Event Addis Media – Telegram
Event Addis Media
9.63K subscribers
6.12K photos
14 videos
4 files
4.74K links
Connect with Addis artistic community!

Website: https://eventaddis.com

Contact: @Tmanaye
Download Telegram
የአፍሪካ ቀንድ የሠላም Advocacy ስልታዊ እቅድ የመክፈቻ ሥነሥርአት እና ሲምፖዚየም ሊካሄድ ነው።

የአፍሪካ ቀንድ የሠላም Advocacy ስልታዊ እቅድ የመክፈቻ ሥነሥርአት እና ሲምፖዚየም ለሁለት ቀናት በሒልተን ሊካሄድ ነው ተብሏል።

"የምንፈልጋት አፍሪካ" (the Africa we want) የሁነቱ ርዕሰ ጉዳይ ነው።

ዝግጅቱን American Friends Community Services እና Bread for fhe World በጋራ አዘጋጅተውታል።

በዚህ ትልቅ ዝግጅት ላይ አገር አቀፍ እና ዓለም አቀፍ ሲቪክ ማህበረሰብ አካላት ፣የሀይማኖት መሪዎች፣ ዲፕሎማቶች ፣የአፍሪካ ህብረት ፣የአውሮፓውያን ህብረት ፣የኢጋድ እና የመንግሥት አካላት ይሣተፋሉ።

ሁነቱ ጥቅምት 6 እና 7 ቀን 2017 ዓ.ም በሂልተን ሆቴል ለሁለት ቀናት ይካሄዳል ተብሏል።

የዝግጅቱ መሪ ሐሳብ እስከ 2033 የሚዘልቅ ሲሆን  ይህም የስድስት ዓመት ፕሮግራም ሠላምን በተመለከተ የተለየ ሀሣብን ይዞ መጥቷል ተብሎ ይታሠባል።

ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌መቅረዝ ሥነኪን የኪነጥበብ ዝግጅት ሐሙስ ይካሄዳል

አንጋፋው ከያኒ ተስፋዬ አበበ (ፋዘር) የክብር እንግዳ የሆነበት "መቅረዝ ሥነኪን" የኪነጥበብ ዝግጅት ሀሙስ ይካሄዳል።

አንጋፋ እና ወጣት የኪነጥበብ ባለሞያዎችን እያጣመር የዘለቀው መቅረዝ ሥነኪን ወርሀዊ የኪነጥበብ  ዝግጅት ሐሙስ ጥቅምት 7 ቀን 2017 ዓ.ም ከምሽቱ 11:00 ጀምሮ በብሔራዊ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት (ወመዘክር )አዳራሽ ውስጥ ይካሄዳል።

በዚህ የዓመቱ የመክፈቻ ዝግጅት ላይ አንጋፋው ከያኒ ተስፋዬ አበበ (ፋዘር) የክብር እንግዳ በመሆን የሚገኙ ሲሆን በተጨማሪም ወጣት የኪነጥበብ ባለሞያዎች የግጥም ፣የሙዚቃ እና  የዳንስ ስራዎቻቸውን ያቀርባሉ።

የዚህ ዝግጅት መግቢያ በነፃ ነው።

ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
በሮፍናን ኮንሰርት እነማን ስራቸውን አቀረቡ ?

ሮፍናን ስኬታማ ኮንሰርት በሀዋሳ ባለፈው ቅዳሜ አድርጎል ።
በሀዋሳ ትልቁ ስታዲየም በተደረገው ኮንሰርት ከአዋሳኝ ከተሞች በተጨማሪ ከአዲስ አበባ ጭምር ወደ ስፍራው ያቀኑ የሙዚቃ አፍቃሪዎች እንደነበሩ ለሁሉ አዲስ ከሀዋሳ የደረሰው መረጃ ያመላክታል ።

ኃይሌ ሩትሥ ፣ቶክቻው ፣ Shumulo shunde በተጋባዥነት ስራቸውን ማቅረባቸው ታውቋል ።

ኮንሰርቱ እንዳይካሄድ አላስፈላጊ የሆነ ተቀፅላ ለሮፍናን በመስጠት በማህበራዊ ሚድያ ቅስስቀሳ ተደርጎበት የነበረ ቢሆንም አላስፈላጊ ስም ማጥፋቱ አግባብ እንዳልሆነ በርካቶች በማስረዳታቸው በሀዋሳ ደረጃውን የጠበቀ ኮንሰርት ለማድረግ መቻሉን ከስፍራው የደረሰን መረጃ ያመለክታል ።

ሮፍናን ሀይሌ ሩትስ መድረኩን በማድመቅ ለነበረው አበርክቶ በይፋ አመስግኗል ።
ጥቅምት 9,2017 ዓም የኔ ትውልድ ኮንሰርት በወላይታ ሶዶ ይካሄዳል ።

©️መረጃው የሁሉአዲስ ነው።

ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌የድምጻዊት አምሳል ምትኬ የባህል ምሽት ቤት የእሳት አደጋ ደረሰበት።

የድምፃዊት አምሳል ምትኬ የባህል ምሽት ቤት እና የምግብ አዳራሽ ጥቅምት 5 2017 ዓ.ም ከምሽቱ 12:30 አካባቢ በተነሳ የእሳት ቃጠሎ አደጋ እንደደረሰበት ዘሐበሻ ዘግቧል።

የባሕር ዳር ነዋሪ እሳቱን ለመቆጣጠር ያደረገው ርብርብ ጥሩ ነበር የተባለ ሲሆን ሆኖም የእሳቱ ሁኔታ ከባድ ስለነበር ንብረት ላይ ጉዳት ማድረሱን እና በሰው ላይ እስካሁን ጉዳት አለማድረሱን ተሰምቷል።

©️መረጃው የዘሐበሻ ነው።

ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌"የወንዜ ሳቢሳ" መጽሐፍ ነገ ይመረቃል

ከአንቷን ቼኮቭ ስራዎች አራት ትርጉም ስብስብ ተውኔቶችን የያዘው "የወንዜ ሳቢሳ"የተሰኘው የትያትር መጽሐፍ በጠበቃ እና የትያትር ባለሙያ በአቶ ሳምሶን ብሬ ተተርጉሞ በቅርቡ ለአንባቢያ ደርሷል፡፡

ይህም መጽሐፍ ነገ ሐሙስ ጥቅምት 7 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 11:00 ሰዓት ጀምሮ በመቅረዝ ሥነኪን ዝግጅት ላይ በብሔራዊ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አግልግሎት (ወመዘክር) አዳራሽ ውስጥ ይመረቃል።

በዝግጅቱም በኢትዮጵያ የሩስያ አምባሳደር እና ጥሪ የተደረገላቸው ታላላቅ እንግዶች ይገኛሉ።

በመጽሐፍ ምረቃው ዝግጅት ላይ የተለያዩ ኪነ-ጥበባዊ ስራዎች የሚቀርቡ ሲሆን በመጽሐፉ ውስጥ ከተተረጎሙ የአንቷን ቼኮቭ ቴአትሮች ውስጥ ባለ አንድ ገቢር የአንድ ሰው አጭር ተውኔት ይቀርባል ተብሏል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌የጋዜጠኛ መኮንን ወ/አረጋይ "እነሆ ማሟሻ" ቅጽ ሁለት መጽሐፍ አርብ ለንባብ ይበቃል

ከዚህ ቀደም በሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ ላይ በሚያቀርባቸው የስንክሳር፣  የማሟሻ፣ የሃኪሞ መልዕክት፣ የአርብ ምሽት ቆየት ያሉ ሙዚቃዎች እና አሁን ላይ በኢንቢሲ ቴሌቪዥን በልዩ ልዩ ዝግጅቶች የምናውቀው ጋዜጠኛ መኮንን ወ/አረጋይ በርካታ ጉዳዮች የተካተቱበትን"እነሆ ማሟሻ" ቅጽ ሁለት መጽሐፍ አርብ ጥቅምት 8 ቀን 2017 ዓ.ም ለንባብ ይበቃል።

"እነሆ ማሟሻ" መጽሐፍ ከቅጽ አንድ የቀጠለ ሲሆን በቅጽ ሁለት መጽሐፍ "ስንክሳር" የሬድዮ ዝግጅት ላይ ከቀረቡ ጥናታዊ ጽሑፎች ውስጥ ለቅምሻ እንደተካተተበት ተነግሯል።

ጋዜጠኛ መኮንን ወ/አረጋይ በመጽሐፉ የቅምሻ ክፍል ላይ የሚከተለውን ብሏል"ቅጽ አንድን ሳዘጋጅ የእኔን የሙያ ትሩፋት ለመስጠት ሳይሆን በእኔ ዘንድ ያለውን ለእናንተ ማካፈል ደስታን ስለሚሰጠኝም ጭምር ነው፡፡ በቅጽ ሁለት ቀሪዎች ስራዎችን ለእናንተ ለማድረስ ደፋ ቀና ስል አንድ ሀሳብ ውስጤ ተጫረ፡፡ ስንክሳር።ስንክሳርን ብዙ የሚዲያ ወዳጆቼ ሰምተው የተደመሙበት የተማሩበትና የተዝናኑበት እንደሆነ ሲነግሩኝ ከርመዋል፡፡ ስንክሳር በተለያዩ ጉዳዮች ማለትም በኢትዮጵያ ማህበራዊ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ እውነቶች ላይ ያተኮረ የጥናትና ምርምር ሥራ ነው፡፡እነሆ ማሟሻ ስታድግ በወርድና ስፋቷ ስንከሳርን ታክላለች፡፡ እና ለወዳጆቼ ለምን ስንክሳርንስ አላጋራም? ነበር ውስጤ የተጫረው ሀሳብ። ከብዙ ስራዎቼ ለሚቀጥሉት ህትመቶች በር መክፈቻ ብትሆን እነሆ የስንከሳርን ቅምሻ ላቀርብ ወደድኩ"።

መጽሐፉ በ200 ገፆች የተነበበ ሲሆን ከአርብ ጀምሮ ለአንባቢያን እንደሚደርስ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ሰምቷል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌በእረፍት ቀንዎ ቴአትር ይመለከቱ !

አንጋፋው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር  እና የቦሌው ዓለም ሲኒማ ሐሙስ፤ አርብ፣ ቅዳሜ እና እሁድ እነዚህን ተውኔቶች ለታዳሚያን ያቀርባሉ።

📍 ጎዶ'ን ጥበቃ

ድርሰት: ሳሙኤል ቤኬት
ትርጉም: ሀይከል ሙባረክ
አዘጋጅ: ዳግም ሲሳይ
ቀን: ሐሙስ
ሰዓት:11:30
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር


📍 የፍቅር ካቴና

ድርሰትና ዝግጅት: አለልኝ መኳንት ፅጌ
ቀን: አርብ
ሰዓት: 12:00
ቦታ: ዓለም ሲኒማ

📍 "እሳት ወይ አበባ"

ድርሰት: ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን እንደጻፈው
ዳንስና ዳንስ ቅንብር: ሽፈራው ታሪኩ ቢረጋ
ቀን: አርብ
ሰዓት:11:30
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር

📍 ባሎች እና ሚስቶች

ድርሰት: ውዱ አለን
አዘጋጅ: ሳሙኤል ተስፋዬ
ቀን: ቅዳሜ
ሰዓት: 8:00
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር

📍 ባቡሩ

ድርሰት: አርኖልድ ሪድሊ
አዘጋጅ:ራሔል ተሾመ መሐመድ
ቀን: ቅዳሜ
ሰዓት:11:30
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር

📍 ሸምጋይ

ድርሰት:ታደለ አያሌው
አዘጋጅ: ሳሙኤል ተስፋዬ
ቀን: እሁድ
ሰዓት: 8:00
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር

📍 እምዩ ብረቷ

ድርሰት: ቤልቶልት ብሬሽት
አዘጋጅ: ማንያዘዋል እንዳሻው
ቀን: እሁድ
ሰዓት:11:30
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር

የእናንተው ኤቨንት አዲስ ድረገፅ መልካም የእረፍት ቀን ይሁንላችሁ ይላል !

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌የሐና ግርማ አዲስ ሙዚቃ ነገ ይለቀቃል

የወጣቷ ድምጻዊት ሐና ግርማ "ምን መሰለህ" የተሰኘ ርዕስ የተሰጠው አዲስ ነጠላ ሙዚቃ ነገ አርብ ጥቅምት 8 2017 ዓ.ም በናሆም ሪከርድ በኩል ይለቀቃል። በዚህ ነጠላ ሙዚቃ ላይ በግጥምና ዜማ አቡዲ፣በቅንብርና ማስተሪንግ ታምሩ አማረ፣በሙዚቃ ቪዲዮ ዳይሬክቲንግ ዮሴፍ ባዬ ተሳትፈውበታል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌የኢትዮጵያ ቱሪዝም ሽልማት መርሐግብር

በኢትዮጵያ የባህልና ቱሪዝም ጋዜጠኞች ማህበር የተዘጋጀውና ለመጀመሪያ ጊዜ የሚካሄደው "የኢትዮጵያ ቱሪዝም ሽልማት" የሽልማት ሥነሥርዓት ዛሬ ጥቅምት 7 ቀን 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ሙዚየም ውስጥ ከቀኑ 10:00 ጀምሮ ይካሄዳል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌ተወዳጁ ድምፃዊ ዳዊት ፅጌ የሙዚቃ አቀናባሪው አበጋዝ ክብረወርቅ ሺዎታ እና ፕሮሞተር ሰለሞን ገብረማሪያም (ኪንግ ሶሎን )ጨምሮ በሲያትል ከተማ  እውቅና ተሰጣቸው ።

ደዊት ፅጌ በ2024 በአሜሪካን ከተሞች ያቀረባቸው የተሳኩ ዝግጅቶች በማስመልከት እና ልዩ ተስጦ ያለው ድምፃዊ በመሆኑ ለሙዚቃው ላበረከተው አስተዋፆ ጭምር እውቅና አግኝቷል።

የሙዚቃ አቅናባሪው አበጋዝ ሺዎታ በኢትዮጵያ የምርጥ ሙዚቃ አቀናባሪ በመሆኑ እና ለኢትዮጵያ ሙዚቃ ላበረከተው ከፍተኛ አስተዋጽዖ እንዲሁ እውቅና በክብር ተሰጥቷቸዋል።

በተያያዘ ዜና - የኪንግ ሶሎ ፕሮሞሽን ባለቤት ፕሮሞተር ሰለሞን ላለፉት 10 ዓመት በሲያትል ውስጥ በርካታ ዝግጅቶችን በማዘጋጀት እውቅና ተሰጥቶታል።

ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ የሃያላኑዋ አሜሪካ ግዙፍ ኢኮኖሚ ከሚንቅሳቅስባቸው ዋንኛዋ ከተማ የሆነው ሲያትል ዋሽግተን ምክትል ከቲባዋ መሆናቸው ለኢትዮጵያን ትልቅ ኩራት መሆኑ ተገልጿል።

ድምፃዊው እና ሙሉ ባንዱ ዝግጅታቸውን አጠናቀው ወደ አዲስ አበባ ተመልሰዋል።

በቅርቡም በአዲስ አበባ ትልቅ ኮንሰርት እንደሚያዘጋጁም ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ሰምቷል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌"የሚልየነሮች መንገድ" የተሰኘ ፕሮጀክት ይፋ ተደረገ

በበላይ አትክልትና አስቤዛ ማዕከል የተዘጋጀውና በርካቶችን ተጠቃሚ ሊያደርግ እንደሚችል ተስፋ የተጣለበት "የሚልየነሮች መንገድ' የተሰኘ ፕሮጀክት በይፋ ተጀመረ።

"የሚልየነሮች መንገድ" የፕሮጀክት ሀሳብ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎችን በሁለት ዓመት ውስጥ ብቻ በተግባርና በተጨባጭ ወደ ሚሊየነርነት የሚቀይር በልምድ የተረጋገጠ ቢዝነስ ፕላን ለወጣቶች፣ለጀማሪ ነጋዴዎች፣ በቢዝነስ ላይ ላሉ ሁሉ የሚጠቅም የስራ ባህላችንን ይበልጥ የሚያሳድግ ፕሮጀክት እንደሆነ ተነግሯል።

በላይ አትክልትና አስቤዛ ማዕከል በሀገሪቱ እየታየ ያለውን የሥራ አጥ ቁጥርን ከመቀነስ ባሻገር ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ስለሚያደርገዉ "የሚሊየነሮች መንገድ" ፕሮጀክት ባስተዋወቁበት መድረክ "ማዕከሉ ከዚህ ቀደም በሀገር ውስጥ እና በውጪ ሀገራት በርካታ አዋጭ የቢዝነስ ዘርፎች ላይ ጥናቱን ሲያካሄድ ቆይቶ  በልምድ የተረጋገጠ የአስር ዓመት አዋጭ የቢዝነስ ዕቅድ በማዘጋጀት የዛሬ ሰባት ዓመት በ500 ብር መነሻ ካፒታል አምስት ፕሮጀክቶችን ወደ ትግበራ በማስገባት ብቻ የጀመሩትን ቢዝነስ አሁን ባለበት ደረጃ በአዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ አምስት መሸጫ ቦታዎች ትላልቅ የአትክልትና አስቤዛ ማዕከል ቅርንጫፎችን በመክፈት ለበርካታ ወጣቶች የሥራ ዕድል ከመፍጠሩም ባሻገር በቋሚነት ከ75ሺ በላይ ደንበኞችን በማፍራት አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል "ብለዋል።

ማዕከሉ በቅርቡም "የሚሊየነሮች መንገድ" የተሰኘ የሬድዮ እና የቴሌቪዥን ፕሮግራሞችን ከጥቅምት 30 2017 ዓ.ም ጀምሮ በኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 እና በሀገሬ ቴሌቪዥን ላይ እንደሚጀምር አስታውቋል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌የኢትዮጵያ ቱሪዝም ሽልማት ተካሄደ

በኢትዮጵያ የባህልና ቱሪዝም ጋዜጠኞች ማህበር የተዘጋጀው የመጀመሪያው "የኢትዮጵያ ቱሪዝም ሽልማት" የሽልማት ሥነሥርዓት ዛሬ ጥቅምት 7 ቀን 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ሙዚየም ውስጥ ተካሄዷል።

በዚህ የሽልማት ሥነሥርዓት ላይ በሰባት ዘርፎች አስር ለሚሆኑ ለኢትዮጵያ ቱሪዝም ዘርፍ የራሳቸውን አስተዋጽኦ ያበረከቱ ተቋማትና ግለሰቦች እውቅና ተሰጥቷቸዋል።

በዚህ መሰረት ተሸላሚ ተቋማትና ግለሰቦች ዝርዝር ታውቋል።

1.የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን (በሚዲያ ዘርፍ)

2. አንድነት ፓርክ (በመዳረሻ ልማት ዘርፍ)

3 ቱሪዝም ማስልጠኛ ኢኒስቲትዩት (በቱሪዝም ተቋማት ዘርፍ)

4.ሀይሌ ሆቴሎች (በሆቴልና ሆስፒታሊቲ ዘርፍ )

5.ሔኖክ ያሬድ (በጋዜጠኝነት ዘርፍ)

6.ጋዜጠኛ ፀሐይ ተፋረደኝ (በጋዜጠኝነት ዘርፍ)

7.አንቶኒዮ ፍዮርንቴ (በፎቶግራፍ ዘርፍ )

8.ህሊና ታፈሰ (በፎቶግራፍ ዘርፍ )

9.ኪሮስ ኃ/ስላሴ (በ"ኢትዮጵያን እንቃኝ" ልዩ ተመስጋኝ )

10.ቴዎድሮስ ደርበው (በቱሪዝም ባለሞያ ዘርፍ)

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌አሻም ቲቪ የስያሜ ለወጥ አያደርግም ተባለ

የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፍተሐብሔር ምድብ ችሎት በመዝገብ ቁጥር 228079 በቀን 20/08/2014 ዓ.ም እና የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመዝገብ ቁጥር 229220 በቀን 21/10/2016 ዓ.ም አሻም የሚለውን ስያሜ ፍርድ ቤት የሰጠውን ትዕዛዝ ለማስፈጸም የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ለአሻም የማሳሰቢያ ደብዳቤ መፃፉ ይታወሳል፡፡

በዚህም ፍርዱ ቤቱ የሰጠውን ውሳኔ መሠረት በማድረግ አሻም የሚለውን ስያሜ መጠቀም እንድታቆም እና እስከ ጥቅምት 10 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ አዲሱን ስያሜ አሻም እንድታሳውቅ ማሳሰቢያ ተሰጥቷት ነበር።

የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ሦስተኛ ፍ/ብሔር ችሎት ሐምሌ 29 ቀን 2016 ዓ.ም ባስቻለው ችሎት የፍርድ ባለዕዳ ‹‹ አሻም ›› በሚል ስያሜ በመጠቀም የሚያስተላልፈውን የቴሌቪዥን ፕሮግራም እንዲያስቆሙ ለኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን እና ለፌደራል ፖሊስ የአፈጻጸም ትዕዛዝ ሰጥቶ ነበር፡፡

ይሁንና የፍርድ ባለመብት (ኢካሽ የማማከር፣ ስልጠናና ፕሮሞሽን ኃ/የተ/የግ/ማ) እና የፍርድ ባለዕዳ (አሻም ሚዲያ ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማ ) ጉዳዩን በእርቅ ለመፍታት ለችሎቱ ጥያቄ አቅርበዋል፡፡ ፍርድ ቤቱም የእርቅ ሥምምነቱ ህግንና ሞራልን የማይቃወም መሆኑን በመረዳት እርቁን ተቅበሎታል፡፡

ፍርድ ቤቱ አክሎ እንደተናገረው ከዚህ በፊት ፍርድ ቤቱ ሐምሌ 29 ቀን 2016 ዓ.ም ባስቻለው ችሎት ሰጥቶ የነበረው የአፈጻጸም ትዕዛዝ በዚህ ተለዋጭ ትዕዛዝ ቀሪ በማድረግ እንዲሁም ይህንን የአፈጻጸም ትዕዛዝ ተከትሎ በኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊሲም ሆነ በኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን የተሰሩ ሥራዎች ያሉ ከሆነ ቀሪ እንዲደረግ አዝዟል፡፡

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌የጉማ አዋርድ የሽልማት ሥነሥርዓት ዛሬ ይካሄዳል

የኢትዮጵያ ፊልሞችንና ፊልም ስሪዎችን ለዘጠኝ ዓመታት እየሸለመ የቆየው ጉማ አዋርድ ዘንድሮ ለአስረኛ ጊዜ የሽልማት ሥነሥርዓቱን ዛሬ ጥቅምት 8 ቀን 2017 ዓ.ም በሸራተን አዲስ ሆቴል ውስጥ እንደሚካሄድ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ሰምቷል።

የዘንድሮውን ሽልማት አስመልክቶ የሽልማቱ አዘጋጆች" በ2015 ዓ.ም በሀገራቸን ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ለእይታ የቀረቡ ፊልሞች ውስጥ 32 ፊልሞች ለውድድር ቀርበዋል። በተጨማሪም ከጉማ ጅማሬ አንስቶ በተለያዩ ሙያተኞች ሲጠየቅ የነበረው የተከታታይ ፊልም ምድብ እና የዘጋቢ ፊልሞችን በዚህ ዓመት እንዲካተቱ ተደርጓል"ያሉ ሲሆን

በተጨማሪም"በዚህ ዓመት ዘርፎቹ ወደ 29 ከፍ ያሉ ሲሆን የጉማ የህይወት ዘመን ተሸላሚ ዘርፍ ፤የጉማ የሄርሜላ የሴቶች ሽልማት ተሸላሚ፤ የጉማ የበጎ ስራ ተሸላሚ ብቻ ያለ ውድድር በኮሚቴው ጥናትና ምርጫ ተወሰኗል"ብለዋል።

ከቀናት በፊትም የጉማ አዋርድ ዕጩ ፊልሞች ይፋ ተደረገዋል። ዶቃ ከ16 ዘርፍ በ14ት ዘርፍ ታጭቶ ከፊት ይገኛል፣ ወዳጅ እና ዝምታዬ  ፊልሞች በ10 ዘርፍ ይከተላሉ፣ ልባም ፊልም በ9 ዘርፍ በመታጨት 3ተኛ ነው፣ ገምዛ እና የአገር ምስጢር አለኝ በ8 ዘርፍ በመታጨት አራተኛ ላይ እንደሚገኙ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ተመልክቷል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌"ሶስት አይጦች" በልዩ ዝግጅት ይቀርባል!

በኤልያስ ተስፋዬ ተደርሶ በካሌብ ዋለልኝ የተዘጋጀውና ዘወትር ማክሰኞ በ11:00 የሚታየው "ሶስቱ አይጦች" ተውኔት በልዩ ፕሮግራም ዛሬ ጥቅምት 8 አርብ በ11:00 በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር እንደሚቀረብ አዘጋጆቹ ለኤቨንት አዲስ ድረገፅ ገለጸዋል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌"ይፈለጋሉ" ፊልም ዛሬ ለእይታ ይበቃል

በፍፁም ወንድወሰን የተዘጋጀው "ይፈለጋሉ" ፊልም ዛሬ ጥቅምት 8 2017 ዓ.ም በተለያዩ ሲኒማ ቤቶች ለእይታ ይበቃል።

"ይፈለጋሉ" ፊልም ላይ ሰለሞን ሙሄ፣ ቃልኪዳን ታምሩ፣ ዋሲሁን በላይ እና ሌሎችም በትወና ተሳትፈውበታል።

የደራሲ እና ዳይሬክተር ፍፁም ወንድወሰን "ይፈለጋሉ" ፊልም ዛሬ አርብ በ8፣ በ9 እና በ10 በሁሉም ሲኒማ ቤቶች በእኩል ሰዓት ይመረቃል ተብሏል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌የቀደሞዋ ጋዜጠኛ ሰላማዊት ካሣ የቱሪዝም ሚኒስቴር ሚኒስትር በመሆን ተሾመች ።

በፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እና በሌሎችም የብዙሃን መገናኛዎች ላይ በጋዜጠኝነት የሰራችው የቀድሞዋ ጋዜጠኛ ሰላማዊት ካሣ ዛሬ ጥቅምት 8 2017 ዓ.ም የቱሪዝም ሚኒስቴር ሚኒስትር በመሆን እንደተሾመች ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ያገኘው መረጃ ያመለከታል።

የቀድሞዋ ጋዜጠኛ ሰላማዊት ካሣ ከዚህ ቀደም በኢፌዴሪ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስቴር ዴአታ በመሆን  እያገለገለች እንደነበር ይታወሳል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1