Event Addis Media – Telegram
Event Addis Media
9.63K subscribers
6.12K photos
14 videos
4 files
4.74K links
Connect with Addis artistic community!

Website: https://eventaddis.com

Contact: @Tmanaye
Download Telegram
📌የጉማ አዋርድ የሽልማት ሥነሥርዓት ዛሬ ይካሄዳል

የኢትዮጵያ ፊልሞችንና ፊልም ስሪዎችን ለዘጠኝ ዓመታት እየሸለመ የቆየው ጉማ አዋርድ ዘንድሮ ለአስረኛ ጊዜ የሽልማት ሥነሥርዓቱን ዛሬ ጥቅምት 8 ቀን 2017 ዓ.ም በሸራተን አዲስ ሆቴል ውስጥ እንደሚካሄድ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ሰምቷል።

የዘንድሮውን ሽልማት አስመልክቶ የሽልማቱ አዘጋጆች" በ2015 ዓ.ም በሀገራቸን ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ለእይታ የቀረቡ ፊልሞች ውስጥ 32 ፊልሞች ለውድድር ቀርበዋል። በተጨማሪም ከጉማ ጅማሬ አንስቶ በተለያዩ ሙያተኞች ሲጠየቅ የነበረው የተከታታይ ፊልም ምድብ እና የዘጋቢ ፊልሞችን በዚህ ዓመት እንዲካተቱ ተደርጓል"ያሉ ሲሆን

በተጨማሪም"በዚህ ዓመት ዘርፎቹ ወደ 29 ከፍ ያሉ ሲሆን የጉማ የህይወት ዘመን ተሸላሚ ዘርፍ ፤የጉማ የሄርሜላ የሴቶች ሽልማት ተሸላሚ፤ የጉማ የበጎ ስራ ተሸላሚ ብቻ ያለ ውድድር በኮሚቴው ጥናትና ምርጫ ተወሰኗል"ብለዋል።

ከቀናት በፊትም የጉማ አዋርድ ዕጩ ፊልሞች ይፋ ተደረገዋል። ዶቃ ከ16 ዘርፍ በ14ት ዘርፍ ታጭቶ ከፊት ይገኛል፣ ወዳጅ እና ዝምታዬ  ፊልሞች በ10 ዘርፍ ይከተላሉ፣ ልባም ፊልም በ9 ዘርፍ በመታጨት 3ተኛ ነው፣ ገምዛ እና የአገር ምስጢር አለኝ በ8 ዘርፍ በመታጨት አራተኛ ላይ እንደሚገኙ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ተመልክቷል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌"ሶስት አይጦች" በልዩ ዝግጅት ይቀርባል!

በኤልያስ ተስፋዬ ተደርሶ በካሌብ ዋለልኝ የተዘጋጀውና ዘወትር ማክሰኞ በ11:00 የሚታየው "ሶስቱ አይጦች" ተውኔት በልዩ ፕሮግራም ዛሬ ጥቅምት 8 አርብ በ11:00 በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር እንደሚቀረብ አዘጋጆቹ ለኤቨንት አዲስ ድረገፅ ገለጸዋል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌"ይፈለጋሉ" ፊልም ዛሬ ለእይታ ይበቃል

በፍፁም ወንድወሰን የተዘጋጀው "ይፈለጋሉ" ፊልም ዛሬ ጥቅምት 8 2017 ዓ.ም በተለያዩ ሲኒማ ቤቶች ለእይታ ይበቃል።

"ይፈለጋሉ" ፊልም ላይ ሰለሞን ሙሄ፣ ቃልኪዳን ታምሩ፣ ዋሲሁን በላይ እና ሌሎችም በትወና ተሳትፈውበታል።

የደራሲ እና ዳይሬክተር ፍፁም ወንድወሰን "ይፈለጋሉ" ፊልም ዛሬ አርብ በ8፣ በ9 እና በ10 በሁሉም ሲኒማ ቤቶች በእኩል ሰዓት ይመረቃል ተብሏል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌የቀደሞዋ ጋዜጠኛ ሰላማዊት ካሣ የቱሪዝም ሚኒስቴር ሚኒስትር በመሆን ተሾመች ።

በፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እና በሌሎችም የብዙሃን መገናኛዎች ላይ በጋዜጠኝነት የሰራችው የቀድሞዋ ጋዜጠኛ ሰላማዊት ካሣ ዛሬ ጥቅምት 8 2017 ዓ.ም የቱሪዝም ሚኒስቴር ሚኒስትር በመሆን እንደተሾመች ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ያገኘው መረጃ ያመለከታል።

የቀድሞዋ ጋዜጠኛ ሰላማዊት ካሣ ከዚህ ቀደም በኢፌዴሪ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስቴር ዴአታ በመሆን  እያገለገለች እንደነበር ይታወሳል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
Event Addis Media
Photo
📌የ10ኛው ጉማ አዋርድ አሸናፊዎች ዝርዝር!

አስረኛው የጉማ አዋርድ የሽልማት ሥነሥርዓት ዛሬ ጥቅምት 8 2017 ዓ.ም በሸራተን አዲስ ሆቴል በደማቅ ሁኔታ እንደተካሄደ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ተመልክቷል።

የዘንድሮው የ #ጉማ አዋርድ ሽልማት አሸናፊዎች ዝርዝር የሚከተለውን ይመስላል።

📌 የህይወት ዘመን ተሸላሚ፦ ፍቅርተ ደሳለኝ

📌 አርአያ ሰብ ከያኒ፦ ይገረም ደጀኔ (አስቴር)

📌 የሐርሜላ ተሻላሚ፦ አዜብ ከበደ

📌ምርጥ አጭር ፊልም፦ "የራስ ጠላት"  እስክንድር አብርሃም

📌 ምርጥ የተማሪዎች አጭር ፊልም፦ "እንደ .." ናርዶስ ይልማ

📌ምርጥ ዶክመንተሪ ፊልም፦"እረኝነት"ብሩክ ሞላ

📌ምርጥ ተከታታይ ድራማ ተዋናይት፦ መዓዛ ታከለ (አፋፍ)

📌ምርጥ ተከታታይ ድራማ ተዋናይ፦ አበበ ባልቻ "በህግ አምላክ"

📌 ምርጥ ድራማ፦  "እንደ አንድ"

📌 ምርጥ ድምፅ፦ አበበ አሰፋ እና ቢንያም ሰለሞን  (ዶቃ)

📌ምርጥ ኤዲተር፦ ነብዩ ሰዓዲ እና ልዑል አባዲ (ዶቃ)

📌ምርጥ ስኮር፦ እዮኤል መንግስቱ (በዶቃ )

📌ምርጥ ማጀቢያ ሙዚቃ፦ ሙሉዓለም ተከለ ፣ ዘቢባ ግርማ እና አቤል ሀጎስ( ወዳጅ)

📌ምርጥ ሲኒማቶግራፈር፦ ብስራት ጌታቸው እና ሰደኪያል አየለ ( ዶቃ )

📌ምርጥ ሜካአፕ፦ ዳግማዊ አለማየሁ (ዶቃ)

📌ምርጥ የፊልም ፅሁፍ፦ ቤዛ ሀይሉ እና ቅድስት ይልማ (ዶቃ)

📌 ተስፋ የተጣለባት ተዋናይት፦ መቅደላዊት ግርማ "(ሌባ እና ሌባ)

📌 ተስፋ የተጣለበት ተዋናይ፦ በረከት ግዛቸው (ጭረት )

📌ምርጥ ረ/ተዋናይት፦  ድርብወርቅ ሰይፉ (ዶቃ)

ምርጥ ረ/ተዋናይ፦ ቴዎድሮስ ተሾመ (ዝምታዬ)

ምርጥ ተዋናይት፦ ቃልኪዳን ጥበብ (ልባም)

📌 ምርጥ ተዋናይ:- ሙሉዓለም ጌታቸው (ገምዛ)

📌የተመልካች ምርጫ፦ ወዳጅ ፊልም

📌 ምርጥ ዳይሬክተር፦ ቅድስት ይልማ (ዶቃ)

📌 ምርጥ ፊልም፦ ዶቃ

ከ16ቱ ዘርፎች ከግማሽ 9ኙን ሽልማት በመውሰድ "ዶቃ" ፊልም ከፊት ይገኛል፣ "ወዳጅ"ፊልም ሁለት ሽልማቶችን  "ሌባ እና ሌባ፣ ልባም፣ ገምዛ፣ ዝምታዬ እና ጭረት ፊልሞች ደሞ አንድ አንድ ሽልማቶችን ወስደዋል።

©️መረጃው የጋዜጠኛ ፅዮን ታምራት ነው።

ለተጨማሪው: @EventAddis1
1
📌"ሎሚ ተራ ተራ" መጽሐፍ በቅርቡ ለንባብ ይበቃል

በገጣሚ ፋሲካው ጌታቸው የተዘጋጀው "ሎሚ ተራ ተራ" የተሰኘ የግጥም መጽሐፍ በቅርቡ ለአንባቢያን እንደሚደርስ የመጽሐፉ አዘጋጅ ለኤቨንት አዲስ ድረገፅ ገልጿል።

"ሎሚ ተራ ተራ" መጽሐፍ በይዘት የግጥም መጽሐፍ ሲሆን በ152 ገፆች ተቀንብቦ በ350 የጀርባ ዋጋ ለአንባቢያን ይደርሳል ተብሏል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌ጋዜጠኛ ግርማ ፍስሃ የክብር እንግዳ የሆነበት ስብሐቲዝም የሀሳብ ውይይት ዝግጅት ነገ ይካሄዳል።

በሸገር 102.1 ሬድዮ "ማንን ምን እንጠይቅልዎ" በተሰኘው ዝግጅት የምናውቀው ጋዜጠኛ ግርማ ፍስሃ የክብር እንግዳ የሆነበት ስብሐቲዝም 76ተኛ መድረክ "ግርማዊ ጋዜጠኝነት" በሚል የሀሳብ ውይይት ይካሄዳል።

ውይይቱ ነገ ጥቅምት 10 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ጀምሮ በብሔራዊ ቤተመዛግብት እና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት (ወመዘክር) አዳራሽ ውስጥ ይከናወናል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌"ውብ ከተማ ለመጭው ትውልድ!"

ኤልቬዜት ኢቨንትስ ከአዲስ አበባ ከተማ ፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ እና  ከአዲስ አበባ ከተማ የህዝብ መዝናኛ ቦታዎች ጋር በመተባበር በጉለሌ ክ/ከተማ   እንጦጦ ፓርክ ሳምንታዊ የፅዳት ንቅናቄ መርሀግብር አካሂዷል።

"ውብ ከተማ ለመጭው ትውልድ!" በሚል መሪ-ቃል የፅዳት ንቅናቄው ተከናውኗል::

የኤልቬዜት ኢቨንትስ ዋና ስራ አስኪያጅ እንደገለፁት "ትውልድ የሚገለገልበትን ስፍራ በማፅዳት ጀምሮ በማፅዳት የመጨረስን ባህል እንዲያዳብር ያስፈልጋል ብለዋል" ስለዚህም ከፊታችን ህዳር1 በእንጦጦ ፓርክ አምፊ ትያትር ላይ በፓ/ር ዘማሪ ዬሴፍ ካሳ ለሚደረገው ታላቅ የዝማሬ ድግስ በተለያዪ ተቋማት ፅዳቱ ተከናውኗል::

በንቅናቄ ስራው ላይም አመራሮችን ጨምሮ የፅዳት አምባሳደሮች የፕሮግራሙ አዘጋጆችና ልዩ ልዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፈዋል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌"ብርቱ ንቁ ጀግና ዜጋ" ለአንድ ሺህ ሰዎች!

የሄኖክ ኪዳነወልድ ስፖርት ስልጠናዎች፣አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች ስፖርት  ቢሮ እና የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ በመተባበር "ብርቱ ንቁ ጀግና ዜጋ" በሚል መሪ ሀሳብ በውፍረት፣ በኮልሰትሮል፣ በስኳር፣ በደም ግፊት እና በተለያዩ ሱሶች ውስጥ ያሉና የመክፈል አቅም የሌላቸው 1000 ሰዎችን በነጻ የስፖርት እንቅስቃሴ፣የሥርዓተ ምግብና የህይወት ክህሎት ስልጠና መርሐግብር የመክፈቻ ሥነሥርዓት ዛሬ ጥቅምት 10 2017 ዓ.ም በወዳጅነት አደባባይ ተካሂዷል።

"ብርቱ ንቁ ጀግና ዜጋ" የአካል እንቅሳቃሴ ስልጠና ጥቅምት 10 ቀን 2016 ዓ.ም በወዳጅነት አደባባይ በመክፈቻ ሥነሥርዓት በይፋ የተጀመረ ሲሆን ከወዳጅነት አደባባይ በተጨማሪም የአዲስ አበባ አምስቱንም የመውጫ በሮች ያማከሉ አምስት የስልጠና ቦታዎች እንደተዘጋጁ ተገልጿል።

ስልጠናው ለሶስት ወራት የሚቆይ ሲሆን በዓመት ሶስቴ እንደሚዘጋጅና ቀጣይነት እንዳለው ተነግሯል።

ሥልጠናው ላይ የሥርዓተ ምግብና የህይወት ክህሎት ስልጠና ባለሙያዎች ለሰልጣኞች እገዛ የሚያደርጉ ይሆናል ተብሏል።በነፃ የሚሰጠው ስልጠና በገንዘብ ቢለወጥ ሠላሳ ሚልየን ብር ገደማ እንደሚያወጣ ተነግሯል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌"የተረገመው ልጅ" ፊልም ነገ ይመረቃል

በሮቤል አሰፋ እና አንዱዓለም ደጀኔ የተዘጋጀው "የተረገመው ልጅ" አዲስ ፊልም ነገ ጥቅምት 11 ቀን 2017 ዓ.ም ከምሽቱ 11:30 ጀምሮ በዓለም ሲኒማ በፊልሙ የተሳተፉ እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ይመረቃል።

በኤመራልድ ፊልም ፕሮዳክሽን ተዘጋጅቶ በንጉስ ፊልም ፕሮዳክሽን የቀረበው "የተረገመው ልጅ" ፊልም በድርሰት እና ዳይሬክቲንግ ሮቤል አሰፋ እና የአንዱዓለም ደጀኔ ለሁለት ተሳትፈውበታል።

በፊልሙ ላይ ዘላለም ይታገሱ፣ ወለላ አሰፋ፣ ዳዊት አባተ፣ ማስተዋል ወንድወሰን እና ሌሎችም በትወና ተሳትፈውበታል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌የኤስ ኦ ኤስ የህጻናት መንደሮች በኢትዮጵያ የ50ኛ ዓመት ክብረበዓል የማጠቃለያ ፕሮግራም ተካሄደ

ኤስ ኦ ኤስ የህጻናት መንደሮች በኢትዮጵያ ላለፉት አምስት አስርት ዓመታት ያስመዘገባቸውን ልዩ ልዩ ስኬቶችን በመዘከር የተመሰረተበትን 50ኛ ዓመት ክብረበዓሉን ሲያከብር ቆይቷል። ዛሬ ጥቅምት 12 2017 ዓ.ም የክብረበዓሉ የማጠቃለያ መርሐግብሩን በሸራተን አዲስ ሆቴል አካሂዷል።

ክብረ በዓል ተከታታይነት ያላቸው በርካታ ሁነቶችን በማከናወን ሲከበር የቆየ ሲሆን ድርጅቱ ያስመዘገባቸውን ስኬቶች፣ የድርጅቱ ደጋፊዎችና ሰራተኞች እያበረከቱ ያለውን አስተዋጽኦ እውቅና ለመስጠት የተዘጋጀ እንደሆነ ተገልጿል።

ኤስ ኦ ኤስ የህጻናት መንደሮች በኢትዮጵያ የሐምሳኛ ዓመት ክብረበዓሉን  በኤግዚቢሽን ፣ በፓናል ውይይት፣ በገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራሞች እና የችግኝ ተከላ ፕሮግራም ሲያከናውን ቆይቷል፡፡

እነዚህም እንቅስቃሴዎች ስራውን የበለጠ ለማስተዋወቅ፣ ድጋፍ ለማሰባሰብ እንዲሁም ግለሰቦችና ድርጅቶች ለእያንዳንዱ ህጻን ተንከባካቢ ቤተሰብና ብሩህ ተስፋ የማጎናጸፍ አላማ ዙሪያ እንዲሰለፉ በሚያበረታታ መልኩ የተቀረጹ ናቸው ተብሏል።

ኤስ ኦ ኤስ የህጻናት መንደሮች በኢትዮጵያ የአለም አቀፉ ኤስ ኦ ኤስ የህጻናት መንደሮች ፌዴሬሽን ብሄራዊ አባል የሆነ በህጻናት ደህንነትና ልማት ላይ አተኩሮ የሚሰራ ፖለቲካዊም ሃይማኖታዊም ያልሆነ የልማት ድርጅት ነው፡፡ ድርጅቱ ከተመሰረተበት ከ1974 ዓ.ም ጀምሮ በህጻናት፣ ቤተሰቦቻቸውና በማህበረሰብ ላይ አዎንታዊ ለውጦችን በማምጣት ላይ የሚገኝ የልማት አጋር ነው።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1