📌“ የልጆቼን ትምህርት ቤት መክፈል አቅቶኛል” የሙዚቃ ቪዲዮ ዳይሬክተር ስንታየሁ ሲሳይ
የሙዚቃ ዳይሬክተር ስንታየሁ ቁጥራቸው የበዙ ዘመን ተሻጋሪ የሙዚቃ ክሊፖችን ሰርቷል ። የሄለን በርሄ ልቤ ፣ የዳን አድማሱ ከፍቶሽ እንዳላይ ፣ ሚሶ ነጋያ ፣ የጥበቡ ወርቅዬ ሊጋባ ፣ የመስፍን በቀል ደመላሽ ፣ ፍቅርአዲስ ነቃጥበብ ፣ የላፎንቴኖችን ባቡሬ እና ሌሎች በርካታ ክሊፖችን ሰርቷል ።
“..ለገንዘብ ሰርቼ አላውቅም ፤ ዘመን የሚሻገር ስራ ነው መስራት የምወደው ፣ ያላመንኩበትን ሥራ መስራት አልወድም” የሚለው ስንታየሁ ዛሬ ላይ ዋጋ እንዲከፍል እንዳደረገው ገልጿል ። ልጆቹን ለማሳደግ መኪናውን እስከመሸጥ መድረሱን ተናግሯል ።
ስንታየሁ በአሁን ሰዓት የልጆቹን ትምህርት ቤት መክፈል አቅቶት ልጆቹ ትምህርታቸውን ሊያቆሙ እንደሆነ ጭምር በEBS ቅዳሜ ከሰዓት ፕሮግራም ላይ ቀርቦ የእንባ ሳግ እየተናነቀው ተናግሯል።
አንጋፋውን የጥበብ ባለሞያ ስንታየሁ ሲሳይን ለማገዝ የባንክ ሂሳብ ቁጥር ይፋ ተደርጓል። 1000351511285።
ለተጨማሪው:https://news.1rj.ru/str/EventAddis1

📌 የመሬት መንቀጥቀጥ ምክንያት ?
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጂኦ ፊዚክስና ስፔስ ሳይንስ ዳይሬክተር ዶክተር ኤልያስ ሌዊ ለብሔራዊ ቴሌቪዥን በሰጡት ቃል ምን አሉ ?
" እስካሁን ባለው መረጃ እዚህ የመሬት መንቀጥቀጡ እዚህ አዲስ አባባ የተከሰተ ሳይሆን አዋሽ አካባቢ የተከሰተ ነው።
ግን በመሬት ውስጥ አልፎ እዚህ አዲስ አበባ ውስጥ ልዩ ልዩ ቦታዎች ተሰምቷል።
ይሄን ግልጽ ማድረግ እንፈልጋለን እዚህ አዲስ አበባ የተከሰተ አይደለም። ግን በመሬት ውስጥ ተጉዞ መጥቶ እዚህ ያሉ ህንጻዎችን አንቀጥቅጧል።
በሪክተር ስኬል 4.9 ነው ያገኘነው። ይሄም ከፈንታሌ የሚባል ተራራ አለ ወደ መተሃራ አካባቢ ነው የተከሰተው። እስካሁን ያለው መረጃ ይሄ ነው።
ሰውም ይረጋጋ እዚህ አዲስ አበባ የተከሰተ የመሬት መንቀጥቀጥ ሳይሆን ከሩቅ የተከሰተ የመሬት መንቀጥቀጥ ሞገዱ በመሬት ውስጥ ተጉዞ መጥቶ በተለይ እዚህ ሰሜን እና ሰሜን ምስራቅ ያሉ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች በጣም ተረብሸዋል። ልክ ነው ከዛም ሊሰማ ይችላል።
በሬክተር ስኬል 4.9 ነው ይሄ ነው ያለው መረጃ። ተጨማሪ መረጃ እንዳገኘን በግልጽ እንነግራለን። " ብለዋል።
ዛሬ ምሽት በአዲስ አበባ በነበረው የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረት ምክንያት በተለይ የጋራ መኖሪያ ቤቶች የሚኖሩ ነዋሪዎች ህንጻቸው ሲንቀጠቀጥ እንደነበር ገልጸውልናል። በዚህ ምክንያት ከቤታቸው ወጥተው መሬት ላይ ወርደው ተሰባስበዋል።
ምንጭ: ቲክቫ

📌በርካታ የሙዚቃ ቪዲዮዎችን ለሰራው ስንታየሁ ሲሳይ የሚደረገው ድጋፍ ዛሬም ይቀጥላል።
በርካታ የሙዚቃዎች ቪዲዮዎችን የሰራው ዳይሬክተር ስንታየሁ ሲሳይ ቅዳሜ መስከረም 25 ቀን 2017 ዓ.ም በኢቢኤስ ቴሌቭዥን "ቅዳሜ ከሠዓት" ፕሮግራም ላይ በቀረበበት ወቅት ስላለበት ችግር መግለፁን ተከትሎ በርካቶች የድጋፍ እጃቸውን እየዘረጉ ይገኛሉ።
ትላንት መስከረም 26 ቀን 2017 ዓ.ም በ24 ሰዓታት ውስጥ ብቻ 1,528,689 ብር በአርቲስቱ የግል አካውንቱ መሰብሰቡን ስንታየሁ ሲሳይ ገልጿል።
በእዚህም የተሰማውን ደስታ የገለፀው ስንታየሁ ሲሳይ " ሁለት ሐገር የለኝም ያለኝ አንድ ሐገር ነው:: እሱም የኢትዮጵያ ህዝብ እግዝያብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ እዚህ አደረሳችሁኝ ፈጣሪ ጨምሮ ይስጥልኝ ያገሬ ሰው ኑሩልኝ " ሲል አመስግኗል።
ድጋፉ ዛሬም የሚቀጥል ሲሆን ከአምስት መቶ ብር ጀምሮ ድጋፉ እንዲቀጥል በአስተባባሪዎቹ በኩል ጥሪ ቀርቧል።
ንግድ ባንክ: 1000351511285
ዳሽን ባንክ: 514100345ዐዐዐ5
አቢሲኒያ ባንክ:73749093
ስንታየሁ ሲሳይ ወለደጻዲቅ

📌ድምጻዊ ሚካኤል በላይነህ በፕሪስቴጅ አዲስ ዝግጅት ላይ የዓመቱ የመጀመሪያ እንግዳ በመሆን ይቀርባል።
የተለያዩ የጥበብ ባለሞያዎችን እየጋበዝ ልምዶቻቸውን እንዲያጋሩ እያደረገ ያለው ፕሪስቴጅ አዲስ መርሐግብር በአዲሱ ዓመት የመጀመሪያ ፕሮግራሙ በተወዳጅ የፍቅር ዘፈኖቹ የሚታወቀውን ስመ-ጥር እና በአዲሱ የሙዚቃ አልበሙ ደግሞ ተወዳጅነትን ያተረፈውን ድምፃዊ የግጥም እና ዜማ ደራሲ አርቲስት ሚካኤል በላይነህን ጋብዟል::
የፕሪስቴጅ አዲስ አዘጋጆች "ከሚኪ ጋራ በሚኖረን ቆይታ የሥራ፣ የህይወት ልምድ እና ተሞክሮውን የሚያካፍለን ሲሆን ከእናንተ ከወዳጅ እና ድናቂዎቹ የሚቀርቡለትን ጥያቄዎች ደግሞ ማክሰኞ መስከረም 28 2017 ዓ.ም መልስ ለመስጠት ቀጠሮ ይዘናል" ሲሉ ለኤቨንት አዲስ ድረገፅ ገለጸዋል።
በዕለቱ ከአርቲስቱ ጋር የፎቶግራፍ መነሳትና አውቶግራፍ የማስፈረም መርሃግብር ይኖራል ተብሏል::
ፕሪስቴጅ አዲስ ከሚካኤል በላይነህ ጋር የሚያደረገው አዝናኝ እና አስተማሪ ቆይታ ነገ ማክሰኞ መስከረም 28 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ጀምሮ አሜሪካን ኢምባሲ ቅጥር ግቢ ውስጥ ( ከስድስት ኪሎ ወደ ሽሮሜዳ መሄጃ ) ይካሄዳል።
በዝግጅቱ ላይ ለመታደም ከታች ያለውን ሊንክ በመንካት ይመዝገቡ:
https://bit.ly/SatchmoCenterMembership
መታወቂያ መያዝ እንዳይረሳ፣ማርፈድ ወደ ውስጥ እንዳትገቡ ያደርጋል ፕሮግራሙ ከመጀመሩ ቀደም ብላችሁ ለመገኘት ሞክሩም ተብላችኋል።

📌የሠዓሊ ዮሐንስ ባዩ "ምስጋና"አውደርዕይ!
የ"እርሳስ ቤተጥበብ" መስራች ሠዓሊ ዮሐንስ ባዩ "ምስጋና" በሚል ርዕስ ያዘጋጀው ለየት ያለ የሥነጥበብ አውደርዕይ ከነገ ማክሰኞ መስከረም 28 2017 ዓ.ም ጀምሮ ይካሄዳል።
የሠዓሊ ዮሐንስ ባዩ "እርሳስ ቤተ ጥበብ / Ersas art studio / የተመሰረተበትን እና የሠዓሊውን የ10 ዓመት የሙያ ጉዞ ለማክበር የተዘጋጀ የሥዕል አውደርዕይ እና የሥዕል መጽሃፍ ምርቃት በማርዮት ሆቴል መስከረም 28 በልዩ ፕሮግራም እና ግብዣ ጥሪ ለተደረገላቸው እንግዶች እንዲሁም ከመስከረም 29 - ጥቅምት 1 2017 ለጥበብ አድናቂዎች ክፍት ይሆናል ተብሏል።
ሠዓሊ ዮሐንስ ባዩ የ"እርሳስ ቤተ ጥበብ" መስራች እና የሙሉ ጊዜ ሠዓሊ ሲሆን ላለፉት ዓመታት በሙያው በተለያዩ የሥነ ሥዕል እና የ ሞዛይክ ጥበብ ለግለሰቦች፣ለ ኤምባሲዎች፣ ለሆቴሎች፣ለመንግስት እና ለተለያዩ ተቋማት በመስራት እንዲሁም በሀገር ውስጥ እና በባህር ማዶ ሀገራት የሀገራችንን የኢትዮጵያን ስም ከፍ የሚያደርጉ ወደ 20 የሚጠጉ የሥዕል ዐውደርዕዮችን አቅርቧል።
የተለያዩ ዓለም አቀፍ ሽልማቶችን (Oscar of young African 2019) ጨምሮ በማግኘት እውቅናን ያተረፈ ወጣት ሠዓሊ ነው።
በእውነታዊ / realistic / የአሳሳል ዘይቤ የሚታወቀው ሠዓሊው ውበትን፣እምነትን፣ ምስጋናን እና ተስፋን በሥዕሎቹ አጉልቶ ያሳየናል::

📌ዲዛይነር ተሻለች ታደሰ ተሸለመች
በአሜሪካ ነዋሪ የሆነችው ታዋቂዋ የአዶት ዲዛይን መስራችና ባለቤት ተሻለች ታደሰ ኤጋ Adot Enset በፊሊፒኖ አሜሪካ ካንሰር ተቋም የአመቱ ልዩ ተሸላሚ ሆናለች።
ዲዛይነሯ ከሰሞኑ በቨርጂኒያ ሀያት ሬጀንሲ ሆቴል በተካሄደው አመታዊ የካንሰር ህሙማን የግንዛቤ ማስጨበጫና የገቢ ማሰባሰቢያ የእራት ግብዣ ላይ ብቸኛዋ ኢትዮጵያዊትና አፍሪካዊት ሆና የፋሽን ሾው ስራዎቿን አቅርባለች፤ አዘጋጆቹም በአዶት ዲዛይን ፈጠራና ስራ በመደነቅ ልዩ የእውቅና ሽልማት አበርክተውላታል።
ዲዛይነር ተሻለች በተለይ በእንሰትና በሽመና ምርቶች ልዩ ልዩ የፈጠራ አቅርቦቶችን በመስራት ትታወቃለች፤ በ2019 በፋሽን ሾው ዳውን ሂውስተን ከ12 ዲዛይነሮች አንደኛ ወጥታ በቴክሳስ ሂውስተን ተሸልማለች።
በ2021 ደግሞ በሜሪላንድ አናፖሊስ በቨርችዋል ፋሽን ሾው በተመሳሳይ እውቅና አግኝታለች። ከሰሞኑ ደግሞ የመሰረት በጎ አድራጎት ድርጅት የአሜሪካ ከተሞች አምባሳደር ሆና በድርጅቱ ባለቤት ወ/ሮ መሰረት አዛገ ተሹማለች።
"የጫማ ጠጋኙ ልጅ" ዲዛይነር ተሻለች ታደሰ የአባቷን የስራ ትጋትና ችሎታ ተመልክታ የእናቷን የእንሰት ፍቅር አስተውላ ወደ ዲዛይን እና ፋሽን ኢንዱስትሪ መግባቷን ትናገራለች።

📌የደራሲ ዓለማየሁ ገላጋይ አምስት መጻሕፍት በድጋሚ ታትመው ለአንባቢያን ቀረቡ
የደራሲ ዓለማየሁ ገላጋይ "ማዕበል ጠሪ ወፍ" እና ከገበያ የጠፉት አራት መፅሐፎች በድጋሚ ታትመው ገበያ ላይ ውለዋል ።
ድጋሚ ለህትመት የበቁት መጻሕፍት ማዕበል ጠሪ ወፍ፣ ቤባኒያ ፣በፍቅር ስም፣ወሪሳ እና መለያየት ሞት ነው የተሰኙ መጻሕፍት ናቸው።
የመጻህፍቱ አሳታሚና አከፋፋዩ ደግሞ ዋሊያ መጻሕፍት መደብር ነው።
©️መረጃው የይትባረክ ዋለልኝ ነው።
ለተጨማሪው:https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
የደራሲ ዓለማየሁ ገላጋይ "ማዕበል ጠሪ ወፍ" እና ከገበያ የጠፉት አራት መፅሐፎች በድጋሚ ታትመው ገበያ ላይ ውለዋል ።
ድጋሚ ለህትመት የበቁት መጻሕፍት ማዕበል ጠሪ ወፍ፣ ቤባኒያ ፣በፍቅር ስም፣ወሪሳ እና መለያየት ሞት ነው የተሰኙ መጻሕፍት ናቸው።
የመጻህፍቱ አሳታሚና አከፋፋዩ ደግሞ ዋሊያ መጻሕፍት መደብር ነው።
©️መረጃው የይትባረክ ዋለልኝ ነው።
ለተጨማሪው:https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌የዛሬው የፕሪስቴጅ አዲስ መርሐግብር ተራዝሟል
ፕሪስቴጅ አዲስ ከድምጻዊ ሚካኤል በላይነህ ጋር ዛሬ ማክሰኞ መስከረም 28 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ጀምሮ አሜሪካን ኢምባሲ ቅጥር ግቢ ውስጥ ለማካሄድ አስቦት የነበረው የዓመቱ የመጀመሪያ መሰናዶ በአንዳንድ ምክንያቶች እንደተራዘመ አዘጋጆቹ ለኤቨንት አዲስ ድረገፅ ገልጽዋል።
የተለያዩ የጥበብ ባለሞያዎችን እየጋበዝ ልምዶቻቸውን እንዲያጋሩ እያደረገ ያለው ፕሪስቴጅ አዲስ መርሐግብር በአዲሱ ዓመት የመጀመሪያ ፕሮግራሙ በተወዳጅ የፍቅር ዘፈኖቹ የሚታወቀውን ስመ-ጥር እና በአዲሱ የሙዚቃ አልበሙ ደግሞ ተወዳጅነትን ያተረፈውን ድምፃዊ የግጥም እና ዜማ ደራሲ አርቲስት ሚካኤል በላይነህን በልዩ እንግድነት ጋብዞት ነበር።
እዚህ መርሐግብር ላይ ለመታደም ተመዝገባችሁ ቀጠሮ የያዛችሁ ታዳሚያን እንዳትንገላቱ መርሐግብሩ መራዘሙን እወቁት ብለዋል አዘጋጆቹ።

📌ካናል ፕላስ የሳትላይት ቴሌቪዥን ከታህሣሥ 22 ጀምሮ ስርጭቱን እንደሚያቋርጥ አስታወቀ።
የፈረንሳዩ ሳተላይት ቴሌቪዥን ቻናል ካናል ፕላስ በኢትዮጵያ ከታህሣሥ 22 ጀምሮ ስርጭቱን እንደሚያቋርጥ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ከጣቢያው ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
ካናል ፕላስ በማህበራዊ ትስስር ገፁ "የፕሮግራም ስርጭታችንን ታህሳስ 22 2017 ስለምናቋርጥ የደንበኝነት እድሳት ከጥቅምት 21 2017 ይቆያል" ብሏል።
በተጨማሪም ቴሌቪዥን ጣቢያው"ለነበረንም ቆይታ በድጋሚ ከልብ እናመሰግናለን " በማለት ምስጋናውን አቅርቧል።
ካናል ፕላስ በኢትዮጵያ ከስታር ታይምስ እና ዲ ኤስ ቲቪ ቀጥሎ ሶስተኛው የሳተላይት ቴሌቪዥን ቻናል ነበር ።
ለተጨማሪው:https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
የፈረንሳዩ ሳተላይት ቴሌቪዥን ቻናል ካናል ፕላስ በኢትዮጵያ ከታህሣሥ 22 ጀምሮ ስርጭቱን እንደሚያቋርጥ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ከጣቢያው ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
ካናል ፕላስ በማህበራዊ ትስስር ገፁ "የፕሮግራም ስርጭታችንን ታህሳስ 22 2017 ስለምናቋርጥ የደንበኝነት እድሳት ከጥቅምት 21 2017 ይቆያል" ብሏል።
በተጨማሪም ቴሌቪዥን ጣቢያው"ለነበረንም ቆይታ በድጋሚ ከልብ እናመሰግናለን " በማለት ምስጋናውን አቅርቧል።
ካናል ፕላስ በኢትዮጵያ ከስታር ታይምስ እና ዲ ኤስ ቲቪ ቀጥሎ ሶስተኛው የሳተላይት ቴሌቪዥን ቻናል ነበር ።
ለተጨማሪው:https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌አሻም ቲቪ "የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ" ተሰጠው!
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ዛሬ መስከረም 29 ቀን 2017 ዓ.ም ለአሻም ሚዲያ ትሬዲንግ አክሲዮን ማህበር በጻፈው ደብዳቤ ‹‹ የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ›› ሰጥቷል፡፡
ባለስልጣኑ ለእዚህ ውሳኔ ያበቃው ‹‹ ትክክለኛ ያልሆኑ መረጃዎችን፣ ግጭት አባባሽ ዘገባዎችን፣ የሕዝብን አብሮነት የሚሸረሸሩ፣ የአገርና ብሔራዊ ጥቅም የሚጎዱ መረጃዎችን በቂ ማጣራትና ምክንያታዊ ጥረት ሳያደርግ በተደጋጋሚ ማሰራጨቱን በይዘት ክትትል በማረጋገጤ ነው ›› ብሏል፡፡
ይህ ለአሻም ቲቪ የተሰጣት የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ደብዳቤ ሲቀጥል ‹‹ ከዚህ ቀደም ባሰራጨው ግጭት ተኮር እና ሚዛናዊነት የጎደለው ዘገባ ከደርጊቱ እንዲቆጠብ በተደጋጋሚ በባለስልጣኑ የጽሁፍና የቃል ማሳሰቢያ ሲሰጠው መቆየቱን ›› አስታውሶ ‹‹ ጣቢያው ግን የባለስልጣኑን ማሳሰቢያ ባለማክበር የሀገሪቱን ህጎች የሚጥሱ ይዘቶችን በማሰራጨት ላይ ይገኛል ›› ብሏል።
አሻም ቲቪ በበኩሉ "ባለስልጣኑ ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ አሻም በምትሰራቸው ሚዛናዊ ዘገባዎች ላይ ኢ-አሰማኝ የሆኑ የማሳሰቢያ ደብዳቤዎችን ሲጽፍ ሰንብቷል፤ የሥራ ኃላፊዎችም በቃል ሲስጠነቅቁ ከርመዋል፡፡ ይሁን እንጂ አሻም ለሁሉም ደብዳቤዎች ተገቢ ምላሾችን ከነማስረጃዎቹ በመጥቀስ ምላሽ ስትሰጥ ከርማለች፡፡ አንድም ጊዜ ግን አሻም የሰጣቻቸው የጽሁፍ ምላሾች ስህተት ስለመሆናቸው አልያም ውድቅ ስለመደረጋቸው ባለስልጣኑ የመልስ-መልስ ደብዳቤ ጽፎ አያውቅም" ብሏል።
በተጨማሪም ቴሌቪዥን ጣቢያው" የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ለአሻም ቲቪ የሰጠው የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ አንድም በተጨባጭ የተረጋጋጠ ማስረጃ የሌለው ነው " ሲል ምላሽ ሰጥቷል።

"ግራ ቀኝ" ተከታታይ ድራማ ወደ ፊልም ሊቀየር ነው።
"ግራ ቀኝ" ተከታታይ ሲትኮም ድራማ ወደ ፊልም ተቀይሮ ሊሰራ እንደሆነ ኤቨንት አዲስ ድረገጽ ከአዘጋጆቹ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
በሀማ ቱማ በእንግሊዝኛ ተጽፎ በህይወት ታደሰ "የሶሻሊስቱ ጠንቋይ ነገር" በሚል ርዕስ ወደ አማርኛ የተተረጎ መጽሐፍን መነሻ በማድረግ የተዘጋጀው "ግራ ቀኝ" ተከታታይ ሲትኮም ድራማ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ሲቀረብ ቆይቷል።
"ግራ ቀኝ" በተከታታይ ሲትኮም ድራማ መልክም በሁለት ምዕራፎች እና በ24 ክፍሎች የቀረበ ሲሆን አበበ ባልቻ፣ ግሩም ዘነበ፣ ሚካኤል ታምሬ ከተጋባዥ ተዋናዮች ጋር በጋራ ተውነውበታል።
ዛሬ መስከረም 29 ቀን 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ራስ መኮንን አዳራሽ ውስጥ የድራማው የምዕራፎች ማጠቃለያ መርሐግብርም ተካሄዷል።
በምዕራፎቹ የማጠቃለያ ዝግጅት ላይም "ግራ ቀኝ" ተከታታይ ሲትኮም ድራማ ወደ ዘጠና ደቂቃ የሚፈጅ ፊልም ተቀይሮ ለተመልካቾች እንደሚቀርብ የድራማው አዘጋጅ ድርብድል አሰፋ ተናግሯል።

📌የሮፍናን ኮንሰርት በሐዋሳ ከተማ ይካሄዳል!
ሁለገቡ ሙዚቀኛ ሮፍናን ኑሪ ከዋሊያ ቢራ ጋር በመሆን ያዘጋጁት የሙዚቃ ኮንሰርት ቅዳሜ ጥቅምት 2 ቀን 2017 ዓ.ም አመሻሽ ላይ በሐዋሳ ከተማ ትልቁ ስታዲየም እንደሚካሄድና ፍቃድ እንዳገኘ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ከታማኝ ምንጭ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
በትላትናው ዕለትም ይህ የሮፍናን ኮንሰርት በሐዋሳ ከተማ የተወሰኑ ነዋሪዎች በተነሳበት ተቃውሞ "ኮንሰርቱ በከተማው እንዳይካሄድ ተሰርዟል" የሚል መረጃ በማህበራዊ ትስስር ገፆች በስፋት ሲሰራጭ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ተመልክቷል።
ነገር ግን ከኮንሰርቱ አዘጋጆችም ሆነ ከከተማው አስተዳደር ኮንሰርቱ ስለመሰረዙ በይፋ የተገለፀ ነገር አልነበረም።
ዛሬ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ከታማኝ ምንጮቹ እንደሰማሁ ከሆነ የሙዚቀኛ ሮፍናን ኑሪ "የኔ ትውልድ " ኮንሰርት ቅዳሜ ጥቅምት 2 2017 ዓ.ም በሐዋሳ ከተማ ትልቁ ስታዲየም ይካሄዳል ተብሏል።
በተጨማሪም የሮፍናን "የኔ ትውልድ" ኮንሰርት ሲቀጥል የፊታችን ጥቅምት 9 ቀን 2017 ዓ.ም በወላይታ ሶዶ ከተማም ይካሄዳል።

📌ኦቢኤስ ቴሌቪዥን ጣቢያ መደበኛ ስርጭቱን አቋረጠ
ኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ሰርቪስ (ኦቢኤስ) ቴሌቪዥን ጣቢያ መደበኛ ስርጭቱን ማቋረጡን አስታውቋል። ጣቢያው ስርጭቱን ያቋረጠው የሳተላይት ኪራይ ወጪውን “መቋቋ ስላልቻልኩ ነው” ብሏል።
ኦቢኤስ በይፋዊ የፌስቡክ ገጹ ላይ ይፋ ባደረገው መልዕክት መሰረት፣ ከመስከረም 27 ቀን 2017 ዓ.ም. ጀምሮ የሳተላይት ስርጭቱን እንዳቋረጠ ገልጿል። በማያያዝም፣ ስርጭቱን የማቋረጡ ምክንያት የዶላር የምንዛሪ ዋጋ ላይ የተከሰተውን ለውጥ ተከትሎ የሳተላይት ኪራይ ወጪው መጨመሩን አመልክቷል።
ተከታታዮቹ በተለያዩ ማሕበራዊ ትስስር ድረ ገጾች ላይ ድጋፋቸውን መግለጻቸውን በምስጋና የጠቀሰው ኦቢኤስ፣ የጣቢያው ስራ አመራር በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ ሳተላይት ስርጭት ለመመለስ የተለያዩ ጥረቶችን እያደረገ እንደሚገኝ በዚሁ መልዕክት ላይ አብራርቷል፣ ጣቢያው። “ድጋፍ እያደረጉልኝ ነው” ላላቸው ወገኖችም ምስጋናውን አቅርቧል።
ኦቢኤስ የሳተላይት ስርጭቱ ቢቋረጥም፣ በዩቲዩብ ቻናሉ ግን መደበኛ ፕሮግራሞቹን ለተመልካቾቹ እያደረሰ እንደሚገኝ ለማወቅ ተችሏል።
ቴሌቪዥን ጣቢያው የሪፍትቫሊ ዩኒቨርስቲ እና ሌሎች የንግድ ተቋማት ባለቤት በሆኑት አቶ ድንቁ ደያስ ድጋፍ መቋቋሙ የሚታወቅ ነው።
©️መረጃው የአዲስ አድማስ ጋዜጣ ነው።

📌በእረፍት ቀንዎ ቴአትር ይመለከቱ !
አንጋፋው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር እና የቦሌው ዓለም ሲኒማ አርብ፣ ቅዳሜ እና እሁድ እነዚህን ተውኔቶች ለታዳሚያን ያቀርባሉ።
📍 ጎዶ'ን ጥበቃ
ድርሰት: ሳሙኤል ቤኬት
ትርጉም: ሀይከል ሙባረክ
አዘጋጅ: ዳግም ሲሳይ
ቀን: ሐሙስ
ሰዓት:11:30
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር
📍 የፍቅር ካቴና
ድርሰትና ዝግጅት: አለልኝ መኳንት ፅጌ
ቀን: አርብ
ሰዓት: 12:00
ቦታ: ዓለም ሲኒማ
📍 "እሳት ወይ አበባ"
ድርሰት: ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን እንደጻፈው
ዳንስና ዳንስ ቅንብር: ሽፈራው ታሪኩ ቢረጋ
ቀን: አርብ
ሰዓት:11:30
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር
📍 ባሎች እና ሚስቶች
ድርሰት: ውዱ አለን
አዘጋጅ: ሳሙኤል ተስፋዬ
ቀን: ቅዳሜ
ሰዓት: 8:00
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር
📍 ባቡሩ
ድርሰት: አርኖልድ ሪድሊ
አዘጋጅ:ራሔል ተሾመ መሐመድ
ቀን: ቅዳሜ
ሰዓት:11:30
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር
📍 ሸምጋይ
ድርሰት:ታደለ አያሌው
አዘጋጅ: ሳሙኤል ተስፋዬ
ቀን: እሁድ
ሰዓት: 8:00
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር
📍 እምዩ ብረቷ
ድርሰት: ቤልቶልት ብሬሽት
አዘጋጅ: ማንያዘዋል እንዳሻው
ቀን: እሁድ
ሰዓት:11:30
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር
የእናንተው ኤቨንት አዲስ ድረገፅ መልካም የእረፍት ቀን ይሁንላችሁ ይላል !
ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1

"ኢትዮ ከለር" የባህል ቡድን የኢትዮጵያን ባህል በጃፓን እያስተዋወቀ ይገኛል።
በዓለም ሎሬት አርቲስት መላኩ በላይ የሚመራው "ኢትዮ ከለር" የባህል ቡድን የኢትዮጵያን ባህል በጃፓን ሀገር እያስተዋወቀ እንደሚገኝ ተገልጿል።
"ኢትዮ ከለር" የባህል ቡድን በጃፓን ትምህርት ቤቶች የኢትዮጵያን ባህል አስተዋውቋል። የጃፓን ልጆች ለኢትዮጵያ ባህል ሙዚቃ እና ውዝዋዜ ያላቸው ፍቅር የተለየ ነው ሲል የገለፀው የዓለም ሎሬት መላኩ፤ ይህንን በማየታችን እና የሀገራችንን ባህል በማስተዋወቃችን ክብርና ደስታ ይሠማናል ብሏል።
የሀገራችንን ባህል በማካፈል ከጃፓን ሙዚቀኞች ጋር ውብ የሆነ የፈጠራና የባህል ልምድ ልውውጥ እየተደረገ መኾኑም ተገልጿል።