Event Addis Media – Telegram
Event Addis Media
9.62K subscribers
6.12K photos
14 videos
4 files
4.74K links
Connect with Addis artistic community!

Website: https://eventaddis.com

Contact: @Tmanaye
Download Telegram
📌የድምጻዊ መሳይ ተፈራ የሙዚቃ አልበም ምርቃት !

የድምጻዊ መሳይ ተፈራ ካሣ "የልቤን" የሙዚቃ አልበም የምርቃት ሥነሥርዓት በርካታ ዝነኛ ሙዚቀኞች በተገኙበት ዛሬ አመሻሹን በማርዮት ሆቴል ውስጥ እንደሚካሄድ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌የጁፒተር ብራና ንባብ ቡድን ውይይት

ዛሬ በጁፒተር ብራና የንባብ ቡድን "በትውልዶች መካከል የሚደረግ ወግ " በሚል አብይ ርዕስ ውይይት ይካሄዳል። የዕለቱም እንግዳ የህግ ባለሙያ ታምራት ኪዳነማርያም ናቸው።

ቀን፡ ቅዳሜ ነሀሴ 18 ፣ 2016
ሰዓት፡ ከቀኑ 9፡45 – 12፡00
ቦታ፡ ጁፒተር ሆቴል ካዛንቺስ ቅርንጫፍ

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌ሲልከን ቫሊ ኮሌጅ ተማሪዎቹን አስመረቀ !

ሲልከን ቫሊ ኮሌጅ ዛሬ ነሐሴ 18 2016 ዓ.ም በተለያየ የሙያ ዘርፍ ያስተማራቸውን ተማሪዎችን በአምባሳደር ቴአትር ቤት አስመርቋል።

በምርቃት ሥነሥርዓቱ ላይ የክብር እንግዳ በመሆን የኢንተርፕረነርሺፕ ልማት ማዕከል ስራ አስፈጻሚ ሃሰን ሁሴን (ዶ/ር) የተገኙ ሲሆን በተጨማሪም የኮሌጁ ዲን ቴዎድሮስ አበበ (ረዳት ፕሮፌሰር) እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው የክብር እንግዶች ተገኝተዋል።

የኮሎጁ ዲን ቴዎድሮስ አበበ (ረዳት ፕሮፌሰር) የ"እንኳን ደስ ያላችሁ" መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን፣ "ኮሌጃችን በአካውንቲንግ እና ፋይናንስ በዲግሪ መርሃ ግብር ለመጀመሪያ ጊዜ ተማሪዎችን አስመርቋል" ብለዋል። አያይዘውም ሲልከን ቫሊ ኮሌጅ የመክፈል አቅም ለሌላቸው ዜጎች ነጻ የትምሕርት ዕድል እየሰጠ እንደሚገኝም ጠቁመዋል።

በኮሮና ቫይረስ ወቅት ትምሕርት ላይ የነበሩ፣ በኋላም በሌሎች ተጽዕኖዎች መሃል ሆነው ለተማሩ ተማሪዎች ምስጋናቸውን አቅረበዋል።

በመጀመሪያ ዲግሪ፤ አካውንቲንግና ፋይናንስ፣ ማኔጅመንት፣ በማስተርስ፤ ቢዝነስ ማኔጅመንትና ሂዩማን ሪሶርስ ማኔጅመንት፣ እንዲሁም በደረጃ 4 በሰባት የቴክኒክ እና ሞያ ስልጠና ዘርፎች 850 ተማሪዎች የተመረቁ ሲሆን፣ ከእነዚህም ውስጥ 54 በመቶ ሴቶች መሆናቸው ተገልጿል።

በዛሬ በተካሄደው የምርቃት ሥነሥርዓት ላይ የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች የዋንጫ እና የሜዳልያ ሽልማት ከኮሌጁ ዲን እና ከዕለቱ የክብር ዕንግዳ ተበርክቷል።

ኮሌጁ በማኔጅመንት 418 ተማሪዎችን ያስመረቀ ሲሆን፣ ከዚህ ውስጥ 315ቱ ሴቶች፣203ቱ ደግሞ ወንዶች ናቸው።

በማስተርስ ደረጃ  በኤክስቴንሽንና በመደበኛ ትምህርት ወንድ 109 ሴት 82 ተማሪዎችን አጠቃላይ 191 ተማሪዎች ማስመረቁን ተቋሙ ገልጿል።

https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌 ደራሲው የላዳ ሹፌር ነገ መጽሐፉን ያስመርቃል!

ጌታቸው ከበደ ይባላል። የላድ ታክሲ ሹፌር ነው። ከስራውም ጎን ለጎን በሥነጽሑፉም ላይ ተሳትፎ ያደርጋል።

ለረጅም ጊዜያት ሲጽፍው የቆየው የልቦለድ መጽሐፉ ቀኑ ደርሶለት ለህትመት ብርሃን በቅቷል።መጽሐፉንም ነገ እንደሚያስመርቅ ኤቨንት አዲስ ድረገጽ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

የጌታቸው ከበደ አዲስ መጽሐፍ "የወርቅ መርዝ" የተሰኘ ርዕስ ያለው ሲሆን በዘውግ ደረጃ ረጅም ልቦለድ ነው።

በ236 ገፆች የተቀነበበው መጽሐፉ በ413 ብር ለአንባቢያን ይቀርባል ተብሏል።በውስጡም 18 ምዕራፎችን ይዟል።

"የወርቅ መርዝ" ነገ ነሐሴ 19 2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00 ጀምሮ በብሔራዊ ቤተመዛግብት እና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት (ወመዘክር ) አዳራሽ ውስጥ በድምቀት ይመረቃል።

በዚህ የምርቃት ሥነሥርዓት ላይ ጸሐፊ ተውኔት አያልነህ ሙላቱ፣ ደራሲ ኃይለመለኮት መዋዕል፣አርቲስት ሽፈራው ታሪኩ፣ገጣሚ መንበረማርያም ኃይሉ እና ሌሎችም ይገኛሉ ተብሏል።

ደራሲው ስለመጽሐፉ ርዕስ በመግቢያው የሚከተለውን ብሏል" ይህ መጽሐፍ "የወርቅ መርዝ" ተብሎ ሲሰየም በወርቅ የተመሰለው ፍቅር ሲሆን በመርዝ የተመሰለው ደግሞ ፍቅርን ተከትለው የመጡትን አሉታዊ ተፅእኖዎች ነው"።

የሥነጽሑፍ ቤተሰብ የሆነ ሁሉ በነገው የምርቃት ሥነሥርዓት ላይ እንዲገኙለት ጥሪውን አስተላልፏል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌የወጣቷ ድምጻዊት ሔለን አበራ የሙዚቃ ድግስ!

ወጣቷ ድምጻዊት ሔለን አበራ በመድረክ ላይ በቀጥታ የሙዚቃ ስራዎቿን የምታቀርብበት የሙዚቃ ድግስ ነገ ነሐሴ 19 2016 ዓ.ም ከምሽቱ 12:00 ጀምሮ ሳር ቤት አካባቢ በሚገኘው ተምሳሌት ኪቺን ውስጥ ይካሄዳል።

በዚህ የሙዚቃ ዝግጅት ልዩ ልዩ የሙዚቃ ስራዎችን እንደምታቀርብ ድምጻዊት አስታውቃለች።

ድምጻዊት ሔልን አበራ በአዲሱ ዓመት የጃዝ ጣዕም ያለው የሙዚቃ አልበሟን ለአድማጮች እንደምታደርስ ለኤቨንት አዲስ ድረገፅ የተናገረች ሲሆን ነገ የሚካሄደው የሙዚቃ ዝግጅትም የአልበሟ መደረሻ እንደሆነ ገልጻለች።

https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌የባቡጂ የቀብር ሥነሥርዓት

አርቲስት ጌታቸው እጅጉ (ባቡጂ) ከትላንትና በስቲያ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።

ባቡጂ ሼፉ 2፣ ወደ ልጅነት፣ ጀማሪ ሌባ፣ እድሜ ለሴት የተሰኙና ሌሎች ከ60 በላይ ፊልሞች ላይ በመተወን በሙያው የራሱን አስተዋፅዖ ያበረክተው አርቲስት ጌታቸው እጅጉ (ባቡጂ) ነሐሴ 18 2016 ዓ.ም በመኖሪያ ቤት ሕይወቱ ማለፉ ይታወሳል።

የአርቲስት ጌታቸው እጅጉ(ባቡጂ) የቀብር ሥነሥርዓት 
ዛሬ ነሐሴ 20 2016 ዓ.ም ከቀኑ 8:30 ላይ በቅዱስ ዮሴፍ ቤተክርስቲያን ወዳጅ ዘመዶቹ በተገኙበት ይፈፀማል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
Event Addis Media
Photo
📌አርቲስት ኩራባቸው ደነቀ አረፈ

አርቲስት ኩራባቸው ደነቀ ማረፉን ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ከጋዜጠኛ ግርማ ፍስሃ ያገኘው መረጀ ያመለክታል።

ስለ አርቲስት ኩራባቸው ደነቀ ከተወዳጅ ሚዲያ ያገኘው የሚከተለውን ይመስላል።

"አርቲስት ኩራባቸው የ1979 ከአዲስ አበባ የቴአትር አርትስ ዲፓርትመንት የተመረቀ ሲሆን ባለፉት 35 አመታት ከትወና እስከ ዝግጅት ሙያዊ አደራውን በሚገባ የተወጣ ሰው ነው፡፡

ኩራባቸው በተለይ በአርትስ ቲቪ በተሰራው "እረኛዬ" በተባለው የቲቪ ተከታታይ ድራማ ድንቅ የትወና ብቃቱን አሳይቷል፡፡

አርቲስት ኩራባቸው ደነቀ የተወለደው በ1957 ዓ.ም በሐረር ከተማ ልዩ ስሙ ሸንኮር በሚባለው መንደር ውስጥ ነው።

አርቲስት ኩራባቸው ደነቀ በትወና በመድረክ ቴአትሮች ላይ ከ1982 ዓ ም ጀምሮ ከተሳተፈባቸው በጥቂቱ  በህፃናትና ወጣቶች ቴአትር 'የዝናቧ እመቤት ' እና 'የገንፎ ተራራ' ቴአትሮች ፤ በሀገር ፍቅር ቴአትር 'የጨረቃ ቤት' ፣ 'ዓይነ ሞራ' ፣ 'ንጉሥ ሊር' ፣ 'ፍሬህይወት' ፣ 'ጥሎሽ' ፣ 'አሉ' ፣ 'ጣውንቶቹ' ፣ 'ከራስ በላይ ራስ' እና 'የሸክላ ጌጥ' ቴአትሮች ፤ በቴአትርና ባህል አዳራሽ 'የጫጉላ ሽርሽር' ቴአትር ፤ በራስ ቴአትር 'ቅርጫው' ቴአትር ይገኙበታል።

ከዳይሬክቲንግ ሥራዎቹ ካዘጋጃቸው የመድረክ ቴአትሮች በሀገር ፍቅር ቴአትር 'ስጦታ'፣'ጥሎሽ'እና 'መዳኛ' ቴአትሮች ፤ በቴአትርና ባህል አዳራሽ 'ሶስና'፣'አንድ ክረምት'፣ጥቁሩ መናኝ'  እና የጫጉላ ሽርሽር'(ዝግጅት በተዋንያን ነበር) ቴአትሮች ፤ በራስ ቴአትር 'ትንታግ' የተሰኘ ቴአትር በማዘጋጀት ተሳትፏል።

ካዘጋጃቸው ሙዚቃዊ ድራማዎች መካከል በተለይ በአንጋፋዋ አርቲስት አስናቀች ወርቁ ህይወት ላይ ተመስርቶ የተፃፈውና ያዘጋጀው  'አስናቀች ኢትዮጵያ' የተሰኘው ሥራ ስራ ይጠቀሳል።

'የተዋቡ እጆች'የተሰኘ ፊልም አዘጋጅቷል።

በበርካታ የሬድዮ ድራማዎች ላይ በተለይም ደራሲ ሀይሉ ፀጋዬ በፃፋቸውና በቅዳሜ መዝናኛ ፕሮግራም በተላለፉት በአብዛኞቹ ተሳትፏል።

ለሁለት ለሁለት ሳምንታት በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የቀረቡ 'ጩኒና ቾምቤ'የተሰኘ የህፃናት ቴአትር እና 'የማለዳ ጤዛ' የተሰኘው ድራማ ይገኙበታል።

የቴሌቪዥን ድራማዎች 'ገመና 1' እና 'ገመና 2' እና "እረኛዬ"  ድራማዎች ብዙ አድናቂዎች ያፈሩለት ስራዎች ናቸው።

አርቲስት ኩራባቸው ደነቀ ከወ/ሮ አስቴር ታደሰ ጋር በ1985 ዓ. ም በጋብቻ ተሳስሮ ሁለት ወንዶች እና አንዲት ሴት ልጆች አፍርቷል።

@EventAddis1
📌የአርቲስት ኩራባቸው ደነቀ የቀብር ሥነሥርዓት

የአርቲስት ኩራባቸው ደነቀ የቀብር ሥነሥርዓት ነገ ነሐሴ 21 ቀን 2016 ዓ.ም በቀጨኔ መድኃኒያለም ቤተክርስቲያን ከቀኑ 5:00 እስከ 6:00 ይፈፀማል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌ካናል-ፕላስ የኢትዮጵያን ገበያ ለቆ ሊወጣ ነው

የፈረንሳዩ ሳተላይት ቴሌቪዥን ቻናል ካናል ፕላስ (Canal +) የኢትዮጵያ ገበያን ለቆ ሊወጣ መሆኑን መሠረት ሚድያ ዘግቧል።

ከሶስት ዓመት በፊት ወደ ኢትዮጵያ የገባው ቻናሉ ለበርካታ ተጠቃሚዎች አገልግሎት እየሰጠ ቢቆይም በበቂ ሁኔታ ገበያውን ተቀላቅሎ ትርፍ ማግኘት ስላልቻለ ውሳኔው ላይ እንደደረሰ ታውቋል።የስፖርት ቻናሉ ከተቋረጠ በርካታ ግዜም ተቆጥሯል።

"የስፖርት ቻናሉ መቋረጥን ተከትሎ ሌሎቹ ቻናሎች በቅርብ ሳምንታት ይቋረጣሉ። ይህም ማለት ኤጀንት ከነበረው ብሩህ Plc ጋር ያለውን ስራውን ያቆማል" ብሎ አንድ ጉዳዩን የሚያውቅ ምንጭ መረጃ ሰጥቷል።

አክሎም "ዋናው እና ግልፁ ምክንያት ገበያውን በደንብ ሰብሮ መግባት አለመቻሉ ነው" ብሏል።

ካናል ፕላስ የኢትዮጵያ ስራውን የጀመረው ከኢዩቴልሳት ጋር ስምምነት ተፈራርሞ የነበረ ሲሆን ስርጭቶቹንም በኢዩቴልሳት 7ሲ ቻናሎች ላይ ሲያስተላልፍ ቆይቷል።

ካናል ፕላስ በኢትዮጵያ ከስታር ታይምስ እና ዲ ኤስ ቲቪ ቀጥሎ ሶስተኛው የሳተላይት ቴሌቪዥን ቻናል መሆን ችሎ ነበር።

📍መረጃው የመሰረት ሚዲያ ነው።

ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌የአንደኛው "ሚዲያ አዋርድ" ተሸላሚዎች !

አንደኛው "የሚዲያ አዋርድ" የሽልማት ሥነሥርዓት ዛሬ ነሐሴ 22 ቀን 2016 ዓ.ም አመሻሽ ላይ ካዛንቺስ በሚገኘው በኢንተርሌግዠሪ ሆቴል ተከናውኗል።

በዚህ መሰረት የተሸላሚዎች ዝርዝርም ታውቋል።

በምርጥ የቴሌቪዥን መዝናኛ ፕሮግራም ሴት አቅራቢ: አስካለ ተስፋዬ

በምርጥ ዜና ዘጋቢ ዘርፍ: ግርማ ፍሰሃ

ምርጥ የስፖርት ጋዜጠኛ: መንሱር አብዱልቀኒ

በምርጥ ዶክመንተሪ አዘጋጅ: አክሊሉ ሲራጅ

በምርጥ የሬድዮ ሴት ዜና አንባቢ: ለምለም ዮሐንስ

በምርጥ የሬድዮ ወንድ ዜና አንባቢ: ሶዶ ለማ

በምርጥ የቴሌቪዥን ሴት የዜና አንባቢ: የሸዋ ማስረሻ

በምርጥ የቴሌቪዥን ወንድ የዜና አንባቢ: ሠለሞን ኃይለኢየሱስ

በምርጥ የቴሌቪዥን መዝናኛ ፕሮግራም ወንድ አቅራቢ :ሀብተማርያም መንግስቴ

በምርጥ የአምድ ፀሃፊ:አክሲያ ኢታሎ

በምርጥ የምርመራ ዘገባ: ክብረት ካህሳይ

በምርጥ ዲጄ : ዲጄ ኪንግስተን (ወዝወዝ አዲስ)

ልዩ ተሸላሚ: የፎቶግራፍ ጋዜጠኛ ዳኜ አበራ

ምርጥ የትምህርት ፕሮግራም: የእርቅ ማዕድ የሬድዮ ፕሮግራም

ምርጥ የሬድዮ ፕሮግራም: ታዲያስ አዲስ

በህዝብ ድምፅ ብቻ የተመረጠ የዓመቱ ምርጥ ጋዜጠኛ: አንዋር ጀማል

የህይወት ዘመን ተሸላሚ: መዓዛ ብሩ

ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌ሶስተኛው የሺህ ጋብቻ ካርኒቫል ኤክስፖ 

ያሜንት ኤቨንትስ ከባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ጋር በመተባበር የሚዘጋጀው የየሺህ ጋብቻ 2017 መርሐግብር ለሶስተኛ ጊዜ ይካሄዳል ተብሏል።

ይህንም አስመልክቶ ባህልና ስፖርት ሚኒስቴር እና ያሜንት ኤቨንትስ  በጋራ ለመስራት የሚያስችል ስምምነት አድርጓል።

በ2017 የሺህ ጋብቻ ካርኒቫል ኤክስፖ ላይ ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት ጋብቻቸውን የሚፈፅሙ ጥንዶች የሚሳተፍበት መሆኑ ለየት ያደርገዋል ተብሏል።

ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌ተዋናይት ፍናን ህድሩ እና ኢንፊኒክስ ኢትዮጵያ

ኢንፊኒክስ ኢትዮጵያ ተዋናይት ፍናን ህድሩን የብራንድ አምባሳደር በማድረግ አብሮ ለመስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ዛሬ ነሐሴ 23 2016 ዓ.ም በሐያት ሪንጀሲ ተፈራርመዋል።

ስምምነቱ የአንድ ዓመት ቆይታ አለው የተባለ ሲሆን ኢንፊንክስ ኢትዮጵያ ተዋናይት ፍናን ከብራንዱ ጋር በቅርበት በመስራት በተለይም ወጣቱን ከብራንዱ ጋር በማስተዋወቅ የራሷን ድርሻ ትወጣለች ብሎ እንደሚጠበቅ ገልጿል።

ተዋናይት ፍናን በፊልሙ ኢንደስትሪ በተለይም በወጣቱ ዘንድ ያገኘችውን ተቀባይነት እና ያላት የፈጠራ ችሎታ ከኢንፊኒከስ ብራንድ ጋር አብሮ ለመስራት ምቹ እንደሚያደርገው የተገለፀ ሲሆን ኢንፊኒከስ ከሚታወቅበት የስልክ ገበያ በተጨማሪ ወደ ቲቪ፣ ላፕቶፕ፣ ስማርት ዋች፣ ኤር ፖድ እና መሰል ምርቶችን ወደ ገበያው ለማቅረብ ያለውን ዓላማ በመደገፍ ረገድ ጉልህ ተሳትፎ ይኖራታል ተብሏል።

ኢንፊኒከስ ዓለም አቀፍ የኤሌከትሮኒክስ አምራች ኩባንያ ሲሆን በተለይም በሚያመርታቸው የስማርት ስልኮች አለም አቀፍ ተቀባይነትን ያገኘ ብራንድ ነው::

በምርቶቹ አዳዲስ ቴከኖሎጂዎችን በማስተዋወቅ የሚተወቀው ኢንፊኒከስ አሁን ደግሞ በቲቪ፣ ላፕቶፕ፣ ስማርት ዋች፣ ኤር ፖድ እና የመሳሰሉት ምርቶቹ ወደ ገበያው እየመጣ ይገኛል፡፡

ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌የድምጻዊት ቬሮኒካ አዳነ አልበም ተለቀቀ

የድምጻዊት ቬሮኒካ አዳነ "መጠሪያዬ" የተሰኘ አልበም ዛሬ ሐሙስ ነሐሴ 23 2016 ዓ.ም በራሷ በቬሮኒካ አዳነ ዩቲዩብ ቻናል እና ዓለም አቀፍ የሙዚቃ መተግበሪያዎች ላይ እንደተለቀቀ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ተመልክቷል።

የድምጻዊት ቬሮኒካ አዳነ"መጠሪያዬ" አልበም 12 የሙዚቃ ስራዎችን የያዘ ሲሆን አልበሙ ላይ በግጥም እና ዜማ አቤል ሙሉጌታ፣አቡዲ እና ሱራፌል የሺጥላ ተሳትፈዋል በተጨማሪም በሙዚቃ ቅንብር ታምሩ አማረ ፤አዲስ ፍቃዱ፣ አብርሃም ኪዳኔ ፣ሮቤል እንዳለ በሚክሲንግ እና ማስተሪንግ ሠለሞን ኃ/ማሪያም ተሳትፈውበታል።

አልበሙ ላይ ሁለት የሙዚቃ ቪዲዮዎች ያሉት ሲሆን ክሊፑ በአሜሪካ አትላንታ መሠራቱን ተነግሯል።

ይህ አልበም አጠቃላይ ከስድስት ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የወጣበት ሲሆን የአልበሙ ሙሉ በሙሉ ወጪ በድምጻዊት ቬሮኒካ አዳነ ፕሮዲዩስ ተደርጓል።

ይህ አልበም ዞጃክ ወርልድ ዋይድ የተሰኘ ዓለም አቀፍ የሙዚቃ ካምፓኒ በ160,000 ዶላር በመላው ዓለም ለማከፋፈል ከአርቲስቷ ጋር ተስማምተዋል፡፡

ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌 ድምጻዊ ዳዊት ፅጌ እና ሐበሻ ቢራ

ድምፃዊ ዳዊት ፅጌ "የእልል ያልኩ ሐበሻ" የብራንድ አምባሳደር ሆኖ ተመረጠ።

ወጣቱ ድምጻዊ ዳዊት ፅጌ የሀበሻን ባህላዊ እሴቶችን እንዲሁም ሐበሻ ቢራን እንዲያስተዋውቅ በሐበሻ ቢራ ፋብሪካ እንደተመረጠ በዛሬው ዕለት ይፋ ተደርጓል።

በ"የኔ ዜማ" አልበም እና በተለያዩ ነጠላ ዜማዎች ተወዳጅነትን ያተረፈው  ድምፃዊ ዳዊት ፅጌ ብራንድ አምባሳደር ሆኖ በመመረጡ የሀበሻ መገለጫ የሆኑ እሴቶች በዓለም አደባባይ ጎልተው እንዲወጡ ይሰራል ተብሏል።

"እልል ያልኩ ሀበሻ "በሐበሻ ቢራ አዘጋጅነት ዛሬ ነሐሴ 23 2016 ዓ.ም በቃና ዌርሀውስ ለየት ያለ ፕሮግራም የተዘጋጅቶ የነበረ ሲሆን የኢትዮጵያዊያን ባህል፤ ዕሴት ፣ ማንነት እና ወግ ላይ ያተኮሩ በተለያዩ ክዋኔዎች ባህላዊውን ከዘመነኛው ጋር ያሰናሰኑ ዝግጅቶች ተካሄደዋል።

በዚህም ዝግጅት በምግብ አዘገጃጀት፤በፋሽን ትርዒት፤ በሙዚቃ እና በሌሎች የጥበብ ስራዎች ባህላዊው ከዘመናዊ ጋር በማሠናሠል ስራ የበረቱ ባለሞያዎች ስራዎቻቸውን አቅርበዋል።

የዛሬው የዝግጅት ዓላማ የሀበሻ መገለጫ የሆኑ አለባበሰ፣ምግብ ዝግጅት ፣ሙዚቃ እና የመሳሰሉትን በተለያዩ ሀገረኛ መድረኮች ብሎም በዓለም አቀፍ ደረጃ እንዲታወቁ ማድረግ እና እነዚህ ሁነቶች ላይ የሚሳተፉ ባለሙያዎች ጎን ለጎን ራሳቸውንም እንዲያስተዋውቁ መደገፍ  እንደሆነም ተገልጿል።

ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌በእረፍት ቀንዎ ቴአትር ይመለከቱ !

አንጋፋው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር  እና የቦሌው ዓለም ሲኒማ አርብ፣ ቅዳሜ እና እሁድ እነዚህን ተውኔቶች ለታዳሚያን ያቀርባሉ።

📍 የፍቅር ካቴና

ድርሰትና ዝግጅት: አለልኝ መኳንት ፅጌ
ቀን: አርብ
ሰዓት: 12:00
ቦታ: ዓለም ሲኒማ

📍 "እሳት ወይ አበባ"

ድርሰት: ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን እንደጻፈው
ዳንስና ዳንስ ቅንብር: ሽፈራው ታሪኩ ቢረጋ
ቀን: አርብ
ሰዓት:11:30
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር

📍 ባሎች እና ሚስቶች

ድርሰት: ውዱ አለን
አዘጋጅ: ሳሙኤል ተስፋዬ
ቀን: ቅዳሜ
ሰዓት: 8:00
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር

📍 ባቡሩ

ድርሰት: አርኖልድ ሪድሊ
አዘጋጅ:ራሔል ተሾመ መሐመድ
ቀን: ቅዳሜ
ሰዓት:11:30
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር

📍 ሸምጋይ

ድርሰት:ታደለ አያሌው
አዘጋጅ: ሳሙኤል ተስፋዬ
ቀን: እሁድ
ሰዓት: 8:00
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር

📍 እምዩ ብረቷ

ድርሰት: ቤልቶልት ብሬሽት
አዘጋጅ: ማንያዘዋል እንዳሻው
ቀን: እሁድ
ሰዓት:11:30
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር

የእናንተው ኤቨንት አዲስ ድረገፅ መልካም የእረፍት ቀን ይሁንላችሁ ይላል !

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌የልጅ ሚካኤል "የድሬ ልጅ" ሙዚቃ ቪዲዮ

ሙዚቀኛ ልጅ ሚካኤል (ፋፍ) "አዲስ አራዳ" የተሰኘ ሙሉ አልበሙን በዚህ ሳምንት ነሐሴ 22 2016 ዓ.ም ለአድማጮች አድርሷል።

"አዲስ አራዳ" አልበም 15 የሙዚቃ ስራዎችን ይዟል። የሙዚቃ ቅንብሩን ዮናስ ነጋሽ (ዮኒ) ሰርቶታል። አልበሙ ላይ ሳያት ደምሴን ጨምሮ በአጃቢነት (ፊቸሪንግ)የተሳተፉ ሙዚቀኞች እንዳሉበት ኤቨንት አዲስ ተመልክቷል።

እዚህ አልበም ውስጥ ከተካተቱ ስራዎች "የድሬ ልጅ"ለተሰኘው ሙዚቃ የሙዚቃ ቪዲዮ ተሰርቶለታል። ይህም የሙዚቃ ቪዲዮ ዛሬ አርብ ነሐሴ 24 2016 ዓ.ም በሙዚቀኛው የዩቲዩብ ቻናል በኩል ይለቀቃል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌የገጣሚና ሐያሲ በለው ገበየሁ መጽሐፍ ምርቃት

የገጣሚና ሐያሲ በለው ገበየሁ "እንኳንም መሃይም ሆንኩ" የተሰኘ መጽሐፍ ነገ ቅዳሜ ነሐሴ 25 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ጀምሮ በብሔራዊ ቤተመዛግብት እና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት (ወመዘክር) አዳራሽ ውስጥ ይመረቃል።

በዚህ የመጽሐፍ ምርቃት ሥነሥርዓት ላይ ዘነበ ወላ፣ፀጋዬ ደቦጭ፣ ኃይሉ ፀጋዬ፣ በኃይሉ ገብረመድህን፣ ዘመዱ ደምስስ፣የሻው ተሰማ፣ታምሩ ብርሃኑ፣አንዱዓለም አባተ ሀሳቦቻቸውን ያጋራሉ ተብሏል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌"ብርቱ ንቁ ጀግና ዜጋ" ለአንድ ሺህ ሰዎች!

አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች ስፖርት ቢሮ፣ የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ እና ሄኖክ ኪዳነወልድ ስፖርት ስልጠናዎች በመተባበር "ብርቱ ንቁ ጀግና ዜጋ" በሚል መሪ ሀሳብ በውፍረት፣ በኮልሰትሮል፣ በስኳር፣ በደም ግፊት እና በተለያዩ ሱሶች ውስጥ ያሉና የመክፈል አቅም የሌላቸው 1000 ሰዎችን በነጻ የስፖርት እንቅስቃሴ፣የሥርዓተ ምግብና የህይወት ክህሎት ስልጠና ለመስጠት ዝግጅታቸውን ማጠናቀቃቸውን በዛሬው ዕለት ይፋ አድርገዋል።

"ብርቱ ንቁ ጀግና ዜጋ" የአካል እንቅሳቃሴ ስልጠና ጳጉሜን 2 ቀን 2016 ዓ.ም በወዳጅነት አደባባይ የሚጀመር ሲሆን ከወዳጅነት አደባባይ በተጨማሪም የአዲስ አበባ አምስቱንም የመውጫ በሮች ያማከሉ  አምስት የስልጠና ቦታዎች እንደተዘጋጁ ተገልጿል።

በኮሌስትሮል ፣በስኳር ፣በደም ግፊት፣ በውፍረት ፣በሱስ እንዲሁም ሌሎች ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች የተጠቁ ነዋሪዎች በስልጠናው የሚሳተፉ ሲሆን ጤናቸውን በአካል እንቅስቃሴ ማስተካከል የሚፈልጉ ሰዎችም በአቅራቢያቸው ካለ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ሄደው መመዝገብ እንደሚችሉ ተገለጿል።

ስልጠናው ለሶስት ወራት የሚቆይ ሲሆን በዓመት ሶስቴ እንደሚዘጋጅና ቀጣይነት እንዳለው ተነግሯል።

ሥልጠናው ላይ የሥርዓተ ምግብና የህይወት ክህሎት ስልጠና ባለሙያዎች ለሰልጣኞች እገዛ የሚያደርጉ ይሆናል ተብሏል።በነፃ የሚሰጠው ስልጠና በገንዘብ ቢለወጥ ሠላሳ ሚልየን ብር ገደማ እንደሚያወጣ ተነግሯል።

ይሄን ስልጠና ለመስጠት ሶስቱ አካላት በቅንጅት ለመስራት የስምምነት ፊርማ ዛሬ ነሐሴ 25 2016 ዓ.ም በካፒታል ሆቴል ተፈራርመዋል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌በቀን 150 ሺህ መጻሕፍትን የሚጠርዝ ማሽን!

በቀን 150 ሺህ መጻሕፍትን የሚጠርዝ ዘመናዊ ማሽን ወደ ሥራ ማስገባቱን የትምህርት መሳሪያዎች ማምረቻና ማከፋፈያ ድርጅት አስታወቀ።

የድርጅቱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ተመስገን ጋሩማ (ዶ/ር) እንደገለጹት፥ በ178 ሚሊዮን ብር ወጪ ከውጭ ሀገር የገባው አዲስ ማሽን በቀን እስከ 150 ሺህ መጻሕፍት የመጠረዝ አቅም አለው።

ማሽኑ በሰዓት 7 ሺህ መጻሕፍትን መጠረዝ ይችላል ያሉት ዋና ሥራ አስፈጻሚው፤ ድርጅቱ በ3 ፈረቃ እየሠራ በመሆኑ በቀን ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው መጻሕፍትን መጠረዝ እንደሚቻል ጠቁመዋል።

በርካታ የትምህርት መርጃ መጻሕፍት ከውጭ ሀገራት እንደሚገቡ ገልጸው፤ አዲሱ ማሽን መጻሕፍቱን በሀገር ውስጥ በመጠረዝ የውጭ ምንዛሬ ወጪን ለመቀነስ እንደሚረዳ ተናግረዋል።

በሀገር ውስጥ የማዘጋጀት ሒደቱ መጻሕፍት ከውጭ ሀገራት ተጓጉዘው ሲገቡ የሚወስደውን ረጅም ጊዜ የሚቀንስ መሆኑም የተገለጸ ሲሆን፤ ማሽኑ በዛሬው ዕለት ለምረቃ በቅቷል።

📌መረጃው የኢቢሲ ነው።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
"የካሲናዬ" ፊልም አዘጋጅና ማያ ሚዲያ ይቅርታ ጠየቁ

በብርሃኑ ወርቁ ተዘጋጅቶ የቀረበው "ካሲናዬ" የተሰኘ የአማርኛ ፊልም ከቀናት በፊት በማያ ሚዲያ በኩል የተለቀቀ ሲሆን ፊልሙ ላይ አንዲት ሴት፣ ሱሪ አድርጋ፣ሊፒስቲክ ተቀብታ  በቤተክርቲያ ውስጥ መግባቷ ይህም ድርጊቷ በፊልሙ ውስጥ መካተቱ የቤተክርስቲያንን ሥርዓት አይወክልም በሚል ብዙ የኢትዮጵያ ኦሮቶዶክስ ተዋሕዶ ምዕመናንን አሳዝኗል:: በዚህ ምክንያት በማያ ሚዲያ እና በፊልሙ አዘጋጆች ላይ ተቃውሞ ተነስቷል።

ከደቂቃዎች በፊትም ማያ ሚዲያና የፊልሙ አዘጋጅ በማያ ሚዲያ የይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገፁ ላይ በይፋ ይቅርታ እንደጠየቁ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ተመልክቷል።

ማያ ሚዲያ እና የፊልሙ አዘጋጅ"በቅርቡ በማያ ሚዲያ "#ካሲናዬ" የተሰኘ አዲስ ኢትዮጵያዊ ይዘት ያለው ፊልም መለቀቁ ይታወሳል፡፡ሃይማኖታዊ ሥርአቱን ያልጠበቀ ትዕይንት በፊልሙ ውስጥ ባለማስተዋል በመካተቱ ምክንያት ለተፈጠረው ስህተት የፊልሙ ባለሙያዋች፣ የፊልሙ አዘጋጅ እና ማያ ሚዲያ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንን እና የእምነቱን ተከታዮች በሙሉ ልባዊ የሆነ ይቅርታ እንጠይቃለን" ያሉ ሲሆን

በተጨማሪም " ቅሬታ ያስነሳው የፊልሙን ክፍል በመቁረጥ ለእይታ አብቅተናል "ብለዋል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1