Event Addis Media – Telegram
Event Addis Media
9.62K subscribers
6.12K photos
14 videos
4 files
4.74K links
Connect with Addis artistic community!

Website: https://eventaddis.com

Contact: @Tmanaye
Download Telegram
📌የሠዓሊ ዮሐንስ ባዩ "ምስጋና"አውደርዕይ!

የ"እርሳስ ቤተጥበብ" መስራች ሠዓሊ ዮሐንስ ባዩ "ምስጋና" በሚል ርዕስ ያዘጋጀው ለየት ያለ የሥነጥበብ አውደርዕይ ከፊታችን ማክሰኞ መስከረም 28 2017 ዓ.ም ጀምሮ ይካሄዳል።

የሠዓሊ ዮሐንስ ባዩ "እርሳስ ቤተ ጥበብ / Ersas art studio / የተመሰረተበትን እና የሠዓሊውን የ10 ዓመት የሙያ ጉዞ ለማክበር የተዘጋጀ የሥዕል አውደርዕይ እና የሥዕል መጽሃፍ ምርቃት በማርዮት ሆቴል መስከረም 28 በልዩ ፕሮግራም እና ግብዣ ጥሪ ለተደረገላቸው እንግዶች እንዲሁም ከመስከረም 29 - ጥቅምት 1 2017 ለጥበብ አድናቂዎች ክፍት ይሆናል ተብሏል።

ሠዓሊ ዮሐንስ ባዩ የ"እርሳስ ቤተ ጥበብ" መስራች እና የሙሉ ጊዜ ሠዓሊ ሲሆን ላለፉት ዓመታት በሙያው በተለያዩ የሥነ ሥዕል እና የ ሞዛይክ ጥበብ ለግለሰቦች፣ለ ኤምባሲዎች፣ ለሆቴሎች፣ለመንግስት እና ለተለያዩ ተቋማት በመስራት እንዲሁም በሀገር ውስጥ እና በባህር ማዶ ሀገራት የሀገራችንን የኢትዮጵያን ስም ከፍ የሚያደርጉ ወደ 20 የሚጠጉ የሥዕል ዐውደርዕዮችን አቅርቧል።

የተለያዩ ዓለም አቀፍ ሽልማቶችን (Oscar of young African 2019) ጨምሮ በማግኘት እውቅናን ያተረፈ ወጣት ሠዓሊ ነው።

በእውነታዊ / realistic / የአሳሳል ዘይቤ የሚታወቀው ሠዓሊው ውበትን፣እምነትን፣ ምስጋናን እና ተስፋን በሥዕሎቹ አጉልቶ ያሳየናል::

ለተጨማሪው:https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌የቬሮኒካ አዳነ አልበም በ"Grammy Award"

የድምጻዊት ቬሮኒካ አዳነ "መጠሪያዬ" አልበም በዓለምአቀፍ ደረጃ ዝነኛ ሽልማት በሆነው"Grammy Award" ላይ የመጀመሪያውን ዙርን እንዳለፈ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ከድምጻዊት ቬሮኒካ አዳነ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

በተጨማሪያም ድምጻዊት ቬሮኒካ አዳነ" ለመላው ኢትዮጵያውያን የሀገሬ ልጆች በሙሉ "መጠሪያዬ" የተሰኘው አልበማችን ለ Grammy የመጀመሪያውን ዙር ማለፋችንን አሳውቀውናል ፤ እዚ ስራ ላይ የተሳተፋችው በሙሉ እንኳን ደስ አላችው" ብላለች።

ለተጨማሪው:https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌የቀድሞው የዛሚ ኤፍ ኤም ሬድዮ ጣብያ ስራ አስኪያጅ አቶ ዘሪሁን ተሾመ የመንግስት ሹመት እንዳገኙ ተሰማ

አቶ ዘሪሁን የደህንነት ቢሮ ሀላፊ የሆኑት የአቶ ሬድዋን ሁሴን አማካሪ ሆነው ከጥቂት ወራት በፊት ሹመት እንደተሰጣቸው ተጠቁሟል።

የዛሬ ሰባት አመት ገደማ የአሁኑ መንግስት ስልጣን በያዘበት ወቅት የሰላ ትችት በመሰንዘር የሚታወቁት እና የጋዜጠኛ ሚሚ ስብሀቱ ባለቤት የሆኑት አቶ ዘሪሁን ለቀድሞው የኢህአዴግ ባለስልጣናት እና ለስርዐቱ አራማጆች እጅግ ቅርብ እንደነበሩ ብዙዎች ይናገራሉ።

ለውጥ መጣ የተባለበትን ወቅት "የጎበዝ አለቆች ወጥቶ መግባትን ከባድ ያደረጉበት ግዜ ነው" በማለት በመተቸት የሚታወቁት ግለሰቡ ወቅቱ መደማመጥ የሌለበት ስለሆነ በጥሞና ዝም ለማለት በመፈለጋቸው ከሚድያ እይታ ርቀው እንደነበር ተናግሮ ነበር። ዛሚ ኤፍ ኤም ከተዘጋ በኋላም አብዛኛ ግዜያቸውን በአሜሪካ እንዳሳለፉ ታውቋል።

አሁን ግን በአዲስ ሹመት መንግስትን የተቀላቀሉ ቢሆንም እስከዛሬ ድረስ ሹመቱ በመንግስት ይፋ አልሆነም፣ ይሁንና ከሶስት ቀን በፊት በዋልታ ሚድያ ላይ ቀርበው ስለ ወቅታዊው የሶማልያ፣ ግብፅ እና ኢትዮጵያ ውጥረት ትንታኔ ሲሰጡ እንደነበር ተመልክተናል።

©️መረጀው የመሰረት ሚዲያ ነው።

ለተጨማሪው:https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
1
📌የሜሪ ፈለቀ "ጠበኛ እውነቶች"መጽሐፍ አምስተኛ ዕትም መጽሐፍ ለንባብ በቃ

ከዓመታት በፊት ለንባብ የቀረበው የደራሲ ሜሪ ፈለቀ "ጠበኛ እውነቶች" አምስተኛ ዕትም መጽሐፍ ለአንባቢያን ቀርቧል። 

"ጠበኛ እውነቶች" መጽሐፍ በ4 ክፍሎች የተከፈለ ልብወለድ ሲሆን የተለያዩ ማህበራዊ እና ግላዊ ሕይወትን የሚዳስስ መፅሐፍ ነው። በዚህ መጽሐፍ ውስጥ የተካተቱ የአራቱ ታሪኮች ርዕሳቸው ቅዳሴና ቀረርቶ፣ቀላውጦ ማስመለስ፣ እናቴን ተመኘኋት፣ምርጫ አልባ ምርጫ ይሰኛሉ ::

መጽሐፉ በ252 ገፆች የተቀነበበ ሲሆን በ350 ብር የጀርባ ዋጋ ለአንባቢያን ቀርቧል። በተለያዩ መጻሕፍት መደብሮችም ይገኛል ተብሏል።

ለተጨማሪው:https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌"ያ-ሻር" መጽሐፍ ነገ ይመረቃል

በኢሳይያስ አንበሳ የተዘጋጀው "ያ-ሻር: ሹክሹክታ:እና: ማሚቶ" የተሰኘ መጽሐፍ ነገ እሁድ መስከረም 26 ቀን 2017 ዓ.ም በአሶሳ ከተማ ቤንስ አይከን ሆቴል ከጠዋቱ 3:30 ጀምሮ ይመረቃል።

ስለ መጽሐፍ አጭር ገለፃ

➾ርዕስ፦ ያ-ሻር (ሹክሹክታ እና ማሚቶ)
➾ዘውግ:- ልብ-ወለድ
➾የገጽ ብዛት፦ 217
➾ትርጓሜ፦ 'ያ-ሻር'... ሻር- በመተከል ዞን በቡለን ወረዳ የሚገኝ ወንዝ ስም፤ ያ-ያልተነገረለት ሻር እንደማለት።

➾ቅርጽ፦ ወንዝኛ... ህይወት በወንዝ ስትፈከር...ወይም ህይወት በወንዝ ሲገለጽ። ድህረ ዘመናዊ አፃፃፍ የተከተለ... በአምስት ታሪኮች የተዋቀረ...እያንዳንዱ ታሪክ በድልድዮች ወይም በራሱ በሻር የተያያዙ ናቸው።

➾የመጽሐፉ ትልም፦ ሻራውያን...የሻር ውሃ ጠጥተው ያደጉ የኛ ዘመን ሰዎች ናቸው...ልክ እንደ ወንዙ ከፈለቁበት መተከል እንጀራ ፍለጋ፣ ዕውቀት ፍለጋ፣ የተሻለ ስራ ፍለጋ ወጥተው በመንፈሳቸው የፈለቁበትን ያልለቀቁ፣ ነገር ግን ከቋንቋ ጀምሮ ሙሉ እሱነታቸው በሌላ ባህል እና ታሪክ ሲተካ የሚመለከቱ ናቸው።

➾ሻራውያን ወጣቶች፣ አስተማሪዎች፣ የዩኒቨርስቲ ሙምህራን፣ የቤት እመቤቶች ፣ የቤት ሰራተኞች፣ ደሃ አደጎች፣ አፍቃሪዎች፣ ተፈቃሪዎች ናቸው።

በተጨማሪም ጥቃቅን የምንላቸው የህይወታችን ሽንቁሮች ግዙፍ ነገር ሊያስከትሉ እንደሚችሉ የሚያሳይ the butterfly effect ወይም የቢራቢሮ ተፅእኖና የሚለውን ሳይንሳዊ የትርምስ ንድፈ ሃሳብ ላይ የተሞረከዘ ነው።

መፅሐፉ በሀገራችን ስነፁሑፍ ተዳስሶ የማያውቅ የሺናሻ ማህበረሰብ በከፊሉ የሚዳስስ እና የሚያሳይ ሲሆን ለየትኛውም አንባቢ በሚመች እና በድንቅ አተራረክ የተፃፈ ነው።

ለተጨማሪው:https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌“ የልጆቼን ትምህርት ቤት መክፈል አቅቶኛል” የሙዚቃ ቪዲዮ ዳይሬክተር ስንታየሁ ሲሳይ

የሙዚቃ ዳይሬክተር ስንታየሁ ቁጥራቸው የበዙ ዘመን ተሻጋሪ የሙዚቃ ክሊፖችን ሰርቷል ።  የሄለን በርሄ ልቤ ፣ የዳን አድማሱ ከፍቶሽ እንዳላይ ፣ ሚሶ ነጋያ ፣ የጥበቡ ወርቅዬ ሊጋባ ፣ የመስፍን በቀል ደመላሽ ፣ ፍቅርአዲስ ነቃጥበብ ፣ የላፎንቴኖችን ባቡሬ እና ሌሎች በርካታ ክሊፖችን ሰርቷል ።

“..ለገንዘብ ሰርቼ አላውቅም ፤   ዘመን የሚሻገር ስራ ነው መስራት የምወደው ፣ ያላመንኩበትን ሥራ መስራት አልወድም”  የሚለው ስንታየሁ ዛሬ ላይ ዋጋ እንዲከፍል እንዳደረገው ገልጿል ። ልጆቹን ለማሳደግ መኪናውን እስከመሸጥ መድረሱን ተናግሯል ። 

ስንታየሁ በአሁን ሰዓት የልጆቹን ትምህርት ቤት መክፈል አቅቶት ልጆቹ ትምህርታቸውን ሊያቆሙ እንደሆነ ጭምር  በEBS ቅዳሜ ከሰዓት ፕሮግራም ላይ ቀርቦ የእንባ ሳግ እየተናነቀው ተናግሯል።

አንጋፋውን የጥበብ ባለሞያ ስንታየሁ ሲሳይን ለማገዝ የባንክ ሂሳብ ቁጥር ይፋ ተደርጓል። 1000351511285።

ለተጨማሪው:https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌 የመሬት መንቀጥቀጥ ምክንያት ?

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጂኦ ፊዚክስና ስፔስ ሳይንስ ዳይሬክተር ዶክተር ኤልያስ ሌዊ ለብሔራዊ ቴሌቪዥን በሰጡት ቃል ምን አሉ ?

" እስካሁን ባለው መረጃ እዚህ የመሬት መንቀጥቀጡ እዚህ አዲስ አባባ የተከሰተ ሳይሆን አዋሽ አካባቢ የተከሰተ ነው።

ግን በመሬት ውስጥ አልፎ እዚህ አዲስ አበባ ውስጥ ልዩ ልዩ ቦታዎች ተሰምቷል።

ይሄን ግልጽ ማድረግ እንፈልጋለን እዚህ አዲስ አበባ የተከሰተ አይደለም። ግን በመሬት ውስጥ ተጉዞ መጥቶ እዚህ ያሉ ህንጻዎችን አንቀጥቅጧል።

በሪክተር ስኬል 4.9 ነው ያገኘነው። ይሄም ከፈንታሌ የሚባል ተራራ አለ ወደ መተሃራ አካባቢ ነው የተከሰተው። እስካሁን ያለው መረጃ ይሄ ነው።

ሰውም ይረጋጋ እዚህ አዲስ አበባ የተከሰተ የመሬት መንቀጥቀጥ ሳይሆን ከሩቅ የተከሰተ የመሬት መንቀጥቀጥ ሞገዱ በመሬት ውስጥ ተጉዞ መጥቶ በተለይ እዚህ ሰሜን እና ሰሜን ምስራቅ ያሉ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች በጣም ተረብሸዋል። ልክ ነው ከዛም ሊሰማ ይችላል።
በሬክተር ስኬል 4.9 ነው ይሄ ነው ያለው መረጃ። ተጨማሪ መረጃ እንዳገኘን በግልጽ እንነግራለን። " ብለዋል።

ዛሬ ምሽት በአዲስ አበባ በነበረው የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረት ምክንያት በተለይ የጋራ መኖሪያ ቤቶች የሚኖሩ ነዋሪዎች ህንጻቸው ሲንቀጠቀጥ እንደነበር ገልጸውልናል። በዚህ ምክንያት ከቤታቸው ወጥተው መሬት ላይ ወርደው ተሰባስበዋል።

ምንጭ: ቲክቫ

ለተጨማሪው:https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌በርካታ የሙዚቃ ቪዲዮዎችን ለሰራው ስንታየሁ ሲሳይ የሚደረገው ድጋፍ ዛሬም ይቀጥላል።

በርካታ የሙዚቃዎች ቪዲዮዎችን የሰራው ዳይሬክተር ስንታየሁ ሲሳይ ቅዳሜ መስከረም 25 ቀን 2017 ዓ.ም በኢቢኤስ ቴሌቭዥን "ቅዳሜ ከሠዓት" ፕሮግራም ላይ በቀረበበት ወቅት ስላለበት ችግር መግለፁን ተከትሎ በርካቶች የድጋፍ እጃቸውን እየዘረጉ ይገኛሉ።

ትላንት መስከረም 26 ቀን 2017 ዓ.ም በ24 ሰዓታት ውስጥ ብቻ  1,528,689 ብር በአርቲስቱ የግል አካውንቱ መሰብሰቡን ስንታየሁ ሲሳይ ገልጿል።

በእዚህም የተሰማውን ደስታ የገለፀው ስንታየሁ ሲሳይ " ሁለት ሐገር የለኝም ያለኝ አንድ ሐገር ነው:: እሱም የኢትዮጵያ ህዝብ እግዝያብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ እዚህ አደረሳችሁኝ ፈጣሪ ጨምሮ ይስጥልኝ ያገሬ ሰው ኑሩልኝ " ሲል አመስግኗል።

ድጋፉ ዛሬም የሚቀጥል ሲሆን ከአምስት መቶ ብር ጀምሮ ድጋፉ እንዲቀጥል በአስተባባሪዎቹ በኩል ጥሪ ቀርቧል።

ንግድ ባንክ: 1000351511285
ዳሽን ባንክ: 514100345ዐዐዐ5
አቢሲኒያ ባንክ:73749093

ስንታየሁ ሲሳይ ወለደጻዲቅ

ለተጨማሪው:https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌ድምጻዊ ሚካኤል በላይነህ በፕሪስቴጅ አዲስ ዝግጅት ላይ የዓመቱ የመጀመሪያ እንግዳ በመሆን ይቀርባል።

የተለያዩ የጥበብ ባለሞያዎችን እየጋበዝ ልምዶቻቸውን እንዲያጋሩ እያደረገ ያለው ፕሪስቴጅ አዲስ መርሐግብር በአዲሱ ዓመት የመጀመሪያ ፕሮግራሙ በተወዳጅ የፍቅር ዘፈኖቹ የሚታወቀውን ስመ-ጥር እና በአዲሱ የሙዚቃ አልበሙ ደግሞ ተወዳጅነትን ያተረፈውን ድምፃዊ የግጥም እና ዜማ ደራሲ አርቲስት ሚካኤል በላይነህን ጋብዟል::

የፕሪስቴጅ አዲስ አዘጋጆች "ከሚኪ ጋራ በሚኖረን ቆይታ የሥራ፣ የህይወት ልምድ እና ተሞክሮውን የሚያካፍለን ሲሆን ከእናንተ ከወዳጅ እና ድናቂዎቹ የሚቀርቡለትን ጥያቄዎች ደግሞ ማክሰኞ መስከረም 28 2017 ዓ.ም መልስ ለመስጠት ቀጠሮ ይዘናል" ሲሉ ለኤቨንት አዲስ ድረገፅ ገለጸዋል።

በዕለቱ ከአርቲስቱ ጋር የፎቶግራፍ መነሳትና አውቶግራፍ የማስፈረም መርሃግብር ይኖራል ተብሏል::

ፕሪስቴጅ አዲስ ከሚካኤል በላይነህ ጋር  የሚያደረገው አዝናኝ እና አስተማሪ ቆይታ ነገ ማክሰኞ መስከረም 28 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ጀምሮ አሜሪካን ኢምባሲ ቅጥር ግቢ ውስጥ ( ከስድስት ኪሎ ወደ ሽሮሜዳ መሄጃ ) ይካሄዳል።
                                                                                                                             
በዝግጅቱ ላይ ለመታደም ከታች ያለውን ሊንክ በመንካት ይመዝገቡ:
https://bit.ly/SatchmoCenterMembership

መታወቂያ መያዝ እንዳይረሳ፣ማርፈድ ወደ ውስጥ እንዳትገቡ ያደርጋል ፕሮግራሙ ከመጀመሩ ቀደም ብላችሁ ለመገኘት ሞክሩም ተብላችኋል።

ለተጨማሪው:https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌የሠዓሊ ዮሐንስ ባዩ "ምስጋና"አውደርዕይ!

የ"እርሳስ ቤተጥበብ" መስራች ሠዓሊ ዮሐንስ ባዩ "ምስጋና" በሚል ርዕስ ያዘጋጀው ለየት ያለ የሥነጥበብ አውደርዕይ ከነገ ማክሰኞ መስከረም 28 2017 ዓ.ም ጀምሮ ይካሄዳል።

የሠዓሊ ዮሐንስ ባዩ "እርሳስ ቤተ ጥበብ / Ersas art studio / የተመሰረተበትን እና የሠዓሊውን የ10 ዓመት የሙያ ጉዞ ለማክበር የተዘጋጀ የሥዕል አውደርዕይ እና የሥዕል መጽሃፍ ምርቃት በማርዮት ሆቴል መስከረም 28 በልዩ ፕሮግራም እና ግብዣ ጥሪ ለተደረገላቸው እንግዶች እንዲሁም ከመስከረም 29 - ጥቅምት 1 2017 ለጥበብ አድናቂዎች ክፍት ይሆናል ተብሏል።

ሠዓሊ ዮሐንስ ባዩ የ"እርሳስ ቤተ ጥበብ" መስራች እና የሙሉ ጊዜ ሠዓሊ ሲሆን ላለፉት ዓመታት በሙያው በተለያዩ የሥነ ሥዕል እና የ ሞዛይክ ጥበብ ለግለሰቦች፣ለ ኤምባሲዎች፣ ለሆቴሎች፣ለመንግስት እና ለተለያዩ ተቋማት በመስራት እንዲሁም በሀገር ውስጥ እና በባህር ማዶ ሀገራት የሀገራችንን የኢትዮጵያን ስም ከፍ የሚያደርጉ ወደ 20 የሚጠጉ የሥዕል ዐውደርዕዮችን አቅርቧል።

የተለያዩ ዓለም አቀፍ ሽልማቶችን (Oscar of young African 2019) ጨምሮ በማግኘት እውቅናን ያተረፈ ወጣት ሠዓሊ ነው።

በእውነታዊ / realistic / የአሳሳል ዘይቤ የሚታወቀው ሠዓሊው ውበትን፣እምነትን፣ ምስጋናን እና ተስፋን በሥዕሎቹ አጉልቶ ያሳየናል::

ለተጨማሪው:https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌ዲዛይነር ተሻለች ታደሰ ተሸለመች

በአሜሪካ  ነዋሪ የሆነችው ታዋቂዋ የአዶት ዲዛይን መስራችና ባለቤት ተሻለች ታደሰ ኤጋ Adot Enset በፊሊፒኖ አሜሪካ ካንሰር ተቋም የአመቱ ልዩ ተሸላሚ ሆናለች።

ዲዛይነሯ ከሰሞኑ በቨርጂኒያ ሀያት ሬጀንሲ ሆቴል በተካሄደው አመታዊ የካንሰር ህሙማን የግንዛቤ ማስጨበጫና የገቢ ማሰባሰቢያ የእራት ግብዣ ላይ ብቸኛዋ ኢትዮጵያዊትና አፍሪካዊት ሆና የፋሽን ሾው ስራዎቿን አቅርባለች፤ አዘጋጆቹም በአዶት ዲዛይን ፈጠራና ስራ በመደነቅ ልዩ የእውቅና ሽልማት አበርክተውላታል።

ዲዛይነር ተሻለች በተለይ በእንሰትና በሽመና ምርቶች ልዩ ልዩ የፈጠራ አቅርቦቶችን በመስራት ትታወቃለች፤ በ2019 በፋሽን ሾው ዳውን ሂውስተን ከ12 ዲዛይነሮች አንደኛ ወጥታ በቴክሳስ ሂውስተን ተሸልማለች።

በ2021 ደግሞ በሜሪላንድ አናፖሊስ በቨርችዋል ፋሽን ሾው በተመሳሳይ እውቅና አግኝታለች። ከሰሞኑ ደግሞ የመሰረት በጎ አድራጎት ድርጅት የአሜሪካ ከተሞች አምባሳደር ሆና በድርጅቱ ባለቤት ወ/ሮ መሰረት አዛገ ተሹማለች።

"የጫማ ጠጋኙ ልጅ" ዲዛይነር ተሻለች ታደሰ የአባቷን የስራ ትጋትና ችሎታ ተመልክታ የእናቷን የእንሰት ፍቅር አስተውላ ወደ ዲዛይን እና ፋሽን ኢንዱስትሪ መግባቷን ትናገራለች።

ለተጨማሪው:https://news.1rj.ru/str/EventAddis1