Event Addis Media – Telegram
Event Addis Media
9.62K subscribers
6.12K photos
14 videos
4 files
4.75K links
Connect with Addis artistic community!

Website: https://eventaddis.com

Contact: @Tmanaye
Download Telegram
Event Addis Media
Photo
📌“አዲስ ነገር በአዲስ ዓመት” ኤክስፖ

ታሜሶል ኮሙኒኬሽን ከአሴንቲክ ሶሉሽን ጋር በመተባበር ያዘጋጀውና “አዲስ ነገር በአዲስ ዓመት” በሚል መሪ ቃል የሚካሄደው ኤክስፖ 2017፤ ነሃሴ 15 ቀን 2016 ዓ.ም ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች፣ የንግዱ ማህበረሰብ አባላትና ታዋቂ ሰዎች በተገኙበት ይከፈታል፡፡

ከ500 ሺህ በላይ ሰዎች ይጎበኙታል ተብሎ በሚጠበቀው በዚህ ታላቅ የአዲስ ዓመት ኤክስፖ፤ ከ400 በላይ የሀገር ውስጥና የውጪ የንግድ ተቋማት የሚሳተፉ ሲሆን፤ ጎብኚዎች ሁሉን በአንድ ቦታ የሚያገኙባቸው ከ10 በላይ ዘርፎች በመንደር ተከፋፍለዋል፡፡

አዘጋጆቹ ጨረታውን በ62 ሚ. ብር ያሸነፉበትና አጠቃላይ ለኤክስፖው ከ100 ሚ. ብር በላይ ወጪ እንደወጣበት የተነገረለት የአዲስ ዓመት ኤክስፖ፤ ለ20 ቀናት  ክፍት ሆኖ የሚቆይ ሲሆን፤ አጠቃላይ የንግዱን እንቅስቃሴ የሚያነቃቃና በአገር ኢኮኖሚ ላይም የራሱን አሻራ የሚያሳርፍ እንደሚሆን አዘጋጆቹ ገልፀዋል፡፡

አዘጋጆቹ ታሜሶል ኮሙኒኬሽንና አሴንቲክ ሶሉሽንስ እስከ ዛሬ የተካሄዱትን ኤክስፖዎች ጠንካራና ደካማ ጎኖች በመለየት በአይነቱ ልዩ የሆነ ኤክስፖ ማሰናዳታቸውን የገለፁ ሲሆን፤ ሸማቹ ማህበረሰብ እንዳይንገላታና ሁሉን በአንድ ቦታ እንዲያገኝ አስሩን ዘርፎች በአስር ዘመናዊ መንደሮች  መከፋፈላቸውን ተናግረዋል፡፡

እነዚህ መንደሮች ከመግቢያው በር እስከ መውጫው ድረስ በተደራጀ መንገድ ተከፋፍለው የተቀመጡ ሲሆን፤ መንደሮቹም “ውብ መንደር” የሚል መጠሪያ እንደተሰጣቸው የጠቆሙት አዘጋጆቹ፤ እስከዛሬ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ የኤግዚቢሽኑን አቀማመጥ ውብና ደማቅ አድርገነዋል፤ብለዋል፡፡

ከመንደሮቹ አንዱ “የትዝታ መንደር” የሚሰኝ ሲሆን፤ በኤግዚቢሽኑ መግቢያና መውጫ በር ላይ ተዘጋጅተው ሁሉም ጎብኚዎች በግል ስልካቸው አልያም በሌሎች የፎቶግራፍና የቪዲዮ ባለሙያዎች ትዝታቸውን በፎቶና በቪዲዮ የሚያስቀሩበት ነው ተብሏል፡፡

ሌላው መንደር “የፋይናንስ መንደር” ሲሆን፤ ይህ መንደር ባንኮች ኢንሹራንሶችና ሌሎች የፋይናንስ ተቋማት በአንድ ቦታ የሚገኙበት ነውም ተብሏል፡፡ “የመዝናኛ መንደር” ደግሞ ከመክፈቻው ቀን ጀምሮ የሙዚቃ ኮንሰርቶች እንዲሁም  ምግብና መጠጥን የያዘ የመዝናኛ ስፍራ ሲሆን፤ “የቴክኖሎጂ መንደር“ ደግሞ ከሮቦት ጀምሮ ዘመኑ ያፈራቸው ቴክኖሎጂዎች ለእይታ የሚቀርቡበት ራሱን የቻለ መንደር ነው ተብሏል፡፡

“የባህል መንደር” በበኩሉ፣ ሀገራችንን ለዓለም ይበልጥ የምናስተዋውቅበትና ከባህል ምግቦች እስከ አልባሳትና ጌጣጌጥ እንዲሁም የባህል መጠጦችን ጨምሮ ባህላዊ የተባሉ  ነገሮች ሁሉ የሚገኙበት  መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡

ሌላኛው መንደር “የእውቀት መንደር” ሲሆን፤ ለአዳዲስ ተማሪዎችም ሆነ ለነባሮቹ ከህፃናት ማቆያ ጀምሮ ከሀገር ውስጥ እስከ ውጪ ሀገር ት/ቤቶች የራሳቸውን አገልግሎት የሚገልፁበት፣ ሁሉም አይነት የትምህርት ቁሳቁሶችና መጻሕፍት የሚገኙበት መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

“የውበት መንደር” የተሰኘው ደግሞ የውበት ምርቶችንና አገልግሎቶችን በአንድ ላይ ጎብኚዎች የሚያገኙበት ቦታ ሲሆን፤ የዘርፉ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት የሚሰየሙበት ሥፍራ ነው፡፡

“ዘናጭ መንደር” የተሰኘው ይሄኛው መንደር ደግሞ የህፃናት፣ የአዋቂዎች፣ የሴትና የወንድ ዘመናዊ አልባሳት በአይነትና በጥራት በአንድ ቦታ የሚገኙበት ሲሆን፤ በጤና ዙሪያ አገልግሎት የሚገኝበት “የጤና መንደር”፣ ከ20 በላይ ሙያዎች ተመርጠው ልጆች ሙያዎቹን የሚተዋወቁባቸው፣ በየቀኑ ብዙ ህፃናት ጨዋታን ጨምሮ አገልግሎት የሚያገኙባቸው ደግሞ “የልጆች መንደር” ተሰኝቷል፡፡

ታሜሶል ኮሙኒኬሽንና አሴንቲክ ሶሉሽን ሽልማትን በተመለከተም ለጎብኚዎች ትልቅ የምስራች እንዳላቸው ያስታወቁ ሲሆን፤ ጎብኚዎች የ100 ብር ትኬት ገዝተው ሲገቡ በሚወጣ እጣ ከ5 ሺህ እስከ 500 ሺህ ብር የሚደርስ የአስቤዛ መግዣ ኩፖንን ጨምሮ ከ2 ሚ. ብር በላይ የሚያወጣ አዲስ አውቶሞቢል ለሽልማት መዘጋጀቱን አስታውቀዋል፡፡

ለህፃናቱ ደግሞ ከህፃናት መጫዎቻዎች ጀምሮ በርካታ ሽልማቶች ተዘጋጅተዋል ነው የተባለው፡፡ ታላቁ የአዲስ ዓመት ኤክስፖ ከነሐሴ 15 እስከ ጳጉሜ 5 ቀን 2016 ዓ.ም  በድምቀት እንደሚቀጥልም አዘጋጆቹ ተናግረዋል፡፡ ፡

በዚህ ኤክስፖ ላይ ለሚሳተፉ ተቋማት በኤግዚቢሽን ማዕከል  ሱቆች በዱቤ  የተዘጋጁላቸው ሲሆን  የሱቆቹን ዋጋ 50 በመቶ በመክፈል ተመራጭ ቦታዎችን ይዘው 101 ፐርሰንት እንዲያተርፉ ታሜሶል ኮሙኒኬሽን ግብዣ አቅርቧል።ቀድመው የሚመጡ አስር  ተቋማት የዚህ ልዩ ዕድል ተጠቃሚ ይሆናሉም ተብሏል።

ለተጨማሪው:@EventAddis1
📌"ካሴት" የተሰኘ የኦዲዮ ማሰራጫ ይፋ ሆነ

"ካሴት” የተሰኘ የኦዲዮ ስራዎች መሸጫ የቴሌግራም ቦት ይፋ ተደረገ።ካሴት የአዲዮ ስራዎችን ማለትም ዘፈን፣ መዝሙር፣ ወግ፣ ትረካ፣ ግጥም በጃዝና መሰል ስራዎችን ለአድማጮች በጣም ቀላል በሆነ መንገድ ለመሸጥ ታልሞ የተሰራ የቴሌግራም ቦት መሆኑን ኦንላይን ኮምኒኬሽንስ አስታውቋል።

አድማጮች በቀላሉ በስልካቸው ላይ ሌላ አዲስ መተግበሪያን መጫን ሳያስፈልጋቸው በሚያዘወትሩት ቴሌግራም ላይ ካሴት ወይም @kasetrobot ብለው ቦቱን በመክፈት ወይም ሊንክ በመጫን መቀላቀል እንዲችሉ  ተደርጎ የተሰራ እና በሶስት ቋንቋዎች (አማርኛ፣ እንግሊዘኛ እና አፋን ኦሮሞ) አማራጩ የቀረበ ሲሆን በሰከንዶች ውስጥ አልበሙን በቴሌብር እና ኤም ፔሳ ገዝተው ማዳመጥ እንዲችሉ ተደርጎ መሠራቱ ተገልጿል።

አርቲስቶች በካሴት ቴሌግራም ቦት ስራዎቻቸው ለገበያ ሲያውሉ አድማጮች የገዙትን አልበም ለሌሎች መላክና መስጠት የማያስችል በመሆኑ የኮፒራይት ጥሰትን ይከላከላል ተብሏል።

ካሴት ላይ አልበም ከ100 ብር ጀምሮ መሸጥ የሚቻል ሲሆን መሸጫ ዋጋውን የሚወስነው ራሱ አርቲስቱ ይሆናል።

ካሴት ከብሔራዊ ባንክ ፈቃድ ከተሰጠው የክፍያ ተቋም ጋር የሚሰራ ሲሆን እያንዳንዱ ሽያጭ መንግስት የሚያውቀው ሲሆን የአንድ አልበም መሸጨ ዋጋ 15 በመቶ ተጨማሪ እሴት ታክስን ያካትታል፡፡

ከዚህም ውስጥ አርቲስቱ ከጠቅላላ ገቢ ላይ 70 በመቶ በየወሩ የሚያገኝ ይሆናል። ድርሻቸውን ሲወስዱም 5 በመቶ የሮያሊት ታክስ ለመንግስት ይከፍላሉ ተብሏል።

ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌 "ግጥም ሲጥም" የኪነጥበብ ዝግጅት ነገ ይካሄዳል

"ግጥም ሲጥም "ለሁሉም ክፍት የሆነ የኪነጥበብ  መድረክ ነገ ረቡዕ ነሐሴ 1 2016 ዓ.ም ከምሽቱ 12:00 ጀምሮ ገርጂ በሚገኘው ደስክ አዲስ ውስጥ ይካሄዳል።

የግጥም ሲጥም አዘጋጆችም "በቻይና ከተዘጋጀው ዓለምአቀፍ የወጣቶች የሥነግጥም ፌስቲቫል ተሳትፏችን መልስ የግጥም ሲጥም ክፍቱ መድረክ እልል ብሎ መጥቷል ልዩ ተጋባዥ አጣሚያንን ይዘን በአዲስ መልክ እንጠብቃችኋለን" ብለዋል።

የዚህ ኪነጥበባዊ ዝግጅት መግቢያ በጊዜ መገኘታችሁ ነው ተብላችኋል።

ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌"ጂ ፓወር እንቁጣጣሽ" የተሰኘ የሙዚቃ ኮንሰርት በዱባይ ከተማ እንደሚካሄድ አዘጋጆቹ አስታወቁ

በጂ ፓወር አማካኝነት የተዘጋጀው የ2017 አዲስ ዓመት መቀበያ "ጂ ፓወር እንቁጣጣሽ" የሙዚቃ ኮንሰርት በቀጣይ ጷጉሜ 2 ቀን በዱባይ ከተማ እንደሚካሄድ ተገልጿል።

የኢትዮጵያን አዲስ ዓመት ምክንያት በማድረግ በተዘጋጀው የሙዚቃ ኮንሰርት ላይ ንዋይ ደበበ፣ ጎሳዬ ተስፋዬ፣አብርሃም ገብረመድህን፣አንዱአለም ጎሳ፣ዮሃና በኮንሰርቱ ላይ የሚገኙ ድምጻዊያን ናቸው ተብሏል።

ጂ ፓወር እንቁጣጣሽ ኮንሰርትን ያዘጋጀው ከአሁን ቀደም የቴዲ አፍሮ ኮንሰርትን በዱባዩ ኮካ ኮላ አሬና ያዘጋጀውና የቴክኖሎጂ እቃዎችን በማስመጣት የሚታወቀው ጂ- ፓወር ማኑፋክቸሪንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ ነው።

ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌አላቲኖስ የፊልም ውይይት ነገ ይካሄዳል

አላቲኖስ ኢትዮጵያዊ ፊልም ሰሪዎች ማሕበር ፒያሳ በሚገኘው የሩሲያ ሳይንስና ባህል ማዕከል (ፑሽኪን) አዳራሽ ውስጥ በሚያዘጋጀው የፊልም ውይይት መርሐግብር ነገ ሐሙስ ነሐሴ 2 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 10:30 ጀምሮ" የፌርናንዶ ሶላኖስ አርጀንቲናዊ ሲኒማቶግራፊ"  በሚል ርዕስ እይታ እና ውይይት ያካሄዳል።በዕለቱም መነሻ ሀሳብ በምኒሊክ መርዕድ ይቀርባል።

ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌መቅረዝ ሥነኪን የኪነጥበብ ዝግጅት ነገ ይካሄዳል

አንጋፋው ደራሲ አበራ ለማ የክብር እንግዳ የሆነበት "መቅረዝ ሥነኪን" የኪነጥበብ ዝግጅት ሀሙስ ይካሄዳል።

አንጋፋ እና ወጣት የኪነጥበብ ባለሞያዎችን እያጣመር የዘለቀው መቅረዝ ሥነኪን ወርሀዊ የኪነጥበብ  ዝግጅት ነገ ሐሙስ ነሐሴ 2 2016 ዓ.ም ከምሽቱ 11:00 ጀምሮ  ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት (ወመዘክር )አዳራሽ ውስጥ ይካሄዳል።

በዚህ የዓመቱ የመዝጊያ ዝግጅት ላይ  አንጋፋው ደራሲ አበራ ለማ የክብር እንግዳ በመሆን የሚገኙ ሲሆን በተጨማሪም ወጣት የኪነጥበብ ባለሞያዎች የግጥም ፣የሙዚቃ እና  የዳንስ ስራዎቻቸውን ያቀርባሉ።

የዚህ ዝግጅት መግቢያ በነፃ ነው።

ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌ዓለምአቀፍ ፕሮፌሽናል የቦክስ ውድድር በአዲስ አበባ ሊካሄድ ነው

የአፍሪካ ቦክስ ኮንፌደሬሽን ዋና ቢሮውን በአዲስ አበባ የከፈተ ሲሆን ቅዳሜ ነሐሴ 11 2016 ዓ.ም በደማቅ ዝግጅት በይፋ ያስመርቃል፡፡

ከቢሮ ምርቃቱ በተጨማሪም በአፍሪካ ለመጀመሪያ ጊዜ አለም አቀፍ ቦክስ ውድድርም ይካሄዳል፡፡

ይህ ዓለምአቀፍ የቦክስ ውድድርን የዓለምአቀፉ የቦክስ ማህበር ከአፍሪካ የቦክስ ኮንፌደሬሽን እንዲሁም ከኢትዮጵያ የቦክስ ፌደሬሽን ጋር በመተበበር በአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም የሚዘጋጅ ሲሆን፣ 20 ዓለም አቀፍ ፕሮፌሽናል ቦክሰኞች ከራሺያ፣ ከሜክሲኮ፣ ከእንግሊዝ፣ ከካዛኪስታን፣ ከሞሮኮ፣ ከናይጄሪያ እና ከሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ወደ አዲስ አበባ በመምጣት በአፍሪካ ታይቶ ለማይታወቅ ከፍተኛ የገንዘብ ሽልማት በ10 የቦክስ ውድድሮች ይፋለማሉ፡፡

ይህን ዓለምአቀፍ የቦክስ ውድድርን ለመዘገብ በርካታ ሚዲያዎች ከተለያዩ ሀገራት እንደሚመጡ ተገልጿል። መሰል ፕሮፌሸናል ውድድር ለማዘጋጀት ኢትዮጵያ የመጀመሪያዋ አፍሪካዊት ሀገር ትሆናለችም ተብሏል።

ስመጥርና ፕሮፌሽናል ቦክሰኞችን ውድድር ማንኛውም ስፖርት ወዳድ በአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም ከቀኑ 11 ሰዓት ጀምሮ በመገኘት መታደም ይችላልም ተብሏል።

ቅድሚያ የመግቢያ ትኬት ለሚገዙና ለጥንዶች ልዩ ቅናሽ መኖሩ የተገለጸ ሲኾንን፣ ትኬቱንም ለመግዛት በ https://chapa.link/event/view/EV-6xynuuPvIkUK መጠቀም እንደሚቻል አዘጋጆቹ ለትርታ በላኩት መግለጫ ላይ አስታውቀዋል።

ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌ገጣሚ ሠዓሊና ቀራፂ ከበደች ተክለአብ የሥነጥበብ ጉዞዋን ያካፈለችበት ዝግጅት ተካሄደ

አለ የሥነጥበብና ዲዛይን ት/ቤት ከአሜሪካ ኤምባሲ ጋር በመሆን "ALONG WALK TO CREATIVITY  THE JOURNEY OF RESILIENT ARTIST "  በሚል ርዕስ  ሠዓሊ ቀራጺና ገጣሚ  ከበደች ተክለአብ  ያዘጋጁት ፕሮግራም ነሐሴ 1 2016 ዓ.ም  በአለ የሥነጥበብና ዲዛይን ት/ቤት አዳራሽ  ተካሄደ::

ሠዓሊ ቀራጺና ገጣሚ  ከበደች ተክለአብ ከረጅም ዓመታት የአሜሪካን ቆይታ በኃላ ወደ ሐገሯ በመምጣት በአለ የሥነጥበብና ዲዛይን ት/ቤት አዳራሽ  ተገኝታ ከረጅሙ የማስተማር  የስነጥበብ ጉዟዋ ሰዓት የፈቀደውን ሁሉ አካፍላለች::

በዚህ ፕሮግራም ላይ ከበደች ተክለአብ 
የሥነጥበብ ጉዞዋ ምን እንደሚመስል በፕሮጀክተር በተደገፉ ምስሎች ስለ ግጥም ስራዎቿ በአሜሪካና በተለያዩ ሐገሮች ስላካሄደቻቸው የስዕል አውደርዕዮቿ  በዝርዝር ነግራናለች:: በተለይ የስዕል ስራዎቿና ውጣ ውረድ የሞላበትን የስነጥበብ ጉዞዋን እውቀቷንና የልምዷን አካፍላለች:: ከታዳሚው  ለተነሳላት  በርካታ  ጥያቄዎችም መልስና ማብራሪያ ሰጥታለች::

ከበደች ተክለአብ "የት ነው?" የተሰኘው የግጥም መፅሐፏ በወቅቱ በሳንሱር ምክንያት እንዳይታተሙ የተደረጉትን ግጥሞች ጨምራና የመፅሐፉን መግቢያ አስተካክላ በድጋሚ እንደታተመ ተናግራለች::  አዲሱንም መፅሐፍ አሳይታናለች:: በተጨማሪም " ሱታፌ " የተሰኘው  አዲሱ መፅሐፏም ታትሞ ለንባብ እንደበቃ በዚሁ ፕሮግራም ላይ ተናግራለች::

በአሁኑ ወቅት በኒውዮርክ ከተማ በሚገኘው ዘ ሲቲ ዩኒቨርሲቲ ኦፍ ኒውዮርክ ኩዊንስቦሮ ውስጥ  አሲስታንት ፕሮፌሰር በመሆን ታስተምራለች::

📍መረጃው የይትባረክ ዋለልኝ ነው።

ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌"ጎዶን ጥበቃ" የተሰኘ አዲስ ተውኔት ዛሬ ሐሙስ ከምሽቱ 11:00 በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ለእይታ ይበቃል።

ድርሰት: ሳሙኤል ቤኬት

ትርጉም:ሀይከል ሙባረክ

አዘጋጅ: ዳግም ሲሳይ

ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌ኮሜዲያን ልመንህ ታደሰ

ተወዳጁ ኮሜዲያን ልመንህ ታደሰ ከቤተሰቡ ጋር ተቀላቅሏል

ተወዳጁ ኮሜዲያን ልመንህ ታደሰ ሲከታተል የቆየውን ህክምና ጨርሶ በጥሩ ጤንነት በዛሬው ዕለት ወደ ቤቱ ገብቷል።

አርቲስት ልመንህ ታደሰ ላለፉት ጥቂት ወራት በአቢቹ መታሰቢያ የአእምሮ ክሊኒክ ሲደረግለት የነበረው ክትትልን ጨርሶ በሙሉ ጤንነት ወደ ቤቱ መግባቱን ድጋፍ እና ክትትል ሲያደርጉ የነበሩ ወዳጆቹ ገልፀዋል።

ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌ነገረ መጻሕፍት (ዛሬ ከሰዓት)

ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌ስብሐቲዝም (ነገ ከሰዓት )

ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌የአእምሮ እድገት ውስንነት ቀንን (CP-day) አስመልክቶ የፊታችን መስከረም 26 የእግር ጉዞ መርሐ-ግብር መዘጋጀቱ ተገለፀ

ስለ ሲፒ ጉዳት ይመለከተኛል በሚል በዛሬው እለት በእዝነት አካል ጉዳተኛ ህጻናትና ወላጆች መርጃ ድርጅት ውስጥ የግንዛቤ ማስጨበጥ መርሐ-ግብር የተካሄደ ሲሆን  ይህን አስመልክቶ የፊታችን መስከረም 26 የእግር ጉዞ መርሐ-ግብርም መዘጋጀቱ ተገልጿል።

ይህንንም የእግር ጉዞ ይፋ ለማድረግ እና የቲሸርት ምረቃ መርሐ ግብር የተካሄደ ሲሆን 10000 የሚሆኑ ቲሸርቶች መዘጋጀታቸው ተገልጿል

ቲሸርቱ ከዛሬ ጀምሮ ለሽያጭ የቀረበ ሲሆን የአንዱ ቲሸርት ዋጋ 400 ብር ነው ትብሏል
የCP ጉዳተኛ ህፃናት ራሳቸውን ችለው መቀመጥ፥ መቆም፥ መመገብ፥ ንፅህናቸውን መጠበቅ፥ መናገር አንዳንዱም ማየት የማይችሉ፥ እዲሁም በየቀኑ በተደጋጋሚ seizure የሚከሰትባቸው ህፃናት ናቸው።

እዝነት እነዚህ ህፃናት እንደማንኛውም ዜጋ ማግኘት ያለባቸውን እንከብካቤ እያገኙ ጤንነታቸው እና ምቾታቸው ተጠብቆ እንዲኖሩ የሚጥር ማእከል እንደመሆኑ መጠን የCP ጉዳት ምንነትን አስመልክቶ የማሕበረሰቡ ግንዛቤ ከፍ እንዲል ለማድረግ የአይምሮ ውስንነት ቀንን (CP-day) ተንተርሶ ይህን የእግር ጉዞ መርሐ-ግብር ለማዘጋጀት መዘጋጀቱን የማዕከሉ ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ዘቢባ አህመድ ገልጸዋል።

ወ/ሮ ዘቢባ አክለው እንደገለጹት ህብረተሰቡ በሐገራችን ለመጀመሪያ ጊዜ የአለም ሴሬብራል ፓልሲ ቀንን በማስመልከት በተዘጋጀው በዚህ የእግር ጉዞ መርሐግብር ላይ በመሳተፍ ለአካል ጉዳተኛ ህጻናት በተለይም ለሲፒ ጉዳተኛ ህጻናት አለኝታ በመሆን ከድርጅቱ ጎን እንዲቆም ጠይቀዋል።

ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1