በአቅም ግንባታ እና በግብዓት ማሟላት ያተኮረ ስራን ለመስራት አቅዷል፡፡
በእዚህ መነሻነትም ማህበሩ ከእዚህ ቀደም ከሰራቸው የሰብዓዊነት ስራዎች በተጨማሪ በእዚህ ወቅት እያከናወናቸው የሚገኙ ተግባራትን እና ወደፊት ሊከውን ያቀዳቸውን ውጥኖቹን መነሻ በማድረግ ተወዳጇን ተዋናይት እና የቴሌቪዥን ፕሮግራም አቅራቢ አርቲስት ትዕግስት ግርማን የበጎ አድራጎት አምባሳደር አድርጎ ሾሟል።

የበዓሉ ግርማ "ቤርሙዳ" ቴአትር ዛሬ አይቀርብም
በውድነህ ክፍሌ ተደርሶ በተሻለ አሰፍ የተዘጋጀውና በቅርቡ ወደ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር መድረክ የመጣው "በዓሉ ግርማ ቤርሙዳ" ቴአትር ዛሬ ሐሙስ ሰኔ 20 2016 ዓ.ም "በአንድ ተዋናይ መቅረት" ምክንያት እንደማይቀርብ የተውኔቱ አዘጋጅ ውድነህ ክፍሌ አስታውቋል።
የተውኔቱ አዘጋጅ ውድነህ ክፍሌ ተውኔቱ ስለማይቀርብበት ምክንያት በማህበራዊ ትስስር ገፁ የሚከተለውን ብሏል።
"ሰሞኑን በ'በዓሉ ግርማ -ቤርሙዳ' ቴአትር እየገጠመን ያለውም ይኸው ነው።ባለፈው ሳምንት ማለትም ሰኔ 13 ተዋናይት ሳምራዊት ገ/ስላሴ የድምጽ መዘጋት ገጥሟት ነበር። ቴአትሩ አይታይም ከተባለ በኋላ በተአምር ለተመልካች ቀረበ "
"በእዚህኛው ሳምንት ደግሞ ተዋናይ ሰለሞን ሀጎስ ከምሽቱ 1፡30 ላይ እንዲህ የሚል መልዕክት ላከልን"በድንገተኛ የስራ ጥሪ ምክንያት ለጥናት በመግባቴ የነገው የመድረክ ተውኔት አይኖረንም ። አመሰግናለሁ" የሚል። እንግዲህ የሀገር ፍቅር ቴአትር ሱሉሉታ ወደሚገኘው ልህቀት ስፍራ ለጥናት ልኮት ነው። 'መውጣት ስለማይቻል አይገኝም' የሚል መልእክት የደረሰን። "
"የትኛውም ተዋናይ ችግር ሊገጥመው ይችላል። ቀድሞ መፍትሄ መፈለግ ግን ከባለሙያው ይጠበቃል።"
"ለማንኛውም በዛሬው ዕለት አንደኛ አመታችንን እናከብራለን ብላችሁ ለጠበቃችሁት የ"በዓሉ ግርማ ቤርሙዳ" ቴአትር አባላት ያው በቴክኒክ ምክንያት ኬካችን ለሌላ ጊዜ ተሸጋግሯል" ብሏል።

ዛሬ ሲኒማ ግቡ ፣ ፊልም ተመልከቱ !
እነዚህ አራት የፊልም ማሳያዎች(ሲኒማ ቤቶች) ዛሬን ጨምሮ በሳምንቱ መጨረሻ ቀናት እነዚህን ፊልሞች ለተመልካቾች ያቀርባሉ: ምስሎቹን ይመልከቱ።
የሲኒማ ቤቶቹ አድራሻ:
📍ሲኤምሲ ሚካኤል አካባቢ : ጋስት ሲኒማ
📍ለም ሆቴል አካባቢ: ቫምዳስ ሲኒማ
📍ጉርድ ሾላ አካባቢ : ሴንቸሪ ሲኒማ
📍ቦሌ አካባቢ : ዓለም ሲኒማ
መልካም የእረፍት ቀናት !
https://news.1rj.ru/str/EventAddis1

"አሁን" የተሰኘ የሥነጥበብ ውይይት ዛሬ ይካሄዳል
በሠዓሊ ዳዊት ገረሱ "አሁን " በተሰኘው የሥዕል አውደርዕይ ላይ ዛሬ አርብ ሰኔ 21 2016 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ጀምሮ ስድሰት ኪሎ በሚገኘው በገብረክርስቶስ ደስታ ዘመናዊ ሙዚየም ውስጥ ውይይት ይካሄዳል። በዕለቱም መምህር በቀለ መኮንን፣ሐሌታ ይረጋ ፣ ነፃነት ገብረሚካኤል ሀሳቦቻቸውን ያቀርባሉ ተብሏል።
ይህ የሠዓሊ ዳዊት ገረሡ "አሁን" የተሰኘ የሥዕል አውድርዕይ ከግንቦት 23 እስከ ሰኔ 14 2016 ዓ.ም በእይታ ላይ ቆይቷል።
ሠዓሊ ዳዊት ገረሱ የመጀመሪያ ዲግሪውን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የሥነጥበባትና ዲዛይን ት/ቤት በ1993 ዓ.ም አግኝቷል። በርካታ የሥዕል አውደርዕዮችን በግልና በቡድን በተለያዩ ጋለሪዎች አሳይቷል::
ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1

የማስታወቂያ ምልክቶች ላይ ውይይት ተካሄደ
የአዲስ አበባ ከተማ ባህል፣ ኪነጥበብና ቱሪዝም ቢሮ ከዕይታዊ ጥበባት እና ከኪነ-ህንጻ ውበት አኳያ በከተማዋ እየተስተዋሉ ያሉ የማስታወቂያና የምልክት/ሳይንኤጅ/ አጠቃቀም ችግርን ለመቅረፍ ከዲዛይንና ግንባታ ፈቃድ ቢሮ፣ ከዘርፉ ምሁራንና ባለሙያዎች ጋር በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በአለ የሥዕልና ዲዛይን ትምህርት ቤት ውይይት ተካሂዷል።
በውይይቱ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የአለ የሥዕልና ዲዛይን ትምህርት ቤት ዳይሬክተር አቶ አገኘሁ አዳነና የዲዛይን ትምህርት ክፍል ኃላፊ አቶ ኦስማን ሃሰን መነሻ ሃሳብ ቀርቧል፡፡
እንደ አቶ አገኘሁ አዳነ የትኛውም የማስታወቂያ ቀለም ውህደት እና የአንድ ትርጉም አመላካች ጉዳይና ይዘት በሳይንሳዊ፣ በቀለማትና በተፈጥሮ ስሪት መልክ መሆን እንደሚገባ አመላክተዋል፡፡
አክለውም በከተሞች ላይ የሚታዩ የሳይንኤጅ አጠቃቀም ችግሮች የማስታወቂያ አጠቃቀም መመሪያ አለመኖር ዋነኛ ችግር መሆኑን አመላክተዋል፡፡
📍መረጃው የአ/አ/ባ/ኪ/ቱ/ቢ ነው።

የአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ አዲስ ቻናልና የ"አዲስ ታለንት ሾው"ውድድር ማስጀመር መርሐግብር ዛሬ ይካሄዳል
አዲስ ሚዲያ ኔትወርክ አዲሱን የቋንቋዎች ቻናል (AMN PLUS) እንዲሁም “አዲስ ታለንት ሾው” የተሰኘ የኪነ-ጥበብ ውድድር ማስጀመሪያ መርሀግብር በዛሬው ዕለት ይካሄዳል ተብሏል።
በዛሬው ዕለት በይፋ የሚጀምረው አዲሱ ቻናል (AMN PLUS) ተጨማሪ ቋንቋዎች ለተመልካች ተደራሽ የሚሆኑበት ነው።
በተጨማሪም ዛሬ በሚጀመረው በ"አዲስ ታለንት ሾው" በድራማዎች፣ ዳንስ፣ አጭር ፊልምና የህፃናት ታለንት ሾው ልዩ ተሰጥኦ ያላቸው የአዲስ አበባ ተወዳዳሪዎች እንደሚሳተፉ ተገልጿል።
ተወዳዳሪዎቹ በሰፈራቸው ስም ተወክለው በክፍለ ከተሞች መካከል ውድድር እንደሚደረግ ተጠቁሟል።
በተጨማሪም ከእያንዳንዱ ክፍለ ከተማ 20 ተወዳዳሪዎች ይካተቱበታል ተብሏል።
አዲስ ታለንት ሾው የድሮ ሙዚቃና ድራማን በአዲስ መልክ ለውድድሩ እንደሚጠቀምም ተነግሯል።
በዓድዋ ድል መታሰቢያ በሚካሄደው ዝግጅት ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች፣ የተቋሙ አመራሮች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ይገኛሉ።
"የትውልድ ድምጽ" የሚል መሪ ቃል ያለው አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ በአዲስ ቴሌቪዥን በሰባት ቋንቋዎች መረጃዎችን ለተመልካች እንደሚያቀርብ ይታወቃል።

📍የቅዳሜ የሥነጽሑፍ ውይይቶች
1.የኢትዮጵያ ቡክ ፎረም በ’ክለብ ሀውስ’ መተግበሪያ የመጻሕፍት ውይይት አራተኛ ዙር መርሐግብር ከደራሲያን እና ተጋባዥ እንግዶች ጋር ዛሬ ቅዳሜ ሰኔ 22 2016 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 እስከ 11:30 ድረስ በአካል ውይይት ያካሂዳል።በዚህ የውይይት መርሐግብር ላይ "የሦስት ትውልዶች ወግ በመጻሕፍት፣ ንባብና ሌሎች ርዕስ ጉዳዮች"በሚል ርዕስ ከደራሲ አለማየሁ ገላጋይ፣ ከዶ/ር ዳዊት ወንድማገኝ፣ ከደራሲ ይፍቱስራ ምትኩ እና ከፕ/ር ጴጥሮስ ቶጃ ጋር ከእስጢፋኖስ ቤተክርስትያን ፊትለፊት በሚገኘው ከቤት እስከ ከተማ የከተማ ማዕከል ውስጥ ይካሄዳል ተብሏል።
2.በዛጎል መጻሕፍት ባንክ የሚዘጋጀው "ነገረ መጻሕፍት" የመጽሐፍ ውይይት ዛሬ ቅዳሜ በኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ይካሄዳል። በዚህ ሳምንት ከዶ/ር ስንታየሁ ካሣ እና ከደራሲ በሁሉም አለበል ጋር "ታሪክ የምትመሰክርልን ካሣ ገብረማርያም " እና "የተዳፈነዉ ታሪክ: ራስ ጉግሳ ወሌ" በተሰኙ መጻሕፍት ላይ ውይይት ይካሄዳል።የዕለቱ አወያይ ደራሲ እንዳለጌታ ከበደ ነው። ይህ መርሐግብር ዛሬ ቅዳሜ ሰኔ 22 2016 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 እስከ 10:30 ይካሄዳል።

📍ቴአትርን በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ቤት
አንጋፋው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ዛሬ ቅዳሜ እና ነገ እሁድ እነዚህን ተውኔቶች ለታዳሚያን ያቀርባል።
ባሎች እና ሚስቶች
ድርሰት: ውዱ አለን
አዘጋጅ: ሳሙኤል ተስፋዬ
ቀን: ቅዳሜ
ሰዓት: 8:00
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር
ባቡሩ
ድርሰት: አርኖልድ ሪድሊ
አዘጋጅ:ራሔል ተሾመ መሐመድ
ቀን: ቅዳሜ
ሰዓት:11:30
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር
ሸምጋይ
ድርሰት:ታደለ አያሌው
አዘጋጅ: ሳሙኤል ተስፋዬ
ቀን: እሁድ
ሰዓት: 8:00
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር
እምዩ ብረቷ
ድርሰት: ቤልቶልት ብሬሽት
አዘጋጅ: ማንያዘዋል እንዳሻው
ቀን: እሁድ
ሰዓት:11:30
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር
መልካም የእረፍት ቀን !

የቴዲ አፍሮ ኮንሰርት እንዴት ነበር ?
የድምጻዊ ቴዲ አፍሮ ኮንሰርት ትላንት እሁድ ሰኔ 23 2016 ዓ.ም በዱባይ ኮላኮላ አሬና ውስጥ ተካሄዷል።
በኮንሰርቱ ላይ ከታደመው ከጋዜጠኛ አቤል ገብረኪዳን ስለነበረው ዝግጅት ኤቨንት አዲስ ድረገፅ አጭር መረጀ ደርሶታል።
እንደሚከተለው ይቀርባል"ኮንሰርቱ ከመግቢያው ስንጀምር የኮካኮላ አሬና ድንቅ ነው፡፡ትክክለኛ የኮንሰርት ስፍራ ነው፡፡ለታዳሚ ይመቻል፣ለአቅራቢዎቹም እጀ ሰባራ የማያደርግ ምርጥ ቦታ ነው፡፡ግዝፈቱ ስቴድየምን የሚመስለው አሬና ውስጡም በጣም ቆንጆ ነው፡፡ለዝግጅቱ የተመደበው አብዛኛው ቦታም ሙሉ ነበር፡፡ ጸጥታ አስከባሪዎች ወደ አዳራሽ መጠጥ እንዳይገባ ማድረጋቸውም ትክክለኛ ውሳኔ ሆኖ ታይቶኛል፡፡"
"ድምጻዊ #ቴዲ አፍሮ በዱባይ አቆጣጠር 3 ሰዓት ካለፈ ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ "አፍሪካ" በሚለው ሙዚቃ ተጀምሮ "ጥቁር ሰው" በሚለው ሙዚቃ እስኪጠናቀቅ ድረስ ከአስር የሚበልጥ ሙዚቃዎችን የተጫወተ ሲሆን አንዳንዶቹ ሙዚቃዎች በተለይ ታዳሚውን አሳብደው አሬናውን መነቅነቅ የቻሉ ነበሩ"።
"ባንዱ ገራሚ ነው፡፡በሚጫወቱት መሳሪያ ማስተር ያረጉ ሙዚቀኞች የተሰባሰቡበት ነው ማለት ይቻላል፡፡ጊታሩ፣ሳክሱ፣ማሲንቆው እና ሌሎቹ ለየብቻ በሙዚቃው መሃል የተጫወቷቸው ዜማዎች ለብቻ ሊከፈልባቸው ሁሉ የሚገባ ናቸው፡፡በጣም ድንቅ ነበሩ፡፡በእረፍት ሰአት የተጫወቱትም ኢትዮጵያውያን ዲጄዎች የኮንሰርቱ ቫይብ እንደደመቀ እንዲቀጥል ማድረግ ችለዋል"።
"በጥቅሉ ቴዲም በጥሩ አቋም ታዳሚውን እንደያዘ ያጠናቀቀ ሲሆን ህዝቡም በኮንሰርት እንደተለመደው ሳይጉላላ አብሮ ዘፍኖ እና ጨፍሮ ወጥቷል፡፡ነቅለው ለኮንሰርት የወጡት የዱባይ ነዋሪ ኢትዮጵያውያን ኮንሰርቱን ትክክለኛ ኮንሰርት አስመስለውታል፡፡"

"ሔሎ ኢትዮጵያ " የሬድዮ ዝግጅት እየመራ ነው
ሰኔ 18 2016 ዓ.ም በተጀመረው እና የሚድያ ተቋማትን፣ ጋዜጠኞችን እና አቅራቢዎችን ፣ፕሮግራሞችን ዕውቅና በሚሠጠው የሚድያ አዋርድ ላይ ሔሎ ኢትዮጵያ ከኤፍ ኤም አዲስ 97.1 763 ድምጽ በማግኘት አብረው የቀረቡትን ከልዩ ልዩ የሬድዮ ጣቢያ የተውጣጡ ፕሮግራሞች በድምጽ በልጦ ተገኝቷል።
ከሔሎ ኢትዮጵያ በመቀጠል በሰይፉ ፋንታሁን የሚዘጋጀው ታዲያስ አዲስ 2ኛ የፋና ኤፍ ኤሙ ማረፊያ የ 3ኛ ደረጃን ይዘዋል።
ይህ ውጤት ይህ መረጃ እስከ ተጠናከረበት ያለውን ነጥብ የሚገልጽ ሲሆን የድምጽ አሰጣጡም እስከ ሀምሌ 1 2016 የሚቀጥል ይሆናል።
"ሔሎ ኢትዮጵያ" ዳጉ ኮምኒኬሽን ፒኤል ሲ ከኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ጋር በመተባባር በአንጋፋው ኤፍ ኤም አዲስ 97.1 ሬድዮ የሚቀርብ ተወዳጅ የሬድዮ ፕሮግራም ነው።
"ሔሎ ኢትዮጵያ" ዘወትር ረቡዕ ከረፋዱ 4:00 እስከ 6:00 ለሁለት ሰዓታት በአንጋፋው ኤፍ ኤም አዲስ 97.1 ላይ ይደመጣል።
"ውብ ህዝብ ፤ ውብ ሀገር ፤ ኢትዮጵያ" መሪ ቃሉ ነው።
የ"ሔሎ ኢትዮጵያ" ተወዳጅ የሬድዮ ፕሮግራም ይዘቶች የሚከተሉት ናቸው፦
1. የሔሎ ኢትዮጵያ ማስታወሻ
በሔሎ ኢትዮጵያ ማስታወሻ ለሀገር ፣ለወገን ታላቅ ሥራ የሰሩ ኢትዮጵያዊያንን እናስታውሳለን። እንዘክራለን።
2. የሔሎ ኢትዮጵያ ኢቨንቶች
በሔሎ ኢትዮጵያ ኤቨንቶች የተመራረጡ ልዩ ልዩ የኤቨንት መረጃዎችን ለአድማጮች እናቀርባለን።
3. የሔሎ ኢትዮጵያ ሰሞነኛ ጉዳይ
በሔሎ ኢትዮጵያ ሰሞነኛ ጉዳዮች አነጋጋሪ እና አወያይ ሰሞነኛ ጉዳዮች ይቀርቡበታል።
3. የሔሎ ኢትዮጵያ ዓለምአቀፍ ጉዳዮች
በሔሎ ኢትዮጵያ ዓለምአቀፍ ጉዳዮች አዝናኝ ፣ አስገራሚ እና ሰሞነኛ ዓለምአቀፍ ጉዳዮች ይቀርቡበታል።
4. የሔሎ ኢትዮጵያ ጉብኝት
በሔሎ ኢትዮጵያ ጉብኝት አድማጮች በቀጥታ ስልክ መስመር ላይ በመገኘት አካባቢያቸውን በምናብ ያስጎበኛሉ።
5. የሔሎ ኢትዮጵያ የጠፋ ሰው
በሔሎ ኢትዮጵያ "የጠፋ ሰው" ልዩ ፕሮግራማችን በተለያዩ ምክንያቶች የተጠፋፉ ሰዎችን እናፋልጋለን። ወዴት ናችሁ እንላለን።የጠፉ ሰዎችን አብረን እንፈልጋለን።
6.የሔሎ ኢትዮጵያ ምርጥ ሙዚቃዎች
በሔሎ ኢትዮጵያ ምርጥ ሙዚቃዎች በየሳምንቱ የተመረጡ ርዕሶችን የያዙትን ምርጥ ሙዚቃዎች ይጋበዙበታል።
የፕሮግራሙ አዘጋጆች ማናዬ እውነቱ ፣ ናትናኤል ደበና (ናቲ ማናዬ) እና ሶዮሜ ጌታቸው ናቸው።
"ሔሎ ኢትዮጵያ" ከዚህ ቀደም በኢቢሲ ሬድዮ 104.7 በእንግሊዝኛ ቋንቋ በአዲስ አበባ ተቀማጭነታቸውን ላደርጉ የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ አባላት የሚመጥን ተደማጭ እና ተወዳጅ መሰናዶዎች በፈርጅ በፈረጁ ሲያቀርብ ቆይቷል። ሔሎ ኢትዮጵያን ይምረጡ።
https://ethio-mediaaward.com/%e1%8b%a8%e1%8b%93%e1%88%98%e1%89%b1-%e1%88%9d%e1%88%ad%e1%8c%a5-%e1%8b%a8%e1%88%ac%e1%8b%b2%e1%8b%ae-%e1%8d%95%e1%88%ae%e1%8c%8d%e1%88%ab%e1%88%9d/?fbclid=IwZXh0bgNhZW0CMTEAAR1zYeZTKqkSZWrpS4b_88imi4EO8EKg_7PV4jcUkAAMP__du07Tlhr4sO4_aem_c3AvVNjhsHI_Q0M1hl3Pfg
Credit: ተወዳጅ ሚዲያ

ሰላም አታላይ በአርትስ ቴሌቪዥን "ሎሚ ብወረውር" የተሰኘ ዝግጅት ማቅረብ ልትጀምር ነው ።
የሥነልቦና ባለሞያዋ ሰላም አታላይ "ሎሚ ብወረውር" የተሰኘ የቴሌቪዥን ዝግጅት በቅርቡ በአርትስ ቴሌቪዥን ማዘጋጀት እንደምትጀምር በማህበራዊ ትስስር ገጿ አስታውቃለች።
ሁሉገቧ የሥነልቦና እና የሚዲያ ባለሞያ ሰላም አታላይ በቡና ፖድካስት እና በአዋሽ ኤፍ ኤም 90.7 ሬድዮ "አዋሽ ስፔሻል" በተሰኘ የሬድዮ ፕሮግራም ላይ በምታቀርባቸው የሥነልቦና ጉዳዮች መሰናዶዋ እናውቃታለን።
በተጨማሪም በቴሌግራም ፣ በቲክቶክ አማራጮች በህይወት እና ሥነልቦናዊ ጉዳዮች ላይ በርካታ ቁምነገሮችን አጋርታለች።
ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
የሥነልቦና ባለሞያዋ ሰላም አታላይ "ሎሚ ብወረውር" የተሰኘ የቴሌቪዥን ዝግጅት በቅርቡ በአርትስ ቴሌቪዥን ማዘጋጀት እንደምትጀምር በማህበራዊ ትስስር ገጿ አስታውቃለች።
ሁሉገቧ የሥነልቦና እና የሚዲያ ባለሞያ ሰላም አታላይ በቡና ፖድካስት እና በአዋሽ ኤፍ ኤም 90.7 ሬድዮ "አዋሽ ስፔሻል" በተሰኘ የሬድዮ ፕሮግራም ላይ በምታቀርባቸው የሥነልቦና ጉዳዮች መሰናዶዋ እናውቃታለን።
በተጨማሪም በቴሌግራም ፣ በቲክቶክ አማራጮች በህይወት እና ሥነልቦናዊ ጉዳዮች ላይ በርካታ ቁምነገሮችን አጋርታለች።
ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
አብርሆት አገልግሎት እየሰጠ አይደለም
አራት ኪሎ የሚገኘው አብርሆት የህዝብ ቤተመጻሕፍት ለአንባቢያን አግልግሎት እየሰጠ እንዳይደለ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ተመልክቷል።
በቤተመጻሕፍቱ ውስጥ ለተማሪዎች "ኦላይን" ፈተና እየተሰጠ በመሆኑ ምክንያት ለሚቀጥሉት ቀናትም ለአንባቢያን ዝግ ሆኖ እንደሚቆይ ተነግሯል።

የዲጂታል ጥበብ አውደርዕይ በፈንድቃ
በግራፊክስ ዲዛይነር ፋኑኤል ልዑል የተዘጋጁ የዲጂታል ጥበብ ስራዎች የሚቀርቡበት "የተሰወረውን መሻት" የተሰኘ የዲጂታል ጥበብ አውደርዕይ ዛሬ ሰኔ 24 2016 ዓ.ም ከምሽቱ 12:00 ጀምሮ ካዛንቺስ በሚገኘው ፈንድቃ የባህል ማዕከል ውስጥ ይከፈታል።
ይህ የዲጂታል ጥበብ አውደርዕይ እስከ ሐምሌ 8 2016 ዓ.ም ድረስ በእይታ ላይ ይቆያል ተብሏል።
የግራፊክስ ዲዛይነሩ ፋኑኤል ልዑል ከዓመታት በፊት ለአድማጮች የደረሰው የሮፍናን ኑሪ"ስድስት" አልበም ሽፋን(ከቨር) ዲዛይኑን መስራቱ ይታወሳል።

ዛሬ ዓለምአቀፍ የስፖርት ጋዜጠኞች ቀን ነው
የዓለም ስፖርት ጋዜጠኞች ቀን ሐምሌ 2 ቀን የስፖርት ጋዜጠኞች ስፖርትን ለማስተዋወቅ የሚያገለግሉትን አገልግሎት ለማክበር በሚል በዓለምአቀፍ ደረጃ ተከብሮ ይውላል።
ይህ ቀን በ1924ቱ የፓሪስ ኦሊምፒክ የዓለም አቀፍ ስፖርት ፕሬስ ማህበር የተመሰረተበት ቀን በመሆኑ በይፋ "የዓለምአቀፍ የስፖርት ጋዜጠኞች ቀን" ተብሎ ተወስኗል።
በህትመት (ጋዜጣና መጽሔት ) ፣በሬድዮና ቴሌቪዥን፣በዲጂታል የሚዲያ አማራጮች ከልባችሁ የምትሰሩ ውድ ኢትዮጵያዊያን የስፖርት ጋዜጠኞች እንኳን አደረሳችሁ እንላለን።

"ጥቁር አደይ" ፊልም ሊመረቅ ነው
በደራሲ እና ዳይሬክተር ፍፁም ካሣሁን የተሰራው "ጥቁር አደይ" ፊልም የፊታችን ሐምሌ 10 2016 ዓ.ም በሸራተን አዲስ ሆቴል ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ይመረቃል ተብሏል።
በፊልሙ ላይ ኤደን አይሸሹም፤ ካሣሁን ፍስሐ ማንዴላ፤ ናታን ጌታቸው፤ ነቢዩ እንድሪስ ጨምሮ ከ186 በላይ ተዋናያን እንደተሳተፉበት አዘጋጆቹ ለኤቨንት አዲስ ድረገፅ ተናግረዋል።
"ጥቁር አደይ" ፊልም አንድ ሰዓት ከሐምሳ ደቂቃ ረዝመት ያለው ሲሆን ከ6.7 ሚሊየን ብር በላይ ውጪ እንደወጣበት ተነግሯል።