📍ቴአትርን በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ቤት
አንጋፋው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ዛሬ ቅዳሜ እና ነገ እሁድ እነዚህን ተውኔቶች ለታዳሚያን ያቀርባል።
ባሎች እና ሚስቶች
ድርሰት: ውዱ አለን
አዘጋጅ: ሳሙኤል ተስፋዬ
ቀን: ቅዳሜ
ሰዓት: 8:00
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር
ባቡሩ
ድርሰት: አርኖልድ ሪድሊ
አዘጋጅ:ራሔል ተሾመ መሐመድ
ቀን: ቅዳሜ
ሰዓት:11:30
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር
ሸምጋይ
ድርሰት:ታደለ አያሌው
አዘጋጅ: ሳሙኤል ተስፋዬ
ቀን: እሁድ
ሰዓት: 8:00
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር
እምዩ ብረቷ
ድርሰት: ቤልቶልት ብሬሽት
አዘጋጅ: ማንያዘዋል እንዳሻው
ቀን: እሁድ
ሰዓት:11:30
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር
መልካም የእረፍት ቀን !
ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1

የቴዲ አፍሮ ኮንሰርት እንዴት ነበር ?
የድምጻዊ ቴዲ አፍሮ ኮንሰርት ትላንት እሁድ ሰኔ 23 2016 ዓ.ም በዱባይ ኮላኮላ አሬና ውስጥ ተካሄዷል።
በኮንሰርቱ ላይ ከታደመው ከጋዜጠኛ አቤል ገብረኪዳን ስለነበረው ዝግጅት ኤቨንት አዲስ ድረገፅ አጭር መረጀ ደርሶታል።
እንደሚከተለው ይቀርባል"ኮንሰርቱ ከመግቢያው ስንጀምር የኮካኮላ አሬና ድንቅ ነው፡፡ትክክለኛ የኮንሰርት ስፍራ ነው፡፡ለታዳሚ ይመቻል፣ለአቅራቢዎቹም እጀ ሰባራ የማያደርግ ምርጥ ቦታ ነው፡፡ግዝፈቱ ስቴድየምን የሚመስለው አሬና ውስጡም በጣም ቆንጆ ነው፡፡ለዝግጅቱ የተመደበው አብዛኛው ቦታም ሙሉ ነበር፡፡ ጸጥታ አስከባሪዎች ወደ አዳራሽ መጠጥ እንዳይገባ ማድረጋቸውም ትክክለኛ ውሳኔ ሆኖ ታይቶኛል፡፡"
"ድምጻዊ #ቴዲ አፍሮ በዱባይ አቆጣጠር 3 ሰዓት ካለፈ ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ "አፍሪካ" በሚለው ሙዚቃ ተጀምሮ "ጥቁር ሰው" በሚለው ሙዚቃ እስኪጠናቀቅ ድረስ ከአስር የሚበልጥ ሙዚቃዎችን የተጫወተ ሲሆን አንዳንዶቹ ሙዚቃዎች በተለይ ታዳሚውን አሳብደው አሬናውን መነቅነቅ የቻሉ ነበሩ"።
"ባንዱ ገራሚ ነው፡፡በሚጫወቱት መሳሪያ ማስተር ያረጉ ሙዚቀኞች የተሰባሰቡበት ነው ማለት ይቻላል፡፡ጊታሩ፣ሳክሱ፣ማሲንቆው እና ሌሎቹ ለየብቻ በሙዚቃው መሃል የተጫወቷቸው ዜማዎች ለብቻ ሊከፈልባቸው ሁሉ የሚገባ ናቸው፡፡በጣም ድንቅ ነበሩ፡፡በእረፍት ሰአት የተጫወቱትም ኢትዮጵያውያን ዲጄዎች የኮንሰርቱ ቫይብ እንደደመቀ እንዲቀጥል ማድረግ ችለዋል"።
"በጥቅሉ ቴዲም በጥሩ አቋም ታዳሚውን እንደያዘ ያጠናቀቀ ሲሆን ህዝቡም በኮንሰርት እንደተለመደው ሳይጉላላ አብሮ ዘፍኖ እና ጨፍሮ ወጥቷል፡፡ነቅለው ለኮንሰርት የወጡት የዱባይ ነዋሪ ኢትዮጵያውያን ኮንሰርቱን ትክክለኛ ኮንሰርት አስመስለውታል፡፡"

Event Addis Media
Photo
"ሔሎ ኢትዮጵያ " የሬድዮ ዝግጅት እየመራ ነው
ሰኔ 18 2016 ዓ.ም በተጀመረው እና የሚድያ ተቋማትን፣ ጋዜጠኞችን እና አቅራቢዎችን ፣ፕሮግራሞችን ዕውቅና በሚሠጠው የሚድያ አዋርድ ላይ ሔሎ ኢትዮጵያ ከኤፍ ኤም አዲስ 97.1 763 ድምጽ በማግኘት አብረው የቀረቡትን ከልዩ ልዩ የሬድዮ ጣቢያ የተውጣጡ ፕሮግራሞች በድምጽ በልጦ ተገኝቷል።
ከሔሎ ኢትዮጵያ በመቀጠል በሰይፉ ፋንታሁን የሚዘጋጀው ታዲያስ አዲስ 2ኛ የፋና ኤፍ ኤሙ ማረፊያ የ 3ኛ ደረጃን ይዘዋል።
ይህ ውጤት ይህ መረጃ እስከ ተጠናከረበት ያለውን ነጥብ የሚገልጽ ሲሆን የድምጽ አሰጣጡም እስከ ሀምሌ 1 2016 የሚቀጥል ይሆናል።
"ሔሎ ኢትዮጵያ" ዳጉ ኮምኒኬሽን ፒኤል ሲ ከኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ጋር በመተባባር በአንጋፋው ኤፍ ኤም አዲስ 97.1 ሬድዮ የሚቀርብ ተወዳጅ የሬድዮ ፕሮግራም ነው።
"ሔሎ ኢትዮጵያ" ዘወትር ረቡዕ ከረፋዱ 4:00 እስከ 6:00 ለሁለት ሰዓታት በአንጋፋው ኤፍ ኤም አዲስ 97.1 ላይ ይደመጣል።
"ውብ ህዝብ ፤ ውብ ሀገር ፤ ኢትዮጵያ" መሪ ቃሉ ነው።
የ"ሔሎ ኢትዮጵያ" ተወዳጅ የሬድዮ ፕሮግራም ይዘቶች የሚከተሉት ናቸው፦
1. የሔሎ ኢትዮጵያ ማስታወሻ
በሔሎ ኢትዮጵያ ማስታወሻ ለሀገር ፣ለወገን ታላቅ ሥራ የሰሩ ኢትዮጵያዊያንን እናስታውሳለን። እንዘክራለን።
2. የሔሎ ኢትዮጵያ ኢቨንቶች
በሔሎ ኢትዮጵያ ኤቨንቶች የተመራረጡ ልዩ ልዩ የኤቨንት መረጃዎችን ለአድማጮች እናቀርባለን።
3. የሔሎ ኢትዮጵያ ሰሞነኛ ጉዳይ
በሔሎ ኢትዮጵያ ሰሞነኛ ጉዳዮች አነጋጋሪ እና አወያይ ሰሞነኛ ጉዳዮች ይቀርቡበታል።
3. የሔሎ ኢትዮጵያ ዓለምአቀፍ ጉዳዮች
በሔሎ ኢትዮጵያ ዓለምአቀፍ ጉዳዮች አዝናኝ ፣ አስገራሚ እና ሰሞነኛ ዓለምአቀፍ ጉዳዮች ይቀርቡበታል።
4. የሔሎ ኢትዮጵያ ጉብኝት
በሔሎ ኢትዮጵያ ጉብኝት አድማጮች በቀጥታ ስልክ መስመር ላይ በመገኘት አካባቢያቸውን በምናብ ያስጎበኛሉ።
5. የሔሎ ኢትዮጵያ የጠፋ ሰው
በሔሎ ኢትዮጵያ "የጠፋ ሰው" ልዩ ፕሮግራማችን በተለያዩ ምክንያቶች የተጠፋፉ ሰዎችን እናፋልጋለን። ወዴት ናችሁ እንላለን።የጠፉ ሰዎችን አብረን እንፈልጋለን።
6.የሔሎ ኢትዮጵያ ምርጥ ሙዚቃዎች
በሔሎ ኢትዮጵያ ምርጥ ሙዚቃዎች በየሳምንቱ የተመረጡ ርዕሶችን የያዙትን ምርጥ ሙዚቃዎች ይጋበዙበታል።
የፕሮግራሙ አዘጋጆች ማናዬ እውነቱ ፣ ናትናኤል ደበና (ናቲ ማናዬ) እና ሶዮሜ ጌታቸው ናቸው።
"ሔሎ ኢትዮጵያ" ከዚህ ቀደም በኢቢሲ ሬድዮ 104.7 በእንግሊዝኛ ቋንቋ በአዲስ አበባ ተቀማጭነታቸውን ላደርጉ የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ አባላት የሚመጥን ተደማጭ እና ተወዳጅ መሰናዶዎች በፈርጅ በፈረጁ ሲያቀርብ ቆይቷል። ሔሎ ኢትዮጵያን ይምረጡ።
https://ethio-mediaaward.com/%e1%8b%a8%e1%8b%93%e1%88%98%e1%89%b1-%e1%88%9d%e1%88%ad%e1%8c%a5-%e1%8b%a8%e1%88%ac%e1%8b%b2%e1%8b%ae-%e1%8d%95%e1%88%ae%e1%8c%8d%e1%88%ab%e1%88%9d/?fbclid=IwZXh0bgNhZW0CMTEAAR1zYeZTKqkSZWrpS4b_88imi4EO8EKg_7PV4jcUkAAMP__du07Tlhr4sO4_aem_c3AvVNjhsHI_Q0M1hl3Pfg
Credit: ተወዳጅ ሚዲያ

ሰላም አታላይ በአርትስ ቴሌቪዥን "ሎሚ ብወረውር" የተሰኘ ዝግጅት ማቅረብ ልትጀምር ነው ።
የሥነልቦና ባለሞያዋ ሰላም አታላይ "ሎሚ ብወረውር" የተሰኘ የቴሌቪዥን ዝግጅት በቅርቡ በአርትስ ቴሌቪዥን ማዘጋጀት እንደምትጀምር በማህበራዊ ትስስር ገጿ አስታውቃለች።
ሁሉገቧ የሥነልቦና እና የሚዲያ ባለሞያ ሰላም አታላይ በቡና ፖድካስት እና በአዋሽ ኤፍ ኤም 90.7 ሬድዮ "አዋሽ ስፔሻል" በተሰኘ የሬድዮ ፕሮግራም ላይ በምታቀርባቸው የሥነልቦና ጉዳዮች መሰናዶዋ እናውቃታለን።
በተጨማሪም በቴሌግራም ፣ በቲክቶክ አማራጮች በህይወት እና ሥነልቦናዊ ጉዳዮች ላይ በርካታ ቁምነገሮችን አጋርታለች።
ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
የሥነልቦና ባለሞያዋ ሰላም አታላይ "ሎሚ ብወረውር" የተሰኘ የቴሌቪዥን ዝግጅት በቅርቡ በአርትስ ቴሌቪዥን ማዘጋጀት እንደምትጀምር በማህበራዊ ትስስር ገጿ አስታውቃለች።
ሁሉገቧ የሥነልቦና እና የሚዲያ ባለሞያ ሰላም አታላይ በቡና ፖድካስት እና በአዋሽ ኤፍ ኤም 90.7 ሬድዮ "አዋሽ ስፔሻል" በተሰኘ የሬድዮ ፕሮግራም ላይ በምታቀርባቸው የሥነልቦና ጉዳዮች መሰናዶዋ እናውቃታለን።
በተጨማሪም በቴሌግራም ፣ በቲክቶክ አማራጮች በህይወት እና ሥነልቦናዊ ጉዳዮች ላይ በርካታ ቁምነገሮችን አጋርታለች።
ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
አብርሆት አገልግሎት እየሰጠ አይደለም
አራት ኪሎ የሚገኘው አብርሆት የህዝብ ቤተመጻሕፍት ለአንባቢያን አግልግሎት እየሰጠ እንዳይደለ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ተመልክቷል።
በቤተመጻሕፍቱ ውስጥ ለተማሪዎች "ኦላይን" ፈተና እየተሰጠ በመሆኑ ምክንያት ለሚቀጥሉት ቀናትም ለአንባቢያን ዝግ ሆኖ እንደሚቆይ ተነግሯል።

የዲጂታል ጥበብ አውደርዕይ በፈንድቃ
በግራፊክስ ዲዛይነር ፋኑኤል ልዑል የተዘጋጁ የዲጂታል ጥበብ ስራዎች የሚቀርቡበት "የተሰወረውን መሻት" የተሰኘ የዲጂታል ጥበብ አውደርዕይ ዛሬ ሰኔ 24 2016 ዓ.ም ከምሽቱ 12:00 ጀምሮ ካዛንቺስ በሚገኘው ፈንድቃ የባህል ማዕከል ውስጥ ይከፈታል።
ይህ የዲጂታል ጥበብ አውደርዕይ እስከ ሐምሌ 8 2016 ዓ.ም ድረስ በእይታ ላይ ይቆያል ተብሏል።
የግራፊክስ ዲዛይነሩ ፋኑኤል ልዑል ከዓመታት በፊት ለአድማጮች የደረሰው የሮፍናን ኑሪ"ስድስት" አልበም ሽፋን(ከቨር) ዲዛይኑን መስራቱ ይታወሳል።

ዛሬ ዓለምአቀፍ የስፖርት ጋዜጠኞች ቀን ነው
የዓለም ስፖርት ጋዜጠኞች ቀን ሐምሌ 2 ቀን የስፖርት ጋዜጠኞች ስፖርትን ለማስተዋወቅ የሚያገለግሉትን አገልግሎት ለማክበር በሚል በዓለምአቀፍ ደረጃ ተከብሮ ይውላል።
ይህ ቀን በ1924ቱ የፓሪስ ኦሊምፒክ የዓለም አቀፍ ስፖርት ፕሬስ ማህበር የተመሰረተበት ቀን በመሆኑ በይፋ "የዓለምአቀፍ የስፖርት ጋዜጠኞች ቀን" ተብሎ ተወስኗል።
በህትመት (ጋዜጣና መጽሔት ) ፣በሬድዮና ቴሌቪዥን፣በዲጂታል የሚዲያ አማራጮች ከልባችሁ የምትሰሩ ውድ ኢትዮጵያዊያን የስፖርት ጋዜጠኞች እንኳን አደረሳችሁ እንላለን።

"ጥቁር አደይ" ፊልም ሊመረቅ ነው
በደራሲ እና ዳይሬክተር ፍፁም ካሣሁን የተሰራው "ጥቁር አደይ" ፊልም የፊታችን ሐምሌ 10 2016 ዓ.ም በሸራተን አዲስ ሆቴል ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ይመረቃል ተብሏል።
በፊልሙ ላይ ኤደን አይሸሹም፤ ካሣሁን ፍስሐ ማንዴላ፤ ናታን ጌታቸው፤ ነቢዩ እንድሪስ ጨምሮ ከ186 በላይ ተዋናያን እንደተሳተፉበት አዘጋጆቹ ለኤቨንት አዲስ ድረገፅ ተናግረዋል።
"ጥቁር አደይ" ፊልም አንድ ሰዓት ከሐምሳ ደቂቃ ረዝመት ያለው ሲሆን ከ6.7 ሚሊየን ብር በላይ ውጪ እንደወጣበት ተነግሯል።

"የሚስቶቼ ባሎች" ተውኔት በዓለም ሲኒማ መቅረብ ከጀመረ አንድ ዓመት እንደሞላው አዘጋጆቹ አስታወቁ
በአበባየሁ ታደሰ ተደርሶ በተስፋዬ ገ/ማርያምና ይገረም ደጀኔ (አስቴር ) የተዘጋጀው "የሚስቶቼ ባሎች" ኮሜዲ ተውኔት በዓለም ሲኒማ መቅረብ ከጀመረ አንድ ዓመት እንደሞላው አዘጋጆቹ ለኤቨንት አዲስ ድረገፅ ተናገረዋል።
አዘጋጆቹ "የዛሬ ዓመት ሰኔ 21 የተከፈተው "የሚስቶቼ ባሎች" በተወዳጅነቱ እንደዘለቀ ይኸው አንድ ዓመት ሞላው።ረቡዕ በ12:00 ሰዓት ብቅ ብለው እየተዝናኑ አንደኛ ዓመታችንን ከእኛ ጋር ያክብሩ" ያሉ ሲሆን
በተጨማሪም "የሚስቶቼ ባሎች" ተውኔት ዘወትር ረቡዕ በ12:00 ሰዓት በዓለም ሲኒማ መታየቱን ይቀጥላል " ብለዋል።
ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
በአበባየሁ ታደሰ ተደርሶ በተስፋዬ ገ/ማርያምና ይገረም ደጀኔ (አስቴር ) የተዘጋጀው "የሚስቶቼ ባሎች" ኮሜዲ ተውኔት በዓለም ሲኒማ መቅረብ ከጀመረ አንድ ዓመት እንደሞላው አዘጋጆቹ ለኤቨንት አዲስ ድረገፅ ተናገረዋል።
አዘጋጆቹ "የዛሬ ዓመት ሰኔ 21 የተከፈተው "የሚስቶቼ ባሎች" በተወዳጅነቱ እንደዘለቀ ይኸው አንድ ዓመት ሞላው።ረቡዕ በ12:00 ሰዓት ብቅ ብለው እየተዝናኑ አንደኛ ዓመታችንን ከእኛ ጋር ያክብሩ" ያሉ ሲሆን
በተጨማሪም "የሚስቶቼ ባሎች" ተውኔት ዘወትር ረቡዕ በ12:00 ሰዓት በዓለም ሲኒማ መታየቱን ይቀጥላል " ብለዋል።
ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
ታላቁ የጥበብ ሰው ነብይ መኮንን አረፈ
አንጋፋው ጋዜጠኛ፣ ደራሲ ፣ ገጣሚ እና ትርጓሜ ነብይ መኮንን ከዚህ ዓለም በሞት እንደተለየ አዲስ አድማስ ጋዜጣ አስታውቋል።
ገጣሚና ደራሲ ነቢይ መኮንን ባደረበት ህመም ህክምና ሲከታተል ቆይቶ፣ ድንገት ያረፈው ዛሬ ሰኔ 26 ቀን 2016 ዓ.ም ረፋዱ ላይ ነው።
አንጋፋው ጋዜጠኛ ነብይ መኮንን ለረጅም ዓመታት የአዲስ አድማስ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ሆኖ ሰርቷል።
ነብይ መኮንን ከአዲስ አድማስ መሥራቾች አንዱ ሲሆን በዋና አዘጋጅነት ጋዜጣዋን በመምራት ተወዳጅ ካደረጓት በቀዳሚነት ስሙ ይጠቀሳል።
"ነገም ሌላ ቀን ነው" "የመጨረሻው ንግግር" እና "የእኛ ሰው በአሜሪካ" የተሰኙ መጻሕፍትን ለአንባቢያን አድርሷል።
ኤቨንት አዲስ ድረገፅ በታላቁ የጥበብ ሰው ነብይ መኮንን ህልፈት ሀዘኑን ይገልጻል።ለቅርብ ቤተሰቦቹ፣ አድናቂዎቹ ከልብ መፅናናትን ይመኛል።

ታላቁ የጥበብ ሰው ነብይ መኮንን አረፈ አንጋፋው ጋዜጠኛ፣ ደራሲ ፣ ገጣሚ እና ትርጓሜ ነብይ መኮንን ከዚህ ዓለም በሞት እንደተለየ አዲስ አድማስ ጋዜጣ አስታውቋል። ገጣሚና ደራሲ ነቢይ መኮንን ባደረበት ህመም ህክምና ሲከታተል ቆይቶ፣ ድንገት ያረፈው ዛሬ ሰኔ 26 ቀን 2016 ዓ.ም ረፋዱ ላይ ነው። አንጋፋው ጋዜጠኛ ነብይ መኮንን ለረጅም ዓመታት የአዲስ አድማስ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ሆኖ ሰርቷል።…
ስለ ነቢይ መኮንን አንዳንድ መረጃዎች
ታላቁ የጥበብ ሰው ነቢይ መኮንን ዛሬ ረቡዕ ሰኔ 26 2016 ዓ.ም ማረፉ ተሰምቷል።ስለዚህ ግዙፍ ኢትዮጵያዊ የጥበብ ሰው ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ያገኘውን መረጃ እንደሚከተለው ያቀርባል።
📍ነበይ መኮንን
አንጋፋ ጋዜጠኛ፣ ደራሲ ፣ ገጣሚ እና ትርጓሜ ነው።
📍ጋዜጠኛው ነቢይ መኮንን
-አንጋፋው ጋዜጠኛ ነቢይ መኮንን ለረጅም ዓመታት የአዲስ አድማስ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ሆኖ ሰርቷል።
-ነቢይ መኮንን ከአዲስ አድማስ መሥራቾች አንዱ ሲሆን በዋና አዘጋጅነት ጋዜጣዋን በመምራት ተወዳጅ ካደረጓት በቀዳሚነት ስሙ ይጠቀሳል።
📍ገጣሚው ነቢይ መኮንን
ገጣሚ ነቢይ መኮንን፤ “ስውር ስፌት” ቁጥር አንድና ሁለት፣ የግጥም መድበሎችን ጨምሮ በርካታ የግጥም ስራዎችን በተለያዩ መድረኮች በማቅረብ ይታወቃል፡፡
📍ደራሲው ነቢይ መኮንን
“የኛ ሰው በአሜሪካ” እና "የመጨረሻው ንግግር " የተሰኙ መጻሕፍቱ ዝነኛ ስራዎቹ ናቸው።
📍ተርጓሚው ነቢይ መኮንን
በአሜሪካዊቷ ደራሲ ማርጋሬት ሚሼል ተደርሶ፤ በመላው ዓለም ከፍተኛ ተነባቢነትን ያገኘውን “Gone With The Wind” የተሰኘውን ረጅም ልብ ወለድ መጽሐፍ በቁርጭራጭ የሲጋራ ወረቀቶች ላይ ተርጉሞ“ነገም ሌላ ቀን ነው” በሚል ርዕስ አስነብቧል፡፡
📍ተረት ጸሐፊው ነቢይ መኮንን
ነቢይ መኮንን ወደ 700 ገደማ ተረቶችን ጽፏል። እነዚህንም ተረቶች በአዲስ አድማስ ጋዜጣ ርዕስ አንቀጽ ውስጥ አስነብቦናል።ይህም የእሱ መለያ ነበር።
📍ወግ አዋቂው ነቢይ መኮንን
ነቢይ መኮንን ሲጽፍ ብቻ ሳይሆን ሲናገርም ለዛ ካላቸው ወግ አዋቂ ጥቂት የጥበብ ሰዎች መካከል አንደኛው ነው። ለረጀም ሳምንታት በሸገር ሬድዮ" የቅዳሜ ጨዋታ" ዝግጅት ላይ በተደጋጋሚ በመቅረብ ብዙ ጉዳዮች ላይ ተጨዋውቷል።
📍ነቢይ በተውኔት ውስጥ
ነቢይ መኮንን "ናትናኤል ጠቢቡ" እና " ጁሊየስ ቄሳር" የተሰኙ ተውኔቶችን ተርጉሟል።በቀድሞ ጊዜም በአንዳንድ ተውኔቶች ላይ በተዋናይነት እንደተሳተፈም ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
📍የቴሌቪዥን ድራማ ጸሐፊው ነቢይ መኮንን
ነቢይ መኮንን በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ይተላለፍ በነበረው "ባለጉዳይ" የተሰኘ ተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማ ላይ በድርሰት እና ተዋይነት ሰርቷል።
📍የሙዚቃ ግጥም ጸሐፊው ነቢይ መኮንን
ነቢይ መኮንን በሙዚቃ ግጥም የተሳተፈባቸው የሙዚቃ ስራዎችም አሉ።ከእነዚህም መካከል በኤችአይቪ ወረርሽኝ ጊዜ የተሰራው "ማለባበስ ይቅር" በተሰኘው ሙዚቃ ላይ በግጥም ተሳትፏል።
📍የነቢይ ህልፈት
ገጣሚና ደራሲ ነቢይ መኮንን ባደረበት ህመም ህክምና ሲከታተል ቆይቶ፣ ድንገት ያረፈው ዛሬ ሰኔ 26 ቀን 2016 ዓ.ም ረፋዱ ላይ ነው።
1948 እንደተወለደ የሚነገረው ደራሲ እና ወግ አዋቂው ነቢይ ህይወቱ ያለፈው በተወለደ በ68 ዓመቱ ነው።
የሶስት ሴት ልጆች አባት የሆነው የነቢይ መኮንን የቀብር ስርዓት፤ ባለቤቱ እና ልጁ ከውጭ ሀገር ከመጡ በኋላ እንደሚፈፀም ተነግሯል።
(መረጃ አሰባሳቢ: ናቲ ማናዬ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ)
ለተጨማሪው: @EventAddis1
@EventAddis1

ስለ ነቢይ መኮንን አንዳንድ መረጃዎች ታላቁ የጥበብ ሰው ነቢይ መኮንን ዛሬ ረቡዕ ሰኔ 26 2016 ዓ.ም ማረፉ ተሰምቷል።ስለዚህ ግዙፍ ኢትዮጵያዊ የጥበብ ሰው ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ያገኘውን መረጃ እንደሚከተለው ያቀርባል። 📍ነበይ መኮንን አንጋፋ ጋዜጠኛ፣ ደራሲ ፣ ገጣሚ እና ትርጓሜ ነው። 📍ጋዜጠኛው ነቢይ መኮንን -አንጋፋው ጋዜጠኛ ነቢይ መኮንን ለረጅም ዓመታት የአዲስ አድማስ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ…
የነቢይ መኮንን የቀብር ሥነሥርዓት ነገ ይፈፀማል
ታላቁ ብዕረኛ ነቢይ መኮንን ዛሬ ማለዳ ለዘላለም ከማሸለቡ አስቀድሞ ይህንን አለ፦ "በምወዳት ከተማዬ ናዝሬት፣ ከምወዳት እናቴ ማረፊያ ቅድስት ማርያም ቤ/ክርስቲያን ቅበሩኝ"
ቤተሰቦቹ እንደገለጹልኝ ከኾነ የቀብር ስነሥርዓቱ ነገ ሐሙስ ሰኔ 27 ቀን 2016 ዓ/ም ከቀኑ በ9 ሰዓት አዳማ /ናዝሬት ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ይፈጸማል።
ከዚያ አስቀድሞ አንጋፋ የኪነጥበብ ሙያ አጋሮቹ ወዳጅ ዘመዶቹ እና አድናቂዎቹ በተገኙበት በታላቁ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ከጠዋት 3፣30 ሰዓት ጀምሮ እስከ 5፣00 ሰዓት ድረስ የሽኝት መርሐ ግብር ይከናወናል።
መላው የሚዲያ ማሕበረሰብ መረጃውን እንዲያዳርስላቸው እንዲሁም የሙያ አጋሮቹና አድናቂዎቹ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር በመገኘት የሽኝት ሥነስርዓቱን እንዲታደሙ ጥሪ አቅርበዋል።
📍መረጃው የያሬድ ሹመቴ ነው።

የሐሙስ መረጃዎች
የሳምንቱን ኪናዊ መረጃዎችን እነሆ:
📍መረጃውን ሲጠቀሙ ምንጭ ይጠቀሱ!
1.የአንጋፋው ጋዜጠኛ ፣ገጣሚ፣ ደራሲና ተርጓሚ ነቢይ መኮንን የሽኝትና ቀብር ሥነሥርዓት ዛሬ ሰኔ 27 2016 ዓ.ም ይፈፀማል።የሽኝት መርሐግብሩ ከጠዋቱ 3:30 እስከ 5:00 በብሔራዊ ቴአትር የሚካሄድ ሲሆን ከቀኑ 9:00 ላይ በአዳማ ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን የቀብር ሥነሥርዓቱ ይፈፀማል ተብሏል።
2.ሙዚቀኛ ሮፍናን ኑሪ በ"USA TOUR" በአሜሪካ ከዛሬ ጀምሮ የሙዚቃ ስራውን ማቅረብ ይጀምራል ተብሏል። ሙዚቀኛው ዛሬ በአትላንታ የሙዚቃ ስራውን ማቅረብ የሚጀምር ሲሆን በማስከተል በስድስት የአሜሪካ ግዛቶች የሙዚቃ ኮንሰርቱን እንደሚያቀርብ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ሰምቷል። ይህም የሙዚቃ ዝግጅት ጉዞው የሮፍናን ኑሪ ዘጠኛ(ኖር እና ሐራንቤ) አልበም ከተለቀቀ በኃላ የመጀመሪያው ነው።
3.የድምጻዊት ሰላማዊት ዮሐንስ "ሰንቢደ" የተሰኘ የትግርኛ ሙዚቃ ነገ በናሆም ሪከርድስ በኩል ለአድማጮች ይደርሳል።በሙዚቃው ላይ በግጥም ውቅያኖስ ጉዕሽ በዜማና ሙዚቃ ቅንብር በረኸት ወልዱ ተሳትፈዋል።ድምጻዊት ሰላማዊት ዮሐንስ ከዚህ ቀደም በዩቲዩብ ከፍተኛ ተመልካች ያገኘችባቸውን "ዞማዋ" "ሰናይ " "የብለኒሎ"ን ጨምሮ በርካታ ነጠላ ሙዚቃዎችን ለአድማጮች አድርሳለች።
4."የአርክውድ አፍሪካ የፊልም ገበያ እና ሽልማት 2017 ቅደመ ዝግጅት" የተሰኘ ጉባኤ ሰኔ 28 እና 29 2016 ዓ.ም ለሁለት ቀናት በአዲስ አበባ አድዋ መታሰቢያ ሙዚየም ውስጥ ይካሄዳል። ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገሮች የተወጣጡ የፊልም ባለሞያዎች በዚህ ጉባኤ ላይ እንደሚሳተፉ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ሰምቷል።
5.ከደራስያን ጋር የመጨዋወት እና መጽሐፍ የማስፈረም ልዩ ሥነ-ሥርዓት የፊታችን ቅዳሜ በዋልያ መጻሕፍት ይካሄዳል። በዚህ ሳምንት በደራሲ አለማየሁ ገላጋይ "ማዕበል ጠሪ ወፍ" በተሰኘው መጽሐፍ ላይ ውይይት ይካሄዳል ።በመጽሐፉ ላይ ደራሲ እንዳለጌታ ከበደ እና ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ ዳሰሳ ያቀርባሉ ተብሏል። ይህ ውይይት የፊታችን ቅዳሜ ሰኔ 29 2016 ዓ. ም ከሰዓት 10:00 እስከ 12:30 ድረስ አራት ኪሎ በሚገኘው ዋልያ መጻሕፍት ውስጥ ይካሄዳል።
6.የገጣሚ መንበረማርያም ኃይሉ "የጊዜ ሰሌዳ" የተሰኘ የግጥም መጽሐፍ የፊታችን ሰኞ ሐምሌ 1 2016 ዓ.ም ከምሽቱ 11:00 ጀምሮ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር አዳራሽ ልዩ ልዩ ተጋባዥ እንግዶች በተገኙበት ይመረቃል። "የጊዜ ሠሌዳ" መጽሐፍ በ103 ገፆች ተቀንብቡ በ250 ብር የጀርባ ዋጋ ለአንባቢያን ቀርቧል። ገጣሚዋ ከዚህ ቀደም "የቃል ሠሌዳ" የተሰኘ መጽሐፍ ለንባብ ማብቃቷ ይታወሳል።
7. በኔትፍሊክስ በኩል ለተመልካቾች ሊቀረብ ይችላል የተባለውና በደራሲ እና ዳይሬክተር ፍፁም ካሣሁን የተሰራው "ጥቁር አደይ" ፊልም የፊታችን ሐምሌ 10 2016 ዓ.ም በሸራተን አዲስ ሆቴል ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ይመረቃል ተብሏል።በፊልሙ ላይ ሚኪ ተስፋዬ ፤ ካሣሁን ፍስሐ፣ማንዴላ፤ ናታን ጌታቸው፤ ነቢዩ እንድሪስ፣ ኤደን አይሸሹምን ጨምሮ ከ186 በላይ ተዋናያን እንደተሳተፉበት አዘጋጆቹ ለኤቨንት አዲስ ድረገፅ ተናግረዋል።
8."እሳት ወይ አበባ" ተውኔት ነገ ወደ መድረክ ይመለሳል። በሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን ግጥሞች ላይ የተመሰረተው "እሳት ወይ አበባ" ግጥማዊ ዳንስ ተውኔት በብሔራዊ ቴአትር ከነገ ሰኔ 28 2016 ዓ.ም ጀምሮ ወደ መድረክ እንደሚመለስ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ከአዘጋጆቹ ያገኘው መረጀ ያመለክታል።
9.በዓለምአቀፍ ደረጃ ስመ ገናና የሆነውን "MosFilm" ስቱዲዮ 100ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ የሩሲያ ሳይንስና ባህል ማዕከል ከአላቲኖስ ኢትዮጵያዊ ፊልም ሰሪዎች ማህበር ጋር በመተባበር ዘመን አይሽሬ የMosFilms ፊልሞችን ከዛሬ ሐሙስ ሰኔ 27 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 10:00 እና 12:00፣ቅዳሜ ሰኔ 29 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 10:00 እስከ 12:00 እንዲሁም እሁድ ሰኔ 30 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 10:00 እስከ 12:00 ከአንድሬ ታርኮቭስኪ እስከ ኦስካር አሸናፊ ፊልሞች በነፃ ለታዳሚያን ያቀርባል። ይህም የፊልም ሳምንት ፒያሳ በሚገኘዉ የፑሽኪን ሲኒማ አዳራሽ ውስጥ ይካሄዳል።
10.በግራፊክስ ዲዛይነር ፋኑኤል ልዑል የተዘጋጁ የዲጂታል ጥበብ ስራዎች የሚቀርቡበት "የተሰወረውን መሻት" የተሰኘ የዲጂታል ጥበብ አውደርዕይ ባሳለፍነው ሰኞ ሰኔ 24 2016 ዓ.ም ከምሽቱ 12:00 ጀምሮ ካዛንቺስ በሚገኘው ፈንድቃ የባህል ማዕከል ውስጥ ተከፍቷል።ይህ የዲጂታል ጥበብ አውደርዕይ እስከ ሐምሌ 8 2016 ዓ.ም ድረስ በእይታ ላይ ይቆያል ተብሏል።የግራፊክስ ዲዛይነሩ ፋኑኤል ልዑል ከዓመታት በፊት ለአድማጮች የደረሰው የሮፍናን ኑሪ"ስድስት" አልበም ሽፋን(ከቨር) ዲዛይኑን መስራቱ ይታወሳል።
አዘጋጅ: ናቲ ማናዬ
ቀን: ሰኔ 27 2016 ዓ.ም
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
በድረገጻችን በተሻለ አቀራረብ ያንብቡ:
https://eventaddis.com
ቴሌግራም: @EventAddis1

የአንጋፋው ከያኒ ነቢይ መኮንን ሥርዓተ ቀብር ተፈጸመ
አንጋፋው የኪነ ጥበብ ባለሞያ፣ ገጣሚ፣ ደራሲ፣ ፀሃፊና ተርጓሚ ነብይ መኮንን ባደረበት ህመም በህክምና ሲረዳ ቆይቶ ትላንት ሰኔ 26 ቀን 2016 ዓ.ም ከዚህ ዓለም ማለፉ መገለጹ ይታወሳል፡፡
በዛሬው ሰኔ 27 2016 ዓ.ም በብሄራዊ ቴአትር ቤት በሙያ ጓደኞቹ የአሸኛኘት ፕሮግራም የተከናወነለት ሲሆን፣ በመቀጠልም በተወለደበት እና ባደገበት ናዝሬት ከተማ ሥርዓተ ቀብሩ ተፈጽሟል፡፡
ለተጨማሪው: @EventAddis1
@EventAddis1
አንጋፋው የኪነ ጥበብ ባለሞያ፣ ገጣሚ፣ ደራሲ፣ ፀሃፊና ተርጓሚ ነብይ መኮንን ባደረበት ህመም በህክምና ሲረዳ ቆይቶ ትላንት ሰኔ 26 ቀን 2016 ዓ.ም ከዚህ ዓለም ማለፉ መገለጹ ይታወሳል፡፡
በዛሬው ሰኔ 27 2016 ዓ.ም በብሄራዊ ቴአትር ቤት በሙያ ጓደኞቹ የአሸኛኘት ፕሮግራም የተከናወነለት ሲሆን፣ በመቀጠልም በተወለደበት እና ባደገበት ናዝሬት ከተማ ሥርዓተ ቀብሩ ተፈጽሟል፡፡
ለተጨማሪው: @EventAddis1
@EventAddis1
የቅድስት ይልማ "ጀስቲሺያ" ፊልም ለእይታ ሊበቃ ነው
የዳይሬክተር ቅድስት ይልማ "ጀስቲሺያ" የተሰኘ ፊልም ከሐምሌ 5 2016 ዓ.ም ጀምሮ በዓለም ሲኒማ ለእይታ እንደሚበቃ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ሰምቷል።
የ"ጀስቲሺያ" ፊልም ዳይሬክተር ቅድስት ይልማ ስትሆን አዜብ ወርቁ እና ቅድስት ይልማ በፊልም ጽሑፍ ተሳትፈዋል።
ህሊና ሲሳይ ፣እድለወርቅ ጣሰው ፣ ድርብወርቅ ሰይፉ ፣ቢታኒያ መስፍን ፣ኤደን ግርማና ሌሎችሞ በተዋናይነት ተሳትፈዋል።
"ጀስቲሺያ" የቤት ሰራተኞን የተመለከተ የህግ ማዕቀፍ እንዲወጣ ግንዛቤ መፍጠርን ዓላማ ይዞ የተሰራ ፊልም እንደሆነ ተሰምቷል።

በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ኦንላየን ሲኒማ ተመረቀ
በሀገራችን የተለያዩ ቴክኖሎጂዎችን በማበልፀግ የሚታወቀው ኢግልላየን ቴክኖሎጂ ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመተባበር "ቴሌ ቲቪ" የተሰኘ በኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የኦንላይን ሲኒማ አስመርቋል።
"ቴሌ ቲቪ" በኢትዮጵያ ያለውን ፊልም የመከራየት ልምድ በቴክኖሎጂ በማዘመን ፊልሞችን ለተገደቡ ቀናት በመከራየት ማየት የሚያስችል መተግበሪያ ነው።
መተግበሪያውም ከቅርብ ግዜ ወዲህ በፊልሙ ኢንዱስትሪ መሰናክል ሆኖ የቆየውን የፊልም ስርቆት የሚያስቀር መሆኑን የኤግላየን ሲስተም ቴክኖሎጂ መስራች እና ስራ አስፈጻሚ የሆኑት በእርሱፍቃድ ጌታቸው ገልጸዋል።
ተመልካቾች ከዛሬ ጀምረው ፊልሞችን መከራየት የሚችሉ እንደሆነ እና ክፍያም ለሀገር ውስጥ ደንበኞች በቴሌ ብር እንዲሁም በውጪ ሀገር ለሚኖሩ የአማርኛ ፊልም ተመልካቾች በቪዛ፣ ማስተር ካርድ እና አሜሪካን ኤክስፕረስ በመጠቀም ይችላሉ ተብሏል።
📍መረጃው የኤንቢሲ ቴሌቪዥን ነው።

የሜንታል ሄልዝ አዲስ መርሃግብር ነገ ይካሄዳል
ወርሃዊው የሜንታል ሄልዝ አዲስ መርሃግብር ነገ ቅዳሜ ሰኔ 29 ቀን 2016 ዓም አትላስ አካባቢ በሚገኘው በአዶር አዲስ ሆቴል ከቀኑ 10፡00 ጀምሮ ይካሄዳል።
የዚህ ወር ርዕስም፡- “A Journey to Deal with Secondary Trauma of Health Professionals and Gender-Based Violence Survivors” የሚል ሲሆን የዚህ ወር እንግዳ ዶ/ር ሰብለ ሃይሉ ናቸው፡፡
ለመታደም ይህን መስፈንጠሪያ ይጫኑና ይመዝገቡ፡፡
https://forms.gle/gMnmRBBSfhR7YyYB6
የማስታወሻ መልዕክት እና የቦታውን አቅጣጫ ምልክት ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችንን ይከተሉ https://news.1rj.ru/str/mhaddisababa

የመጻሕፍት አውደርዕይ በኢግዚብሽን ማዕከል
የአዲስ አበባ ከተማ ባህል ኪነጥበብና ቱሪዝም ቢሮ ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመተባበር ያዘጋጀው 9ኛ ዙር የንባብ ፌስቲቫል “ንባብ ለትውልድ ግንባታ!” በሚል መሪ ቃል ከዛሬ ሰኔ 28 እስከ ሰኔ 30 2016 ዓ.ም ድረስ በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል ይካሄዳል፡፡
ቴሌግራም: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
ድረገፅ: https://eventaddis.com

"ሚውዚኮሎጂ" የቴሌቪዥን ዝግጅት በአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ(Addis TV) መቅረብ ሊጀምር ነው።
በሄኖክ መሓሪ (መሓሪ ብራዘርስ) እየተዘጋጅ የሚቀረበው "ሚውዚኮሎጂ" የሙዚቃ እና ሙዚቀኞች የቴሌቪዥን ዝግጅት በቅርቡ በአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ( Addis TV) መቅረብ እንደሚጀመር ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ከአዘጋጁ ሄኖክ መሓሪ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
በ ቃና እና አቦል ቴሌቪዥን ጣቢያዎች ለዓመታት ሲቀረብ የቆየው "ሚውዚኮሎጂ" የቴሌቪዥን ዝግጅት ዘወትር እሁድ በአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ (Addis TV) እና በዩቲዩብ አማራጮች ለተመልካቾች ይቀርባል ተብሏል።