📌የፎቶ ኤግዚቢሽን ዛሬ ለእይታ ይበቃል
ቴክኖ ካሞን 30 ፕሮ 5G ከቦርድ ሴልፎን ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ያዘጋጀው የፎቶ ኤግዚቢሽን ዛሬ ከቀኑ 9 ሰዓት ጀምሮ ኤድና ሞል ፊት ለፊት በሚገኘው ቤስት ዌስተርን ፕላስ ሆቴል ውስጥ ለእይታ ይበቃል።
ይህ የፎቶግራፍ አውደርዕይ ከሀምሌ 19 እስከ 21 2016 ዓ.ም ለህዝብ እይታ ክፍት ሆኖ ይቆያል።
በዚህ አውደርዕይ ላይ መሰረታዊ የSmart Phone ፎቶግራፊ ስልጠና ቅዳሜ ሐምሌ 20 2016 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ጀምሮ በፎቶግራፍ ባለሞያው እዮብ ቤዛነህ ይሰጣል ተብሏል።
የዚህ አውደርዕይ መግቢያ በነፃ ነው።
ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1

በእረፍት ቀንዎ ቴአትር ይመለከቱ !
አንጋፋው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር እና የቦሌው ዓለም ሲኒማ አርብ፣ ቅዳሜ እና እሁድ እነዚህን ተውኔቶች ለታዳሚያን ያቀርባሉ።
📍 የፍቅር ካቴና
ድርሰትና ዝግጅት: አለልኝ መኳንት ፅጌ
ቀን: አርብ
ሰዓት: 12:00
ቦታ: ዓለም ሲኒማ
📍 "እሳት ወይ አበባ"
ድርሰት: ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን እንደጻፈው
ዳንስና ዳንስ ቅንብር: ሽፈራው ታሪኩ ቢረጋ
ቀን: አርብ
ሰዓት:11:30
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር
📍 ባሎች እና ሚስቶች
ድርሰት: ውዱ አለን
አዘጋጅ: ሳሙኤል ተስፋዬ
ቀን: ቅዳሜ
ሰዓት: 8:00
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር
📍 ባቡሩ
ድርሰት: አርኖልድ ሪድሊ
አዘጋጅ:ራሔል ተሾመ መሐመድ
ቀን: ቅዳሜ
ሰዓት:11:30
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር
📍 ሸምጋይ
ድርሰት:ታደለ አያሌው
አዘጋጅ: ሳሙኤል ተስፋዬ
ቀን: እሁድ
ሰዓት: 8:00
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር
📍 እምዩ ብረቷ
ድርሰት: ቤልቶልት ብሬሽት
አዘጋጅ: ማንያዘዋል እንዳሻው
ቀን: እሁድ
ሰዓት:11:30
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር
የእናንተው ኤቨንት አዲስ ድረገፅ መልካም የእረፍት ቀን ይሁንላችሁ ይላል !

📌በእረፍት ቀንዎ ፊልም ይመልከቱ !
እነዚህ አራት የፊልም ማሳያዎች(ሲኒማ ቤቶች) ዛሬን ጨምሮ በሳምንቱ መጨረሻ ቀናት እነዚህን ፊልሞች ለተመልካቾች ያቀርባሉ: ምስሎቹን ይመልከቱ።
የሲኒማ ቤቶቹ አድራሻ:
✔️ሲኤምሲ ሚካኤል አካባቢ : ጋስት ሲኒማ
✔️ለም ሆቴል አካባቢ: ቫምዳስ ሲኒማ
✔️ጉርድ ሾላ አካባቢ : ሴንቸሪ ሲኒማ
✔️ቦሌ አካባቢ : ዓለም ሲኒማ
መልካም የእረፍት ቀናት ይሁንላችሁ !
https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1

📌 የደራሲ ሌሊሣ ግርማ "ደማቆቹ” አዲስ መፅሐፍ ለንባብ በቃ
የደራሲ ሌሊሣ ግርማ "ደመቆቹ" የተሰኘ የትርጉም መጽሐፍ ዛሬ ሐምሌ 19 2016 ዓ.ም ለንባብ እንደበቃ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
ይህ የትርጉም መጽሐፍ በዓለም ዙሪያ እና በዘመን መካከል ብቅ ካሉ እንደ እነ አንቷን ቼኮቭ፣ ኧርነስት ሄሚንግዌይ፣ ፍራንዝ ካፍካ፣ ገብሬል ጋርሻ ማርኩዌዝ፣ ናጂብ ማህፉዝ፣ ማርጋሬት አትዉድ፣ ሼርውድ አንደርሰን፣ ዊልያም ሳሮያን፣ ሳኪ፣ ሶመርሴት ሞም፣ ፍራንክ አር እስቶክተን፣ አየን ራንድ፣ ያሉ ምርጥ ጸሐፊያን ውስጥ ስመ ጥር የሆኑ አጫጭር ታሪኮች ስብስብ እንደሆነ ተነግሯል።
ደራሲ ሌሊሣ ግርማ ከዚህ ቀደም በግሉ የንፋስ ሕልም እና ሌሎችም አጫጭር ታሪኮች ፣ አፍሮጋዳ ፣ መሬት - አየር - ሰማይ ፣ የሰከረ እውነታ፣ እስቲ ሙዚቃ፣ ነፀብራቅ እና ይመስላል ዘላለም የተሰኙ መጻሕፍትን ለአንባቢያን አድርሷል።
የመጽሐፉ ዋና አከፋፋይ ጃፋር መፅሀፍት መደብር ነው። ዴሊቨር እንዲደረግላችሁ የምትፈልጉ በዚህ t.me/Demakochu1 ማዘዝ ትችላላችሁ ተብላችኋል።

📌ላይፍ ሴንተር ኢትዮጵያ ከአጋሩ ሆራይዘን ኢንተርናሽናል ጋር በመተባበር ለልጃገረዶች ስልጠና ሰጠ
ላይፍ ሴንተር ኢትዮጵያ የበጎ አድራጎት ድርጅት ከአጋሩ ሆራይዘን ኢንተርናሽናል ጋር በመተባበር ከ15 ዓመት በላይ ለሚሆናቸው ልጃገረዶች ስልጠና እና ልምድ የማካፈል መርሐግብርን ሐምሌ 19 2016 ዓ.ም አካሂዷል።
የስልጠናው ዋና ሀሳብም "ልጃገረዶች በህይወታቸው ላይ ትክክለኛ ውሳኔን እንዲወሰኑ እና ውሳኔያቸው ጤናማ እንዲሆን ማገዝ " እንደሆነ የላይፍ ሴንተር ኢትዮጵያ መስራች ወ/ሮ ሙሉ ግርማይ ተናግረዋል።
በዚህ የስልጠና እና ልምምድ ማካፈል መርሐግብር ላይ ከሀምሳ በላይ ልጃገረዶች ተሳትፈዋል።
በመርሐግብሩ ላይ የኪነጥበብ ባለሞያዋ ኮሜዲያን ቤተልሔም ጌታቸው (ቤት ዋኖስ) ያለፈችበትን የህይወት ልምዷን ለልጃገረዶቹ አካፍላለች።
የበጎ አድራጎት ድርጅቱ በትላንትናው ዕለትም ለወጣት ወንዶች በተመሳሳይ የህይወት ክህሎት ላይ ያተኮረ ስልጠና እና የልምድ ልውውጥ መርሐግብር አካሄዷል።
11 ዓመታትን ያስቆጠረው ድርጅቱ "የአንድ ሺ ማይል ጉዞ በአንድ እርምጃ ይጀምራል” እንዲሉ በጥቂት ህጻናት ብቻ የጀመሩት የስፖንሰርሺፕ እርዳታ ፕሮግራም አሁን ከ300 የሚበልጡ ወላጅ አልባ ህፃናትን የተመጣጠነ ምግብ፣ ልብስ፣ የትምህርት መርጃ መሳሪያዎችንና የመሳሰሉትን እያቀረበ የህይወት ክህሎት ስልጠና እና የምክር አገልግሎት እየሰጠ መልካም ዜጋን ለማፍራት አስተዋፅኦ እያደረገ ያለ ድርጅት ነው::

📌"ስብሐቲዝም" ኪናዊ ውይይት እሁድ ይካሄዳል
ሐሳብ፣ ንባብ፣የውይይት መንገድ ላይ ትኩረቱን ያደረገው "ስብሐቲዝም" ኪናዊ ውይይት 70ኛ ዙር መድረክ ነገ እሁድ ሐምሌ 21 2016 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ጀምሮ በብሔራዊ ቤተመዛግብት እና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት (ወመዘክር) አዳራሽ ውስጥ ይካሄዳል ።
በዚህኛውም ዙር መድረክ "ጂጂን ስናስታውስ " በሚል ርዕስ በድምጻዊት እጅግአየሁ ሽባባው (ጂጂ) ላይ ያተኮረ ውይይት ይካሄዳል።
አዘጋጆቹም"እጅጋየሁ ሽባባው በላቀ የሙዚቃ ስራዋ የክብር ዶክትሬት ከተቀበለች ወርሃ ሐምሌ 1 ዓመት ሞላው። እኛም በክብር እናስታውሳታለን።ጂጂን በልኳ ከሚነግሩን እጅግ ጥቂቶች አንዱ ጋዜጠኛ ጥበቡ በለጠ ነው፤ ከሌሎች እንግዶች ጋር ተገኝቶ ስለጂጂ ያወሳናል"ብለዋል።

📌የደራሲ ሄኖክ በቀለ አዲስ መጽሐፍ ለንባብ በቃ
ከዚህ ቀደም "ሀገር ያጣ ሞት" በተሰኘው የልቦለድ መጽሐፉ የምናውቀው ደራሲ ሄኖክ በቀለ "ይናፍቀኛል" የተሰኘ የግጥም ስብስቦች መጽሐፍ ዛሬ ሐምሌ 20 2016 ዓ.ም ለአንባቢያን አቅርቧል።
"ይናፍቀኛል" የተሰኘው የግጥም መጽሐፉ 88 የግጥም ስብስቦችን የያዘ ሲሆን በ128 ገፆች ተቀንብቦ በ300 ብር የጀርባ ዋጋ ለንባብ በቅቷል።
መጽሐፉን ለማዘዝ የምትፈልጉ ከሆነ በዚህኛው የቴሌግራም አድራሻ https://news.1rj.ru/str/ynafkegnal ማዘዝ እንደምትችሉ ተገልጿል።
ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
ከዚህ ቀደም "ሀገር ያጣ ሞት" በተሰኘው የልቦለድ መጽሐፉ የምናውቀው ደራሲ ሄኖክ በቀለ "ይናፍቀኛል" የተሰኘ የግጥም ስብስቦች መጽሐፍ ዛሬ ሐምሌ 20 2016 ዓ.ም ለአንባቢያን አቅርቧል።
"ይናፍቀኛል" የተሰኘው የግጥም መጽሐፉ 88 የግጥም ስብስቦችን የያዘ ሲሆን በ128 ገፆች ተቀንብቦ በ300 ብር የጀርባ ዋጋ ለንባብ በቅቷል።
መጽሐፉን ለማዘዝ የምትፈልጉ ከሆነ በዚህኛው የቴሌግራም አድራሻ https://news.1rj.ru/str/ynafkegnal ማዘዝ እንደምትችሉ ተገልጿል።
ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌የደራሲ እንዳለጌታ ከበደ አዲስ መጽሐፍ
የደራሲ እንዳለጌታ ከበደ " ሲ ጥ ል" የተሰኘ ረጅም ልቦለድ አዲስ መጽሐፍ ሐምሌ 27 2016 ዓ.ም ለንባብ እንደሚበቃ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ከደራሲው ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
ደራሲ እንዳለጌታ ከበደ በማህበራዊ ትስስር ገጹ የሚከተለውን ብሏል"ሲ ጥ ል" የተሰኘ ረጅም ልቦለዴን ከሐምሌ 27/2016 ጀምሮ ገበያ ላይ ይውላል::
አሳታሚው ዋልያ መጻሕፍት ሲሆን በመጽሐፉ ጀርባም የሚከተለው ጽሁፍ ሰፍሮበታል::
ከዚህ ቀደም፣ ‹ዛጎል›፣ ‹ደርሶ መልስ›፣ ‹እምቢታ (የቃቄ ወርድወት)› እና ‹ምሳሌ› በተሰኙ ረጃጅም ልቦለዶቹ የምታውቁት፤ በጭብጥ አመራረጡና በአጻጻፍ ስልቱ የተወዳጃችሁት እንዳለጌታ ከበደ፣ አሁን ደግሞ ‹ሲጥል› የተሰኘ ልቦለድ አበርክቶልናል፡፡
‹ሲጥል› የመንገደኞች ታሪክ ነው፤ መንገደኞቹ ለየጉዳዮቻቸው ከቤታቸው ወጥተው አንድ ላይ ቢሳፈሩም፣ በአንድ ባልታሰበ ሰበብ አብረው የሚሰነብቱበት አጋጣሚ ይፈጠራል፡፡ መንገደኞቹ፣ የየራሳቸው የሕይወት ፍልስፍና እና መርሆ ያላቸው ናቸው፡፡ እናም፣ በረገጡት ሥፍራ እንግዳ የሚሆኑት እነሱ ብቻ አይሆኑም - ሃሳቦቻቸውም ጭምር እንጂ፡፡"
" ‹ሲጥል› እንደ ከዚህ ቀደም የእንዳለጌታ መጻሕፍት ከራሳችን ጋር የሚያጨዋውቱ፣ ለሙግትም የሚጋብዙ ሃሳቦች የተስተናገዱበት ኪናዊ ማዕድ ነው፡፡ የድኅረ ዘመናዊ ደራስያንን የአጻጻፍ መንገድ በከፊል ተከትሎ፣ የትረካ ስልቱን ደግሞ እንደ ጃዝ ሙዚቃ አድርጎታል፡፡"

📌ሪፍት ቫሊ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቹን አስመረቀ
ሪፍት ቫሊ ዩኒቨርሲቲ በቴክኒክና ሙያ፣ በመጀመሪያ ዲግሪና በሁለተኛ ዲግሪ ያሰለጠናቸውን ከ9,200 በላይ ተማሪዎችን ዛሬ ሐምሌ 20 2016 ዓ.ም አስመርቋል።
ዛሬ በሚሊኒየም አዳራሽ የተመረቁት ተማሪዎች በአዲስ አበባና የሸገር ከተማ በሚገኙ 17 የዩንቨርቲው ካምፓሶች በጤና፤በቢዝነስና በማህበራዊ ሳይንስ፣በቴክኖሎጂ በቴክኒክና ሙያ፣ በመጀመሪያ ዲግሪና በሁለተኛ ዲግሪ ሲማሩ የነበሩ ናቸው ተብሏል።
በምርቃት ሥነሥርዓቱም ላይ የሪፍት ቫሊ ዩኒቨርሲቲ ባለቤትና ሥራ አስኪያጅ አቶ ድንቁ ደያሳ ፣በኢፌዲሪ የትምህርት ሚኒስተር እና የትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን ከፍተኛ የበላይ የሥራ ኃላፊዎችን ፣የክብር እንግዶች፣ የተመራቂ ቤተሰቦች ተገኝተዋል።

📌“ናዋዥ” የተሰኘ አዲስ መፅሐፍ ለንባብ በቃ
በደራሲ እያዩ ዳኛው የተሰናዳውና “ናዋዥ” የተሰኘው አዲስ የግለ ታሪክ መፅሐፍ ሰሞኑን ለንባብ በቃ፡፡ መፅሐፉ በዋናነት በደራሲው የግል ህይወት ላይ የሚያጠነጥን ቢሆንም፤ ኢትዮጵያዊያን በሱዳንና በሊቢያ በኩል ወደ አውሮፓ ለመግባት የሚያደርጉትን አስከፊና አስቸጋሪ የስደት ህይወት የሚያሳይ ነው ተብሏል፡፡
ነዋሪነቱን በጀርመን ያደረገው ደራሲ እያዩ ዳኛው፤ መፅሐፉ ከደቡብ ጎንደር ክምር ድንጋይ እስከ ጣሊያን የወደብ ከተማ ትራፓኒ የዘለቀውን የስደትና የውጣ ውረድ ጉዞ የሚዳስስ መሆኑን ለአዲስ አድማስ ተናግሯል፡፡
“ናዋዥ”፤ደራሲው ልጅነቱን የአፍላ ወጣትነቱን፣ የኢትዮጵያውያንን የስደት ኑሮ፣ በሱዳንና በሰሃራ በረሃ ለማቋረጥ ስደተኞች የሚከፍሉትን መስዋዕትነት እንዲሁም በመንግሥት አልባዋ ሊቢያ የነበረውን ኑሮና በሜድትራንያን ባህር የሚያጋጥምን ፈተና ያስቃኛል፡፡
በ470 ገፅ የተቀነበበው “ናዋዥ”፤ የግለ ታሪክ መፅሐፍ በ500 ብር ለገበያ ቀርቧል፡፡
📍መረጃው የአዲስ አድማስ ጋዜጣ ነው

📌 " አዎ ነቢይ በሀገሩ ይከበራል ! "
በቅርቡ በአጸደ ስጋ የተለየውን ሁለገቡ እና አንጋፋውን ከያኒ ነቢይ መኮንንን ለማክበር ዛሬ ሐምሌ 22 2016 ዓ.ም ልዩ ዝግጅት ተሰናድቷል።
የነቢይ ወዳጆች ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ጋር በመተባበር ያዘጋጁት ይህ መርሐግብር ዛሬ ሰኞ ሐምሌ 22 ቀን 2016 ዓ.ም ከ11:00 ሰዓት ጀምሮ በኢትዮጵያ ብሔራዊ አዳራሽ ይካሄዳል።
በዚህ "አዎን ነቢይ በሀገሩ ይከበራል!" በተሰኘ የክብር ማስታወሻ ዝግጅት ላይ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ሁላችሁም ተጋብዛችኋል።

📌"ንስሩ ልጅ" የተሰኘ ፊልም ለእይታ ቀረበ
በሱራፌል መልቲሚዲያ አማካኝነት የተሰናዳው "ንስሩ ልጅ" የተሰኘ አንድ ሰዓት ከሃያ ደቂቃ ርዝማኔ ያለው እና የቤተሰብ ፊልም በዓለም ሲኒማ ለእይታ መቅረብ ጀመረ።
በኢትዮጵያ ፊልም ኢንዱስተሪ ውስጥ የተለያዩ ፊልሞችን በድርሰት ፣ በዳይሬክቲንግ እና በፕሮዲውሲንግ ስራዎች መስክ ከፍተኛ አስተዋጾ እያደረገ በሚገኘው በደራሲና ዳይሬክተር ሱራፌል ኪዳኔ አማካኝነት የተዘጋጀው "ንስሩ ልጅ" ፊልም በትናንትናው ዕለት በዓለም ሲኒማ በይፋ ተመርቋል።
የፊልሙ ደራሲና ዳይሬክተር ሱራፌል ኪዳኔ በፊልም ምርቃቱ መርሐግብር ላይ እንገለጸው ስድስት ዓመት በላይ የወሰደው "ንስሩ ልጅ" ፊልም በብዙ ጥናት ላይ በመመርኮዝ በታዳጊ ልጆች እና ወላጆቻቸው ላይ ትኩረት በማደረግ ልጅን ከወላጅ ጋር በማቀራረብ መልካም ትውልድን ለመፈጠር እየተሰራ ባለው ስራ ላይ ተጨማሪ ግብዓት እንዲሆን በማሰብ መዘጋጀቱን ገልጿል።
"ንስሩ ልጅ" ፊልም ለተከታዮቹ አራት ሳምንታት ዘወትር እሁድ ከረፋዱ 5:00 ሰዓት ጀምሮ በዓለም ሲኒማ እና በቀጣይ በተለያዩ ትምህርት ቤቶች እና በተለያዩ ሲኒማ ቤቶች ለእይታ የሚቀርብ ሲሆን ወላጆች ከልጆቻቸው ጋር እንዲመለከቱት ደራሲ መልዕክት አስተላልፏል።
📍መረጃው የጌች ሀበሻ ነው።

📌አርቲስት ትንሣኤ ብርሃን ብራንድ አምባሳደር ሆነ
በኢቢኤስ ቴሌቪዥን በሚተላለፈው "እሁድን በኢቢኤስ " ፕሮግራም ላይ አቅራቢ የሆነው እና በድራማ ፣ ፊልሞች ተዋናይነቱ የምናውቀው አርቲስት ትንሣኤ ብርሃን የባሊ ምግብ ማቀነባበሪያ ብራንድ አምባሳደር ሆኖ ተሹሟል።
ባሊ ፉድ ፕሮሰሲንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ ድርጅት አርቲስት ትንሣኤ ብርሃንን በብራንድ አምባሳደርነት የሾመው ለሚያመርታቸው በማር ወለላ የተቀመመ "QQ yammy snack" እና በኦቾሎኒ ጣዕም ለሚያመርተው "QQ coated peanut" ምርቶቹ ነው።
ይህ የብራንድ አምባሳደር የሥራ ስምምነት ፊርማ ለአንድ ዓመት ይቆያል ተብሏል።
ባሊ ፉድ ፕሮሰሲንግ ከተመሰረተ 4 ዓመታትን ያስቆጠረ ሲሆን በማር ወለላ የተቀመመ QQ yammy snack እና በኦቾሎኒ ጣዕም የሚያመርተው QQ coated peanut በማምረት ላይ የሚገኝ ድርጅት ነው።
ተቋሙ እነዚህን ጣፋጭ ምግቦች በተመጣጣኝ ዋጋ እና በከፍተኛ ጥራት ለገበያ እንደሚያቀርብ በስምምነቱ ቀን ላይ ተገልጿል።

📌ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ከሁለት ክሶች ነፃ ተባለ
ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በሐምሌ 2014 ዓ.ም “ጥብቅ የመከላከያ ሠራዊትን ምስጢር ማባከን”፣ “መከላከያ ሠራዊቱን መከፋፈል” እና “የመከላከያ ሠራዊቱን ስም ማጥፋት” የሚሉ ሦስት ክሶች ተመስርተውበት በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ሆኖ ለስድስት ወራት በእስር ላይ ነበር።
ሆኖም ግን በፌደራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት የሕገ-መንግሥት እና የሽብር ወንጀል ችሎት ሰብሳቢ የሆኑት የተከበሩ ዳኛ ዘላለም ተስፋዬ እና የተከበሩ የቀኝ ዳኛ ወ/ሮ ሐረገውይን ተክሉ ተሰይመው የመጀመሪያ እና ሁለተኛውን ክስ ውድቅ አድርገው ሦስተኛው ክስ ደግሞ አንቀጽ ተቀይሮ እንዲከላከል በመወሰናቸው ከወህኒ ቤት በዋስ መፈታቱ ይታወሳል፡፡
ይሁንና፣ የፌደራል መንግሥት ዓቃቢ ሕግ ጋዜጠኛው ነፃ የተባለባቸው ከ15 ዓመት እስከ እድሜ ልክ እና ከ10 እስከ 15 ዓመት ከሚያስፈርዱበት ሁለት ክሶች “ነፃ መባል አልነበረበትም” በሚል ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት የይግባኝ ቅሬታውን አቅርቧል፡፡ ጋዜጠኛውም በጠበቃዎቹ በኩል ሲከራከር ቢቆይም ጉዳዩን እየመረመረው በነበረው በአቶ ሽምሱ ሲርጋጋ ሰብሳቢነት የሚመራው ችሎት ላይ “የዳኛ ይቀየርልኝ” ጥያቄ አቅርቦ ውድቅ ተደርጎበት ነበር፡፡
በወርሃ ሚያዚያ 2016 ዓ.ም ሦስቱም ዳኞች ተቀይረው በምትካቸው ሰብሳቢ የተከበሩ ዳኛ ምጽላል ኃይሌ እንዲሁም የተከበሩ ዳኛ ከበቡሽ ወርቁና የተከበሩ ዳኛ ኡመር መሐመድ የግራ እና ቀኝ ዳኛ ሆነው ተመድበዋል፡፡
ዛሬ ሐምሌ 23/2016 ዓ.ም በተከበሩ ዳኛ ምጽላል ኃይሌ ሰብሳቢነት የሚመራው ችሎት “የከፍተኛው ፍርድ ቤት ውሳኔ ትክክልና የሚነቀፍ ሆኖ ስላላገኘነው ጋዜጠኛው በነፃ እንዲሰናበት የተሰጠው ውሳኔ ጽንቷል” በሚል ፍርድ ሰጥተዋል፡፡
©️ይድነቃቸው ከበደ
@EventAddis1

📌"ሀገር በአንድ ሺህ ቀን" መጽሐፍ ምርቃት
"ሀገር በአንድ ሺህ ቀን" መጽሐፍ ነገ ይመረቃል።በወ/ሮ ፍሬዓለም ሽባባው “ሀገር በአንድ ሺህ ቀን” በሚል ርዕስ የተፃፈ አዲስ መጽሐፍ ነገ ሐሙስ ሐምሌ 25 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 9:ዐዐ ጀምሮ በኃይሌ ግራንድ ሆቴል ተጋባዥ እንግዶች በሚገኙበት ይመረቃል።በዕለቱም ገጣሚ ታገል ሰይፉ ፣ ጸሐፊ ተውኔት ዳግማዊ አመለወርቅ ፊይሳ ፣ ዶ/ር ይሁኔ አየለ ፣ ኪያኒ ተስፋዬ ማሞ ፣ ኢ/ሮ ቢጃይ ናይከር እና ሌሎችም ይገኛሉ ተብሏል።
መጽሐፉ የገፅ ብዛቱ 89 ሲሆን "የእኛ ቤት ኢትዮጵያ፥ከባንዲራው በታች፥ሰቆጣ ዴክለሬሽን" በሚሉ ሦስት ክፍሎች ተቀንብቦ ቀርቧል።

📌"ለእርቃን ሩብ ጉዳይ" መጽሐፍ ምርቃት
የደራሲ ሕይወት እምሻው "ለእርቃን ሩብ ጉዳይ" የተሰኘ አዲስ መጽሐፍ ነገ ሐሙስ ሐምሌ 25 2016 ዓ.ም ከምሽቱ 11:00 ጀምሮ አራት ኪሎ በሚገኘው ዋልያ መጻሕፍት መደብር ውስጥ ይመረቃል።
ሐያ ስምንት ታሪኮችን የያዘው አዲሱ መጽሐፏ በ208 ገፆች ተቀንብቦ በ300 ብር የጀርባ ዋጋ ለአንባቢያን ይቀርባል ተብሏል። ደራሲዋ ከዚህ ቀደም ባሪቾ ፣ ፍቅፍቂ ፣ ማታ ማታ የተሰኙ መጻሕፍትን ለንባብ አብቅታለች።

📌የኢቢኤስ ሲኒማ እና አርቲስት ፍቃዱ ከበደ ጉዳይ
የኢቢኤስ ሲኒማ ቻናል ጾታ አሳስቶ የጠየቀው ጥያቄ ዛሬ በሀገራችን ማህበራዊ ትስስር ገፆች መነጋገሪያ ሆኗል።
ኢቢኤስ ሲኒማ ለተመልካቾቹ በየዕለቱ በሚያቀርበው ጥያቄው የአርቲስት ፍቃዱ ከበደ ፎቶን በመጠቀም "የዚህችን ተዋናይት ሙሉ ስም እና ከሰራቸው ፊልሞች መካከል አንድ ጥቀስ ?" በማለት የጠየቀው ጥያቄ መነጋገሪያ ሆኗል።በዚህም ከአርቲስቱ ጋር ውዝግብ ውስጥ ገብተዋል።
አርቲስቱም በማህበራዊ ትስስር ገፁ " አንዳንድ ቴሌቪዥን ጣቢያዎች ነገር ፈልገዋችሁ ታዋቂ ለመሆን ሲሞክሩ አይገርምም?። በርግጥ ጉዳዩን ጠበቃዬ ይዞታል እኔ የ3 ልጆች አባት ፆታዬ ወንድ ኢትዮጵያዊ ነኝ። ከቴሌቪዥን ጣቢያው ጋር በቅርብ በጠረጴዛ ዙሪያ ውይይት የምናደርግ ይሆናል" ስለማለቱ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ተመልክቷል።

📌ሜንታል ሄልዝ አዲስ የሥነልቦና ውይይት
ወርሃዊው የሜንታል ሄልዝ አዲስ መርሃግብር ቅዳሜ ሐምሌ 27 ቀን 2016 ዓም አትላስ አካባቢ በሚገኘው በአዶር አዲስ ሆቴል ከቀኑ 10፡00 ጀምሮ ይካሄዳል::
የዚህ ወር ርዕስም፡- “የጭንቀት ስነልቦናዊ ትንታኔ” የሚል ሲሆን የዚህ ወር እንግዳ ዶ/ር አወቀ ምህረቱ ናቸው፡፡
ለመታደም ይህን መስፈንጠሪያ ይጫኑና ይመዝገቡ፡፡
https://forms.gle/bGmE6wXeZroTGrV86