Event Addis Media – Telegram
Event Addis Media
9.62K subscribers
6.12K photos
14 videos
4 files
4.75K links
Connect with Addis artistic community!

Website: https://eventaddis.com

Contact: @Tmanaye
Download Telegram
📌አፍታ ሜይራ ግሩፕ ከብራይት ጋር 25/75 የብድር አቅርቦት በጋራ ለመስራት ተፈራረሙ::

በአፍታ ሜይራ ግሩፕ ስር የሚገኘው አፍታ ሜይራ ሪል ስቴት በዘመናዊ ቴክኖሎጂ በማስገንባት ላይ የሚገኘውን ዘመናዊ ቤቶችን ለቤት ፈላጊው እጅግ ተመጣጣኝ በሆነ ዋጋ እያቀረበ ይገኛል።

በመሆኑም ብራይት የፋይናንስ ተቋም ለቤት ፈላጊዎች ከብድር ጋር በተያያዘ  የፋይናንስ ድጋፍ ለማድረግ በቀጣይም አብረው የሚሰሩባቸውን ዝርዝር ጉዳዮች ላይ የጋራ ውል ስምምነት ፈፅመዋል በቅርቡም ሚድያዎች በተገኙበት የጋራ መግለጫ እንደሚሰጡ አሳውቀዋል።

አፍታ ሜይራ ሪል ስቴት የቤት ችግርን ዘመኑን በሚመጥን ተፈጥሯዊ ውበት የተላበሱ ቤቶችን በዓለማቀፉ SAGA እና FOG የዲዛይን ንድፍ ሐሳብ በመገንባት እና በመሸጥም ላይ ይገኛል።

በሐምሌ 26 2016 ዓ.ም በተለይ ለሀገራችን የቤት ፈላጊውን እና የፋይናንስ ፍላጎትን ለመፍታት ታሳቢ ያደረገ ስምምነት ነው።

ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌የደራሲ በኃይሉ ሙሉጌታ አዲስ መጽሐፍ

የደራሲ በኃይሉ ሙሉጌታ "ሁለተኛው ዕትብት" የተሰኘ የልቦለድ መጽሐፍ ለንባብ እንደበቃ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ሰምቷል።መጽሐፉ በዋናነት "አባት መጥላት" ፣ "አባት ማምለክ" እና "አባት ማጣት" የተሰኙ ሶስት ክፍሎችን በውስጡ የያዘ የልቦለድ መጽሐፍ ነው።

"ሁለተኛው ዕትብት" መጽሐፍ በ215 ገፆች ተቀንብቦ በ350 ብር የጀርባ ዋጋ ለአንባቢያን ቀርቧል።

መጽሐፉን ጃፋር መጽሐፍ መደብርን ጨምሮ በተለያዩ መጻህፍት መደብሮች ይገኛል ተብሏል።

ደራሲ በኃይሉ ሙሉጌታ ከዚህ ቀደም "ቤተልሔም" መጽሐፍ እና "ጥላ" የግጥም ሲዲ ለአንባቢያን እና አድማጮች አድርሷል።

ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌የፕ/ር ጌታቸው ኃይሌ "ባሕረ ሐሳብ" መጽሐፍ

የፕ/ር ጌታቸው ኃይሌ "ባሕረ ሐሳብ" የተሰኘ መጽሐፍ በድጋሚ ታትሞ ለንባብ ቀረበ

የፕ/ር ጌታቸው ኃይሌ "ባሕረ ሐሳብ: የዘመን ቁጠራ ቅርሳችን ከታሪክ ማስታወሻ ጋራ" የተሰኘ መጽሐፍ በድጋሚ ታትሞ ለአንባቢያን ቀርቧል። መጽሐፉን በብራና መጻሕፍት መደብር  ማግኘት ትችላላችሁ ተብላችኋል።

ብራና መጻሕፍት መደብር 5 ኪሎ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፊት ለፊት ማኅበረ ቅዱሳን ዋናው ሕንፃ ሥር ይገኛል፡፡

ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌የደራሲ እንዳለጌታ ከበደ መጽሐፍ ለንባብ በቃ

የደራሲ እንዳለጌታ ከበደ " ሲ ጥ ል" የተሰኘ ረጅም ልቦለድ መጽሐፍ ዛሬ ለንባብ እንደበቃ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ  ያገኘው መረጃ ያመለክታል።መጽሐፉን ዋልያ መጻሕፍት መደብርን ጨምሮ በተለያዩ መጻሕፍት መደብሮች ይገኛል።

በመጽሐፉ ጀርባም የሚከተለው  ጽሁፍ ሰፍሮበታል:: "ከዚህ ቀደም፣ ‹ዛጎል›፣ ‹ደርሶ መልስ›፣ ‹እምቢታ (የቃቄ ወርድወት)›  እና ‹ምሳሌ› በተሰኙ ረጃጅም ልቦለዶቹ የምታውቁት፤ በጭብጥ አመራረጡና በአጻጻፍ ስልቱ የተወዳጃችሁት እንዳለጌታ ከበደ፣  አሁን ደግሞ ‹ሲጥል› የተሰኘ ልቦለድ አበርክቶልናል፡፡
 
‹ሲጥል›  የመንገደኞች ታሪክ ነው፤ መንገደኞቹ  ለየጉዳዮቻቸው ከቤታቸው ወጥተው አንድ ላይ ቢሳፈሩም፣ በአንድ ባልታሰበ ሰበብ  አብረው የሚሰነብቱበት አጋጣሚ ይፈጠራል፡፡ መንገደኞቹ፣ የየራሳቸው የሕይወት ፍልስፍና እና መርሆ  ያላቸው ናቸው፡፡ እናም፣  በረገጡት ሥፍራ እንግዳ የሚሆኑት እነሱ ብቻ አይሆኑም - ሃሳቦቻቸውም ጭምር እንጂ፡፡" 

" ‹ሲጥል› እንደ ከዚህ ቀደም የእንዳለጌታ መጻሕፍት ከራሳችን ጋር የሚያጨዋውቱ፣ ለሙግትም የሚጋብዙ ሃሳቦች የተስተናገዱበት ኪናዊ ማዕድ ነው፡፡  የድኅረ ዘመናዊ ደራስያንን የአጻጻፍ መንገድ  በከፊል ተከትሎ፣  የትረካ ስልቱን ደግሞ እንደ ጃዝ ሙዚቃ  አድርጎታል፡፡"
 
ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌የተጓዡ ጋዜጠኛ ሔኖክ ስዩም አዲስ መጽሐፍ

የተጓዡ ጋዜጠኛ ሔኖክ ስዩም "መንገድ ዓይኑ ይፍሰስ" የተሰኘ አዲስ መጽሐፍ ለንባብ በቅቷል። መጽሐፉ ጃፋርን ጨምሮ በተለያዩ  መጻሕፍት መደብሮች ይገኛል።

ተጓዡ ጋዜጠኛ በማህበራዊ ትስስር ገፁም "እነሆ አዲሱ መጽሐፌ "እንካችሁ መጽሐፍ" ብዬ "አምጣው" ለማለት ላላመነታችሁ አንባቢዎቼ የምስራች አለኝ። ፈጣሪ ምስጋና ይግባው። "መንገድ ዓይኑ ይፍሰስ..." ያልኩት አዲሱ ስራዬ ገበያ ላይ ውሏል። በጃአፈር እና በሌሎች መጻሕፍት መደብሮች ታገኙታላችሁ። ከቀናት በኋላ እንደ እኔ ወደ ሁሉም የኢትዮጵያ ምድር ይደርሳል" ብሏል።

ስለመጽሐፉም" ስለምታነቡልኝ ወልዶ የተሳመልኝ ነኝና ደስታዬ ወደር የለውም። እንግዲህ ከኮንሶ ጥበብ ጋር ተገናኙበት። ወደ ጌዴኦ የተፈጥሮ ምስጢር ቅረቡ። የላስታን ሌላ ገፅ ታዩበታላችሁ። አናጂና ያየሁትን ከአነበብኩት አዋድጄ የምትወዱት እንዲሆን ጥሬያለሁ። ለዚያች ሙሽራ ከተማ ለጎንደር መልኳን ደርሼ "መልከአ ጎንደር" የዚህ መጽሐፍ አካል ኾኗል። መልከአ ግዮንን ስለመጻፍ አስብ ነበር ግን ተቀድሜያለሁ። ያም ሆኖ "መልከአ ጣና" እንዴት እንዲህ ተፃፈልኝ! ለእኔም እንቆቅልሽ ነው። የኢትዮጵያ ነቢይ ምን ሊል ፈልጎ ይኾን? ይሄ ነገር ሳይቀጥል አይቀርም። የአንድ ጉራጌ ቤት የዓለምን ያኽል ሰፊ እንደኾነ የተረዳሁት ማፌድ ስከርም ነው። እሱም አለ....ሌላም ሌላም....ታዲያ መንገድ ለምን ዐይኑ ይፍሰስ?መንገድ ዓይኑ ይፍሰስ"በማለት ሀሳቡን አስፈሯል።

ሃያ አራት ርዕሰጉዳዮችን በ172 ገጾች የሚያነሳሳው ይህ መጽሐፍ  ጃፋርን ጨምሮ በተለያዩ  መጻሕፍት መደብሮች ይገኛል ተብሏል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌"ብላቴናት" የልጆች መጽሔት ተመረቀ

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት የነገ ሃገር ተረካቢዎችን ማነጽ ያስችላል ያለዉን "ብላቴናት" የልጆች መጽሔት ይፋ አድርጓል። ዛሬ ለምረቃ የበቃችው "ብላቴናት" የተሰኘችዉ የልጆች መጽሄት ባለ 40 ገጽ እና ባለ ሙሉ ቀለም ህትመት ያላት ወራዊ መጽሄት ነች።

በዋናነት በሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ፣ ባህልና ታሪክ፣ ተፈጥሮ፣ ማህበራዊና ሌሎች ጉዳዮች የተካተቱባት ነች።የአምዶቿ ስያሜ የልጆችን ስነ ልቦና፣ግብረ ገብነት፣ኢትዮጵያዊነት፣አብሮነት ፣አሳታፊነትን ታሳቢ ያደረገ ነዉ።

በኢ-ልቦለዳዊና በልቦለዳዊ ይዘቶች እያዝናናች የልጆችን ስነ መግባር የምታንጽ ፣የንባብ ልምድን የምታዳብር እንዲሁም ልጆችን ከሳይንስና ጋር የምታስተዋዉቅ መጽሄት ነች። ከ3 እስከ 6፣ከ7 እስከ 9 እና ከ 9 ዓመት በላይ አመት የሚገኙ ልጆች የመጽሄቷ ዋና ታላሚ አንባቢያን ናቸዉ ።

ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌የአስቴር አወቀ ኮንሰርት በመጨረሻው ሰዓት ተሰረዘ

በአውሮፓ የኢትዮጵያ ስፖርትና ባህል ፌደሬሽን አማካኝነት የሚዘጋጀው የ2024 አመታዊ እግር ኳስ ውድድር ከጁላይ 30 እስከ ኦገስት 3 ድረስ ተካሂዷል።

የዝግጅታችን መዝጊያ የአስቴር አወቀ ኮንሰርት በተፈጠረው የአዳራሽ ሳውንድ ችግር ምክንያት ለመሰረዝ ተገዷል።

በተፈጠረው ችግር ፌዴሬሽናችን የተሰማውን ሀዘንሽገልጾ ሲሆን ትኬቱን ቀደም ብለው የገዛሁ ተሳታፊዎች በሙሉ ወጭያችሁ ተመላሽ እንደሚያደርግ አስታውቋል።

በአውሮፓ የኢትዮጵያ ስፖርትና ባህል ፌደሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ አሳዬ ጥላሁን ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን እንደተናገሩት ዓመታዊ የእግር ኳስ ውድድሩ እና ባህላዊ ፌስቲቫሉ በድምቀት ቢካሄድም በመዝጊያው ቀን ባጋጠመው የቴክኒክ ችግር ኮንሰርቱ ተሰርዟል።

ፌዴሬሽኑ በዋናነንት በስፖርቱ ላይ የሚሰራ ሲሆን የኮንሰርቱን ስራ ለፕሮሞተሮች ሰጥቷል። ኃላፊነቱን የወሰደው ሰው በፈጠረው ሰዋዊ ችግር የተነሳ ኮንሰርቱ ተሰርዟል።

ከሙያ ባልደረቦቿ ጋር ውይይት በማድረግ ድምፃዊቷን በፌዴሬሽኑ ስም ይቅርታ ለመጠየቅ እያቀናን ነው ሲሉ አቶ አሳዬ በተለይ ለብስራት ተናግረዋል።

ፌደሬሽኑ ምንም እንኳን ከድምፃዊቷ ጋር ውል ባይኖረውም አዳራሽ መያዙን ማረጋገጡን እና ለድምፃዊቷ ገንዘቡ መከፈሉን አስቀድሞ ሲከታተል ነበር ብለዋል።

ነገር ግን ከሳውንድ ሲስተም ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን እኛ አልተከታተልነውም ይህ ሙያዊ ስራ በመሆኑ ነው ሆኖም እኛን ብሎ ለመጣው ታዳሚ እና ድምፃዊቷ ይቅርታ እንጠይቃለን ብለዋል።

📍መረጃው የስምኦን ደረጄ ነው።

ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
‹‹ጉብዝና ያሸልማል››ሀገር አቀፍ የሒሳብ ትምህርት የፍጻሜ ውድድር እየተካሄደ ይገኛል

ማይ ሶሮባን ኢትዮጵያ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ‹‹ሒሳብ ትምህርት ይከብዳል›› የሚል የተሳሳተ አመለካከትን በማስወገድ ‹‹ጉብዝና ያሸልማል !›› በሚል መሪ ቃል ሀገር አቀፍ የሒሳብ ትምህርት እና የስሌት ውድድር በሀገራችን በሚገኙ ሁለም ትምህርት ቤቶች ለማከናወን የተቋቋመ በኢትዮጵያ ብቸኛው የሒሳብ ትምህርት አወዳዳሪ ተቋም ነው፡፡

ይህም ሀገር አቀፍ የሒሳብ የትምህርት ውድድር የመዝጊያ መርኃግብር ከሐምሌ 28 እስከ ነሐሴ 1 2016 ዓ.ም በአዲስ አበባ ሚሊኒየም አዳራሽ እየተካሄደ ይገኛል።

ሐምሌ 28 2016 ዓ.ም በተካሄደው የመክፈቻ ሥነሥርዓት ላይ ጥሪ የተደረገላቸው የክብር እንግዶች ተገኝተዋል፣ በውድድሩ ላይ የራሳቸውን አስተዋጽኦ ላበከረቱ አጋር ተቋማት የሰርተፊኬት እውቅና ሥነሥርዓት ተካሄዷል።

ይህ የፍጻሜ ውድድር እስከ ረቡዕ ነሐሴ 1 2016 ዓ.ም የሚቆይ ሲሆን ተወዳዳሪዎቹም የመጨረሻውን የአሸናፊዎች አሸናፊ ውድድር ለማሸነፍ ይፎካከራሉ።

የዚህ ውድድር አሸናፊ ተማሪዎች በጠቅላላ 4 ሚሊየን ብር የሚፈጅ የገንዘብና የዓይነት ሽልማት እንደተዘጋጀላቸው አዘጋጆች አስታውቀዋል።

የአሸናፊዎች አሸናፊ ተማሪዎች ተለይተው ለአህጉር እና አለም አቀፍ ውድድሮች ላይ እንዲሳተፉ እንደሚደረግ ተነግሯል።

ተቋሙ በ2016 ዓም ሀገር አቀፍ የሒሳብ ትምህርት ውድድር፤ ከ50 ከተሞች በላይ የተውጣጡ ከ2 ሺህ በላይ ትምህርት ቤቶች እና ከ3 መቶ ሺህ በላይ ተማሪዎችን ማሳተፍ መቻሉ ተጠቁሟል።

የፍጽሜው ውድድር የሽልማት ሥነሥርዓት በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የቀጥታ ስርጭት ሽፋን ያገኛል።

ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
Event Addis Media
Photo
📌“አዲስ ነገር በአዲስ ዓመት” ኤክስፖ

ታሜሶል ኮሙኒኬሽን ከአሴንቲክ ሶሉሽን ጋር በመተባበር ያዘጋጀውና “አዲስ ነገር በአዲስ ዓመት” በሚል መሪ ቃል የሚካሄደው ኤክስፖ 2017፤ ነሃሴ 15 ቀን 2016 ዓ.ም ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች፣ የንግዱ ማህበረሰብ አባላትና ታዋቂ ሰዎች በተገኙበት ይከፈታል፡፡

ከ500 ሺህ በላይ ሰዎች ይጎበኙታል ተብሎ በሚጠበቀው በዚህ ታላቅ የአዲስ ዓመት ኤክስፖ፤ ከ400 በላይ የሀገር ውስጥና የውጪ የንግድ ተቋማት የሚሳተፉ ሲሆን፤ ጎብኚዎች ሁሉን በአንድ ቦታ የሚያገኙባቸው ከ10 በላይ ዘርፎች በመንደር ተከፋፍለዋል፡፡

አዘጋጆቹ ጨረታውን በ62 ሚ. ብር ያሸነፉበትና አጠቃላይ ለኤክስፖው ከ100 ሚ. ብር በላይ ወጪ እንደወጣበት የተነገረለት የአዲስ ዓመት ኤክስፖ፤ ለ20 ቀናት  ክፍት ሆኖ የሚቆይ ሲሆን፤ አጠቃላይ የንግዱን እንቅስቃሴ የሚያነቃቃና በአገር ኢኮኖሚ ላይም የራሱን አሻራ የሚያሳርፍ እንደሚሆን አዘጋጆቹ ገልፀዋል፡፡

አዘጋጆቹ ታሜሶል ኮሙኒኬሽንና አሴንቲክ ሶሉሽንስ እስከ ዛሬ የተካሄዱትን ኤክስፖዎች ጠንካራና ደካማ ጎኖች በመለየት በአይነቱ ልዩ የሆነ ኤክስፖ ማሰናዳታቸውን የገለፁ ሲሆን፤ ሸማቹ ማህበረሰብ እንዳይንገላታና ሁሉን በአንድ ቦታ እንዲያገኝ አስሩን ዘርፎች በአስር ዘመናዊ መንደሮች  መከፋፈላቸውን ተናግረዋል፡፡

እነዚህ መንደሮች ከመግቢያው በር እስከ መውጫው ድረስ በተደራጀ መንገድ ተከፋፍለው የተቀመጡ ሲሆን፤ መንደሮቹም “ውብ መንደር” የሚል መጠሪያ እንደተሰጣቸው የጠቆሙት አዘጋጆቹ፤ እስከዛሬ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ የኤግዚቢሽኑን አቀማመጥ ውብና ደማቅ አድርገነዋል፤ብለዋል፡፡

ከመንደሮቹ አንዱ “የትዝታ መንደር” የሚሰኝ ሲሆን፤ በኤግዚቢሽኑ መግቢያና መውጫ በር ላይ ተዘጋጅተው ሁሉም ጎብኚዎች በግል ስልካቸው አልያም በሌሎች የፎቶግራፍና የቪዲዮ ባለሙያዎች ትዝታቸውን በፎቶና በቪዲዮ የሚያስቀሩበት ነው ተብሏል፡፡

ሌላው መንደር “የፋይናንስ መንደር” ሲሆን፤ ይህ መንደር ባንኮች ኢንሹራንሶችና ሌሎች የፋይናንስ ተቋማት በአንድ ቦታ የሚገኙበት ነውም ተብሏል፡፡ “የመዝናኛ መንደር” ደግሞ ከመክፈቻው ቀን ጀምሮ የሙዚቃ ኮንሰርቶች እንዲሁም  ምግብና መጠጥን የያዘ የመዝናኛ ስፍራ ሲሆን፤ “የቴክኖሎጂ መንደር“ ደግሞ ከሮቦት ጀምሮ ዘመኑ ያፈራቸው ቴክኖሎጂዎች ለእይታ የሚቀርቡበት ራሱን የቻለ መንደር ነው ተብሏል፡፡

“የባህል መንደር” በበኩሉ፣ ሀገራችንን ለዓለም ይበልጥ የምናስተዋውቅበትና ከባህል ምግቦች እስከ አልባሳትና ጌጣጌጥ እንዲሁም የባህል መጠጦችን ጨምሮ ባህላዊ የተባሉ  ነገሮች ሁሉ የሚገኙበት  መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡

ሌላኛው መንደር “የእውቀት መንደር” ሲሆን፤ ለአዳዲስ ተማሪዎችም ሆነ ለነባሮቹ ከህፃናት ማቆያ ጀምሮ ከሀገር ውስጥ እስከ ውጪ ሀገር ት/ቤቶች የራሳቸውን አገልግሎት የሚገልፁበት፣ ሁሉም አይነት የትምህርት ቁሳቁሶችና መጻሕፍት የሚገኙበት መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

“የውበት መንደር” የተሰኘው ደግሞ የውበት ምርቶችንና አገልግሎቶችን በአንድ ላይ ጎብኚዎች የሚያገኙበት ቦታ ሲሆን፤ የዘርፉ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት የሚሰየሙበት ሥፍራ ነው፡፡

“ዘናጭ መንደር” የተሰኘው ይሄኛው መንደር ደግሞ የህፃናት፣ የአዋቂዎች፣ የሴትና የወንድ ዘመናዊ አልባሳት በአይነትና በጥራት በአንድ ቦታ የሚገኙበት ሲሆን፤ በጤና ዙሪያ አገልግሎት የሚገኝበት “የጤና መንደር”፣ ከ20 በላይ ሙያዎች ተመርጠው ልጆች ሙያዎቹን የሚተዋወቁባቸው፣ በየቀኑ ብዙ ህፃናት ጨዋታን ጨምሮ አገልግሎት የሚያገኙባቸው ደግሞ “የልጆች መንደር” ተሰኝቷል፡፡

ታሜሶል ኮሙኒኬሽንና አሴንቲክ ሶሉሽን ሽልማትን በተመለከተም ለጎብኚዎች ትልቅ የምስራች እንዳላቸው ያስታወቁ ሲሆን፤ ጎብኚዎች የ100 ብር ትኬት ገዝተው ሲገቡ በሚወጣ እጣ ከ5 ሺህ እስከ 500 ሺህ ብር የሚደርስ የአስቤዛ መግዣ ኩፖንን ጨምሮ ከ2 ሚ. ብር በላይ የሚያወጣ አዲስ አውቶሞቢል ለሽልማት መዘጋጀቱን አስታውቀዋል፡፡

ለህፃናቱ ደግሞ ከህፃናት መጫዎቻዎች ጀምሮ በርካታ ሽልማቶች ተዘጋጅተዋል ነው የተባለው፡፡ ታላቁ የአዲስ ዓመት ኤክስፖ ከነሐሴ 15 እስከ ጳጉሜ 5 ቀን 2016 ዓ.ም  በድምቀት እንደሚቀጥልም አዘጋጆቹ ተናግረዋል፡፡ ፡

በዚህ ኤክስፖ ላይ ለሚሳተፉ ተቋማት በኤግዚቢሽን ማዕከል  ሱቆች በዱቤ  የተዘጋጁላቸው ሲሆን  የሱቆቹን ዋጋ 50 በመቶ በመክፈል ተመራጭ ቦታዎችን ይዘው 101 ፐርሰንት እንዲያተርፉ ታሜሶል ኮሙኒኬሽን ግብዣ አቅርቧል።ቀድመው የሚመጡ አስር  ተቋማት የዚህ ልዩ ዕድል ተጠቃሚ ይሆናሉም ተብሏል።

ለተጨማሪው:@EventAddis1
📌"ካሴት" የተሰኘ የኦዲዮ ማሰራጫ ይፋ ሆነ

"ካሴት” የተሰኘ የኦዲዮ ስራዎች መሸጫ የቴሌግራም ቦት ይፋ ተደረገ።ካሴት የአዲዮ ስራዎችን ማለትም ዘፈን፣ መዝሙር፣ ወግ፣ ትረካ፣ ግጥም በጃዝና መሰል ስራዎችን ለአድማጮች በጣም ቀላል በሆነ መንገድ ለመሸጥ ታልሞ የተሰራ የቴሌግራም ቦት መሆኑን ኦንላይን ኮምኒኬሽንስ አስታውቋል።

አድማጮች በቀላሉ በስልካቸው ላይ ሌላ አዲስ መተግበሪያን መጫን ሳያስፈልጋቸው በሚያዘወትሩት ቴሌግራም ላይ ካሴት ወይም @kasetrobot ብለው ቦቱን በመክፈት ወይም ሊንክ በመጫን መቀላቀል እንዲችሉ  ተደርጎ የተሰራ እና በሶስት ቋንቋዎች (አማርኛ፣ እንግሊዘኛ እና አፋን ኦሮሞ) አማራጩ የቀረበ ሲሆን በሰከንዶች ውስጥ አልበሙን በቴሌብር እና ኤም ፔሳ ገዝተው ማዳመጥ እንዲችሉ ተደርጎ መሠራቱ ተገልጿል።

አርቲስቶች በካሴት ቴሌግራም ቦት ስራዎቻቸው ለገበያ ሲያውሉ አድማጮች የገዙትን አልበም ለሌሎች መላክና መስጠት የማያስችል በመሆኑ የኮፒራይት ጥሰትን ይከላከላል ተብሏል።

ካሴት ላይ አልበም ከ100 ብር ጀምሮ መሸጥ የሚቻል ሲሆን መሸጫ ዋጋውን የሚወስነው ራሱ አርቲስቱ ይሆናል።

ካሴት ከብሔራዊ ባንክ ፈቃድ ከተሰጠው የክፍያ ተቋም ጋር የሚሰራ ሲሆን እያንዳንዱ ሽያጭ መንግስት የሚያውቀው ሲሆን የአንድ አልበም መሸጨ ዋጋ 15 በመቶ ተጨማሪ እሴት ታክስን ያካትታል፡፡

ከዚህም ውስጥ አርቲስቱ ከጠቅላላ ገቢ ላይ 70 በመቶ በየወሩ የሚያገኝ ይሆናል። ድርሻቸውን ሲወስዱም 5 በመቶ የሮያሊት ታክስ ለመንግስት ይከፍላሉ ተብሏል።

ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌 "ግጥም ሲጥም" የኪነጥበብ ዝግጅት ነገ ይካሄዳል

"ግጥም ሲጥም "ለሁሉም ክፍት የሆነ የኪነጥበብ  መድረክ ነገ ረቡዕ ነሐሴ 1 2016 ዓ.ም ከምሽቱ 12:00 ጀምሮ ገርጂ በሚገኘው ደስክ አዲስ ውስጥ ይካሄዳል።

የግጥም ሲጥም አዘጋጆችም "በቻይና ከተዘጋጀው ዓለምአቀፍ የወጣቶች የሥነግጥም ፌስቲቫል ተሳትፏችን መልስ የግጥም ሲጥም ክፍቱ መድረክ እልል ብሎ መጥቷል ልዩ ተጋባዥ አጣሚያንን ይዘን በአዲስ መልክ እንጠብቃችኋለን" ብለዋል።

የዚህ ኪነጥበባዊ ዝግጅት መግቢያ በጊዜ መገኘታችሁ ነው ተብላችኋል።

ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌"ጂ ፓወር እንቁጣጣሽ" የተሰኘ የሙዚቃ ኮንሰርት በዱባይ ከተማ እንደሚካሄድ አዘጋጆቹ አስታወቁ

በጂ ፓወር አማካኝነት የተዘጋጀው የ2017 አዲስ ዓመት መቀበያ "ጂ ፓወር እንቁጣጣሽ" የሙዚቃ ኮንሰርት በቀጣይ ጷጉሜ 2 ቀን በዱባይ ከተማ እንደሚካሄድ ተገልጿል።

የኢትዮጵያን አዲስ ዓመት ምክንያት በማድረግ በተዘጋጀው የሙዚቃ ኮንሰርት ላይ ንዋይ ደበበ፣ ጎሳዬ ተስፋዬ፣አብርሃም ገብረመድህን፣አንዱአለም ጎሳ፣ዮሃና በኮንሰርቱ ላይ የሚገኙ ድምጻዊያን ናቸው ተብሏል።

ጂ ፓወር እንቁጣጣሽ ኮንሰርትን ያዘጋጀው ከአሁን ቀደም የቴዲ አፍሮ ኮንሰርትን በዱባዩ ኮካ ኮላ አሬና ያዘጋጀውና የቴክኖሎጂ እቃዎችን በማስመጣት የሚታወቀው ጂ- ፓወር ማኑፋክቸሪንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ ነው።

ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌አላቲኖስ የፊልም ውይይት ነገ ይካሄዳል

አላቲኖስ ኢትዮጵያዊ ፊልም ሰሪዎች ማሕበር ፒያሳ በሚገኘው የሩሲያ ሳይንስና ባህል ማዕከል (ፑሽኪን) አዳራሽ ውስጥ በሚያዘጋጀው የፊልም ውይይት መርሐግብር ነገ ሐሙስ ነሐሴ 2 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 10:30 ጀምሮ" የፌርናንዶ ሶላኖስ አርጀንቲናዊ ሲኒማቶግራፊ"  በሚል ርዕስ እይታ እና ውይይት ያካሄዳል።በዕለቱም መነሻ ሀሳብ በምኒሊክ መርዕድ ይቀርባል።

ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌መቅረዝ ሥነኪን የኪነጥበብ ዝግጅት ነገ ይካሄዳል

አንጋፋው ደራሲ አበራ ለማ የክብር እንግዳ የሆነበት "መቅረዝ ሥነኪን" የኪነጥበብ ዝግጅት ሀሙስ ይካሄዳል።

አንጋፋ እና ወጣት የኪነጥበብ ባለሞያዎችን እያጣመር የዘለቀው መቅረዝ ሥነኪን ወርሀዊ የኪነጥበብ  ዝግጅት ነገ ሐሙስ ነሐሴ 2 2016 ዓ.ም ከምሽቱ 11:00 ጀምሮ  ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት (ወመዘክር )አዳራሽ ውስጥ ይካሄዳል።

በዚህ የዓመቱ የመዝጊያ ዝግጅት ላይ  አንጋፋው ደራሲ አበራ ለማ የክብር እንግዳ በመሆን የሚገኙ ሲሆን በተጨማሪም ወጣት የኪነጥበብ ባለሞያዎች የግጥም ፣የሙዚቃ እና  የዳንስ ስራዎቻቸውን ያቀርባሉ።

የዚህ ዝግጅት መግቢያ በነፃ ነው።

ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌ዓለምአቀፍ ፕሮፌሽናል የቦክስ ውድድር በአዲስ አበባ ሊካሄድ ነው

የአፍሪካ ቦክስ ኮንፌደሬሽን ዋና ቢሮውን በአዲስ አበባ የከፈተ ሲሆን ቅዳሜ ነሐሴ 11 2016 ዓ.ም በደማቅ ዝግጅት በይፋ ያስመርቃል፡፡

ከቢሮ ምርቃቱ በተጨማሪም በአፍሪካ ለመጀመሪያ ጊዜ አለም አቀፍ ቦክስ ውድድርም ይካሄዳል፡፡

ይህ ዓለምአቀፍ የቦክስ ውድድርን የዓለምአቀፉ የቦክስ ማህበር ከአፍሪካ የቦክስ ኮንፌደሬሽን እንዲሁም ከኢትዮጵያ የቦክስ ፌደሬሽን ጋር በመተበበር በአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም የሚዘጋጅ ሲሆን፣ 20 ዓለም አቀፍ ፕሮፌሽናል ቦክሰኞች ከራሺያ፣ ከሜክሲኮ፣ ከእንግሊዝ፣ ከካዛኪስታን፣ ከሞሮኮ፣ ከናይጄሪያ እና ከሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ወደ አዲስ አበባ በመምጣት በአፍሪካ ታይቶ ለማይታወቅ ከፍተኛ የገንዘብ ሽልማት በ10 የቦክስ ውድድሮች ይፋለማሉ፡፡

ይህን ዓለምአቀፍ የቦክስ ውድድርን ለመዘገብ በርካታ ሚዲያዎች ከተለያዩ ሀገራት እንደሚመጡ ተገልጿል። መሰል ፕሮፌሸናል ውድድር ለማዘጋጀት ኢትዮጵያ የመጀመሪያዋ አፍሪካዊት ሀገር ትሆናለችም ተብሏል።

ስመጥርና ፕሮፌሽናል ቦክሰኞችን ውድድር ማንኛውም ስፖርት ወዳድ በአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም ከቀኑ 11 ሰዓት ጀምሮ በመገኘት መታደም ይችላልም ተብሏል።

ቅድሚያ የመግቢያ ትኬት ለሚገዙና ለጥንዶች ልዩ ቅናሽ መኖሩ የተገለጸ ሲኾንን፣ ትኬቱንም ለመግዛት በ https://chapa.link/event/view/EV-6xynuuPvIkUK መጠቀም እንደሚቻል አዘጋጆቹ ለትርታ በላኩት መግለጫ ላይ አስታውቀዋል።

ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌ገጣሚ ሠዓሊና ቀራፂ ከበደች ተክለአብ የሥነጥበብ ጉዞዋን ያካፈለችበት ዝግጅት ተካሄደ

አለ የሥነጥበብና ዲዛይን ት/ቤት ከአሜሪካ ኤምባሲ ጋር በመሆን "ALONG WALK TO CREATIVITY  THE JOURNEY OF RESILIENT ARTIST "  በሚል ርዕስ  ሠዓሊ ቀራጺና ገጣሚ  ከበደች ተክለአብ  ያዘጋጁት ፕሮግራም ነሐሴ 1 2016 ዓ.ም  በአለ የሥነጥበብና ዲዛይን ት/ቤት አዳራሽ  ተካሄደ::

ሠዓሊ ቀራጺና ገጣሚ  ከበደች ተክለአብ ከረጅም ዓመታት የአሜሪካን ቆይታ በኃላ ወደ ሐገሯ በመምጣት በአለ የሥነጥበብና ዲዛይን ት/ቤት አዳራሽ  ተገኝታ ከረጅሙ የማስተማር  የስነጥበብ ጉዟዋ ሰዓት የፈቀደውን ሁሉ አካፍላለች::

በዚህ ፕሮግራም ላይ ከበደች ተክለአብ 
የሥነጥበብ ጉዞዋ ምን እንደሚመስል በፕሮጀክተር በተደገፉ ምስሎች ስለ ግጥም ስራዎቿ በአሜሪካና በተለያዩ ሐገሮች ስላካሄደቻቸው የስዕል አውደርዕዮቿ  በዝርዝር ነግራናለች:: በተለይ የስዕል ስራዎቿና ውጣ ውረድ የሞላበትን የስነጥበብ ጉዞዋን እውቀቷንና የልምዷን አካፍላለች:: ከታዳሚው  ለተነሳላት  በርካታ  ጥያቄዎችም መልስና ማብራሪያ ሰጥታለች::

ከበደች ተክለአብ "የት ነው?" የተሰኘው የግጥም መፅሐፏ በወቅቱ በሳንሱር ምክንያት እንዳይታተሙ የተደረጉትን ግጥሞች ጨምራና የመፅሐፉን መግቢያ አስተካክላ በድጋሚ እንደታተመ ተናግራለች::  አዲሱንም መፅሐፍ አሳይታናለች:: በተጨማሪም " ሱታፌ " የተሰኘው  አዲሱ መፅሐፏም ታትሞ ለንባብ እንደበቃ በዚሁ ፕሮግራም ላይ ተናግራለች::

በአሁኑ ወቅት በኒውዮርክ ከተማ በሚገኘው ዘ ሲቲ ዩኒቨርሲቲ ኦፍ ኒውዮርክ ኩዊንስቦሮ ውስጥ  አሲስታንት ፕሮፌሰር በመሆን ታስተምራለች::

📍መረጃው የይትባረክ ዋለልኝ ነው።

ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌"ጎዶን ጥበቃ" የተሰኘ አዲስ ተውኔት ዛሬ ሐሙስ ከምሽቱ 11:00 በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ለእይታ ይበቃል።

ድርሰት: ሳሙኤል ቤኬት

ትርጉም:ሀይከል ሙባረክ

አዘጋጅ: ዳግም ሲሳይ

ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌ኮሜዲያን ልመንህ ታደሰ

ተወዳጁ ኮሜዲያን ልመንህ ታደሰ ከቤተሰቡ ጋር ተቀላቅሏል

ተወዳጁ ኮሜዲያን ልመንህ ታደሰ ሲከታተል የቆየውን ህክምና ጨርሶ በጥሩ ጤንነት በዛሬው ዕለት ወደ ቤቱ ገብቷል።

አርቲስት ልመንህ ታደሰ ላለፉት ጥቂት ወራት በአቢቹ መታሰቢያ የአእምሮ ክሊኒክ ሲደረግለት የነበረው ክትትልን ጨርሶ በሙሉ ጤንነት ወደ ቤቱ መግባቱን ድጋፍ እና ክትትል ሲያደርጉ የነበሩ ወዳጆቹ ገልፀዋል።

ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1