Event Addis Media – Telegram
Event Addis Media
9.62K subscribers
6.12K photos
14 videos
4 files
4.74K links
Connect with Addis artistic community!

Website: https://eventaddis.com

Contact: @Tmanaye
Download Telegram
📌"እሺ አትለኝም ወይ" ሙዚቃ ነገ ይለቀቃል

የድምጻዊት ማህሌት ወንድሙ "እሺ አትለኝም ወይ" የተሰኘ አዲስ ነጠላ ሙዚቃ ነገ መስከረም 10 ቀን 2017 ዓ.ም በሰዋሰው መተግበሪያ በኩል ለአድማጮች ይደርሳል። በዚህ ሙዚቃ ላይ በግጥም ወንድወሰን ይሁብ ፣ በዜማ ምህረትአብ ደስታ፣ሙዚቃ ቅንብር ፋኑ ጊዲቦ ተሳትፉበታል።

ድምጻዊት ማህሌት ከዚህ ቀደም "አምባሰል" የተሰኘ ነጠላ ሙዚቃ ለአድማጮች ማድረሷ አይዘነጋም።

ለተጨማሪው:https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌 የድምጻዊት ለምለም ኃ/ሚካኤል "ትዝታ" የሙዚቃ ቪዲዮ ነገ ይለቀቃል

የድምጻዊት ለምለም ኃ/ሚካኤል "ትዝታ" የተሰኘው የሙዚቃ ቪዲዮ ነገ መስከረም 10 ቀን 2017 ዓ.ም በናሆም ሪከርድስ በኩል ይለቀቃል።

ሙዚቃው ላይ በግጥም ወንደሰን ይሁብ፣በዜማ አንተነህ ወራሽ፣ በቅንብር አበጋዝ ክብረወርቅ ሺዎታ ተሳትፈውበታል።የሙዚቃው ቪዲዮው ዳይሬክተር ኤዲተር እመቤት ካሣ ነች።ይህ የሙዚቃ ስራ "ማያዬ" ከተሰኘው የሙዚቃ አልበም ውስጥ የተካተተ ነው።

ለተጨማሪው:https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌አርቲስት አዜብ ከግማሽ ቀን እስር በኃላ ተፈታለች

ሰሞኑን አርቲስት አዜብ ወርቁ "ልማት የሰውን ልጅ ሲያፈርስ በዓይኔ አየሁት!" የሚል ጽሁፍ በማህበራዊ ሚዲያዋ ካጋራች በኋላ ጽሁፉ መነጋገሪያ ሆኖ እንደነበርና በኋላም ከማህበራዊ ገጿ ጽሁፉን ማንሳቷን ማስታወቋ ይታወሳል።

በዚህ ጽሑፍ መነሻ ይሁን በሌላ ለጊዜው ባልታወቀ ምክንያት አርቲስት አዜብ ወርቁ ዛሬ መስከረም 9 2017 ዓ.ም በ3ኛ ፖሊስ ጣቢያ ለግማሽ ቀን ያህል ታስራ እንደነበር ተሰምቷል።

ዛሬ በቁጥጥር ስር ውላ የነበረችው አዜው ወርቁ ለግማሽ ቀን ያህል በእስር ከቆየች በኋላ መለቀቋን ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ሰምቷል።

ለተጨማሪው:https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌"ጉርሻና ቅምሻ" መጽሐፍ እሁድ ይመረቃል

በደራሲና ገጣሚ ማትያስ ከተማ የተፃፈዉ "ጉርሻና ቅምሻ" የተሰኘ አዲስ መፅሃፍ የሀገራችን ደራሲዎችና የኪነጥበብ ባለሙያዎች በተገኙበት እሁድ መስከረም 12 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 3:00 ጀምሮ በኢትዮጵያ ቤተመዛግብት እና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት (ወመዝክር) አዳራሽ ውስጥ ይመረቃል።

በዕለቱም ደራሲ አበራ ለማ፣ ደራሲ ኃ/መለኮት መዋዕል ፣ፀሐፊተውኔት አያልነህ ሙላቱ፣ ደረሲ አበረ አዳሙ ፣ጋዜጠኛ ግሩም ተበጀ፣ አዲስ ዘገየ፣ ቤተማርያም ተሾመ እና ሌሎችም ሀሳቦቻቸውን ያጋራሉ ተብሏል።

ለተጨማሪው:https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
የኢትዮጵያ ፊልሞች በአውሮፓ ለእይታ ሊቀርቡ ነው።

በሐበሻቪው አዘጋጅነት በለንደን ለ5ተኛ ጊዜ እንዲሁም በማልታ ለመጀመሪያ ጊዜ ለእይታ ይቀርባሉ ተብሏል።

ለእይታ ከሚቀርቡ ፊልሞች ውስጥ አፊኒ፣አባይ ወይስ ቬጋስ፣ዝምታዬ ፣ላምባዲና የተሰኙ ፊልሞች እንደሚገኙበት ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ሰምቷል።

አምስተኛው የፊልም ፌስቲቫል በለንደን እና የመጀመሪያው ፊልም ፌስቲቫል በማልታ ሊካሄድ ነው ።በዓመት አንድ ጊዜ በለንደን ፊልም ፌስቲቫል ዝግጅት ይደረጋል። ዘንድሮም ለ5ኛ ጊዜ ይህው ሁነት ይቀጥላል።

ለመጀመሪያ ጊዜም በደሴታማዋ ሀገር ማልታ የኢትዮጵያ ፊልም ፌስቲቫል ይካሄዳል።

ከሰሞኑ ቀንም ማልታ 60ኛ የነፃነት በዓሏን እያከበርች ትገኛለች። ሐበሻ ቪው ዝግጅቶችን አሰናድቷል።

ይህንንም ዝግጅት አስመልክቶ መስከረም 9 2017 ዓ.ም በሀያት ሪጀንሲ የሽኝት መርሐግብር ተካሂዷል።

"ሐበሻ ቪው" በውጪ ሀገር የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንን ከኢትዮጵያ ሥነጥበብ ፣ ኪነጥበብ ፣ክውን ጥበባት ጋር የሚያገናኙ ስራዎችን እየሰራ እንደሚገኝ ተገለጿል።

ለተጨማሪው:https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌"አፍሪካን እናክብር" ፌስቲቫል ሊካሄድ ነው

የ2024 "አፍሪካን እናክብር" ወይም "አፍሪካን እናክብር" ፌስቲቫል ከጥቅምት 27 እስከ ህዳር 1 ቀን 2017 ዓ.ም  በአዲስ አበባ ከተማ እንደሚከበር አዘጋጆቹ ገልጸዋል።

አፍሪካ ያላትን ባህል፣ ሥነ ጥበብ፣ ቅርስ፣ ቴክኖሎጂ እንዲሁም የቢዝነስ ሀብቶቿን ለዓለም ለማስተዋወቅ ፌስቲቫሉ ጠቀሜታ እንዳለው ነው የተገለፀው።

በተጨማሪም የአፍሪካ ሴቶች እና ወጣቶች እርስ በእርስ እንዲተዋወቁ እና እንዲገኙ ዕድል እንደሚፈጥርም ታምኖበታል።

የተለያዩ ሥራ ፈጣሪ ባለቤቶችም ስራዎቻቸውን እንዲያስተዋውቁ ያስችላል ተብሏል።

ፈስቲቫሉ ከፈረንጆቹ 2021 ጀምሮ ሲካሄድ የነበረ ሲሆን ለመጀመሪያ ጊዜ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በዚህኛው ዓመት ለማክበር በጋራ እንደሚሰራ ታውቋል።

የኢፌዴሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና የአፍሪካ ህብረትን ጨምሮ መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ያደረጉ የተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት ኤምባሲዎች በአዘጋጅነት ተሳትፈውበታል።

ለተጨማሪው:https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌"አዳብና ፌስቲቫል" ለ3ኛ ጊዜ ሊካሄድ ነው

የአዳብና በክስታኔ ዓለም አቀፍ ወጣቶች ማህበር ከባለድርሻ ተቋማት ጋር በመተባበር ያዘጋጁት "አዳብና ፌስቲቫል" ከመስከረም 16 እስከ ጥቅምት 5 ቀን 2017 ዓ.ም ለሶስተኛ ጊዜ በክስታኔ ቤተ-ጉራጌ በተለያዩ መርሐግብሮች እንደሚካሄድ ተገልጿል።

ይህ ፌስቲቫል በዋናነትም በጉራጌ ዞን ሶዶ ወረዳ ኬላ ከተማ መስከረም 18 ቀን 2017 ዓ.ም በአደባባይ በትልቅ ፕሮግራም እንደሚካሄድ አዘጋጆቹ አስታውቀዋል።

በአዳብና ፌስቲቫል ከ30 እስከ 100 ሺህ ጎብኚዎችን የሚጠበቁ ሲሆን በ50 እናቶች የተዘጋጀ 100 ኪሎ ክትፎንና 100 ኪሎ የክትፎ ቅቤ በአፍሪካ ድንቃድንቅ መዝገብ ላይ ለማስፈር ስራዎች እየተሰራ እንደሆነ ተነግሯል።

የአዳብና በክስታኔ ዓለም አቀፍ ወጣቶች ማኅበር አዳብና የጉራጌ የልጃገረዶችና ወንድ ወጣቶች ባህላዊ ጨዋታ መተጫጫ ፌስቲቫል በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ተቋም (ዩኔስኮ) እንዲመዘገብ ለማድረግ እየሠራ ይገኛል።

የአዳብና ባህል የልጃገረዶችና ወጣት ወንዶች ጨዋታና መተጫጫ ስነስርዓት ሲሆን ባህሉ በጥናት በተረጋገጠ መረጃ መሰረት 800 ዓመታት በፊት በክስታኔ ቤተ-ጉራጌ አካባቢ ለዘመናት ሲከበር እንደኖረ ማኀበሩ ገልጿል።

ይህ ድንቅ ባህል በተለያዩ ምክንያቶች ደብዝዞና ለጠፋ ታቃርቦ የነበረ ሲሆን የአዳብና በከስታኔ ዓለም አቀፍ ወጣቶች ማህበር ከአካባቢው የመንግስት መዋቅሮች ጋር በመሆን ባደረገው ጥረት ባህሉ ጥንታዊ ወጉና ቱባ ባህሉ ይዞ በከፍተኛ ሁኔታ በማንሰራራት በአሁን ሰዓት በአካባቢው ላይ በፌስቲቫልነት እየተከበረ እንደሚገኝ ተገልጿል።

ለተጨማሪው:https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌የደራሲ እስከዳር ግርማይ "የፈረንጅ ሚስት" መጽሐፍ በእንግሊዝኛ ተተረጎመ

የደራሲ እስከዳር ግርማይ "የፈረንጅ ሚስት" የተሰኘ መጽሐፍ "WHITE MAN'S  WIFE"በሚል ርዕስ በእንግሊዝኛ እንደተተርጎመ ተወዳጅ ሚዲያ ዘግቧል።

የእስከዳር ግርማይ አዲሱ የእንግሊዝኛ መጽሀፏ እውነተኛ ታሪኮችን ይተርካል። በተለይም በተለያየ የኑሮ ሁኔታ ላይ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ሴቶችንና የውጭ ሀገር ዜጋ ያገባ ኢትዮጵያዊ ወንድን ከምሳሌ እና ኹነቶች ጋር እያጣቀሰ የዕለት ተዕለት ህይወታቸውን ያስቃኛል።

መጽሀፉ መጀመሪያ የተጻፈው ''የፈረንጅ ሚስት'' በሚል ርዕስ እንደመሆኑ ተደራሽነቱ ኢትዮጵያዊያን ብቻ ማዕከል አድርጎ የተነሳ ነበር። ሆኖም ኢትዮጵያውያን ሴቶች ዜጎቻቸውን ሲያገቡ  የሚያጋጥማቸውን  እይታም ድንበር ተሻጋሪ እንደመሆኑ " WHITE MAN'S  WIFE"  ወደሚል ተተርጉሟል።

የመጽሀፍ ወደ እንግሊዝኛ መተርጎም የኢትዮጵያ ስነጽሁፍን ለአለምአቀፍ  አንባቢያን ተደራሽ  በማድረግ ረገድ የራሱን አስተዋጽኦ እንደሚያዋጣ ይታመናል ተብሏል።

የፈረንጅ ሚስትን  ወደ እንግሊዝኛ መጽሀፉን የተረጎመችው ራሷ ደራሲዋ ስትሆን፣ እንግሊዛዊው የሥነጽሁፍ ባለሙያው ክርስትያን ሀሪፎርድ መጽሀፉን  በአርታኢነት  ሲሠራው፣ አሳታሚው ጆርጅ ኦፍ ሚድልተን "ይህ  የኢትዮጵያን ሴቶች ታሪክ ብቻ ሳይሆን ስለሁላችን እና ስለምርጫዎቻችን ነው" በማለት አስተያየታቸውን መግቢያው ላይ አስፍረውበታል።

ለተጨማሪው:https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌"አንድ ቃል" የሙዚቃ ቪዲዮ ነገ ይለቀቃል

ድምጻዊ ሚካኤል በላይነህ ከወር በፊት ከለቀቀው "አንድ ቃል" የሙዚቃ አልበም ውስጥ ለአልበሙ መጠሪያ ለሆነው "አንድ ቃል" ለተሰኘው ሙዚቃ የተሰራው የሙዚቃ ቪዲዮ ነገ ረቡዕ መስከረም 15 2017 ዓ.ም በራሱ ዩቲዩብ ቻናል እንደሚለቀቅ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ሰምቷል።

ድምጻዊ ሚካኤል በላይነህ በማህበራዊ ትስስር ገፁም"ከአዲሱ አልበሜ አንድ ቃልን በቪዲዮ ረቡዕ ወደ እናንተ እንደማደርስ ስገልፅላችሁ በደስታ ነው" ብሏል።

ለተጨማሪው:https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌ማይንቴክስ ኤክስፖ በሕዳር ወር ይካሄዳል!

ሶስተኛው ማይንቴክስ የማዕድን እና የቴክኖሎጂ ኤክስፖ ከሕዳር 14 እስከ 17 ቀን 2017 ዓ.ም በሚሊኒየም አዳራሽ እንደሚካሄድ የማዕድን ሚኒስቴር አስታወቀ።

በኤክስፖው በርካታ ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች እንደሚሳተፉና ለሁነቱ አስፈላጊው ዝግጅት መደረጉን አመላክቷል።

ኤክስፖው ሀገር በቀል ድርጅቶች ምርታቸውን ለዓለም እንዲያስተዋውቁና እንዲሸጡ ምቹ እድል እንደሚፈጥር የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል።

የማዕድን ሚኒስቴር በማዕድን እና በቴክኖሎጂ ዘርፍ የተሰማሩ ድርጅቶች በኤክስፖው ላይ በመሳተፍ ምርት እና አገልግሎታቸውን እንዲያስተዋውቁ ጥሪውን አቅርቧል።

©️መረጃው አራዳ ኤፍ ኤም 95.1 ነው።

ለተጨማሪው:https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌የድምጻዊ አዲስ ሙላት "ዘማሌ" ሙዚቃ ተለቀቀ

የድምጻዊ አዲስ ሙላት "ዘማሌ" የተሰኘ ርዕስ የተሰጠው አዲስ ነጠላ ሙዚቃ ትላንትና ረቡዕ መስከረም 15 2017 ዓ.ም በድምጻዊው የዩቲዩብ ቻናል በኩል ለአድማጮች ደርሷል።

በ"ዘማሌ" የሙዚቃ ስራ ላይ በግጥም እንዳሻው አለማየሁ፣ በዜማ አዲስ ሙላት፣ በሙዚቃ ቅንብር ሚካኤል ኃይሉ(ሚኪ ጃኖ) ተሳትፈዋል።

ለተጨማሪው:https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌የድምጻዊ ማዲንጎ አፈወርቅ ሁለተኛ ዓመት የመታሰቢያ መርሐግብር ተከናወነ !

ከሁለት ዓመት በፊት መስከረም 17 2015 ዓ.ም በሞት የተለየን ተወዳጁ ድምፃዊ ማዲንጎ አፈወርቅ ሁለተኛ ዓመት መርሐግብር ዛሬ መስከረም 16 2017 ዓ.ም ተካሄዷል።

የህልፈቱን ሁለተኛ ዓመት ምክንያት በማድረግም ቤተሰቦቹ የሞያ አጋሮቹ እና አድናቂዎቹ በተገኙበትም የመታሰቢያ ዝግጅቱ በቅድስት ስላሴ ካቴደራል ተከናውናል።

ድምጻዊ ማዲንጎ አፈወርቅ በህይወት እያለ የሰራቸው የተጠናቀቁና እና በጅምር ላይ የነበሩ የማዲንጎ ሙዚቃዎችም አስፈላጊው ማስተካከያ ተደርጎላቸው ለህዝብ እንደሚቀርቡም ከተነገረ አንድ ዓመት ተቆጥሯል።

ድምጻዊ ማዲንጎ ሶስት የሙዚቃ አልበሞችን አበርክቷል "ስያሜ አጣሁላት" ፣ "አይደረግም" እና "ስወድላት" የአልበሞቹ ርዕሶች ናቸው ።

ለተጨማሪው:https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌የሳሌሚያ "ዓለም ብሬ" ሙዚቃ ተለቀቀ

በወጣቷ ድምጻዊት ሳሌሚያ በተለየ የሙዚቃ ቅርጽ የተሰራው "ዓለም ብሬ" የተሰኘ የሙዚቃ ከሰሞኑ በድምጻዊት "SALEMIA" የዩቲዩብ ቻናል በኩል ተለቋል።

የሳሌሚያ "አለም ብሬ" ሙዚቃ በእንግሊዘኛና አማርኛ የሰራችው የሙዚቃ ስራ ነው።

ለሙዚቃው የሙዚቃ ቪዲዮ የተሰርለት ሲሆን ዮናታን መስፍን ዳይሬክት አድርጎታል።

ለተጨማሪው:https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌"የፍቅር ካቴና" ዛሬ በልዩ ፕሮግራም ይቀርባል!

"የፍቅር ካቴና" የተሰኘ ተውኔት ዛሬ መስከረም 17 2017 ዓ.ም በልዩ ዝግጅት ከምሽቱ 12:00 ጀምሮ ቦሌ በሚገኘው ዓለም ሲኒማ ውስጥ ይቀርባል።

በአርቲስት ወይንሸት አበጀ ፕሮዲዩስ የተደረገው ይህ "የፍቅር ካቴና" ተውኔት ድርሰትና ዝግጅቱ የአለልኝ መኳንንት ፅጌ ነው።በተውኔቱ ድርብወርቅ ሰይፉ ፣ሚኪ ተስፋዬ ፣ ወይንሸት አበጀ ፣አሸናፊ ማህሌት በተዋናይነት ተሳትፈውበታል።

ለተጨማሪው:https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌"ሹቢቲ" የተሰኘ ነጠላ ሙዚቃ በቅርቡ ይለቀቃል

ድምጻዊ አደም መሐመድ ከድምፃዊት ሀሊማ አብደላ ጋር በጋራ ያቀነቀኑትና የ2017 ኢሬቻን በዓል በማስመልከት የጉጂ ባህልን የሚያሳይ "ሹቢቱ" የተሰኘ ነጠላ ዘፈን ለህዝብ ጆሮ ለማድረስ ዝግጅታቸውን ማጠናቀቃቸውን ገልጸዋል።

ይህን የሙዚቃ ቪዲዮ ለማሰናዳት ከ50 በላይ ባለሞያዎች የተሳተፉበት ሲሆን ለሙዚቃው ቪዲዮ ከ1.8 ሚሊዮን ብር በላይ እንደወጣበት ተነግሯል።

በቅንብር እና ማስተሪግ ብርሀን ዘሪሁን እና አብርሐም ኪዳኔ በማስተሪንግ እና ሚክሲንግ እንደተሳተፉበት ታውቋል።

የሙዚቃ ቪዲዮውን ዳሬክት በማድረግ አርቲስት ፋንታ ስንታየሁ እንደተሳተፍ ተገልጿል። ቀረፃውን Ya'a entertainment አከናውኖታል።

ድምጻዊ አደም መሐመድ ቅርቡ"ኦሮሚያ" የተሰኘ የአልበም ስራውን መልቀቁ ይታወሳል።

ለተጨማሪው:https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌በድምጻዊ ቴዎድሮስ ታደሰ ህልፈት ዙርያ እየተሰራጨ ያለው መረጃ የተሳሳተ ነው !

'Yehabesha' የተባለው እና ከ1.9 ሚልዮን በላይ የፌስቡክ ተከታዮች ያሉት ገፅን ጨምሮ በርካታ የማህበራዊ ሚድያ ተጠቃሚዎች ታዋቂው ድምፃዊ ቴዎድሮስ ታደሰ ህይወቱ እንዳለፈ መስከረም 19 2017 ዓ.ም መረጃ ሲያጋሩ ውለዋል።

እነዚህ ፅሁፎች ምንም አይነት ምንጭ ሳይጠቀስባቸው ለህዝብ የተጋሩ ሲሆን በርካታ ሰዎችም መልሰው ሲያጋሩት (ሼር ሲያደርጉት ተመልክተናል)፣ በርካታ የኢትዮጵያ ቼክ ተከታታዮችም ፅሁፉን እንድናጣራ ጥያቄ አቅርበዋል።

የመረጃ ማጣርያ ዴስካችን በዚህ ዙርያ አንድ የአርቲስቱ ጓደኛን እና አንድ የቅርብ ቤተሰብን ያነጋገረ ሲሆን በማህበራዊ ሚድያ የተሰራጨው መረጃ ሀሰተኛ መሆኑን ተናገረዋል።

"እኛም ከመሸ አይተነው ነበር፣ በርካታ ሰው ተደናግጦ ሲደውል ነበር፣ ወሬው ግን ውሸት ነው። ከእንዲህ አይነት በሬ ወለደ ፅሁፍ ምን እንደሚጠቀሙ አይገባኝም" ብለው ምላሽ የሰጡን ምንጫችን ይህ በአርቲስቱ ዙርያ ሲወራ ለሶስተኛ ግዜ መሆኑን ጠቅሰዋል።

ማህበራዊ ሚድያ ላይ የሚሰራጩ መረጃዎችን ትክክለኛነት ሳናጣራ፣ የምናምናቸው ምንጮች ሳይዘግቡት እንዲሁም ማስረጃዎችን ሳንመለከት ባለማመን እና መልሰን ለሌሎች ባለማጋራት የሀሰተኛ መረጃ ስርጭትን እንከላከል።

©️Via ኢትዮጵያ ቼክ

ለተጨማሪው:https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌"እርቅ ከእራስ" ውይይት ቅዳሜ ይካሄዳል

በተከታታይ እየቀረበ የሚገኘው "እርቅ ከእራስ" የውይይት  ዝግጅት "ትውልድ ለማነጽ" በሚል ርዕስ የፊታችን ቅዳሜ መስከረም 25 2017 ዓ.ም ከቀኑ 10:30 ጀምሮ ካዛንቺስ በሚገኘው ትራቩል ኢትዮጵያ ቢሮ ውስጥ ይካሄዳል።በዕለቱም ፕ/ር አህመድ ዘካሪያ፣ኢ/ር ቪጃይ ናይከር፣ሜላት ንጉሴ እና ሌሎችም ሀሳቦቻቸውን ያጋራሉ ተብሏል።

ለተጨማሪው:https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌"ልውጠ ቀርጽ" የሥዕል አውደርዕይ ለእይታ በቃ

የሠዓሊ ዳሪዎስ ኃ/ሚካኤል የሥዕል ስራዎች የቀረቡበት "ልውጠ ቀርጽ" የሥዕል አውደርዕይ ባሳለፍነው ሰኞ መስከረም 20 2017 ዓ.ም ጀምሮ ካዛንቺስ በሚገኘው ፈንድቃ የባህል ማዕከል ውስጥ ለእይታ በቅቷል።

ይህ የሥዕል አወድርዕይ እስከ ጥቅምት 4  2017 ዓ.ም ድረስ ይቆያል ተብሏል።

ለተጨማሪው:https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌የአባ ገብረ ኪዳን ግርማ መጽሐፍ ምረቃ

የርዕሰ ሊቃውንት የኔታ አባ ገብረ ኪዳን ግርማ "አሐቲ ድንግል" የተሰኘ መጽሐፋቸው ቅዳሜ ጥቅምት 2 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 7:30 ጀምሮ በቦሌ መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ይመረቃል።

ለተጨማሪው:https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌"የፍቅር እስሰ መቃብር ሲኒማቶግራፊ"

አላቲኖስ ኢትዮጵያዊ ፊልም ሰሪዎች ማሕበር ፒያሳ በሚገኘው የሩሲያ ሳይንስና ባህል ማዕከል (ፑሽኪን) አዳራሽ ውስጥ በሚያዘጋጀው የፊልም ውይይት መርሐግብር ዛሬ ሐሙስ መስከረም 23 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 10:30 ጀምሮ" የፍቅር እስከ መቃብር ሲኒማቶግራፊ"በሚል ርዕስ ውይይት ያካሄዳል።በዕለቱም የክብር እንግዳ በመሆን የፊልም ባለሞያው ፍስሃፅዮን ንብረት  ይገኛል ተብሏል።

ለተጨማሪው:https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌በእረፍት ቀንዎ ቴአትር ይመለከቱ !

አንጋፋው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር  እና የቦሌው ዓለም ሲኒማ አርብ፣ ቅዳሜ እና እሁድ እነዚህን ተውኔቶች ለታዳሚያን ያቀርባሉ።

📍 ጎዶ'ን ጥበቃ

ድርሰት: ሳሙኤል ቤኬት
ትርጉም: ሀይከል ሙባረክ
አዘጋጅ: ዳግም ሲሳይ
ቀን: ሐሙስ
ሰዓት:11:30
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር


📍 የፍቅር ካቴና

ድርሰትና ዝግጅት: አለልኝ መኳንት ፅጌ
ቀን: አርብ
ሰዓት: 12:00
ቦታ: ዓለም ሲኒማ

📍 "እሳት ወይ አበባ"

ድርሰት: ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን እንደጻፈው
ዳንስና ዳንስ ቅንብር: ሽፈራው ታሪኩ ቢረጋ
ቀን: አርብ
ሰዓት:11:30
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር

📍 ባሎች እና ሚስቶች

ድርሰት: ውዱ አለን
አዘጋጅ: ሳሙኤል ተስፋዬ
ቀን: ቅዳሜ
ሰዓት: 8:00
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር

📍 ባቡሩ

ድርሰት: አርኖልድ ሪድሊ
አዘጋጅ:ራሔል ተሾመ መሐመድ
ቀን: ቅዳሜ
ሰዓት:11:30
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር

📍 ሸምጋይ

ድርሰት:ታደለ አያሌው
አዘጋጅ: ሳሙኤል ተስፋዬ
ቀን: እሁድ
ሰዓት: 8:00
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር

📍 እምዩ ብረቷ

ድርሰት: ቤልቶልት ብሬሽት
አዘጋጅ: ማንያዘዋል እንዳሻው
ቀን: እሁድ
ሰዓት:11:30
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር

የእናንተው ኤቨንት አዲስ ድረገፅ መልካም የእረፍት ቀን ይሁንላችሁ ይላል !

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1