Event Addis Media – Telegram
Event Addis Media
9.62K subscribers
6.13K photos
14 videos
4 files
4.75K links
Connect with Addis artistic community!

Website: https://eventaddis.com

Contact: @Tmanaye
Download Telegram
ተዋናይ ሚካኤል ሚሊዮን የተጋበዘበት  በፊልም አሰራር ጥበብ ላይ ሙያዊ ትንታኔ እና ተሞክሮዎቹን  የሚያካፈልበት መሰናዶ ዛሬ ይካሄዳል።

የተለያዩ ፊልሞችን፣ ቴአትሮችን፣የቴሌቪዥን ተከታታይ ድራማዎችን ፕሮዲዉስ በማድረግ በዝግጅት እና በትወና ላይ በመሳተፍ የሚታወቀው የፊልም ባለሙያ ሚካኤል ሚሊዮን ዛሬ ማክሰኞ  ሐምሌ 16 2016ዓ.ም አራት ኪሎ ኢክላስ ህንፃ ላይ በሚገኘው በልቀት ኮሌጅ ከቀኑ 11:30 ሰዓት ጀምሮ  በመገኘት በፊልም አሰራር ጥበብ ላይ ለተማሪዎች እና በዕለቱ ለሚታደሙ ታዳሚያን ሙያዊ ትንታኔ እና ሙያዊ ተሞክሮዎቹን እንደሚያካፍል ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ከኮሌጁ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

የዚህ የፊልም ሞያ ውይይት መሰናዶው መግቢያ በነፃ እና በሰዓቱ መገኘት ነው ተብሏል ።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
"ዘጠነኛው ሺ" ድራማ በአዲስ ምዕራፍ ሊጀምር ነው

በአብርሆት ኢንተርቴይመንት ተዘጋጅቶ በኢትዮጵያ ብሮደካስቲግ ኮርፖሬሽን የሚቀረበው "ዘጠነኛው ሺ" አስቂኝ የቴሌቪዥን ድራማ በአዲስ ምዕራፍ በቅርቡ እንደሚጀመር ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ሰምቷል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
"የማስረዳት ሸክም" መጽሐፍ ለንባብ በቃ

በህግ ባለሞያው እና ደራሲ ዳዊት በዛብህ የተዘጋጀው "የማስረዳት ሸክም" የተሰኘ መጽሐፍ ከሰሞኑ ለንባብ እንደበቃ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ሰምቷል።

"የማስረዳት ሸክም" የአመክንዮ ሳይንስ (Logic) ፣ ሥነእውቀት (epistemology) እና የማስረጃ እና የሥነሥርዓት ሕግ ላይ ያተኮረ  መጽሐፍ ነው።

ጸሐፊው "የሀገራችን ችግር ለመወያየት እና ለመከራከር ፍላጎት ከማጣትም በላይ መሠረታዊ የሙግት መርሆዎችን ከሕግና ፍልስፍና አንጻር ያለመረዳት ነው። ተሟጋች ማህበረሰብ (Litigant society) ቢኖረንም እውነት እና እውቀትን ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ የመረዳት ችግር አለብን። ይህንንም መሰረታዊ የሙግት ችግር ለመፈታትና መንገድ ለማመላከት የተጻፈ መጽሐፍ ነው"ብሏል።

"የማስረዳት ሸክም" መጽሐፍ በሰባት ምዕራፍ  የተከፈለ ሲሆን በ225 ገፆች የተቀነበበ መጽሐፍ ነው።

በ400 የጀርባ ዋጋ ለአንባቢያን ቀርቧል።በጃፋር፣ሀሁ እና እነሆ መጻሕፍት መደብሮችም ይገኛል ተብሏል።

የህግ ባለሞያው እና ደራሲ ዳዊት በዛብህ አስቀድሞ የሕግ ፍልስፍና፣ ኢትዮጵያ ሥነ ሕግ የተሰኙ መጻሕፍትን ለአንባቢያን አድርሷል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
1
📍 የሥነጽሑፍ ውይይት

የጁፒተር ብራና የንባብ ክበብ አባላት በአንጋፋው ደራሲ ፍቅርማርቆስ ደስታ "የሚሳም ተራራ" መጽሐፍ ላይ ሐምሌ 20 2016 ዓ.ም  ከቀኑ 9:45 እስከ 12:00 በጁፒተር ሆቴል ውስጥ ሥነጽሑፋዊ ውይይት ያካሄዳሉ።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
ሙዚቀኛ ያምሉ ሞላ እና ወጣቷ ድምጻዊት መና ወረደ በጋራ የተሰሩት ገሚስ አልበም ዛሬ ይመረቃል 

ሙዚቀኛ ያምሉ ሞላ እና ወጣቷ ድምጻዊት መና ወረደ በጋራ የተሰሩት "አዲስ ቀለም" የተሰኘ ገሚስ አልበም ዛሬ ሐምሌ 18 2016 ዓ.ም አመሻሽ ላይ ቦሌ ዓለም ሲኒማ አካባቢ በሚገኘው "The Jungle" ውስጥ እንደሚመረቅ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ከሙዚቀኛ ያምሉ ሞላ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።የዚህ ገሚስ አልበም ምርቃት መግቢያ በነፃ ተብሏል።

"አዲስ ቀለም" ገሚስ አልበም በውስጡ ምንድነው ፣ ኤሌክትሪክ፣ ማዕዘን፣ተው ተው፣አንድ ሰሞን የተሰኙ አምስት ሙዚቃዎችን የያዘ እንደሆነ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ተመልክቷል።

የገሚስ አልበሙ ግጥም ፣ ዜማ፣ እንዲሁም ከሙዚቃው ቅንብር እስከ ማስተሪንጉ ድረስ በያምሉ ሞላ ተሰርቷል።

በተጨማሪም በከበሮ አገረሰላም ሻፊ ፣ በመሰንቆ ሀዲንቆ፣በክራራ ፋሲካ ኃይሉ ተሳትፈዋል።

"አዲስ ቀለም" የተሰኘ ርዕስ የተሰጠውና የሙዚቃ አቀናባሪው ያምሉ ሞላ እና ወጣቷ ድምጻዊት መና ወረደ የተጣምሩበት ገሚስ(EP) የሙዚቃ አልበም በዩቲዩብ እና ስፖቲፋይ መተግበሪያዎች በኩል ባሳለፍነው አርብ እንደተለቀቀ ይታወሳል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
"ጥቁር አደይ" ፊልም በሲኒማ ቤት ሊታይ ነው

"ጥቁር  አደይ" ፊልም ለተወሰነ ጊዜ ከነገ ሐምሌ 19 2016 ዓ.ም ጀምሮ  ቦሌ በሚገኘው ዓለም ሲኒማ ብቻ ለእይታ ሊቀርብ እንደሆነ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

"ፊልሙ በተለያዩ ዓለም አቀፍ የፊልም ሽልማቶች ላይ እጩ ሆኖ እንዲቀረብ የግድ ሲኒማ ቤት መታየት አለበት።ስለዚህም ከሐምሌ 19 2016 ዓ.ም  ጀምሮ በዓለም ሲኒማ ብቻ ለተወሰነ ጊዜ ለእይታ ይበቃል"ሲል ተዋናይ ነብዩ እንድሪስ ለኤቨንት አዲስ ድረገፅ ተናግሯል።

በፊልሙ ላይ ኤደን አይሸሹም፣ካሣሁን ፍስሐ (ማንዴላ)፣ናታን ጌታቸው፣ነቢዩ እንድሪስን ጨምሮ ከ186 በላይ ተዋናያን ተሳትፈውበታል።

"ጥቁር አደይ" ፊልም አንድ ሰዓት ከሐምሳ ደቂቃ ረዝመት ያለው ሲሆን ከ6.7 ሚሊየን ብር በላይ ውጪ እንደወጣበት ተነግሯል።ሦስት ዓመታትን የፈጀው ፊልሙ 1 ሰዓት ከ51 ደቂቃ ርዝመት ያለው ነው ተብሏል።

ፊልሙ ከአገር ውጪ እንደተመለሰ በኔትፍሊክስ እና አፕል የፊልም መተግበሪያዎች እንደሚሰራጭ አዘጋጆቹ  አስታውቀዋል።

በደራሲ እና ዳይሬክተር ፍፁም ካሣሁን የተሰራው "ጥቁር አደይ" ፊልም ሐምሌ 10 2016 ዓ.ም በሸራተን አዲስ ሆቴል ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ተመርቋል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌የይስማዕከ ወርቁ አዲስ መጽሐፍ ለንባብ ሊበቃ ነው

"ዲርቶጋዳ"ን ጨምሮ በበርካታ መጻሕፍቱ የምናውቀው  ደራሲ ይስማዕከ ወርቁ "ቀኑም አይመሽልኝም" የሚል ርዕስ የተጻፈ አዲስ መጽሐፍ በቅርቡ ለንባብ እንደሚበቃ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ከደራሲው ያገኘው መረጀ ያመለከታል።

ደራሲው በማህበራዊ ትስስርና ገፁ "ጋሽ ስብሐት(ደራሲ ስብሃት ገ/እግዚአብሔር) በህይዎት ሳለ አንድ ቀን "ሌቱም አይነጋልኝን" የመሰለ ልቦለድ ፅፈሀል። ዙሩ እንዲሞላ ለምን "ቀኑም አይመሽልኝ" ብለህ አትጽፍም? አልኩት ለጋሽ ስብሀት።  አንተ እንደምትለው እኮ በወዘተርፈ የሚኖሩ ማለትም ቀኑ የማይመሽላቸው ሰዎች አሉ። ብዙ ሰዎች በወዘተርፈ ነው የሚኖሩት ስለው። "

"ጥሩ ሀሳብ ነው። ግን እኔ አልጽፈውም። ስለዚህ አንተ እየጻፍክ አምጣውና እንወያይበት" አለኝ።በዛ ጊዜ የዩኒቨርስቲ ተማሪ ነበርኩና በየወሩ ብዙ ምዕራፍ እየያዝኩ እሄዳለሁ። አነብለታለሁ። ያርመኛል። ሳልጨርሰው ሞት ቀደመው ከዛ በኃላ ጊዜ ፈጀብኝ"ሲል ጽፏል።

መጽሐፉ ግን መቼ ለንባብ እንደሚበቃ ቀን እንዳልተቆረጠለት ተገልጿል።

ደራሲው ከአንድ ዓመት በፊትም " ግፉአን " የተሰኘ መጽሐፍ ለአንባቢያን ማድረሱ ይታወሳል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌የፎቶ ኤግዚቢሽን ዛሬ ለእይታ ይበቃል

ቴክኖ ካሞን 30 ፕሮ 5G ከቦርድ ሴልፎን ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ያዘጋጀው የፎቶ ኤግዚቢሽን ዛሬ ከቀኑ 9 ሰዓት ጀምሮ ኤድና ሞል ፊት ለፊት በሚገኘው ቤስት ዌስተርን ፕላስ ሆቴል ውስጥ ለእይታ ይበቃል።

ይህ የፎቶግራፍ አውደርዕይ ከሀምሌ 19 እስከ 21 2016 ዓ.ም ለህዝብ እይታ ክፍት ሆኖ ይቆያል።

በዚህ አውደርዕይ ላይ መሰረታዊ የSmart Phone ፎቶግራፊ ስልጠና ቅዳሜ ሐምሌ 20 2016 ዓ.ም ከቀኑ  8:00 ጀምሮ በፎቶግራፍ ባለሞያው  እዮብ ቤዛነህ ይሰጣል ተብሏል።

የዚህ አውደርዕይ መግቢያ በነፃ ነው።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
በእረፍት ቀንዎ ቴአትር ይመለከቱ !

አንጋፋው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር  እና የቦሌው ዓለም ሲኒማ አርብ፣ ቅዳሜ እና እሁድ እነዚህን ተውኔቶች ለታዳሚያን ያቀርባሉ።

📍 የፍቅር ካቴና

ድርሰትና ዝግጅት: አለልኝ መኳንት ፅጌ
ቀን: አርብ
ሰዓት: 12:00
ቦታ: ዓለም ሲኒማ

📍 "እሳት ወይ አበባ"

ድርሰት: ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን እንደጻፈው
ዳንስና ዳንስ ቅንብር: ሽፈራው ታሪኩ ቢረጋ
ቀን: አርብ
ሰዓት:11:30
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር

📍 ባሎች እና ሚስቶች

ድርሰት: ውዱ አለን
አዘጋጅ: ሳሙኤል ተስፋዬ
ቀን: ቅዳሜ
ሰዓት: 8:00
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር

📍 ባቡሩ

ድርሰት: አርኖልድ ሪድሊ
አዘጋጅ:ራሔል ተሾመ መሐመድ
ቀን: ቅዳሜ
ሰዓት:11:30
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር

📍 ሸምጋይ

ድርሰት:ታደለ አያሌው
አዘጋጅ: ሳሙኤል ተስፋዬ
ቀን: እሁድ
ሰዓት: 8:00
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር

📍 እምዩ ብረቷ

ድርሰት: ቤልቶልት ብሬሽት
አዘጋጅ: ማንያዘዋል እንዳሻው
ቀን: እሁድ
ሰዓት:11:30
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር

የእናንተው ኤቨንት አዲስ ድረገፅ መልካም የእረፍት ቀን ይሁንላችሁ ይላል !

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌በእረፍት ቀንዎ ፊልም ይመልከቱ !

እነዚህ አራት የፊልም ማሳያዎች(ሲኒማ ቤቶች) ዛሬን ጨምሮ በሳምንቱ መጨረሻ ቀናት እነዚህን ፊልሞች ለተመልካቾች ያቀርባሉ: ምስሎቹን ይመልከቱ።

የሲኒማ ቤቶቹ አድራሻ:

✔️ሲኤምሲ ሚካኤል አካባቢ : ጋስት ሲኒማ

✔️ለም ሆቴል አካባቢ: ቫምዳስ ሲኒማ

✔️ጉርድ ሾላ አካባቢ : ሴንቸሪ ሲኒማ

✔️ቦሌ አካባቢ : ዓለም ሲኒማ

መልካም የእረፍት ቀናት ይሁንላችሁ !

https://news.1rj.ru/str/EventAddis1

https://news.1rj.ru/str/EventAddis1

ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌 የደራሲ ሌሊሣ ግርማ "ደማቆቹ” አዲስ መፅሐፍ ለንባብ በቃ

የደራሲ ሌሊሣ ግርማ "ደመቆቹ" የተሰኘ የትርጉም መጽሐፍ ዛሬ ሐምሌ 19 2016 ዓ.ም ለንባብ እንደበቃ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

ይህ የትርጉም መጽሐፍ በዓለም ዙሪያ እና በዘመን መካከል ብቅ ካሉ እንደ እነ አንቷን ቼኮቭ፣ ኧርነስት ሄሚንግዌይ፣ ፍራንዝ ካፍካ፣ ገብሬል ጋርሻ ማርኩዌዝ፣  ናጂብ ማህፉዝ፣ ማርጋሬት አትዉድ፣ ሼርውድ አንደርሰን፣ ዊልያም ሳሮያን፣ ሳኪ፣ ሶመርሴት ሞም፣  ፍራንክ አር እስቶክተን፣ አየን ራንድ፣ ያሉ ምርጥ ጸሐፊያን ውስጥ ስመ ጥር  የሆኑ አጫጭር ታሪኮች ስብስብ እንደሆነ ተነግሯል።

ደራሲ ሌሊሣ ግርማ ከዚህ ቀደም በግሉ የንፋስ ሕልም እና ሌሎችም አጫጭር ታሪኮች ፣ አፍሮጋዳ ፣ መሬት - አየር - ሰማይ ፣ የሰከረ እውነታ፣ እስቲ ሙዚቃ፣ ነፀብራቅ እና ይመስላል ዘላለም የተሰኙ መጻሕፍትን ለአንባቢያን አድርሷል።

የመጽሐፉ ዋና አከፋፋይ ጃፋር መፅሀፍት መደብር ነው። ዴሊቨር እንዲደረግላችሁ የምትፈልጉ በዚህ  t.me/Demakochu1 ማዘዝ ትችላላችሁ ተብላችኋል።

ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌ላይፍ ሴንተር ኢትዮጵያ ከአጋሩ ሆራይዘን ኢንተርናሽናል ጋር በመተባበር ለልጃገረዶች ስልጠና ሰጠ

ላይፍ ሴንተር ኢትዮጵያ የበጎ አድራጎት ድርጅት ከአጋሩ ሆራይዘን ኢንተርናሽናል ጋር በመተባበር ከ15  ዓመት በላይ ለሚሆናቸው ልጃገረዶች ስልጠና እና ልምድ የማካፈል መርሐግብርን ሐምሌ 19 2016 ዓ.ም አካሂዷል።

የስልጠናው ዋና ሀሳብም "ልጃገረዶች በህይወታቸው ላይ ትክክለኛ ውሳኔን እንዲወሰኑ እና ውሳኔያቸው ጤናማ እንዲሆን ማገዝ " እንደሆነ የላይፍ ሴንተር ኢትዮጵያ መስራች ወ/ሮ  ሙሉ ግርማይ ተናግረዋል።

በዚህ የስልጠና እና ልምምድ ማካፈል መርሐግብር ላይ ከሀምሳ በላይ ልጃገረዶች ተሳትፈዋል።

በመርሐግብሩ ላይ የኪነጥበብ ባለሞያዋ ኮሜዲያን ቤተልሔም ጌታቸው (ቤት ዋኖስ) ያለፈችበትን የህይወት ልምዷን ለልጃገረዶቹ አካፍላለች።

የበጎ አድራጎት ድርጅቱ በትላንትናው ዕለትም ለወጣት ወንዶች በተመሳሳይ የህይወት ክህሎት ላይ ያተኮረ ስልጠና እና የልምድ ልውውጥ መርሐግብር አካሄዷል።

11 ዓመታትን ያስቆጠረው ድርጅቱ "የአንድ ሺ ማይል ጉዞ በአንድ እርምጃ ይጀምራል” እንዲሉ በጥቂት ህጻናት ብቻ የጀመሩት የስፖንሰርሺፕ እርዳታ ፕሮግራም አሁን ከ300 የሚበልጡ ወላጅ አልባ ህፃናትን የተመጣጠነ ምግብ፣ ልብስ፣ የትምህርት መርጃ መሳሪያዎችንና የመሳሰሉትን እያቀረበ የህይወት ክህሎት ስልጠና እና የምክር አገልግሎት እየሰጠ መልካም ዜጋን ለማፍራት አስተዋፅኦ እያደረገ ያለ ድርጅት ነው::

ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌"ስብሐቲዝም" ኪናዊ ውይይት እሁድ ይካሄዳል

ሐሳብ፣ ንባብ፣የውይይት መንገድ ላይ ትኩረቱን ያደረገው "ስብሐቲዝም" ኪናዊ ውይይት 70ኛ ዙር መድረክ ነገ እሁድ ሐምሌ 21 2016 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ጀምሮ በብሔራዊ ቤተመዛግብት እና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት (ወመዘክር) አዳራሽ ውስጥ ይካሄዳል ።

በዚህኛውም ዙር መድረክ "ጂጂን ስናስታውስ " በሚል ርዕስ በድምጻዊት እጅግአየሁ ሽባባው (ጂጂ) ላይ ያተኮረ ውይይት ይካሄዳል።

አዘጋጆቹም"እጅጋየሁ ሽባባው በላቀ የሙዚቃ ስራዋ የክብር ዶክትሬት ከተቀበለች ወርሃ ሐምሌ 1 ዓመት ሞላው። እኛም በክብር እናስታውሳታለን።ጂጂን በልኳ ከሚነግሩን እጅግ ጥቂቶች አንዱ ጋዜጠኛ ጥበቡ በለጠ ነው፤ ከሌሎች እንግዶች ጋር ተገኝቶ ስለጂጂ ያወሳናል"ብለዋል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌የደራሲ ሄኖክ በቀለ አዲስ መጽሐፍ ለንባብ በቃ

ከዚህ ቀደም "ሀገር ያጣ ሞት" በተሰኘው የልቦለድ መጽሐፉ የምናውቀው ደራሲ ሄኖክ በቀለ "ይናፍቀኛል" የተሰኘ የግጥም ስብስቦች መጽሐፍ ዛሬ ሐምሌ 20 2016 ዓ.ም ለአንባቢያን አቅርቧል።

"ይናፍቀኛል" የተሰኘው የግጥም መጽሐፉ 88 የግጥም ስብስቦችን የያዘ ሲሆን በ128 ገፆች ተቀንብቦ በ300 ብር የጀርባ ዋጋ ለንባብ በቅቷል።

መጽሐፉን ለማዘዝ የምትፈልጉ ከሆነ በዚህኛው የቴሌግራም አድራሻ https://news.1rj.ru/str/ynafkegnal ማዘዝ እንደምትችሉ ተገልጿል።

ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌የደራሲ እንዳለጌታ ከበደ አዲስ መጽሐፍ

የደራሲ እንዳለጌታ ከበደ " ሲ ጥ ል" የተሰኘ ረጅም ልቦለድ አዲስ መጽሐፍ ሐምሌ 27 2016 ዓ.ም ለንባብ እንደሚበቃ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ከደራሲው ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

ደራሲ እንዳለጌታ ከበደ በማህበራዊ ትስስር ገጹ የሚከተለውን ብሏል"ሲ ጥ ል" የተሰኘ ረጅም ልቦለዴን ከሐምሌ 27/2016 ጀምሮ ገበያ ላይ ይውላል::

አሳታሚው ዋልያ መጻሕፍት ሲሆን በመጽሐፉ ጀርባም የሚከተለው  ጽሁፍ ሰፍሮበታል::

ከዚህ ቀደም፣ ‹ዛጎል›፣ ‹ደርሶ መልስ›፣ ‹እምቢታ (የቃቄ ወርድወት)›  እና ‹ምሳሌ› በተሰኙ ረጃጅም ልቦለዶቹ የምታውቁት፤ በጭብጥ አመራረጡና በአጻጻፍ ስልቱ የተወዳጃችሁት እንዳለጌታ ከበደ፣  አሁን ደግሞ ‹ሲጥል› የተሰኘ ልቦለድ አበርክቶልናል፡፡
 
‹ሲጥል›  የመንገደኞች ታሪክ ነው፤ መንገደኞቹ  ለየጉዳዮቻቸው ከቤታቸው ወጥተው አንድ ላይ ቢሳፈሩም፣ በአንድ ባልታሰበ ሰበብ  አብረው የሚሰነብቱበት አጋጣሚ ይፈጠራል፡፡ መንገደኞቹ፣ የየራሳቸው የሕይወት ፍልስፍና እና መርሆ  ያላቸው ናቸው፡፡ እናም፣  በረገጡት ሥፍራ እንግዳ የሚሆኑት እነሱ ብቻ አይሆኑም  - ሃሳቦቻቸውም ጭምር እንጂ፡፡" 

" ‹ሲጥል› እንደ ከዚህ ቀደም የእንዳለጌታ መጻሕፍት ከራሳችን ጋር የሚያጨዋውቱ፣ ለሙግትም የሚጋብዙ ሃሳቦች የተስተናገዱበት ኪናዊ ማዕድ ነው፡፡  የድኅረ ዘመናዊ ደራስያንን የአጻጻፍ መንገድ  በከፊል ተከትሎ፣  የትረካ ስልቱን ደግሞ እንደ ጃዝ ሙዚቃ  አድርጎታል፡፡"
 
ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌ሪፍት ቫሊ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቹን አስመረቀ

ሪፍት ቫሊ ዩኒቨርሲቲ በቴክኒክና ሙያ፣ በመጀመሪያ ዲግሪና በሁለተኛ ዲግሪ ያሰለጠናቸውን ከ9,200 በላይ ተማሪዎችን ዛሬ ሐምሌ 20 2016 ዓ.ም አስመርቋል።

ዛሬ በሚሊኒየም አዳራሽ የተመረቁት ተማሪዎች በአዲስ አበባና የሸገር ከተማ በሚገኙ 17 የዩንቨርቲው ካምፓሶች  በጤና፤በቢዝነስና በማህበራዊ ሳይንስ፣በቴክኖሎጂ  በቴክኒክና ሙያ፣ በመጀመሪያ ዲግሪና በሁለተኛ ዲግሪ ሲማሩ የነበሩ ናቸው ተብሏል።

በምርቃት ሥነሥርዓቱም ላይ የሪፍት ቫሊ ዩኒቨርሲቲ ባለቤትና ሥራ አስኪያጅ አቶ ድንቁ ደያሳ ፣በኢፌዲሪ የትምህርት ሚኒስተር እና የትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን ከፍተኛ የበላይ የሥራ ኃላፊዎችን ፣የክብር እንግዶች፣ የተመራቂ ቤተሰቦች ተገኝተዋል።

ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1‌‌
📌“ናዋዥ” የተሰኘ አዲስ መፅሐፍ ለንባብ በቃ

በደራሲ እያዩ ዳኛው የተሰናዳውና “ናዋዥ” የተሰኘው አዲስ የግለ ታሪክ መፅሐፍ ሰሞኑን ለንባብ በቃ፡፡ መፅሐፉ በዋናነት በደራሲው የግል ህይወት ላይ የሚያጠነጥን ቢሆንም፤ ኢትዮጵያዊያን በሱዳንና በሊቢያ በኩል ወደ አውሮፓ ለመግባት የሚያደርጉትን አስከፊና አስቸጋሪ የስደት ህይወት የሚያሳይ ነው ተብሏል፡፡

ነዋሪነቱን በጀርመን ያደረገው ደራሲ እያዩ ዳኛው፤ መፅሐፉ ከደቡብ ጎንደር ክምር ድንጋይ እስከ ጣሊያን የወደብ ከተማ ትራፓኒ የዘለቀውን የስደትና የውጣ ውረድ ጉዞ የሚዳስስ መሆኑን ለአዲስ አድማስ ተናግሯል፡፡

“ናዋዥ”፤ደራሲው ልጅነቱን የአፍላ ወጣትነቱን፣ የኢትዮጵያውያንን የስደት ኑሮ፣ በሱዳንና በሰሃራ በረሃ ለማቋረጥ ስደተኞች የሚከፍሉትን መስዋዕትነት እንዲሁም በመንግሥት አልባዋ ሊቢያ የነበረውን ኑሮና በሜድትራንያን ባህር የሚያጋጥምን ፈተና ያስቃኛል፡፡

በ470 ገፅ የተቀነበበው “ናዋዥ”፤ የግለ ታሪክ መፅሐፍ በ500 ብር ለገበያ ቀርቧል፡፡

📍መረጃው የአዲስ አድማስ ጋዜጣ ነው

ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌 " አዎ ነቢይ በሀገሩ ይከበራል ! "

በቅርቡ በአጸደ ስጋ የተለየውን ሁለገቡ እና አንጋፋውን ከያኒ ነቢይ መኮንንን ለማክበር ዛሬ ሐምሌ 22 2016 ዓ.ም ልዩ ዝግጅት ተሰናድቷል።

የነቢይ ወዳጆች ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ጋር በመተባበር ያዘጋጁት ይህ መርሐግብር ዛሬ ሰኞ ሐምሌ 22 ቀን  2016 ዓ.ም ከ11:00 ሰዓት ጀምሮ በኢትዮጵያ ብሔራዊ አዳራሽ ይካሄዳል።

በዚህ "አዎን ነቢይ በሀገሩ ይከበራል!" በተሰኘ የክብር ማስታወሻ ዝግጅት ላይ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ሁላችሁም ተጋብዛችኋል።

ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1