"ግራ ቀኝ" ተከታታይ ድራማ ወደ ፊልም ሊቀየር ነው።
"ግራ ቀኝ" ተከታታይ ሲትኮም ድራማ ወደ ፊልም ተቀይሮ ሊሰራ እንደሆነ ኤቨንት አዲስ ድረገጽ ከአዘጋጆቹ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
በሀማ ቱማ በእንግሊዝኛ ተጽፎ በህይወት ታደሰ "የሶሻሊስቱ ጠንቋይ ነገር" በሚል ርዕስ ወደ አማርኛ የተተረጎ መጽሐፍን መነሻ በማድረግ የተዘጋጀው "ግራ ቀኝ" ተከታታይ ሲትኮም ድራማ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ሲቀረብ ቆይቷል።
"ግራ ቀኝ" በተከታታይ ሲትኮም ድራማ መልክም በሁለት ምዕራፎች እና በ24 ክፍሎች የቀረበ ሲሆን አበበ ባልቻ፣ ግሩም ዘነበ፣ ሚካኤል ታምሬ ከተጋባዥ ተዋናዮች ጋር በጋራ ተውነውበታል።
ዛሬ መስከረም 29 ቀን 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ራስ መኮንን አዳራሽ ውስጥ የድራማው የምዕራፎች ማጠቃለያ መርሐግብርም ተካሄዷል።
በምዕራፎቹ የማጠቃለያ ዝግጅት ላይም "ግራ ቀኝ" ተከታታይ ሲትኮም ድራማ ወደ ዘጠና ደቂቃ የሚፈጅ ፊልም ተቀይሮ ለተመልካቾች እንደሚቀርብ የድራማው አዘጋጅ ድርብድል አሰፋ ተናግሯል።
ለተጨማሪው:https://news.1rj.ru/str/EventAddis1

📌የሮፍናን ኮንሰርት በሐዋሳ ከተማ ይካሄዳል!
ሁለገቡ ሙዚቀኛ ሮፍናን ኑሪ ከዋሊያ ቢራ ጋር በመሆን ያዘጋጁት የሙዚቃ ኮንሰርት ቅዳሜ ጥቅምት 2 ቀን 2017 ዓ.ም አመሻሽ ላይ በሐዋሳ ከተማ ትልቁ ስታዲየም እንደሚካሄድና ፍቃድ እንዳገኘ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ከታማኝ ምንጭ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
በትላትናው ዕለትም ይህ የሮፍናን ኮንሰርት በሐዋሳ ከተማ የተወሰኑ ነዋሪዎች በተነሳበት ተቃውሞ "ኮንሰርቱ በከተማው እንዳይካሄድ ተሰርዟል" የሚል መረጃ በማህበራዊ ትስስር ገፆች በስፋት ሲሰራጭ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ተመልክቷል።
ነገር ግን ከኮንሰርቱ አዘጋጆችም ሆነ ከከተማው አስተዳደር ኮንሰርቱ ስለመሰረዙ በይፋ የተገለፀ ነገር አልነበረም።
ዛሬ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ከታማኝ ምንጮቹ እንደሰማሁ ከሆነ የሙዚቀኛ ሮፍናን ኑሪ "የኔ ትውልድ " ኮንሰርት ቅዳሜ ጥቅምት 2 2017 ዓ.ም በሐዋሳ ከተማ ትልቁ ስታዲየም ይካሄዳል ተብሏል።
በተጨማሪም የሮፍናን "የኔ ትውልድ" ኮንሰርት ሲቀጥል የፊታችን ጥቅምት 9 ቀን 2017 ዓ.ም በወላይታ ሶዶ ከተማም ይካሄዳል።

📌ኦቢኤስ ቴሌቪዥን ጣቢያ መደበኛ ስርጭቱን አቋረጠ
ኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ሰርቪስ (ኦቢኤስ) ቴሌቪዥን ጣቢያ መደበኛ ስርጭቱን ማቋረጡን አስታውቋል። ጣቢያው ስርጭቱን ያቋረጠው የሳተላይት ኪራይ ወጪውን “መቋቋ ስላልቻልኩ ነው” ብሏል።
ኦቢኤስ በይፋዊ የፌስቡክ ገጹ ላይ ይፋ ባደረገው መልዕክት መሰረት፣ ከመስከረም 27 ቀን 2017 ዓ.ም. ጀምሮ የሳተላይት ስርጭቱን እንዳቋረጠ ገልጿል። በማያያዝም፣ ስርጭቱን የማቋረጡ ምክንያት የዶላር የምንዛሪ ዋጋ ላይ የተከሰተውን ለውጥ ተከትሎ የሳተላይት ኪራይ ወጪው መጨመሩን አመልክቷል።
ተከታታዮቹ በተለያዩ ማሕበራዊ ትስስር ድረ ገጾች ላይ ድጋፋቸውን መግለጻቸውን በምስጋና የጠቀሰው ኦቢኤስ፣ የጣቢያው ስራ አመራር በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ ሳተላይት ስርጭት ለመመለስ የተለያዩ ጥረቶችን እያደረገ እንደሚገኝ በዚሁ መልዕክት ላይ አብራርቷል፣ ጣቢያው። “ድጋፍ እያደረጉልኝ ነው” ላላቸው ወገኖችም ምስጋናውን አቅርቧል።
ኦቢኤስ የሳተላይት ስርጭቱ ቢቋረጥም፣ በዩቲዩብ ቻናሉ ግን መደበኛ ፕሮግራሞቹን ለተመልካቾቹ እያደረሰ እንደሚገኝ ለማወቅ ተችሏል።
ቴሌቪዥን ጣቢያው የሪፍትቫሊ ዩኒቨርስቲ እና ሌሎች የንግድ ተቋማት ባለቤት በሆኑት አቶ ድንቁ ደያስ ድጋፍ መቋቋሙ የሚታወቅ ነው።
©️መረጃው የአዲስ አድማስ ጋዜጣ ነው።

📌በእረፍት ቀንዎ ቴአትር ይመለከቱ !
አንጋፋው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር እና የቦሌው ዓለም ሲኒማ አርብ፣ ቅዳሜ እና እሁድ እነዚህን ተውኔቶች ለታዳሚያን ያቀርባሉ።
📍 ጎዶ'ን ጥበቃ
ድርሰት: ሳሙኤል ቤኬት
ትርጉም: ሀይከል ሙባረክ
አዘጋጅ: ዳግም ሲሳይ
ቀን: ሐሙስ
ሰዓት:11:30
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር
📍 የፍቅር ካቴና
ድርሰትና ዝግጅት: አለልኝ መኳንት ፅጌ
ቀን: አርብ
ሰዓት: 12:00
ቦታ: ዓለም ሲኒማ
📍 "እሳት ወይ አበባ"
ድርሰት: ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን እንደጻፈው
ዳንስና ዳንስ ቅንብር: ሽፈራው ታሪኩ ቢረጋ
ቀን: አርብ
ሰዓት:11:30
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር
📍 ባሎች እና ሚስቶች
ድርሰት: ውዱ አለን
አዘጋጅ: ሳሙኤል ተስፋዬ
ቀን: ቅዳሜ
ሰዓት: 8:00
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር
📍 ባቡሩ
ድርሰት: አርኖልድ ሪድሊ
አዘጋጅ:ራሔል ተሾመ መሐመድ
ቀን: ቅዳሜ
ሰዓት:11:30
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር
📍 ሸምጋይ
ድርሰት:ታደለ አያሌው
አዘጋጅ: ሳሙኤል ተስፋዬ
ቀን: እሁድ
ሰዓት: 8:00
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር
📍 እምዩ ብረቷ
ድርሰት: ቤልቶልት ብሬሽት
አዘጋጅ: ማንያዘዋል እንዳሻው
ቀን: እሁድ
ሰዓት:11:30
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር
የእናንተው ኤቨንት አዲስ ድረገፅ መልካም የእረፍት ቀን ይሁንላችሁ ይላል !
ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1

"ኢትዮ ከለር" የባህል ቡድን የኢትዮጵያን ባህል በጃፓን እያስተዋወቀ ይገኛል።
በዓለም ሎሬት አርቲስት መላኩ በላይ የሚመራው "ኢትዮ ከለር" የባህል ቡድን የኢትዮጵያን ባህል በጃፓን ሀገር እያስተዋወቀ እንደሚገኝ ተገልጿል።
"ኢትዮ ከለር" የባህል ቡድን በጃፓን ትምህርት ቤቶች የኢትዮጵያን ባህል አስተዋውቋል። የጃፓን ልጆች ለኢትዮጵያ ባህል ሙዚቃ እና ውዝዋዜ ያላቸው ፍቅር የተለየ ነው ሲል የገለፀው የዓለም ሎሬት መላኩ፤ ይህንን በማየታችን እና የሀገራችንን ባህል በማስተዋወቃችን ክብርና ደስታ ይሠማናል ብሏል።
የሀገራችንን ባህል በማካፈል ከጃፓን ሙዚቀኞች ጋር ውብ የሆነ የፈጠራና የባህል ልምድ ልውውጥ እየተደረገ መኾኑም ተገልጿል።

📌የበዓላት ሙዚቃዎች ላይ የኂስ ውይይት ተካሄደ።
"ኂስን ባህላችን እናድርግ" በሚል መሪ ቃል በዓላትን አስመልክተው የሚሰሩ ዘፈኖች ለማኅበራዊ ትስስር ያላቸው ፋይዳ ላይ ውይይት ተካሂዷል።
የአዲስ አበባ ባህልና ኪነጥበብ ቢሮ ባዘጋጀው 23ኛ የኂስና ውይይት መድረክ ላይ በሀገረሰብ ደረጃ በሚዜሙ የበዓላት ዘፈኖች ከፍተኛ የሆነ የማኅበረሰብ ትስስርን የሚፈጥሩ እንደሆነ ተመላክቷል።
ወጣቶች ባህላዊና ጥንታዊ የሆኑና የማኅበረሰብ አንድነትን የሚፈጥሩ ሀገር በቀል ዜማዎችን ማወቅ፣ ለውይይት መነሻ ማድረግና መጠበቅ እንዳለባቸው ተገልጿል።
ኢትዮጵያ እምቅ የሆነ ባህል ያላት በመሆኑ እነዚህን የማኅበረሰብ መታወቂያዎች የበዓላት ዘፈኖች መሰነድና ጥናትና ምርምሮችን ማድረግ ይገባልም ተብሏል።
በተለይም በዚህ መንገድ ውይይትንና ኂስን ማስቀጠል ወጣቶችን ማሳተፍና የጥበብና የባህል ሽግግር ማድረግ እንደሚገባ ተመላክቷል።
©️መረጃው አራዳ ኤፍ ኤም 95.1 ነው።

📌የገጣሚ ባንቺአየሁ አሰፋ አዲስ የግጥም መጽሐፍ በቅርቡ ለንባብ ይበቃል።
የወጣቷ ገጣሚ ባንቺአየሁ አሰፋ "ላልዪበላይቱ" የተሰኘ ርዕስ የተሰጠው አዲስ የግጥም መጽሐፍ በቅርቡ ለአንባቢያን ይደርሳል ተብሏል።
የግጥም መጽሐፉ በ300 ብር የጀርባ ዋጋ በቅድመ ክፍያ ሽያጭ ለአንባቢያን የቀረበ ነው።
መጽሐፉን አስቀድሞ የመግዛት የሚከተለውን ቅደመተከተል ይመለከቱ ተብለዋል።
የመፅሐፍ ቅድመ ሽያጭ
ርዕስ - ላልዪበላይቱ
ዋጋ - 300 ብር
የባንክ ቁጥር ፦
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፦ 1000070884414
አቢሲኒያ ፦193776469 ባንቺዐየሁ አሰፋ
ለክፉም ለደጉም Screenshot @Banchassefa1 ወይም Messeger መላክወን አይዘንጉ ተብለዋል ።

📌የገጣሚ ዮሐንስ ሞላ አዲስ መጽሐፍ በቅርቡ ለአንባቢያን ይደርሳል።
የገጣሚ ዮሐንስ ሞላ "በከንፈርሽ በራፍ" የተሰኘ የግጥም በቅርቡ ለአንባቢያን ይደርሳል ተብሏል።
ገጣሚ ዮሐንስ በማህበራዊ ትስስር ገፁም"
መቼም ሰው ከአደይ አበባ ጋር ቀጠሮ እንዳለው ሁሉ በመስከረም ሲመጣ "እጅ ከምን" ቢባል ወግ ነውና፣ እነሆ የብቻ ሦስተኛ መጽሐፌን በቅርብ ቀን ብያለሁ።
"በከንፈርሽ በራ'ፍ"ን እንደ ታናናሾቿ እንደ የ"ብርሃን ልክፍት" እና "የብርሃን ሰበዞች" ፊት ሰጥታችሁ፣ ስማችሁ፣ ተቆጥታችሁ፣ ተንከባክባችሁ እንደምታሳድጉልኝ አምናለሁ" ብሏል።
ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
የገጣሚ ዮሐንስ ሞላ "በከንፈርሽ በራፍ" የተሰኘ የግጥም በቅርቡ ለአንባቢያን ይደርሳል ተብሏል።
ገጣሚ ዮሐንስ በማህበራዊ ትስስር ገፁም"
መቼም ሰው ከአደይ አበባ ጋር ቀጠሮ እንዳለው ሁሉ በመስከረም ሲመጣ "እጅ ከምን" ቢባል ወግ ነውና፣ እነሆ የብቻ ሦስተኛ መጽሐፌን በቅርብ ቀን ብያለሁ።
"በከንፈርሽ በራ'ፍ"ን እንደ ታናናሾቿ እንደ የ"ብርሃን ልክፍት" እና "የብርሃን ሰበዞች" ፊት ሰጥታችሁ፣ ስማችሁ፣ ተቆጥታችሁ፣ ተንከባክባችሁ እንደምታሳድጉልኝ አምናለሁ" ብሏል።
ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌ድምፃዊ ሙሉዓለም ታከለ የመጀመሪያ የሙዚቃ አልበሙን በዚህ ዓመት ለአድማጮች እንደሚያደርስ አስታወቀ
በተለያዩ ነጠላ ዜማዎች ከሙዚቃ አፍቃሪያን ጋር የተዋወቀው ወጣቱ ድምፃዊ ሙሉዓለም ታከለ ‹‹ባለክራሩ›› በተሰኘው ፊልም ላይ በክራር ብቻ ያቀነቀናቸውን የሙዚቃ ስራዎች ስብስብ በአዲስ መልክ መስራቱን ለመሰንበቻ የሬድዮ ፕሮግራም አስታውቋል፡፡
በክራር የሙዚቃ መሳሪያ ብቻ ታጅቦ ያቀነቀናቸው የቀደሙ ስራዎችን ጨምሮ ለፊልሙ የተዘጋጀ አንድ ሙዚቃን ጨምሮ በድምሩ አምስት ስራዎች እንደሆኑ ታውቋል፤ ድምፃዊው ከእዚህ ቀደም ‹ህዳር› በተሰኘው ፊልም ላይ ባቀነቀነው የማጀቢያ ሙዚቃ አማካይነት በጉማ አዋርድ ላይ ተሸልሞ እንደነበር ይታወሳል፡፡
ድምፃዊው ከኤፍ ኤም አዲስ 97.1 መሰንበቻ ፕሮግራም ጋር ባደረገው ቆይታ ስለ አዲስ አልበሙ ለተነሳለት ጥያቄ በሰጠው ምላሽ ቢቻል በእዚህ ዓመት አጋማሽ፤ ካልሆነ በ2017ዓ.ም መጨረሻ ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ የማጠናቀቅ ሀሳብ እንዳለው አስታውሷል፡፡
የአልበም ስራው ከተጀመረ ሁለት ዓመታት ሊያስቆጥር ተቃርቧል ያለው ድምጻዊው በስራው ላይ ተሳትፎ ስላደረጉ ባለሙያዎች ባይገልፅም ብዙ ፈተናዎችን አልፎ ቢሆን ለሙዚቃ ወዳጆች የማድረስ ሃሳብ እንዳለው ገልጿል፡፡
ድምፃዊ፤ የግጥምና ዜማ ደራሲ ሙሉዓለም ታከለ ‹እኔ እሻልሻለሁ፤ ሽሩርዬ›ን ጨምሮ በግሉ ሌሎች በርካታ የሙዚቃ ስራዎችን የሰራ ሲሆን ከድምጻዊ ኤፍሬም የማነ ጋር በአብሮነት የሰሩት ‹‹ ተሸንፌያለሁ›› የተሰኘውን ስራም መስራት የቻለ ድምፃዊ ነው፡፡
©️መረጃው የመሰንበቻ የሬድዮ ፕሮግራም ነው።

የአፍሪካ ቀንድ የሠላም Advocacy ስልታዊ እቅድ የመክፈቻ ሥነሥርአት እና ሲምፖዚየም ሊካሄድ ነው።
የአፍሪካ ቀንድ የሠላም Advocacy ስልታዊ እቅድ የመክፈቻ ሥነሥርአት እና ሲምፖዚየም ለሁለት ቀናት በሒልተን ሊካሄድ ነው ተብሏል።
"የምንፈልጋት አፍሪካ" (the Africa we want) የሁነቱ ርዕሰ ጉዳይ ነው።
ዝግጅቱን American Friends Community Services እና Bread for fhe World በጋራ አዘጋጅተውታል።
በዚህ ትልቅ ዝግጅት ላይ አገር አቀፍ እና ዓለም አቀፍ ሲቪክ ማህበረሰብ አካላት ፣የሀይማኖት መሪዎች፣ ዲፕሎማቶች ፣የአፍሪካ ህብረት ፣የአውሮፓውያን ህብረት ፣የኢጋድ እና የመንግሥት አካላት ይሣተፋሉ።
ሁነቱ ጥቅምት 6 እና 7 ቀን 2017 ዓ.ም በሂልተን ሆቴል ለሁለት ቀናት ይካሄዳል ተብሏል።
የዝግጅቱ መሪ ሐሳብ እስከ 2033 የሚዘልቅ ሲሆን ይህም የስድስት ዓመት ፕሮግራም ሠላምን በተመለከተ የተለየ ሀሣብን ይዞ መጥቷል ተብሎ ይታሠባል።
ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1

📌መቅረዝ ሥነኪን የኪነጥበብ ዝግጅት ሐሙስ ይካሄዳል
አንጋፋው ከያኒ ተስፋዬ አበበ (ፋዘር) የክብር እንግዳ የሆነበት "መቅረዝ ሥነኪን" የኪነጥበብ ዝግጅት ሀሙስ ይካሄዳል።
አንጋፋ እና ወጣት የኪነጥበብ ባለሞያዎችን እያጣመር የዘለቀው መቅረዝ ሥነኪን ወርሀዊ የኪነጥበብ ዝግጅት ሐሙስ ጥቅምት 7 ቀን 2017 ዓ.ም ከምሽቱ 11:00 ጀምሮ በብሔራዊ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት (ወመዘክር )አዳራሽ ውስጥ ይካሄዳል።
በዚህ የዓመቱ የመክፈቻ ዝግጅት ላይ አንጋፋው ከያኒ ተስፋዬ አበበ (ፋዘር) የክብር እንግዳ በመሆን የሚገኙ ሲሆን በተጨማሪም ወጣት የኪነጥበብ ባለሞያዎች የግጥም ፣የሙዚቃ እና የዳንስ ስራዎቻቸውን ያቀርባሉ።
የዚህ ዝግጅት መግቢያ በነፃ ነው።

በሮፍናን ኮንሰርት እነማን ስራቸውን አቀረቡ ?
ሮፍናን ስኬታማ ኮንሰርት በሀዋሳ ባለፈው ቅዳሜ አድርጎል ።
በሀዋሳ ትልቁ ስታዲየም በተደረገው ኮንሰርት ከአዋሳኝ ከተሞች በተጨማሪ ከአዲስ አበባ ጭምር ወደ ስፍራው ያቀኑ የሙዚቃ አፍቃሪዎች እንደነበሩ ለሁሉ አዲስ ከሀዋሳ የደረሰው መረጃ ያመላክታል ።
ኃይሌ ሩትሥ ፣ቶክቻው ፣ Shumulo shunde በተጋባዥነት ስራቸውን ማቅረባቸው ታውቋል ።
ኮንሰርቱ እንዳይካሄድ አላስፈላጊ የሆነ ተቀፅላ ለሮፍናን በመስጠት በማህበራዊ ሚድያ ቅስስቀሳ ተደርጎበት የነበረ ቢሆንም አላስፈላጊ ስም ማጥፋቱ አግባብ እንዳልሆነ በርካቶች በማስረዳታቸው በሀዋሳ ደረጃውን የጠበቀ ኮንሰርት ለማድረግ መቻሉን ከስፍራው የደረሰን መረጃ ያመለክታል ።
ሮፍናን ሀይሌ ሩትስ መድረኩን በማድመቅ ለነበረው አበርክቶ በይፋ አመስግኗል ።
ጥቅምት 9,2017 ዓም የኔ ትውልድ ኮንሰርት በወላይታ ሶዶ ይካሄዳል ።
©️መረጃው የሁሉአዲስ ነው።

📌የድምጻዊት አምሳል ምትኬ የባህል ምሽት ቤት የእሳት አደጋ ደረሰበት።
የድምፃዊት አምሳል ምትኬ የባህል ምሽት ቤት እና የምግብ አዳራሽ ጥቅምት 5 2017 ዓ.ም ከምሽቱ 12:30 አካባቢ በተነሳ የእሳት ቃጠሎ አደጋ እንደደረሰበት ዘሐበሻ ዘግቧል።
የባሕር ዳር ነዋሪ እሳቱን ለመቆጣጠር ያደረገው ርብርብ ጥሩ ነበር የተባለ ሲሆን ሆኖም የእሳቱ ሁኔታ ከባድ ስለነበር ንብረት ላይ ጉዳት ማድረሱን እና በሰው ላይ እስካሁን ጉዳት አለማድረሱን ተሰምቷል።
©️መረጃው የዘሐበሻ ነው።
ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
የድምፃዊት አምሳል ምትኬ የባህል ምሽት ቤት እና የምግብ አዳራሽ ጥቅምት 5 2017 ዓ.ም ከምሽቱ 12:30 አካባቢ በተነሳ የእሳት ቃጠሎ አደጋ እንደደረሰበት ዘሐበሻ ዘግቧል።
የባሕር ዳር ነዋሪ እሳቱን ለመቆጣጠር ያደረገው ርብርብ ጥሩ ነበር የተባለ ሲሆን ሆኖም የእሳቱ ሁኔታ ከባድ ስለነበር ንብረት ላይ ጉዳት ማድረሱን እና በሰው ላይ እስካሁን ጉዳት አለማድረሱን ተሰምቷል።
©️መረጃው የዘሐበሻ ነው።
ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌"የወንዜ ሳቢሳ" መጽሐፍ ነገ ይመረቃል
ከአንቷን ቼኮቭ ስራዎች አራት ትርጉም ስብስብ ተውኔቶችን የያዘው "የወንዜ ሳቢሳ"የተሰኘው የትያትር መጽሐፍ በጠበቃ እና የትያትር ባለሙያ በአቶ ሳምሶን ብሬ ተተርጉሞ በቅርቡ ለአንባቢያ ደርሷል፡፡
ይህም መጽሐፍ ነገ ሐሙስ ጥቅምት 7 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 11:00 ሰዓት ጀምሮ በመቅረዝ ሥነኪን ዝግጅት ላይ በብሔራዊ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አግልግሎት (ወመዘክር) አዳራሽ ውስጥ ይመረቃል።
በዝግጅቱም በኢትዮጵያ የሩስያ አምባሳደር እና ጥሪ የተደረገላቸው ታላላቅ እንግዶች ይገኛሉ።
በመጽሐፍ ምረቃው ዝግጅት ላይ የተለያዩ ኪነ-ጥበባዊ ስራዎች የሚቀርቡ ሲሆን በመጽሐፉ ውስጥ ከተተረጎሙ የአንቷን ቼኮቭ ቴአትሮች ውስጥ ባለ አንድ ገቢር የአንድ ሰው አጭር ተውኔት ይቀርባል ተብሏል።

📌የጋዜጠኛ መኮንን ወ/አረጋይ "እነሆ ማሟሻ" ቅጽ ሁለት መጽሐፍ አርብ ለንባብ ይበቃል
ከዚህ ቀደም በሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ ላይ በሚያቀርባቸው የስንክሳር፣ የማሟሻ፣ የሃኪሞ መልዕክት፣ የአርብ ምሽት ቆየት ያሉ ሙዚቃዎች እና አሁን ላይ በኢንቢሲ ቴሌቪዥን በልዩ ልዩ ዝግጅቶች የምናውቀው ጋዜጠኛ መኮንን ወ/አረጋይ በርካታ ጉዳዮች የተካተቱበትን"እነሆ ማሟሻ" ቅጽ ሁለት መጽሐፍ አርብ ጥቅምት 8 ቀን 2017 ዓ.ም ለንባብ ይበቃል።
"እነሆ ማሟሻ" መጽሐፍ ከቅጽ አንድ የቀጠለ ሲሆን በቅጽ ሁለት መጽሐፍ "ስንክሳር" የሬድዮ ዝግጅት ላይ ከቀረቡ ጥናታዊ ጽሑፎች ውስጥ ለቅምሻ እንደተካተተበት ተነግሯል።
ጋዜጠኛ መኮንን ወ/አረጋይ በመጽሐፉ የቅምሻ ክፍል ላይ የሚከተለውን ብሏል"ቅጽ አንድን ሳዘጋጅ የእኔን የሙያ ትሩፋት ለመስጠት ሳይሆን በእኔ ዘንድ ያለውን ለእናንተ ማካፈል ደስታን ስለሚሰጠኝም ጭምር ነው፡፡ በቅጽ ሁለት ቀሪዎች ስራዎችን ለእናንተ ለማድረስ ደፋ ቀና ስል አንድ ሀሳብ ውስጤ ተጫረ፡፡ ስንክሳር።ስንክሳርን ብዙ የሚዲያ ወዳጆቼ ሰምተው የተደመሙበት የተማሩበትና የተዝናኑበት እንደሆነ ሲነግሩኝ ከርመዋል፡፡ ስንክሳር በተለያዩ ጉዳዮች ማለትም በኢትዮጵያ ማህበራዊ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ እውነቶች ላይ ያተኮረ የጥናትና ምርምር ሥራ ነው፡፡እነሆ ማሟሻ ስታድግ በወርድና ስፋቷ ስንከሳርን ታክላለች፡፡ እና ለወዳጆቼ ለምን ስንክሳርንስ አላጋራም? ነበር ውስጤ የተጫረው ሀሳብ። ከብዙ ስራዎቼ ለሚቀጥሉት ህትመቶች በር መክፈቻ ብትሆን እነሆ የስንከሳርን ቅምሻ ላቀርብ ወደድኩ"።
መጽሐፉ በ200 ገፆች የተነበበ ሲሆን ከአርብ ጀምሮ ለአንባቢያን እንደሚደርስ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ሰምቷል።

አንጋፋው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር እና የቦሌው ዓለም ሲኒማ ሐሙስ፤ አርብ፣ ቅዳሜ እና እሁድ እነዚህን ተውኔቶች ለታዳሚያን ያቀርባሉ።
📍 ጎዶ'ን ጥበቃ
ድርሰት: ሳሙኤል ቤኬት
ትርጉም: ሀይከል ሙባረክ
አዘጋጅ: ዳግም ሲሳይ
ቀን: ሐሙስ
ሰዓት:11:30
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር
📍 የፍቅር ካቴና
ድርሰትና ዝግጅት: አለልኝ መኳንት ፅጌ
ቀን: አርብ
ሰዓት: 12:00
ቦታ: ዓለም ሲኒማ
📍 "እሳት ወይ አበባ"
ድርሰት: ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን እንደጻፈው
ዳንስና ዳንስ ቅንብር: ሽፈራው ታሪኩ ቢረጋ
ቀን: አርብ
ሰዓት:11:30
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር
📍 ባሎች እና ሚስቶች
ድርሰት: ውዱ አለን
አዘጋጅ: ሳሙኤል ተስፋዬ
ቀን: ቅዳሜ
ሰዓት: 8:00
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር
📍 ባቡሩ
ድርሰት: አርኖልድ ሪድሊ
አዘጋጅ:ራሔል ተሾመ መሐመድ
ቀን: ቅዳሜ
ሰዓት:11:30
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር
📍 ሸምጋይ
ድርሰት:ታደለ አያሌው
አዘጋጅ: ሳሙኤል ተስፋዬ
ቀን: እሁድ
ሰዓት: 8:00
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር
📍 እምዩ ብረቷ
ድርሰት: ቤልቶልት ብሬሽት
አዘጋጅ: ማንያዘዋል እንዳሻው
ቀን: እሁድ
ሰዓት:11:30
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር
የእናንተው ኤቨንት አዲስ ድረገፅ መልካም የእረፍት ቀን ይሁንላችሁ ይላል !
ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
አንጋፋው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር እና የቦሌው ዓለም ሲኒማ ሐሙስ፤ አርብ፣ ቅዳሜ እና እሁድ እነዚህን ተውኔቶች ለታዳሚያን ያቀርባሉ።
📍 ጎዶ'ን ጥበቃ
ድርሰት: ሳሙኤል ቤኬት
ትርጉም: ሀይከል ሙባረክ
አዘጋጅ: ዳግም ሲሳይ
ቀን: ሐሙስ
ሰዓት:11:30
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር
📍 የፍቅር ካቴና
ድርሰትና ዝግጅት: አለልኝ መኳንት ፅጌ
ቀን: አርብ
ሰዓት: 12:00
ቦታ: ዓለም ሲኒማ
📍 "እሳት ወይ አበባ"
ድርሰት: ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን እንደጻፈው
ዳንስና ዳንስ ቅንብር: ሽፈራው ታሪኩ ቢረጋ
ቀን: አርብ
ሰዓት:11:30
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር
📍 ባሎች እና ሚስቶች
ድርሰት: ውዱ አለን
አዘጋጅ: ሳሙኤል ተስፋዬ
ቀን: ቅዳሜ
ሰዓት: 8:00
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር
📍 ባቡሩ
ድርሰት: አርኖልድ ሪድሊ
አዘጋጅ:ራሔል ተሾመ መሐመድ
ቀን: ቅዳሜ
ሰዓት:11:30
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር
📍 ሸምጋይ
ድርሰት:ታደለ አያሌው
አዘጋጅ: ሳሙኤል ተስፋዬ
ቀን: እሁድ
ሰዓት: 8:00
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር
📍 እምዩ ብረቷ
ድርሰት: ቤልቶልት ብሬሽት
አዘጋጅ: ማንያዘዋል እንዳሻው
ቀን: እሁድ
ሰዓት:11:30
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር
የእናንተው ኤቨንት አዲስ ድረገፅ መልካም የእረፍት ቀን ይሁንላችሁ ይላል !
ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌የሐና ግርማ አዲስ ሙዚቃ ነገ ይለቀቃል
የወጣቷ ድምጻዊት ሐና ግርማ "ምን መሰለህ" የተሰኘ ርዕስ የተሰጠው አዲስ ነጠላ ሙዚቃ ነገ አርብ ጥቅምት 8 2017 ዓ.ም በናሆም ሪከርድ በኩል ይለቀቃል። በዚህ ነጠላ ሙዚቃ ላይ በግጥምና ዜማ አቡዲ፣በቅንብርና ማስተሪንግ ታምሩ አማረ፣በሙዚቃ ቪዲዮ ዳይሬክቲንግ ዮሴፍ ባዬ ተሳትፈውበታል።

📌የኢትዮጵያ ቱሪዝም ሽልማት መርሐግብር
በኢትዮጵያ የባህልና ቱሪዝም ጋዜጠኞች ማህበር የተዘጋጀውና ለመጀመሪያ ጊዜ የሚካሄደው "የኢትዮጵያ ቱሪዝም ሽልማት" የሽልማት ሥነሥርዓት ዛሬ ጥቅምት 7 ቀን 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ሙዚየም ውስጥ ከቀኑ 10:00 ጀምሮ ይካሄዳል።
ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
በኢትዮጵያ የባህልና ቱሪዝም ጋዜጠኞች ማህበር የተዘጋጀውና ለመጀመሪያ ጊዜ የሚካሄደው "የኢትዮጵያ ቱሪዝም ሽልማት" የሽልማት ሥነሥርዓት ዛሬ ጥቅምት 7 ቀን 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ሙዚየም ውስጥ ከቀኑ 10:00 ጀምሮ ይካሄዳል።
ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌ተወዳጁ ድምፃዊ ዳዊት ፅጌ የሙዚቃ አቀናባሪው አበጋዝ ክብረወርቅ ሺዎታ እና ፕሮሞተር ሰለሞን ገብረማሪያም (ኪንግ ሶሎን )ጨምሮ በሲያትል ከተማ እውቅና ተሰጣቸው ።
ደዊት ፅጌ በ2024 በአሜሪካን ከተሞች ያቀረባቸው የተሳኩ ዝግጅቶች በማስመልከት እና ልዩ ተስጦ ያለው ድምፃዊ በመሆኑ ለሙዚቃው ላበረከተው አስተዋፆ ጭምር እውቅና አግኝቷል።
የሙዚቃ አቅናባሪው አበጋዝ ሺዎታ በኢትዮጵያ የምርጥ ሙዚቃ አቀናባሪ በመሆኑ እና ለኢትዮጵያ ሙዚቃ ላበረከተው ከፍተኛ አስተዋጽዖ እንዲሁ እውቅና በክብር ተሰጥቷቸዋል።
በተያያዘ ዜና - የኪንግ ሶሎ ፕሮሞሽን ባለቤት ፕሮሞተር ሰለሞን ላለፉት 10 ዓመት በሲያትል ውስጥ በርካታ ዝግጅቶችን በማዘጋጀት እውቅና ተሰጥቶታል።
ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ የሃያላኑዋ አሜሪካ ግዙፍ ኢኮኖሚ ከሚንቅሳቅስባቸው ዋንኛዋ ከተማ የሆነው ሲያትል ዋሽግተን ምክትል ከቲባዋ መሆናቸው ለኢትዮጵያን ትልቅ ኩራት መሆኑ ተገልጿል።
ድምፃዊው እና ሙሉ ባንዱ ዝግጅታቸውን አጠናቀው ወደ አዲስ አበባ ተመልሰዋል።
በቅርቡም በአዲስ አበባ ትልቅ ኮንሰርት እንደሚያዘጋጁም ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ሰምቷል።

📌"የሚልየነሮች መንገድ" የተሰኘ ፕሮጀክት ይፋ ተደረገ
በበላይ አትክልትና አስቤዛ ማዕከል የተዘጋጀውና በርካቶችን ተጠቃሚ ሊያደርግ እንደሚችል ተስፋ የተጣለበት "የሚልየነሮች መንገድ' የተሰኘ ፕሮጀክት በይፋ ተጀመረ።
"የሚልየነሮች መንገድ" የፕሮጀክት ሀሳብ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎችን በሁለት ዓመት ውስጥ ብቻ በተግባርና በተጨባጭ ወደ ሚሊየነርነት የሚቀይር በልምድ የተረጋገጠ ቢዝነስ ፕላን ለወጣቶች፣ለጀማሪ ነጋዴዎች፣ በቢዝነስ ላይ ላሉ ሁሉ የሚጠቅም የስራ ባህላችንን ይበልጥ የሚያሳድግ ፕሮጀክት እንደሆነ ተነግሯል።
በላይ አትክልትና አስቤዛ ማዕከል በሀገሪቱ እየታየ ያለውን የሥራ አጥ ቁጥርን ከመቀነስ ባሻገር ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ስለሚያደርገዉ "የሚሊየነሮች መንገድ" ፕሮጀክት ባስተዋወቁበት መድረክ "ማዕከሉ ከዚህ ቀደም በሀገር ውስጥ እና በውጪ ሀገራት በርካታ አዋጭ የቢዝነስ ዘርፎች ላይ ጥናቱን ሲያካሄድ ቆይቶ በልምድ የተረጋገጠ የአስር ዓመት አዋጭ የቢዝነስ ዕቅድ በማዘጋጀት የዛሬ ሰባት ዓመት በ500 ብር መነሻ ካፒታል አምስት ፕሮጀክቶችን ወደ ትግበራ በማስገባት ብቻ የጀመሩትን ቢዝነስ አሁን ባለበት ደረጃ በአዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ አምስት መሸጫ ቦታዎች ትላልቅ የአትክልትና አስቤዛ ማዕከል ቅርንጫፎችን በመክፈት ለበርካታ ወጣቶች የሥራ ዕድል ከመፍጠሩም ባሻገር በቋሚነት ከ75ሺ በላይ ደንበኞችን በማፍራት አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል "ብለዋል።
ማዕከሉ በቅርቡም "የሚሊየነሮች መንገድ" የተሰኘ የሬድዮ እና የቴሌቪዥን ፕሮግራሞችን ከጥቅምት 30 2017 ዓ.ም ጀምሮ በኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 እና በሀገሬ ቴሌቪዥን ላይ እንደሚጀምር አስታውቋል።

📌የኢትዮጵያ ቱሪዝም ሽልማት ተካሄደ
በኢትዮጵያ የባህልና ቱሪዝም ጋዜጠኞች ማህበር የተዘጋጀው የመጀመሪያው "የኢትዮጵያ ቱሪዝም ሽልማት" የሽልማት ሥነሥርዓት ዛሬ ጥቅምት 7 ቀን 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ሙዚየም ውስጥ ተካሄዷል።
በዚህ የሽልማት ሥነሥርዓት ላይ በሰባት ዘርፎች አስር ለሚሆኑ ለኢትዮጵያ ቱሪዝም ዘርፍ የራሳቸውን አስተዋጽኦ ያበረከቱ ተቋማትና ግለሰቦች እውቅና ተሰጥቷቸዋል።
በዚህ መሰረት ተሸላሚ ተቋማትና ግለሰቦች ዝርዝር ታውቋል።
1.የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን (በሚዲያ ዘርፍ)
2. አንድነት ፓርክ (በመዳረሻ ልማት ዘርፍ)
3 ቱሪዝም ማስልጠኛ ኢኒስቲትዩት (በቱሪዝም ተቋማት ዘርፍ)
4.ሀይሌ ሆቴሎች (በሆቴልና ሆስፒታሊቲ ዘርፍ )
5.ሔኖክ ያሬድ (በጋዜጠኝነት ዘርፍ)
6.ጋዜጠኛ ፀሐይ ተፋረደኝ (በጋዜጠኝነት ዘርፍ)
7.አንቶኒዮ ፍዮርንቴ (በፎቶግራፍ ዘርፍ )
8.ህሊና ታፈሰ (በፎቶግራፍ ዘርፍ )
9.ኪሮስ ኃ/ስላሴ (በ"ኢትዮጵያን እንቃኝ" ልዩ ተመስጋኝ )
10.ቴዎድሮስ ደርበው (በቱሪዝም ባለሞያ ዘርፍ)